በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
እዚህ ላይም ለ15 ቀን ትንሽ ልንጠፋፋ ነው እና ግሩፑን አደራ አድሚኖች😁😁
ከ2 ሳምንት በኋላ እዚህ ላይ እንደተለመደው በአጫጭር ጽሑፎች እና ቲክቶክ ላይ በቪዲዮ እመለሳለሁ.. ትንሽ እረፍት እናድርግ መሰለኝ.. እውነቱን ለመናገር እዚህ ቻናል ትናፍቁኛላችሁ በጣም ማርያምን
ዝም ብዬ ጥፍት ስል ሌላ ነገር እንዳይመስል ነው ያሳወቅኋችሁ
ይቅርታ ጋይስ አናዶኝ ጻፍኩበት ቅድም.. በቃ ችግር የለም እንደፈለጉ ይሁኑ.. ማናችሁምም አትመልሱላቸው.. የሚያወዛግብ ነገር ካለ ግን ሁሌም ራሴንው ጠይቁኝ
Читать полностью…ዛሬ ከአንድ ኤርትራዊ ሰው ጋር ቲክቶክ ላይ ተገናኝተን አንድ ነገር ቼክ አደረግሁ..
የኤርትራ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው መጽሐፈ መቃቢያን ራሱ የግሪክ ሰብዓ ሊቃናቱ ነው.. ማለትም የጥንት አባቶቻችንም የተጠቀሙበት ማለት ነው
ዌል ዛሬ የተወለድኩበት ቀን ነው😁😁 (እና ምናባህ ይፈጠርልህ ሎል)
ምንም ሳንሰራበት እድሜያችን ቆሰው በስመአብ.. አረጀሁ😁😁 ቢያንስ ግን ሳይገባኝ የጌታን ቃል አብርያቸው የምማማራቸው እናንተን ቤተሰቦቼን ጌታ ሰጥቶኛል.. ይመስገን.. በሥጋ አረጀሁ በመንፈስ ገና ልጅ ነኝ.. ጌታ ግን በመንፈስም ያሳድገኛል..
ስለ ሁሉም ነገር ግን ጌታን አመሰግነዋለሁ.. የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሚሆነው የጌታችን ኢየሱስ አባት ይመስገን..
ሁሌም ቢሆን ርኅራኄውን ተስፋ በማድረግ መጽናናት ይሆንልኛል ስለዚህም በቀሪዋ ትንሽ ዘመኔ የተጣመመውን በምህረቱ ያቃናልኝ(ራሴን ስመርቅ😁😁).. እና ደግሞ ዛሬ የታላቁ መምህር አቡሊዲስ ሥጋው ከባህር የወጣበት መታሰቢያ ነው(ስንክሳር) እንዲሁም እናታችን ቅድስት አርሴማንም የምናስብበት ቀን ነው እና በረከታቸው ትደርብኝ ጸሎታቸው ትርዳኝ
ሰላም ዋሉልኝ
@Apostolic_Answers
አፌ ላይ ምን እያደረግሁ ነው..??😭😂 ሳላማትብ የሆነ ነገር አፌ ውስጥ አስገብቼ ነው ወይስ እያዛጋው..??😆😆
ይሄንን አንዷ ልካልኝ ነው እና የሰዉ ግን ማስተዋል🤣🤣
የእህተማርያም ተከታዮች ጌታችን የተወለደው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው እያሉ ነው.. ጎጃም አካባቢ አሉ.. እና የተጠመቀውም በአባይ ወንዝ ነው አሉ😭😭
ይሄንን አሁን ድንገት አስጽፈው አስቀምጠውት ከ150 ዓመት በኋላ የሚመጡ ክርስቲያኖች ሲያወሩ እንደ ማስረጃ ጥንታዊ ጽሑፍ ብለው ቢጠቅሱት አስባችሁታል..??
በመጽሐፍ የተገኘው ሁሉ በአደባባይ አይወራም.. ባላየ እንለፍ አንዳንዴ
ስለ ጋብቻ
-ለመጋባት ላሰቡ
-ለመጋባት ላላሰቡ
-ቅርብ ጊዜ ለተጋቡ
-ተጋብተው አመታት ላስቆጠሩም
https://vm.tiktok.com/ZMkse4xkT/
መልእክት ከወንድማችን በጋሻው ደሳለኝ..
