በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የፕሮቴስታንት መዝሙር የዘመረችው እህታችን በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ገዳም ውስጥ ነው የተደበቀችው አሉ😬😬
እመቤቴን በጣም ነው ያነደደችሽ ግን በቃ አፉ እንበላታ😬😬
በመንፈሳዊ ሕይወትህ ስትደክም
በደከምክባቸው በእነዚህ ወቅቶች ላይ ራስህን መግዛትና ከኃጢአት መራቅ ሲያቅትህ አስተውለህ ይሆናል.. ይህም ከጌታ ተለይተህ ብቻህን ማሸነፍ እንደማትችል ያስተምርሃል..
ስለዚህም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ሕይወት ስትመለስና የመንፈስ ፍሬዎች ሊታዩብህ ሲጀምሩ እንዳትኮፈስና ሌሎች ደካሞች ላይም እንዳትፈርድ ያደርግሃል..
ምክንያቱም አንተም ያሸንፈከው ኃይልን በሚሰጥህ በክርስቶስ እንጂ በራስህ እንዳልሆነ ታውቀዋለህና.. ስለዛ ለእነርሱም እንድታዝንላቸውና እንድትጸልይላቸው ያደርግሃል..
ጌታ ሁላችንን ያበርታን..
ደግሞ እንኳን አደረሳችሁ.. መልካም ቀን😊🤗
እስቲ ልጠይቃችሁ.. ኮመንት ላይ አሳውቁኝ..
በክርስቲያኖች እና በፕሮቴስታንቶች መካከል ያለ የትምህርት ልዩነት.. ለእናንተ ትልቁ ልዩነት የምትሉትን አንድ ወይም ሁለቱን ብቻ ጻፉልኝ😊😊
በአማራ ክልል አካባቢ ያሉ ወንድም እህቶቻችን አባት እናቶቻችን እንደምታውቁት በብዙ መከራ ውስጥ እያለፉ ነው እና እስቲ እንደው እንጸልይላቸው በጌታ.. ምስኪን ሕዝብ.. ከጦርነት ወደ ጦርነት.. እግዚአብሔር በቃ ይበላቸው.. እንደው ስንጸልይ አንርሳቸው ለማለት ያህል ነው..
አይዟችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን..
ጌታችን ይመጣል ለዘላለምም ከእርሱ ጋር እንኖራለን
ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩት ግን አሁን ላይ እርሱን የወደዱት ናቸው.. "ወንድም ጌታ ይወድሃል" ማለት ብቻ ሳይሆን አንተስ ጌታን ትወደዋለህ ወይ ነው..
እወደዋለሁ ካልክ እንግዲያውስ ቃሉን ጠብቅ.. ለመዳን ተጠመቅ ካለህ አሜን በል.. ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የራሱ ሥጋና ደም እንደሆነ ከነገረህ አሜን በል.. አይ ካልክ በቃ ገና አልወደድኸውም..
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለንም ወደ ቅዱስ ምስጢር እየቀረብን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ካላጠነከርን ትእዛዙን ካልጠበቅን እርሱን መውደዳችን በምን ይታወቃል..??
"ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።"
[1ቆሮ 16: 22]
@Apostolic_Answers
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤
-> በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ
መዝ 27:4
እስልምና እና ኢየሱስ
1️⃣ ቁርአን ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፡
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡" (3፡185)
ስለዚህም ሁሏም ነፍስ ትሞታለች
2️⃣ይኸው ቁርአን ደግሞ በሌላ ሥፍራ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል ፡ "..«ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም.... ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡"(4:157-158)
እዚህ ላይ እንግዲህ የኢየሱስን አለመሰቀልና አለመገደል ይናገራል.. ይልቁንም ደግሞ ሳይሰቀል ሳይገደል አላህ ወደራሱ እንደወሰደው(እንዳነሳው) ይናገራል.. ስለዚህም ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀረ
እና ምን..?? አትሉኝም..?? ካላችሁኝማ ዲየግ ወደ ሙግቴ ልግባ ሎል..
- ነፍስ ሁሉ ሞትን ትቀምሳለች
- ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀርቷል
- ስለዚህም ኢየሱስ "ነፍስ ሁሉ" ተብሎ ከተገለጸው የሰው ዘር አይመደብም።
ከዚህ ቀደምም ለማሳየት እንደ ሞከርነውም ኢየሱስ በእስልምና በዘር ደረጃ ጭራሽ የአዳም ዘርም አይደለም ያስብለዋል የሚለውን ሌላ ማሳያ ይሆናል (ስለዚህም ፍጹም ሰውነቱንም ይክዳል አምላክነቱን ብቻ ሳይሆን ማለት ነው)
ምናልባት ግን ኢየሱስ ተመልሶ መጥቶ ሞትን ይቀምሳል የሚል ሰው ካለ.. ከቁርአን በግልጽ ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣና እንደ ሚሞት የተነገረበትን ክፍል ቢሰጡን..
ቁርአን ላይ አጥተው ምናልባት ወደ ሃዲሳቱ ጎራ ለማለት ከሞከሩ ደግሞ ቁርአኑ ለእስልምና ትምህርት በቂ አይደለም ለማለት ያስደፍረናል ማለት ነው።
@Apostolic_Answers
ሰባኪ ነኝ ዘማሪ ነኝ ምናምን በሚለው ውጭ ያሉ እህቶችን ገንዘብ የምትፈልጥ ከሆነ የምር በቃ ፍልጥ ሰገጥ ነህ🤝
በቃ የምታገለግል ከሆነ አርፈህ አገልግል.. አንቺም ደግሞ አገልጋይ ነኝ ላለ ሁሉ ሳንቲም አትላኪ.. በተለይ አረብ ሃገራት ምናምን ያላችሁ.. ሠራ ሠራ ጠርቀም ጠርቀም አድርጋችሁ ተመለሱ እንጂ አታባክኑ.. ምክንያት እየፈጠሩ ሳያስነቁ ለመንጠቅ ምናምን የሚሞክሩ ስለሚኖሩ..
ያው ምንም ነገር ያለ አግባብ አይሁን ለማለት እንጂ ንፉግነትንም እያስተማርኩ አይደለም..
ቆይ ጽሑፍ እንዳይረዝምብኝ ቀጣይ ደግሞ ከእህቶች ጋር ስላለን ቅርበት እናወራለን🤭🤭 ወይስ ይብራ..?? "ይቅር አይነገር" የሚል ካለ ተበላ😬😬
@Apostolic_Answers
ወሳኝ ነጥብ ትላለህ..
የሆነ ነገር ለማድረግ ስንነሳ በዛ ነገር ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት እንደፍራለን..??
ለምሳሌ ሚስት ኖራህ እርሷን ወደ ጎን አድርገህ ሌላ ሴት ጋር ለመሄድ(በሌላ አማርኛ cheat ለማድረግ) ብታስብ.. በዚህ ጉዳይ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??
እሺ አንድ ሰው ላይ ክፋት ለመስራት ለመነሳት ብትሞክር እዚህ ሥራህ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??
ለምሳሌ እነርዚህ ነገሮች ላይ ጌታችንን ለማሳተፍ ጭራሽ አትደፍርም.. መቼስ እንደው አንደኛውን ካልናቅኸው በስተቀር..
👉ስለዛስ ምን..?? የሆነ ነገርን ስናደርግ የምናደርገውን ነገር በዚህ እንመዝነው.. እዚህ ላይ ኢየሱስን ለማስገባት ያስደፍረኛል..?? እንበል.. የማያስደፍር ከሆነ ከዛ ነገር እንራቅ ምንም ይሁን ምን
ኢየሱስ የሕይወታችን መልኅቅ
@Apostolic_Answers
አይ ያረጋል.. በጣም ነው የምወደው የምር.. ጌታ አብዝቶ ይርዳው.. እውቀት ማስተዋል ጥበብን አሁንም ያብዛለት..
ይህንን ስል ያው ምንም ሊሳሳት የማይችል የክርስትና ልኬት ነው እያልኩም አይደለም.. ያው እርሱም በተደጋጋሚ እንደሚናገረው እንኳን አንድ ግለሰብ ሲኖዶስም ይሳሳታል(እዚህ ላይ ግን እኔ የማውቀው ሎካል ሲኖድ እንጂ አለም አቀፋዊ ሲሆን አይሳሳትም.. እርሱም አለም አቀፋዊውን አላለም)
እንደው ስም መጥራት ዝገት ሊሆን ይችላል ግን መምህር ያረጋል : ብርሃኑ አድማስ እና የኔታ ገብረ መድኅን ያው በተመለከትኩት ልክ በጣም ነው የምወዳቸው..
እናንተም ልክ እንዲሁ የምትወዷቸው መምህራን ይኖራሉ.. ማንንም ስትሰሙ ግን ከጥንት በመጣው በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሚዛንነት ሊሆን ይገባዋል..
@Apostolic_Answers
የአንዲት የጸነሰች ሴት ምራቅ ወደ ሌላኛዋ ሴት ገብቶ ያችኛዋ እንድትጸንስ ምክንያት ሆነ..??
አንዲት በጣም ጎበዝ እህቴ ድርሳነ ዑራኤልን ጠቅሳ ይህ ታሪክ እጅግ ከባድ እንደሆነ አነሳች እና ትንሽ አወራን እና ያወራነው ትንሽዬ ናት ግን ከጠቀማችሁ ጠቅለል ያለውን ነገር ልስጣችሁ..
በቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት ውስጥ ለአእምሮ የሚከብዱ ተአምራትን ብናገኝ እንዲሁ ትክክል ነው አይደለም እያሉ ሲከራከሩ ከመዋል ትክክል ከመሰለህ በእምነት "በእውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን..??" ብለህ ተቀብለህ እለፍ
አይ አልቀበልም ካልክ ደግሞ ያው በመቀበል ባለመቀበል ላይ ድኅነትህ ስለማይመሰረት እንዲሁ ሳትነቅፍ እለፈው.. ነቅፈኸው ምናምን ድንገት ግን የምርም የእግዚአብሔር ተአምር ቢሆንስ..?? ተበላህ ማለት አይደል..
ሰው ለጸሎት እና ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ጊዜ ቢሰጥ መልካም ነው.. ያው እንዲሁ ይሄኛው ተአምር ትክክል ነው ይሄኛው አይደለም ምናምን እያለ ፈራጅ ሆኖ ቁጭ ብሎ ሲከራከር ከሚውል ማለት ነው።
ያው ትምህርት ነክ ነገር ቢሆን ቀላል ነው በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መዝነኸው ታልፋለህ.. ተአምር ሲሆን ግን ይለያል.. ለአእምሮዬ ከባድ ነው ብለህ ብትነቅፍ ያ ተአምር ግን የምርም የእግዚአብሔር ሊሆን ስለሚችል ካልተቀበልክ አልተቀበልክም ነው ቢያንስ ግን አትንቀፍ ነው።
ያው ከእኛ በዘለለ የአንድ መምህርንም ትምህርት ሰማሁና ከሰማሁትም አንጻር አካፈልኳችሁ
@Apostolic_Answers
ለዩኒቨርሲቲ እና high school ተማሪዎች የሰጠሁዋችሁን የቤት ሥራ አሁን አስገቡልኝ🤪🤪
@aba_abi ላይ ላኩልኝ እስከ ነገ ድረስ
የቤት ሥራ ለዩኒቨርሲቲ እና Highschool ተማሪዎች
ትምህርት ቤቶች ላይ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሥራ ይጠበቅባታል..
Highschool ላይ እንዲሁም በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትልቅ ሥራ እንደሚጠበቅብን ግልፅ ማሳያዎች አሉ.. በሌላ ቤተ እምነቶች እና በዓለማዊነት የሚወሰዱ ክርስቲያን ወንድም እህቶቻችን ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም..
እናም የቤት ሥራው ምንድን ነው..
1. በሌላ ቤተ እምነቶች የሚሠሩ ሥራዎች ባስተዋላችሁት ልክ ምን ይመስላል
2. ትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የክርስቲያኖች(ኦርቶዶክስ) እንቅስቃሴ ምን ይመስላል
3. ክርስቲያኖች በእምነት እንዲጸኑ እኛ ጋር ቢኖር ወይም ቢደረግ ብላችሁ የምትመኙት..
ይህንን መልሱና ከዛም ነገ እንድትልኩልኝ አድራሻዬን አስቀምጥላችሁዋለሁ
"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"
"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"
"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"
ዲ/ን ያረጋል
የሮም ካቶሊክ እና ማርያም
- 16ኛው ክ/ዘመን ጉባኤ ትሬንት ላይ እመቤታችን ምንም አይነት ኃጢአት እንዳልሰራች ገልጸዋል.. (ሁሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት ያምናሉ ይሄንን)
- በ1854 immaculate conception የሚል ትምህርት (እመቤታችን አዳም ከወደቀ በሁዋላ ከእርሱ ያልተገኘች የሚያስመስል ትምህርት) ዶግማ አደረጉ.. ይሄን ዶግማ ባያደርጉት መልካም ነበር.. በየትኛውም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት በኢትዮጵያውያም ጨምሮ እንዲህ ያለ ዶግማ የለም.. ካቶሊክም ዶግማ ካደረገችው 160 አመቷ አካባቢ ነው
- በ1950 ደግሞ የእመቤታችንን እርገት ዶግማ አደረጉት(እኛ ጋር ዶግማ አይደለም) ግን ሌላ አወዛጋቢ ነገር አለ እዚህ ላይ.. ጉባኤው ላይ የተወሰነው እንዲህ በሚል ቃል ነው: "የምድራዊ ሕይወቷ ዘመን በተጠናቀቀ ጊዜ በሥጋና ነፍስ ወደ ሰማይ ተወሰደች" ምኑ ነው የሚያወዛግበው..?? እመቤታችን ስትወሰድ እንደ ማንኛውም ሰው ሞታ ከዛ ተነስታ ነው ወይስ እንዲሁ ሳትሞት የሚል ጥያቄ ያስነሳል..
ያው አዳም ከወደቀ በሁዋላ ከእርሱ እንዳልተገኘች የሚመስል ነገርን አስቀድመው ስለደነገጉ "ሞታለች" የሚለውን ቃል በዶግማ ውስጥ ማካተቱን የፈሩት ይመስላሉ.. እና ነገረ ማርያም ሲለጠጥ ወደማይወጡበት ችግር ውስጥ ይገባሉ..
እኛ ጋር ዶግማችን ሁሉ ከክርስቶስ ጋር መገናኘት አለበት.. ስለዚህም ነገረ ማርያም ላይ ዶግማው "ወላዲተ አምላክ" መሆኗ ነው.. ይህ ነገረ ክርስቶስም ስለሆነ.. ከዚህ በተረፈ ድንግልናዋ እና ንጽህናዋ ክብርዋ በምልጃ አጋዥነቷ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ትምህርቶች ናቸው.. ምክንያቱም አባቶቻችን በተለይ ስለ ድንግልናዋ ጥብቅና ሳይቀር ቆመውለት አስተላልፈውልናል.. ሲቀጥል አምልኮዋችን ውስጥም አሉ..
@Apostolic_Answers
ኅቡእ ስሞች..??
አንዳንድ የጸሎት መጽሐፍት ላይ የአምላክ ኅቡእ ስሞች ተብለው የሚዘረዘሩ አሉ ኃይልንም ያደርጋሉ ይባላል..
እና እኔስ ጸሎቴ ውስጥ ልጠቀማቸው..??
ተጠቀም አትጠቀም አልልህም.. ግን እኔ አልጠቀምባቸውም.. በተለያዩ መጽሐፍት ላይ በርካታ ናቸው እና የምርም የአምላክ ስም መሆናቸውን አላውቅም.. በዛ ላይ ትልቅ ሃይልን የሚያደርግ ኢየሱስ የሚል ስም አለን..
ከምንም በላይ ደግሞ ታላቁ ጸሎት ቅዳሴያችን ላይም አንጠቀምም..
እና ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንዲህ ያለ ነገር አይታይም እኔ እስከማውቀው
@Apostolic_Answers
"ፕሮቴስታንቲዝም" ከክርስትና ጋር ያለው ትልቁ ልዩነት ያው ዋናዎቹን ለማስቀመጥ ያህል:
- "ጸጋ ብቻ" ሲሉ የእኛን ነፃ ፈቃድ መካዳቸው(በተለይ ካልቪኒስቶች)
- ጥምቀት ለድኅነት አያስፈልግም ማለታቸው
- ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም ማለታቸው
- ምስጢረ ክህነትን አለማመናቸው
- የምትታይ ቤተ ክርስቲያን የለችም ማለታቸው
- የእውነተኛነት ልኬት የሆነውን ቅዱስ ትውፊት አለመቀበላቸው
ሌሎችም በርካታ ሊነሱ ይችላሉ.. የተሻሉ የሚባሉ ፕሮቴስታንቶችን ያማከለ ነው ይሄ
ኢየሱስ ይማልዳል አይማልድም የሚለውን ዝርዝር ውስጥ አላካተትኩትም ምክንያቱም አሁን አሁን ብዙዎቹ "ይማልዳል" የሚለውን ቃሉን ይጠቀሙታል እንጂ አሳቡ ከእኛው ጋር ተመሳሳይ እየሆነ ነው.. የአሳብ ልዩነት ከሌለ ወሳኞቹ ላይ ትኩረት ማድረጉ መልካም ነው
@Apostolic_Answers
“መልአክን ከሰማይ ወደ ምድር የጣለው ትእቢት ነበረ.. ሰውንም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርገው ትህትና ነው"
ትህትና ትእቢተኛውን ጠላት የምንረታበት ትሁቱን ጌታ የምንመስልበት ትልቅ መሣሪያ ነው.. ትህትና ስላችሁ ሰው ፊት ለመታየት ያህል ብቻ እንዲሁ መተወን ሳይሆን እውነተኛ ትህትናን ማለቴ ነው.. እውነተኛ ትህትና አንደበት ላይ ሳይሆን ልብ ላይ ነው..
እውነተኛ ትህትና የሚመጣው ትሁቱ ጌታ በእኛ ሲኖር ብቻ ነው.. እርሱ በእኛ የሚኖረው ደግሞ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ስንካፈል ነው..
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:
"ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ"
[ማቴ 11:29]
@Apostolic_Answers
ሰይጣንን ፍራቻ..??
ጠንቋይ ትፈራለህ..?? ወይም በሌላ ቤተ እምነት በክርስትና ስም የሚሰራውን መንፈስ ትፈራለህ..??
ፍራቻ የሚመጣው ከእምነት ጉድለት ነው.. የምን እምነት ..?? ከክፉ ሁሉ በሚጠብቀን በእረኛችን ላይ ያለን እምነት.. እግዚአብሔር የምርም እረኛችን እንደሆነ በሙሉ ልባችን ካመንን ምን ያስፈራናል..?? ምክንያቱም ከእርሱ የሚያልፍ የለም..
ስለዛ እረኛችንን ስናውቀው ስናምነው ፍራቻ ይርቃል.. ከመዝሙረኛውም ጋር ሆነን እንዲህ እንላለን:
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው"
ግን.. ከእረኛችን አንራቅ.. ሁሌም እርሱን ጠባቂያችን እናድርግ..
@Apostolic_Answers
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦
"ጌታ ይገሥጽህ" አለው እንጂ #የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
[ይሁዳ 1:3]
አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
[141:3]
@Apostolic_Answers
ጌታችን የእኛን ባህሪ የነሳውና የተዋሃደው ሊፈውሰው ነው..
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዲህ ይላል..
“ያልነሳውን አላዳነውም: ከመለኮቱ ጋር የተዋሐደው እርሱ ግን ድኗል:: ግማሽ አዳም ብቻ ወድቆስ ቢሆን(ነፍሱ ቀርታ ሥጋው ብቻ ቢሆን ውድቀት የገጠመው) እንግዲያውስ ክርስቶስም የሚነሳውና የሚያድነውም ግማሹን ሊሆን ይችላል.. ነገር ግን ሙሉ ሰውነቱ(ባህሪው) ከወደቀ ግን እንግዲያውስ ከሙሉ የወልድ ባህሪ ጋር ሊዋሐድ እና ሙሉ በሙሉ ሊድን ይገባዋል::”
[ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ : መልእክት ወደ ክሊዶንዩስ (To Cledonius the Priest Against Apollinarius)]
@Apostolic_Answers
ትእቢት ላስቸገረው ትሕትናን ለሚፈልግ ሰው ፍቱን መድኃኒት የሆነ ጸሎት.. ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም.. ሉቃስ 1 ላይ ያለው ወላዲተ አምላክ የጸለየችው ማለት ነው..
የሉቃስ ወንጌል 1
47፤ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
በዚህ የሚጀምረው ጸሎት..
ይህ ጸሎት ቅድስት ድንግል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወክላ የጸለየችው ጸሎት ይመስላል.. ያው ጸሎቱ ከእመቤታችን ውጪ በግለሰብ ደረጃ ለአንተ አይመጥን ይሆናል ለቤተ ክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያን ግን ኖርማል ነው.. አንተ ደግሞ የዛች ቤተ ክርስቲያን አባል ነህ እንኳን ደስ አለህ😁😁
ስለዚህም እንዲሁ እመቤታችን እንዲህ አለች ብሎ የመድገም ነገር ብቻ ሳይሆን አንተ ራስህ ደግሞ የቅድስት ቤተክርስቲያን አባል መሆንህን እያሰብክ በጣም ተረጋግተህ ከወላዲተ አምላክ ጋር ጸልየው..
በዚህ ውስጥ ወይ ትእቢት እየተሸነፈ ትሕትና እያየለ ይሄዳል ወይ አንተ ተሸንፈህ ጸሎቱን ከልብ ለመጸለይ ይደብርህና ትተወዋለህ
@Apostolic_Answers
መንፈስ ቅዱስ
ጌታ ኢየሱስ ሲያርግ "ሌላ አጽናኝ" ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች ተጥለን ነበር..
ቤተ ክርስቲያንን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሁላችን ተበትነን ነበር
በክርስቶስ የተሰራውን የማዳን ሥራ በእኛ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ያድሰን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ኖሮ በኢየሱስ የተሠራውንም የማዳን ሥራ ባላገኘንና በሞት ውስጥ በቀረን ነበር
በደከመን ጊዜ ያበረታን ዘንድ በበደልንም ጊዜ ወደ ንስሐ ይመራን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ለኃጢአት ባርያ ሆነን በቀረን ነበር
ቅዱሳንን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ራሱን ክርስቶስን እንዲመስሉ ለፈተናዎች ሁሉ ያስጨክናቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ክርስቶስንስ መምሰል ከየት መጥቶ
ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ያስጨክነን.. ለእርሱ ምስጋና ይሁን.. አሜን😊
@Apostolic_Answers
10,000 ገባን ለካ😝😝 በስንት ጊዜው😁😁
ቴሌግራም በጣም ቀርፋፋ ነው ግን ደግሞ በጣም cool ነው.. ልክ እንደኔ ማለት ነው😎😉 ሎል🤭🤭 የምር ግን ቴሌግራም በጣም ደስ ይላል..
ቲክቶክ በጣም በጥንቃቄ ካልተያዘ ራስን ማጥፊያ ቦታ.. ተመልካቾቹን ብቻ ሳይሆን የሚያገለግሉ ልጆችም የጸሎት እና የማንበቢያ ጊዜያቸውን ይሻማል በጣም..
ቴሌግራምም ጥንቃቄን ይፈልጋል በእርግጥ..
ብቻ ጸልዩ አንብቡ እደጉ ምናምን🤪🤪
የሴት ጓደኛ(ፍቅረኛ ትላለህ😁) ያለችህ ወንድሜ ስለ ኢየሱስ ታወራታለህ..??
ትዝ ይለኛል ከትንሽ ጊዜ በፊት አንድ ጓደኛዬ እንዲህ ብዬ ስጠይቀው ሳቅ እያለ "ምን እንድትጠላኝ ነው..??" ብሎኝ ነበር.. እና ልክ በጊዜው የማይጠበቅ መልስ ስለሆነ አስቆኝ ነበር.. በእርግጥ እሱም እንደ ቀልድ ነው ያለኝ.. አሁን እንደውም እሷ ናት ስለ ኢየሱስ የምትነግረው ሎል
ግን ደግሞ የምርም እንዲህ ያሉ ነገሮች የሚፈጠሩ ከሆነ ከባድ ነው.. አንዳንዶቻችን ጭራሽ ስለ ኢየሱስ መወራት ሲጀመር የምንደነግጥም አለን.. ይህንን ስም ሲሰማ ሊደነግጥና ምቾት ሊነሳው የሚገባው ጠላታችን ዲያቢሎስ ብቻ ነው.. ስለ ኢየሱስ በየቦታው ልናወራ ይገባል.. ልናወራ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን ልንኖረውም ይገባል
ቆንጂት ከጓደኞችሽ ጋር ሆነሽ ስለሆነ ወንድ ለማውራት ካላፈርሽ ስለ ኢየሱስ ማውራት ጭራሽ ሊያሳፍርሽ አይገባም
ብሮዬ አንተም እንዲሁ.. በተለይ ጓደኛ ካለችህ አውራት ስለ ኢየሱስ ለሌሎች ጓደኞችህም አውራቸው.. ከራቁህ ይራቁህ.. የኔ ኢየሱስ የምደራደርበት አይደለም እንበል..
አለም እኮ ቀስ በቀስ በጌታችን ኢየሱስ እንድናፍር እያደረገችንም መሰለኝ..
ሕይወታችን ኢየሱስ ነው
@Apostolic_Answers
መስቀል መድኃኒታችን ነው..??😬😬
"መስቀል" ስንል ምን እያልን ነው የሚለውን እኛን ጠይቁን ፕሊስ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቻችን..
መስቀል ስንል እንደው የሆነ የተመሳቀለ እንጨትን ብቻ የማሰብ ጉዳይ አይደለም.. ይልቁንም እዛ መስቀሉ ላይ የኛ ኢየሱስ እጆቹን ዘርግቶ ምን ያህል እንደሚወደን፤ የአጋንንትንም ራስ ሲቀጠቅጥ፤ በነገሮች ሁሉ ኃይል ሲሆነን ሲያሳየን ይታየናል
ስለዚህም መስቀል ስንል እጹ ብቻውን ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ነው የምናየው.. "መድኃኒት" ካልነው እንግዲያውስ መስቀል ማለታችን እጹ ብቻውን ሳይሆን ኢየሱስንም አብረን ስለምንለው ነው።
ቅዱስ መስቀል ኃይላችን ነው.. የክርስቶስ መስቀል ምርኩዛችን ነው። የክርስቲያኖች ትልቁ አርማችን ምልክታችንም ነው..
አንዳንድ ሰው ጊዜ ሰጥቶ "የኢሉሚናቲ የሰይጣን ምልክት" እያለ ያወራል.. ያውም ምንም በማያውቀው ነገር.. ስለ ክርስቲያኖች ምልክት ስለ ኢየሱስ መስቀልስ ጊዜ ሰጥተህ ታወራለህ ወይ..??
የኢየሱስ መስቀል ስንል ስለ እንጨቱ ብቻ እያልን አይደለም.. ይልቁንም እዛ እንጨት ላይ የኔና የእናንተ ጌታ ኢየሱስ ክንዶቹን ዘርግቶ እለተ ዐርብ ላይ ያለውን ያንን ነው የምንናገረው።
በመስቀሉ አናፍርም.. በእርሱም የምንሰብከው የተሰቀለውን ክርስቶስን ነውና
@Apostolic_Answers
ስትጸልይ ምንድን ነው የሚያጣድፍህ..?? እስቲ ረጋ በል..
ባክህን እኔም እንደዛው ነኝ😭😭 አንዳንዴማ ለራሴውም የምጸልይ አይመስልም እኮ.. የሆነ በቃ ይህንን ማንበብ ወይም ማለት አለብህ ብቻ ተብዬ የተገደድኩ ይመስል እሷን ለመጨረስ ያህል ፈጠን ፈጠን ማለት.. በተለይ ለሆነ ጉዳይ ከቸኮልክማ ተው😁😁
ስትጸልይ ቅዱሳኑ ከአንተ ጋር እንዲሆኑ ትፈልጋለህ.. ግን ቅዱሳኑ እንዳንተ በሩጫ ሲጸልዩ አስበው.. ለምሳሌ በጸሎተ እግዝእትነ ማርያም(የማርያም ጸሎት) ልትጸልይ ቆመህ መቼስ እመቤታችንም አብራህ እንድትጸልይ ትጠብቃለህ.. እና የእርሷ እርጋታ አለ.. ያንተ ግን ጥድፊያ.. እመቤታችን ተረጋግታ እንደምትለው ብትለው ሃሪፍ ነው..
አባታችን ሆይን ስትጸልይ እያንዳንዱን ቃልና ሃረግ በጣም በእርጋታ በለው.. ያኔ ወደ እግዚአብሔር በጣም ያቀርብሃል
ስትጸልይ ከአባትህ ጋር እየተገናኘህ ነው.. አባትህ ደግሞ አምላክህም ነው.. ስለዛ ረጋ በል👊😊
@Apostolic_Answers
"ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላድገዛለት ይገዛል" 1ቆሮ 15: 28
https://vm.tiktok.com/ZM2nqCGCe/
ፊራ ከባድ ሰው.. ጌታ ይመስገን
ታናሽ ወንድማችን ነው(በእድሜ).. እኔ እንኳን የማውቀው ከ2 አመት አካባቢ በፊት "ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ አገልግሎት" በሚል ስም ተከታታይ የክርስትና ትምህርት የምሰጥበት ቻናል ላይ ጀምሮ ይመስለኛል..
እናማ አምና 12ኛ ክፍል ተፈትኖ 609 ነበር ያመጣው.. እና ከዚያም ፈተና ተፈትኖ አልፎ መንግስት የሰጠውን ዱባይ ሄዶ የመማር እድል አገኘ..
ስለ ሁሉም ነገር እምላከ ተክለሃይማኖት ይመስገን.. ጻድቁ አሁንም በአማላጅነቱ አይለይህ.. እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳህ
እንኳን ደስ አለህ ብሮ..
ሰላም ለእናንተ ይሁን የኔ ተወዳጆች
ያው ባለፈው ግእዝ ጀምረን ነበር.. እና በአንዳንድ ምክንያት እዚ ማካሄድ ስላልቻልን.. እኔም ስላልተመለስኩ መምህራችን ጴጥሮስ በሌላ በሱ ቻናል ላይ የሚቀጥለው ይሆናል..
ይጠቅማችሁዋልና እንደው በጌታ ሳትረሱት ከታች ባለው ሊንክ join በሉት
@geazlekulu
@geazlekulu
👆👆👆👆👆👆