በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
አንድ አካል ሁለት ባህሪ..??
አንዳንድ ሰዎች ክርስቶስ "አንድ አካል" ነው ሲሉ የሰውነቱ አካል የለም የመለኮት ብቻ እንጂ በማለት ይህ አንድ አካል የመለኮት ብቻ ነው ይላሉ..
አካል ማለት ማንነት ስለሆነ ክርስቶስ ሁለት አካል እንደሌለው ግልጽ ነውና ዘላለማዊ ከሆነው ከቃል አካል ውጪ ሆኖ ሁለተኛ የሰው አካል ሊኖር አይችልም የለምም ታድያ ግን አስቀድሞ በነበረ ዘላለማዊ የቃል አካል ጋር አብሮ የሰውነትም አካል ተዋሕዶ አንድ ሆኗል ነው እንጂ አንድኛው የጠፋ ሆኖ አይደለም
የሰውነት አካል የለውም ማለት የሰው ማንነት የለውም እንደማለት ነው ይህም ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንትም ያወገዘችው የዶሴቲዝም ምንፍቅና ነው
@apostolic_answers
ደጋግሜ ባየው ልጠግበው ያልቻልኩት intro ቪዲዮዋችን
በነገራችን ላይ ይህንን ሁሉ የሰራው አላዛር የሚባል ወንድሜ(ወንድማችን) ነው.. ላዛሩስ ብሮዬ የምር ጌታ ያክብርልን..
የዛችን ልጅ ጸባዩዋን ችለህ መስራትህ የሚደንቅ ነው🤣🤣
ቤተ ክርስቲያንን ያሳያል ብለን እናስባለን
ከላይ -ሐ (ሐዋርያዊ)
ከታች -መ (መልሶች)
ተደርጎ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ተሰርቷል..
አዲሱን ሎጎዋችንን 12 ሰዓት ሲል የምንቀይረው ይሆናል.. በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በYT በአዲስ አቀራረብ ለመምጣታችን መግቢያ ቪዲዮ ይለቀቃል😬😬
Читать полностью…"ፍቅርህ ማረከኝ"
ካለው ፍቅር የተነሳ እኛ ከመንፈስ እንድንወለድ እርሱ ከሥጋ ተወለደ🤗🤗
እንኳን አደረሳችሁ የኔ ተወዳጆች🤗🤗
https://vm.tiktok.com/ZMFwqchFj/
የና/ደ/አ/አ/ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ስርአተ ማህሌት
https://youtu.be/WKc8mGB1nZs
ጉድ እኮ ነው አሁን ደግሞ በ14 ቀን ውስጥ አሥር ሺህዎች ተቀላቅለውናል😬😬 ጌታ ይመስገን በጸሎታችሁ አትርሱን🤗🤗
Читать полностью…አዲሱን ሎጎዋችንን 12 ሰዓት ሲል የምንቀይረው ይሆናል.. በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በYT(ዩትዩብ) በአዲስ አቀራረብ ለመምጣታችን መግቢያ ቪዲዮ ይለቀቃል😬😬
@apostolic_answers
ዶሮውም አለቀ እኛም ላይቭ ገባን😬😬
https://vt.tiktok.com/ZS8hTmvEL
“ጸጋ የሞላብሽ" አይልም..??😬😬
https://vm.tiktok.com/ZMFEauJb7/
ጌታችን ኢየሱስ የወደቀውን አለም የፈወሰውና ከውድቀት ያወጣው እንዴት ነው..?? ወደ ወደቀው አለም ገብቶ ወይስ ከወደቀው አለም ራቅ ብሎ..??
አካላዊ ቃል የመጣው ወዳልወደቀው ሥጋ ወይስ ወደ ወደቀው ሥጋ..??
ከቃል ጋር ተዋሕዶ የቃልን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ አምላክ የተባለው የወደቀው ሥጋ ወይስ ያልወደቀ ሥጋ..??
ጌታ ቢረዳኝና ቢፈቅድ ሌላ ከዚህ የሚቀድሙ ነገሮች ካልተደራረቡብኝ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአባቶች ትምህርት አድርገን ሰፋ ያለ ነገር እናወራባቸዋለን..
#ቤተክርስቲያን_ምን_ትላለች..??
@Apostolic_Answers
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡
ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!
ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን!
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት!
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት!
የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው!
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!
ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ — በእንተ ምሴተ ልደት
ጌታ ሰው የሆነው ለማርያምም ነው..??
https://vm.tiktok.com/ZMFwQFVpJ/
ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት..??
https://vm.tiktok.com/ZMFTkuGVW/