“ለዝማሬ ውድድሩ የተጠቀማችሁት ዝማሬ ሌላ ስለሆነ በዚህኛው ቀይሩልኝ” ብሏል ሎል
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አሁን ላይ ቢኖርና ወደ እኛ መልእክትን ቢጽፍ ምን የሚል ይመስላችኋል..??
በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ በኢትዮጵያ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን.. ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን..
.
.
.
በመካከላችሁ አንዳንዶች በገድላት ተአምራት ውስጥ የተቀመጠውን ሁሉ ካልተቀበላችሁ በክርስትናችሁ አትቀጥሉም እያሉ ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጧችሁ ሰማን.. የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ግን ፍርድን ራሱ ይሸከማል.. የሚያናውጣችሁ ይቆረጥ። እናንተ ግን መዳን የሚገኝበትን ነገር አስቀድማችሁ አውቃችኋልና በእርሱ ጸንታችሁ ኑሩ.. በዛም ላይ ደግሞ በመካከላችሁ ፍቅርን አብዙ.. እንጀራንም(ቅዱስ ቁርባን) ለመቁረስ በተሰበሰባችሁ ጊዜ ከጌታ ሥጋና ደም አትሽሹ..
በእነርዚህ ሁሉ ጽኑ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
@Apostolic_Answers
ቀረብሃ ወንድም አለም😁😁 ያ ሁሉ የአባቶች ትምህርት ቀረብህ😁😁
ዮሐንስ አፈወርቅ እና ባስልዮስ እኮ ኢትዮጵያውያን አይደሉም.. በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥራዎቻቸው ተላልፈዋል
ዎክ እያደረግሁ አንድ ወንድም አሁን መንገድ ላይ አግኝቶኝ.. እጁ ላይ ያለውን ሰዓት አውልቆ አደረገልኝ በጌታ😭😭 እና ትንሽ አስደነገጠኝና ስልኩን እንኳን ሳልቀበለው.. አሳፍራለሁ..
ይሄንን ምናልባት ካየኸው ጻፍልኝ ፕሊስ ምሳ እንኳን እንብላ
እመቤታችን ከሃጢአት ንጽሕት አይደለችም..??
ሃሰተኛ ክስ ወጋሁ ሎል
https://vm.tiktok.com/ZMkWJ9yX2/
እንዴ ሳላውቅ ዩትዩባቸውን ጀምረውት እነዚህ የተመቱ ሰዎች.. ቤተ ክርስቲያኑን ማወቅ የሚፈልግ በቃ ይኸው የቴዮሶፊያዎች ዩትዩብ..
ሁላችሁም ገብታችሁ ፎሎው አድርጓቸውና ሃላፊነት አብዙባቸው
https://youtu.be/JgZidTEcj5Y
በእባቡ ፈንታ ገብርኤል ሊናገር ተነሳ..
በሔዋንም ምትክ ማርያም ተነሳች በሃሳቡ ልትስማማ
ሁለት መልእክተኞች ወደ ሁለት ድንግሎች ተላኩ..
ሰይጣን ምስጢርን ለሄዋን በእባቡ በኩል ነገረ.. ጌታም በመልአኩ በኩል የምስራቹን ለእመቤታችን ላከ..
