አብ አምላክ
ወልድ አምላክ
መንፈስ ቅዱስ አምላክ
ከሆነ.. እንዴት ታድያ 3 አምላክ አያስብልም..?? ለሚለው
https://vm.tiktok.com/ZMYXMM1jL/
ሰፈር ሰንበት ት/ቤት ውስጥ ትንሽ ነገር አስተምርልን ብለውኝ እያስተማርኳቸው ነበር.. እና በጣም ጸዴ ነበር እኮ
ግን
መሃል ላይ "ጋይስ" አልኳቸው😭😭
Maximilian Kolbe የተባለ ካቶሊክ ካህን "ማርያምን እጅጉን ወደድኩ ብለህ አትስጋ ልጇ ኢየሱስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና" ይላል..
በጣም ደስ የሚል አባባል.. ግን ደግሞ ይህ ለሁላችን የሚሆንም ነው.. ማንም ሰው ቢሆን ምንም ያህል ቢወደን ክርስቶስ የወደደንን ያህል ግን ሊወደን የሚችል የለም..
ሰው አድርጎ ፈጥሮናል.. በወደቅን ጊዜ ደግሞ አምላክ ሲሆን የባርያን መልክ ይዞልናል.. የባርያን መልክ ይዞ ደግሞ የአይሁድን ምራቅ ተቀብሏል.. በጥፊ ተመቶልናል.. ለመስቀል ሞት እንኳን የተዘዘ ሆኗል.. ይህ ሁሉ ስለ ማን ነው..??
በሃይማኖተ አበው የእለ እስክንድሮስ ክፍል ላይ እንዲህ ይላል:
"እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ አለም ይመጣ ዘንድ ከንጽህት ድንግል ማርያም ሥጋን ይዋሃድ ዘንድ ምን አተጋው..??
በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ፣ በበረት ይጣል ዘንድ፣ ከድንግል ጡት ወተትን ይጠባ ዘንድ፣ በዮርዳንኖስ ይጠመቅ ዘንድ ምን አተጋው..??
ሕግ አፍራሽ ጲላጦስ ይዘብትበት ዘንድ በመስቀል ይሰቀል ዘንድ በመቃብር ይቀበር ዘንድ በሦሥተኛውም ቀን ይነሳ ዘንድ ምን አተጋው..??
በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ 👉ለእኛ ብሎ አይደለምን..??"
✝️እና ምን..??
እኛም ደግሞ አምላካችንን እንውደደው.. እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና
1ኛ ዮሐንስ 4
19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
መልካም ሰንበት እናንተ የክርስቶስ ምርጦች እና ውዶች😊🤗
@Apostolic_Answers
የማቴዎስ ወንጌል 24
40፤ በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤
https://vm.tiktok.com/ZMYafcbyM/
ቡድሃ(የቡዲዝም መስራች) ምናልባት ለእስያ የተላከ የአላህ መልእክተኛ ይሆን..??
https://vm.tiktok.com/ZMY554KND/
ክርስቶስ ከልደቱ አንስቶ ጥምቀቱ ፣ ስቅለቱ ፣ ሞቱ ፣ ትንሥኤው ፣ እርገቱ ለቤተክርስትያን ምሳሌዋ የሆነና በአምልኮዋ የምታዘክረው ነው ።
ለዚህ ማሳያ የሚሆነን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ደብረ ታቦር ነው[ማቴ 17:1-9] ፤ ልክ በደብረ ታቦር ነቢያትና ሐዋርያት እንደተገናኙ በቤተ ክርስቲያንም የነቢያትና የሐዋርያት መጻሕፍት ሲነበቡ ሲተረጎሙ ይኖርሉ ። በደብረ ታቦር ደናግላን ከተጋቡት ጋር ሕብረት እንደነበራቸው ሁሉ ቤተክርስትያንም በድንግል ና የሚኖሩም በጋብቻ የሚኖሩም ሰዎች በጋራ የሚያስቀድሱባት ናት ። ከብሔረ ሙታን ሙሴ ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስ እና ሐዋርያት ህብረት እንደነበራቸው ሁሉ በቤተክርስትያንም ሕያዋን ከሙታን ጋር ህብረት አላቸው አንዱ ለሌላው ሲጸልዩ ይኖራሉና። ልክ በደብረ ታቦር ጌታ ብርሀነ መለኮቱን አብርቶ አምላክነቱን እንደገለጠ በቤተክርስትያንም ሁል ጊዜ የክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ይገለጥባታል ይመሰከርባታል ። በተራራው አምስት ሆነው ይህንን ምስጢር አይተው አገልግለዋል በቤተ መቅደስ አምስት ቀዳስያን ቅዱስ ሚስጥርን ያገለግላሉና ነው ። ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ ቦታ ማደሪያ እንሥራ ማለቱ ቤተክርስትያን በተራራ ላይ ትሰራለችና ነው(የእግዚአብሔር ቤት በተራራ ላይ መሠራቱ በነቢዩ ኢሳይያስ አቀድሞ የተነገረ ትንቢት ጭምር ነው ኢሳ 2፡2 ) ። ጌታ አብርቶ መልኩ መለወጡ ኅብስቱ እና ወይኑ ተለውጠው ሥጋ እግዚአብሔር ደመ እግዚአብሔር ይሆናሉና ነው ። ደብረ ታቦር ብቻውን በዚህ ሁሉ ለቤተክርስትያን ምሳሌዋ ነው ።
በቅዳሴ ተገኝቶ ከአምልኮ መካፋል ከደብረ ታቦር እንደሚያካፍለን ሁሉ ከጌቴሴማኒ ያካፋለናል ፤ በጌቴሴማኒ ጌታ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ እንዳለን በቤተክርስትያንም “አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ” ብለን እንድንጸልይ ታዘናለች ። ጌቴሴማኒ በቤተክርስትያንም አለ ። በቀራንዮ በመስቀል ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ መስዋዕት እንዳቀረበ ቤተክርስትያንም ያንኑ መስዋዕት በመንበሩ(ታቦት) ታቀርበዋለች ። ስጋው የተቆረሰበት ደሙ የፈሰሰበት ቀራንዮ በቤተክርስትያን አለ ። የእግዚአብሔር ልጅነታንችን የሚታወጅበት ዮርዳኖስ ቤተክርስትያን አለ ። ከተጠመቅን በኋላ ለ40 ቀን የምንጋደለብት ቆሮንቶስ በቤተክርስትያን አለ ። በአጠቃላይ ክርስቶስ የሄደበት በቤተክርስትያን የማንቀርብበት የለም ራስ ካለበት አካል ይኖራልና
መውደድም ሐዋርያው “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ የሚል፤ ትዕዛዙንም የማይጠብቅ ሐሰተኛ ነው” [1ዮሐ4፡20] እንዳለው ትእዛዙን መፈጸም ነው ትእዛዙን የማይፈጽም በእውነትም ሐሰተኛ ነው ...
እርሱን መውደድስ ይህ ነው፡ ስለስሙ ሰውነታችንን አሳልፈን ከሰጠን ነው፤ እርሱን መውደድስ ፡ ዓለምንና በውስጡ ያለውን ከናቅን ነው ። እርሱን መውደድስ ከትእዛዛቱ እንዳንሰናከል ነው ። እርሱን መውደድስ መጾም፣ መጸለይ ፣ መትጋት ማገልገል፣ መታቀብ ፣ ዝምታን ገንዘብ ማድረግ ናቸው ። እርሱን መውደድስ በዓላቶቹን ሰንበታቱን ማክበር ፣ እርሱን ብቻ ማምለክ፣ ትእዛዝቱንም መጠበቅ ነው ፤ ከዚህ ሌላ ግን የለም። ትእዛዙን ካልጠበቅህ እግዚአብሔርን በምን ትወድደዋለህ ? ተራቁቶ ታለብሰዋለህን? ተርቦስ ታበላዋለህን? ተጠምቶስ ታረካዋለህን ? እርሱ “የላምን ስጋ አልበላም ፤ የፍየልን ደምም አልጠጣም ዓለም በመላው የእኔ ነው፤ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፤ ጸሎትህንም ለልዑል እግዚአብሔር አቅርብ” [መዝ 49፡13] ብሏልና... በሌላ ቦታም “እስራኤል ሆይ ታመልከው፣ ታፈቅረው፣ ትፈራው ዘንድ ነው እንጂ ከዚያ በቀር እግዚአብሔር ከአንተ ምን ይሻል? ”[መዝ 49፡23] አለ ።
ርቱዐ ሃይማኖት ንባብ ዘገብርኄር ላይ የተወሰደ
ዘፈን ኃጢአት ነው..??
ገላትያ ላይ የተጠቀሰውስ "ዘፋኝነት" የምር ሰዎች የሚሰምትን ዘፈን ሁሉ የሚመለከት ነው..??
https://vm.tiktok.com/ZMYuG21Gv/
ሙስሊሞች የክርስትናን ትምህርት ለመተቸት ሲሞክሩ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም.. የሚያሳዝነው ደግሞ በኢትዮጵያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እስልምና ላይ ብዙም እንዳልተሰራ ግልጽ ነው.. ስለዚህም ለጊዜው አንዲት ነገር አስቢያለው..
እስልምና ላይ መስራት የምትፈልጉ ወይም የጀመራችሁ ወንድሞች ወይም እህቶች ሰብሰብ እንበልና አንዳንድ ሥራዎችን ለመስራት ብንሞክር ብናጠና ምናምን..
ብታሟሉ መልካም ነው ብዬ የማስባቸው
1. የምርም እስልምና ላይ የመስራት ፍላጎቱ ያለው
2. የክርስትና ትምህርት ላይ መሠረታዊ እውቀት ያለው
3. ሙስሊም ወንድም እህቶቹን በመሳደብ ወይም በማንቋሸሽ ሳይሆን በእግዚአብሔር እንደተወደዱ ወንድም እህቶቹ እያየ በፍቅር በመስራት የሚያምን
4. በክርስትና ሕይወቱ ውስጥ የሚጸልይ የሚያስቀድስ(በጣም አስፈላጊ)
5. ኢንግሊዘኛ ቋንቋን አንብቦ በደንብ መረዳት የሚችል(ያው fluent መሆን አይጠበቅባችሁም)
@aklil1 ላይ "እኔ አለሁ" ብቻ ብላችሁ ጻፉልኝ አወራችሁዋለው😉😉
ምንጣቕ..??
ካብ ቀደሙ ናይ ክርስትያን ተስፍኦም ክርስቶስ ክመጽእ እዩ ዝብል ናይ ተስፋ ቃል እዩ።
ጎይታና መድሓኒትና ኢየሱስ ክርስቶስ ሞይቱልና እዩ ሞይቱ ከዓ አይተረፈን አብ ሳልሳይ መዓልቱ ካብ ሙውታን ተፈልዩ ተላዒሉ።
ብኽብሪ ከዓ ናብ ሰማይ ዓሪጉ
አብ የማን አብኡ አሎ ሐዚ
ንሱ ባዕሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ካልኣይን ናይ መወዳእታ ግዜ ብሕያዋን እና ብሙውታን ክፈርድ ናብዚ ምድሪ ተመሊሱ ክመጽእ እዩ።
ሽዑ ኩላትና ካብ ሙታን ክንልዓል ኢና ናይ ትንሳኤና ብኹሪ ክርስቶስ ከምቲ ዝተልዓለ
ሽዑ ምስ ክርስቶስ ንዘለአለም ንነብር ኢና።
እዚ አብ ውሽጥ ክርስትና ዓብዪ ተስፋ እዩ።
እቱ ትምህርቱ ከዓ ከም ትምህርቲ eschatology ተባሂሉ ይጽዋዕ።
እዚ ትምህርቲ አብ ቤተክርስትያና ብጣዕሚ ወሳኒ ትምህርቲ እዩ ብፍላይ ብናትና ቤተክርስትያን 5 አእማደ ሚስጥራት ተባሂሎም ዝውሃቡ ወሰንቲ ትምህርቲ አለው።
👉ምሥጥረ ሥላሴ
👉ምሥጥረ ስጋዌ
👉ምሥጥረ ጥምቀት
👉ምሥጥረ ቁርባን
👉ምሥጥረ ትንሳኤ ሙታን (eschatology)
እዚ ናይ eschatology ትምህርቲእዩ። እዚ ትምህርቲ ንሕና ዋና መሰረት ኢልና ኢና ንምልከቶ።እዚ ትምህርቲ እዚ ንምርዳእ ናይ ሐወርያት እመነት መግለጺ ተባሂሉ ዝፍለጥ አሎ ንሱ ጥንታዊ እዩ።
ንሱ ድማ ናይ ኒቅያ ጉባኤና ናይ ቁስጥንጥንያ ጉባኤ እዩ።
አብዚ ናይ ሐወርያት እምነት እንታይ ይብለና ከም ብሓዱሽ👈 ንሕያዋንን ንሙታንን ኽፈርድ ብኽብሪ ክመጽእ እዩ ይብለና።
ንምንታይ እዩ ከም ብሓዱሽ👈 ንብል እንተልና ምኽንያቱ አቐዲሙ መጽዩ ነይሩ እዩ ።
ብሐጥያት ምኽንያት ናይ ሎሚ 2000 ዓመት መጽዩ ነይሩ። ሐዚ ኸዓ ብዘይ ሐጥያት ካልኣይ ግዜ ንኽፈርድ ክመጽእ ስለ ዝኾነ አብ ናይ እምነት መግለጺና ከም ብሓዱሽ ንሕያዋንን ንሙታንን ንኽፈርድ ብምስጋና ይመጽእ ንብል።
ስለዚ ክርስቶስ ክርስትያን ዝኾኑ ይጽበይዎ
ክጽበይዎ ከለው ከዓ ንፍርዲ ከም ዝመጽእ እምበር ካሊእ አይነት አጸባብያ የብሎምን።
ምስ እዚ ዝተትሓሓዘ አብ ራእይ መጽሓፍ..
“እንሆ፡ ቀልጢፈ እመጽእ አሎኹ፡ ንነፍሲ ወከፍ ከከም ግብሩ ኽፈድዮ ኸኣ፡ ዓስበይ ምሳይ እዩ።”
— ራእይ ዮሃንስ 22፥12
እንሆ ቀልጢፈ ክመጽእ እየ ኢሉ ክርስቶስ ብተሎ ክመጽእ እየ ይብለና አሎ እንታይ ክገብር እንተይልና
ንነፍሲ ወከፍ ከከም ግብሩ ኽፈድዮ👈እየ ይብል
ስለዚ ንፍርዲ እዩ ቤተክርስትያ እውን አመጻጽኣኡ ትጽበላ።
“እቲ መንፈስን እታ መርዓትን👈፡ ንዓ፡ ይብሉ አለዉ። እቲ ዚሰምዕውን፡ ንዓ፡ ይበል። ዝጸምኤ ኸኣ ይምጻእ፡ ዝደለየውን ማይ ህይወት ብኸምኡ ይውሰድ።”
— ራእይ ዮሃንስ 22፥17
እታ መርዓት ዝኾነት ቅድስቲ ቤተክርስትያ ናይ ጎይታ ምጽአት ዝትጽበ ዘላ እያ።
“እቲ ነዚ ነገርዚ ዚምስክር፡ እወ፡ ቀልጢፈ እመጽእ አሎኹ፡ ይብል አሎ። ኣሜን፡ ጐይታና የሱስ፡ ንዓ።”
— ራእይ ዮሃንስ 22፥20
ስለዚ ክርስትያናት ብዚ መልክዕ ኽፈርድ ብዝመጽአሉ ኢና ንጽበዮ እምበር ካሊእ ናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ምጽኣት እንጸበ አይኮናን።
ንምንታይ ኢና ከምዚ ንብል ዘለና ፕሮቴስታንት ዓለም ክርስትና ድሕሪ ምምስራቱ ድሕሪ 1800 ዓመታት ብ19 ክ/ዘ ማለት እውን ቅድሚ 100 ዓመት ዝተጀመረ ናይ ግለ ሰባት ሀሳብ ምንጣቕ ዝብል ትምህርቲ አሎ።እዚ ናይ ምንጣቅ ዝብልዎ ትምህርቶም ክርስቶስ ቅድሚ ንፍርዲ ምምጽኡ ሓደ ግዜ ክመጽእ እዩ።በቃ አብ ማእኸል ዝኾነ ግዜ ዝመጸሉ ዘመን አሎ።እብዚ ዝመጸሉ ግዜ ከዓ ሓያል መከራ አሎ
ቅድሚ እቲ ሓያል መከራ ምምጽኡ ክርስቶስ ይመጽእ እሞ ክርስትያን ዝኾኑ ካብ ምድሪ አኪቡ ይወስድ።አብዚ ምድሪ ዝቐርዩ ክርስትያን ዘይኾኑ ሰባት እዮም።
ንሶም አብዚ ይቀርዩ መከራ ይበጽሖም እቶም ክርስትያን ግን መከራ ከይረአዩ ክርስቶስ ይወስዶም ዝብል ትምህርቲ አለዎም።
ነዚ እዮም ምንጣቅ ንሕና ንንጠቅ ኢና ዝብሉና
እዚ ትምህርቲ እዚ ፍጹም ክርስትያናዊ ዘይኮነ ናይ ስሕተት ትምህርቲ እዩ።
ብቤተክርስትያን ታሪኽ ውሽጢ ንብዙሕ ግዜ ከይተፈለጠ ጸኒሑ ዝኾነ ግዜ ምጽእ ዝብል ትምህርቲ ተልዩ እዚ ትምህርቲ ስሕተት ምዃኑ ብቀሊሉ ክንርዳእ ንኽእል ኢና።
“ኣቱም ፍቁራተይ፡ ብዛዕባ ሕብረት ምድሓንና ብዅሉ ቕንኣት ክጽሕፈልኩም ምስ ደሌኹ፡ በታ ሓንሳእ ንቕዱሳት እተዋህበት እምነት ክትጋደሉ ጽሒፈ ኽመኽረኩም፡ ናይ ግዲ ዀነኒ።”
— መልእኽቲ ይሁዳ 1፥3
በታ ሓንቲ ግዜ ንቅዱሳን ዝተውሃበት ሃይማኖት👈 ኽትጋደሉ ጽሒፈ አለኹ ኢሉ ተናጊሩ እዩሞ።ሃይማኖት ሐደ ግዜ ተዋሂቡ አሎ እዚ ሃይማኖት ወይ እምነት ምስተውሃበ አብቲ ቤተክርስትያን ተሓሊው ይነበር እምበር ዝኾነ ዘይተውሃበ ትምህርቲ ሃሊው ድሕሪ 1800 ዓመት ብዝኾኑ ውልቀ ሰባት ወይ ፕሮቴስታንት ዝጅመር ዝኾነ ክርስትያናዊ ግልጸት የለን።
ስለዚ እዚ ንጥቀት ዝብልዎ ብ1800 ብፕሮቴስታንት ዝተጀመረ ትምህርቲ እዩ።
ቀጻሊ ነዚ ትምህርቶም ማስረጃና ኢሎም ዝጠቕስዎም ጥቅስታት ክንርእ ኢና😊😊
ፕሮፌሰር አባ ሳሙኤል(Fr Samuel VC) ይባላሉ..
የሕንድ ኦርቶዶክስ አባት እና ፈላስፋም ናቸው.. በጣም ተወዳጅ ሊቅ ናቸው.. ከቋንቋ እስከ ስነ መለኮት ብዙ ያጠኑ ሲሆን ከቋንቋዎች ውስጥ ለምሳሌ ግሪክ፣ ዕብራይስጥ፣ ሲሪያክ፣ ግዕዝ እና አረብኛ የመሳሰሉትን አጥንተዋል..
ያልሰሩት ሥራ የለም ማለት ይቻላል በተለይ ecumenism ላይ ብዙ አስተዋጽዖ አድርገዋል.. ከካቶሊክ እና ኢስተርን ኦርቶዶክሶች ጋር ብዙ ውይይቶችን አድርገዋል.. የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት ላይም ያለው ግንኙነት እንዲጠነክርም ውይይቶች ውስጥ ተገኝተዋል..
ዶክቶራል ሪሰርቻቸው "Christological controversy" ላይ ነበር እና በተለይ የኬልቄዶን ጉባኤ ላይ ኤክስፐርት ናቸው.. አስቡት ያንን ሁሉ ቋንቋ ይዘው የጥንት ጽሑፎችን በተጻፉበት ቋንቋ ማገላበጡ ምን ያህል እንደሚጠቅማቸው.. ያው አንድ መጽሐፋቸውን እጋብዛችሁዋለው አረጋጉት
በነገራችን ላይ እኚህ ሰው እዚህ አዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ የሥነ መለኮት ዩኑቨርሲቲ ውስጥም ወደ 7 አመት ያህል ምናምን continuously ዲን ነበሩ.. ኡፍ አስባችሁታል ከእሳቸው መማር..?? ከሳቸው ቀርቶ እንደው ከደና ተማሪያቸው መማር እንዴት እንደሚያጓጓ የምር.. ለማንኛውም ድንቅ ሰው ናቸው የምር
የምጋብዛችሁ መጽሐፋቸው: "the council of chalcedon re-examined"
ኢንተርኔት ላይ በነጻ ታገኙታላችሁ ካልሆነ @eotcLIBRARY ላይ አስቀምጥላችኋለው አሁን✌️
@Apostolic_Answers