ያዕቆብ ዘስሩግ: on the mother of God [eve’s legacy overturned]
@Apostolic_Answers
ትዝታው ጥሪ አቀረብልን😭😭
ኧረ እንደ ፕሮቴስታንት ቅዱስ ቁርባን ላይ የቀለደ የለም
https://vm.tiktok.com/ZMkGUJpvw/
በቃ ይብራ ብዙ ወዳጆች ለጊዜው ይብራ አሉኝ.. ሌላ ጊዜ ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር
ያው ጉዳዩን ባለማወቅ ብዙ ሰዎች ያልተገባ ነገርን ሲናገር ስለምሰማ ጉዳዩን እንድታውቁት ነበር ግን ይብራ በቃ ለጊዜው🤗🤗
ኧረ ከዚህ ቀደም ከእኔ ጋር “ጥምቀት ለድኅነት አይደለም” ብሎ የተሟገተ ፕሮቴስታንት ዛሬ ላይ ኦርቶዶክሶች ጥምቀት ያድናል..?? ብለው ሲመጡ መሟገት የለብንም “ፕሮቴስታንቲዝሙ እንዲህ ከመሞገት የራቀ ነው” እያለ ነው😆😆 ለድኅነት ነው እያለም ነው😭😭
ኧረ ልተኛበት አታስቁኝ.. ወጣት ሆናችሁ ሰው ሰራሽ ቤተ እምነት ውስጥ ምን እንደምትሰሩ ግራ ነው ሚገባኝ😁😁
“አባቶች ሊቃውንት እንደሚሉት” እያለ ግን ምንም አባት የማይጠቅስ ጀለስ አለኝ ሎል
አከራካሪ ነገር በመካከላችን ከተነሳ እና ከአባቶች በደምብ ካላሳየሁ “በቃ ይህ በልማድ የያዝከው ነው እውነት ይሁን አይሁን እስኪረጋገጥ ጥፋ ከዚ” በሉኝ😁😁
እኔን ብቻ ሳይሆን የትኛውንም ሰው.. አንዳንድ ጊዜ በልምድ የያዝነው ነገር አስቸጋሪ ነው
ሰላም እደሩ ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ
@Apostolic_Answers
3ኛው የ “ዝማሬ” ተወዳዳሪያችን
“ዘማሪ” በጋሻው ደሳለኝ ሎል
እኔ የተያዝኩ ቀን ግን አለቀልኝ😆😆
ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግብጽ ትበልጣለች..??
ማን አባቱ ነው እንዲህ ሊል የሚደፍረው.. በሥልጣን እኩል ናቸው ማንም ማንንም አይበልጥም.. ያው ግን አንዳችን ከአንዳችን የምንማረው ወይም የምንወስደው ነገር ካለ እናደርገዋለን.. ይህ ብልህነት ነው መንፈሳዊነትም ነው..
እና ደግሞ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዳግም ተወልዶ(ክርስትና ተነስቶ) አንዳች አሳማኝ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ጠቅልዬ ግብጽ እገባለሁ የሚልም ሰው ብዙም አይመቸኝም ከይቅርታ ጋር ይህ የኔ አሳብ ነው.. አንድ ብንሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆንክ በቃ አርፈህ ይህችንው ቤተ ክርስቲያንህን አውቀህ እየቆረብክ መኖር ነው እንጂ ወደዛ ምናምን ማለት አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር አያስፈልግም..
@Apostolic_Answers
ፑል 🎱 አልፎ አልፎ እጫወታለሁ ብዙም ሃሪፍ ባልሆንም.. ምንድን ነው ምትወዱት ጨዋታ እንደ አንድ አልፎ አልፎ እንደሚፍታታ ክርስቲያን..??😁😁
Читать полностью…ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት
“እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው፥ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን አዎንና አይደለም አይሆንም።”
[2ኛ ቆሮንቶስ 1: 18]
ቅዱስ ጳውሎስ የሐዋርያዊ ጉዞውን እቅድ ይቀይርባቸዋል ያው በአስገዳጅ ምክንያት.. ይህ የሱ አሳብ ነበር እና እርሱ ደግሞ ሰው እንደመሆኑ አሳቡ ተቀየረ.. ታድያ ግን በእርሱ የተሰበከ የእግዚአብሔር ቃል ግን ከታመነው ከእግዚአብሔር ነውና ያ ቃል አንዴ “አዎን” አንዴ ደግሞ “አይደለም” የሚባል አይደለም.. ስለዚህ ጉዞው ላይ አሳቡ እንደተቀያየረ ትምህርት ነክ ነገር ላይ ግን አሳብ አይቀያየርም.. ምክንያቱም በጳውሎስ የተሰጠው ትምህርት ከታመነው አምላክ ነውና።
ፕሮቴስታንቶች የሆነ ትምህርት ያውም ድኅነት ላይ ብትጠይቋቸው አንዱ “አዎ” አንዱ “አይደለም” ይላል.. ለምሳሌ ጥምቀት ለድኅነት ነው..?? ብላችሁ ብትጠይቋቸው ማለት ነው.. እንደ ሰው አሳብ እንደሚኖሩ አመልካች ነው
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers