በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ወንጌል አንድምታ ላይ:
ማቴ 12፡32 ትርጓሜ
እውን "መካነ ንስሐ"(purgatory) ኦርቶዶክሳዊ ነው..?? አይደለም ይህ የካቶሊክ ትምህርት ነው.. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም እንዲህ ያለ አስተምህሮ..
አንድምታ በእጅጉ ሕይወትን በሚሰጥ እውቀት የተሞላ ድንቅ ትርጉዋሜ ነው ግን ያው አንዳንዴ እንዲህ በስህተት ሊገባ የሚችል ነገር ደግሞ ሊገኝ ይችላልና የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስለምናውቅ በስህተት እንደ ገባ(ወይም እንደተባለ) አስበን እናልፈዋለን.. ኖርማል ነው..
የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ(ሃይማኖታችን) ውስጥ ግን ምንም እንከን ሊገኝ አይችልም.. እሱን መቼም እንዳትረሱ..
@Apostolic_Answers
አንዳንዴ ክርስቲያኖች አስተሳሰባቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል እያልኩ የማካፍላቸው አሳቦች አንዳንዶችን የሚያስቆጣ አንዳንዶችንም የሚያስደነግጥ ሆኖ አገኘዋለው.. አንዳንዴ የክርስትና አስተምህሮ ምንድን ነው የሚለውን ለይቶ ያለማወቅ ችግር ኖርማል ክርስቲያኖች ላይ ብቻ ሳይሆን "አገልጋዮች" ላይም ይታያል..
ለምሳሌ ተአምሩ ላይ እንዳነሳሁት
እና ለመተቸት የሚሯሯጡ ወንድሞች ምናምን አያስጨንቁም.. የሚያስጨንቀኝ ከኔ አንዳንድ ነገሮችን የሚሰሙ ወንድም እህቶች ጉዳይ ብቻ ናቸው..
ስለዛ የእናንተን አሳብ ማወቅ ፈለኩ.. እንደዚህ ዓይነት ትምህርቶችን ስትሰሙ የተወሰነ ይረብሻችሁዋል ስለዚህም ይቅር ወይስ ለእናንተ ኖርማል ነው.. ያስፈልጋሉ ብዬ የማስባቸውን ላካፍላችሁ..??
ያው ለዚህ pol አዘጋጅላችሁዋለሁ ከታች አንዱን ትመርጣላችሁ ወደ ማታ ላይ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ..
የዮሐንስ ወንጌል 1
19፤ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
20፤ መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
21፤ እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም፡ አለ። #ነቢዩ_ነህን? አይደለሁም፡ ብሎ መለሰ።
ዮሐንስ እርሱ ክርስቶስ እንዳልሆነ መሰከረላቸው በኋላም ዮሐንስ ኤሊያስ እንዳልሆነም መሰከረላቸው ግን ቀጣይ ደግሞ "ነቢዩ ነህን?" ብለው ጠይቀውታል.. ልብ በሉ "ነቢይ ነህን?" አላሉትም ይልቁንም "ነቢዩ ነህን" ነው ያሉት እርሱም "አይደለሁም" አለ..
ጥያቄው፡
"ነቢዩ ነህን?" ሲሉ ማንን እያሰቡ ነው..??
ኧረ ጋይስ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁና መልሱ ከዛም ይህንን ጥያቄ ከየት እንዳመጣሁት እስቲ ገምቱ..
1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንት የብሉይ እና ስንት የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍትን ይዟል..??
2. አብዛኛውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት የጻፈው ማን ነው..??
ይህ ከምን ፈተና ላይ የተገኘ እንደሆነ እስቲ ገምቱ በዛውም😝😝
ዲያቆን ሄኖኬ ለገና ያሰበውን መንፈሳዊ መርሃ ግብር አየሁ እና የምር ይመቸው.. ሄኖኬ ምርጥ ሰው ነው.. ጌታ ይርዳው.. መዝሙር እና ጸሎቱንም እናለማመዳችሁዋለን ቀኑ እስኪደርስ ብለዋል እና ልንቀውጠው ነው..
የምር እቺ ቀን የማትረሳ የምስጋና ቀን ነው የምትሆነው.. እግዚአብሔር ይርዳቸው ይርዳን
ዮኒ በሚም ተመልሷል.. እሱ ነው የሰራው😁😁
ስንቱን ዘለን ዕቅበተ እምነት ላይ እንዳረፍን😁😁ይሄ ዕቅበተ እምነት አይደለም የምር😁😁
@Apostolic_Answers
ኧኸ ምርጦች.. ይህንን ዓመት በቅዳሴ እንደ ጀመራችሁት ተስፋ በማድረግ (ያው ያልሰቀደሳችሁም ኖርማል ነው የዓመቱን የመጀመሪያ እሁድ አትቀሩም😉)
እና ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
"ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል"
[ማቴ 11:5]
ምናልባት ካወቃችሁ.. በመምህራን ወይም በሌሎችም ወንድሞች የሆነ አዳራሽ ተከራይተው ምናምን ለአንድ ቀን መንፈሳዊ ፕሮግራም ያዘጋጃሉ.. ያው ታዳሚዎቹም የተወሰነ ብር ከፍለው ነው የሚገቡት..
እና ምን አሰብኩ..?? እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢረዳን በዚህ ዓመት ቢያንስ አንድ ቀን ጎዳና ላይ የሚኖሩ ወንድም እህቶቻችንን ሰብስበን ጸዴ መንፈሳዊ ፕሮግራም እናዘጋጅላቸዋለን.. እና ወንጌል ለእነርሱም ይሰበካል.. በዚህ ምድር ቤት ባይኖራቸው እንኳን በሰማይ ግን አባታቸው ያዘጋጀላቸው በገንዘብ የማይታመን መኖሪያ እንዳላቸው ይነገራቸዋል.. ወደዚህ ዘላለማዊ መኖሪያቸውም ይገቡ ዘንድ ወደ ንስሐ እና ቅዱስ ምስጢር እንዲቀርቡ ይሰበክላቸዋል.. ስለዚህም የኢየሱስ ፍቅር በልባቸው በዝቶ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል" ወደ ማለት ያድጉ ዘንድ.. ያው ይሄ እየጠነከሩ ሲሄዱ ነው የዛንው ቀን ያልቃል ማለቴ አይደለም😁😁
አዲስ ዓመት ሲመጣ እቅድ የማውጣት አባዜ ሲኖርብህ😁😁 ብቻ ግን እኛ ባንችለው ራሱ ሌሎች የምትችሉ አድርጉት እስቲ😊🤗
@Apostolic_Answers
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥
መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
መዝሙር 27:4
መልካም ቀን😊🤗
ይህ ለቤተ ክርስቲያን እንግዳ ነው..??😬😬
https://vm.tiktok.com/ZMj68Wmyn/
ሃሪፍ ክርስቲያን ዐቃቤ እምነት(የእምነት ጠባቂ) ለመሆን የሚያስፈልግህ ምንድን ነው..??
1. ቅዱስ ቁርባን
2. ቅዳሴ አለመቅጣት (መጸለይም)
3. ከምታወራበት ጊዜ በላይ ማንበብ
4. ቋንቋ ኢንግሊዘኛ አንብበህ መረዳት ብትችል.. ያው ግእዝም ብታውቅ ይጠቅማል..
ምን ላንብብ..?? እንዴትስ ላጥና..?? የሚለውን ዝርዝር አሳብ ቀጣይ ትላለህ😁😁
አስቀያሚ አጋጣሚ😭😭
አርፍጄ ነበር የተኛሁት.. ያው ለቅዳሴ ደግሞ በጊዜ መነሳት አለብኝ.. 11:30 ምናምን ተነስቼ መሄድ አለብኝ(አጠገቤ ነው)
አርፍጄ ወደ 7 ሰዓት ላይ ተኝቼ ጭራሽ 9 ሰዓት ስልክ ቢደወልብኝስ🤦♂️🤦♂️
ይኸው ተመልሼ መተኛት አቅቶኝ ከአንድ ሰዓት በላይ ታገልኩ ለመተኛት ግን ወፍ😭😭
ቅዳሴ ሲያልቅ ደግሞ ጭራሽ ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ጋርም የተወሰነ ጊዜ እንደማሳልፍ ትዝ አለኝ🥹🥹
ይበለኝ አርፍጄ ተኝቼ እና ስልኬን ከፍቼ ነው ጉድ የሆንኩት😆😆
እውን ይህ ኢ-መጽሐፍ ቅዳሳዊ ነው..??
https://vm.tiktok.com/ZMjNBGa4X/
ሐዋርያዊ መልሶች - መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት
ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀመርን.. ስለዛ ከዚህ ቀደም ተመዝግባችሁ አጋጣሚ ትምህርቱ ያለፋችሁ እንዲሁም ጭራሹኑ ያልተመዘገባችሁም አሁን መመዝገብ ይቻላል..
@aklilabi ላይ ጆይን በሉና እዛው ላይ አሳውቃችሁዋለሁ
ዮው.. ገና ላስመርጣችሁ pol ሳላደርግ ብዙ ኮመንት ሰጣችሁና ያው የአብዛኛዎቻችሁን አመለካከት አይቼበታለሁ.. እና ያው ከኔ አሳብ ጋር የተመሳሰለ ነው ምናልባት እዚ ብዙ ጊዜም አብረን ስለቆየን ለመግባባት አንቸገርም መሰለኝ.. ስለዛ ፖሉን ተውኩት
ብቻ ግን እስቲ የጠራውን የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለሁሉም ክርስቲያኖች ማዳረስ ላይ ብቻ ትኩረት እናደርጋለን.. በዚህ መካከል አስተምህሮዋችን ያልሆኑትንም የምናይ ይሆናል..
ጌታ ሁላችንን የእርሱን ትምህርት እናውቅና በእምነትም ከፍ እንል ዘንድ ይርዳን።
ሰላም እደሩልኝ
"ነቢዩ ነህን..??"
በአጭሩ ሙሴ የተናገረው ነገር አለ እንዲህ ሲል:
ኦሪት ዘዳግም 18
16፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ #ነቢይ_ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።
ይህንን ነቢይ ይጠብቃሉ አይሁዳውያን.. እናም ይህ "ነቢይ" የተባለው ደግሞ ይመጣ ዘንድ ያለው መሲሑ(ክርስቶስ) ራሱ ነው.. ጴጥሮስ በቤተ መቅደስ እንዲህ ሲል እንደ መሰከረ:
የሐዋርያት ሥራ 3
22፤ ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።
23፤ ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች፡ አለ።
24፤ ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ 👉ስለዚህ ወራት ተናገሩ።
ኢየሱስ ነቢይ ነውን..?? ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር ሰምቶ የሚናገር እንዲሁም ሰውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምር መምህር እንደማለት ነው.. ጌታ ኢየሱስ ደግሞ በባህሪው ከአብ ጋር አንድ ሆኖ የአብ ልጁ እንደ መሆኑ በአብ ዘንድ ያለውን ገልጦታል ተናግሮታል.. ከዚህ አንጻር ነቢይ ሊባል ይችላል..ከነቢያት እንደ አንዱ ሳይሆን የባህሪ ነቢይ ነው እርሱ..
ታድያ ግን መጥምቁ ዮሐንስን የጠየቁት አይሁዳውያን ሙሴ የተናገረለት ነቢይ ከመሲሑ ሌላ ስለመሰላቸው "መሲሑ ነህን..??" ብለው ከጠየቁና ከተመለሰላቸውም በሁዋላ "ነቢዩ ነህን..??" ብለው ጠይቀውታል..
እና እንዲያ ነው እላችሁዋለሁ..
ጌታ ኢየሱስም ሲናገር እንዲህ አለ:
የዮሐንስ ወንጌል 5
46፤ ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።
@Apostolic_Answers
ነገ እሁድ ነው.. በጠዋት ወደ ቅዳሴ ልንሄድ ነው😃😃
ነገ ቅዳሴ ላይ የሚነበበውን የጳውሎስን መልእክት እና የወንጌል ክፍል ይዛችሁ ጠዋት አካባቢ እሱ ላይ አውሩበት
ለአሁን ግን እስቲ ደስ ያላችሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ኮመንት አድርጉ እና ሁላችሁም ሌላው የለጠፈውን እያነበባችሁ እንቅልፋችሁንም አሳምሩ.. ከቻላችሁ የተረጋጋ መዝሙር እየሰማችሁ አንብቡ ምናምን
የኔን እዚው ላስቀምጥ፡
👇👇👇
"በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ፡
እግዚአብሔር ይመስገን። "
[መዝሙር 31: 21]
እግዚአብሔር አባታችን.. እንወድሃለን አባ.. ተመስገን..
ወኬ ወኬ.. ዛሬ ደግሞ ሁለት ወንድሞቼ ማለትም ልደት እና ዲያቆን አማን(ቲክቶክ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚሰጡት) አዲስ የቴሌግራም ቻናል ስለከፈቱ እናስተዋውቅላቸዋለን🤪🤪
እስቲ ሂዱና ሰርፕራይዝ አድርጓቸው😁😁
ዲያቆን አማን 👉 @house_of_immanuel
ልደተ-ቃል 👉 @christian_answers
ኤዲቲንጉዋን ለጊዜው እርሷት😁😁 ቀጣይ እናሻሽለዋለን
https://vm.tiktok.com/ZMjrC43hq/
ከአንዱ ጉዋደኛዬ የተላከልኝ መልእክት 😁😁
ስማ!!አንተ ዕለታዊ የነዳጅ ዋጋ የሆንክ ሰው🤪🤪አይ እንኳን ሰላም አደረሰህ ይሄ አመት የቅዳሴ(ያው እንደምታስቀድስ አውቃለሁ አለበዚያ እንደዚህ ልትሆን አትችልም)እና የማህሌት አመት (ማህሌት ምናምን ሚቆም ሰው ቅናት ዝሙት ትዕቢት ይጠፋለታል ሲል ሰምቻለሁ ዲ/ን ብርሀን አድማስ)ይሁንልህ በየደብሩ እየዞርን ምናድር ያድርገን!
ከዚህ በላይ በቤቱ ላሉት መልስን ለወጡት ነፍስ ደግሞ መመለስ ምክንያትን አብዝቶ ይስጥህ!!በየቤቱ እየዞርን ልጆቻቸው ጴንጤ የሆኑባቸው ቤተሰቦች ቤት ሄደን ተከራክረን ወደ በረት ምንመልስ ያድርገን! ከዛ ወላጆች ደስ ብሏቸው ምን እናድርግላችሁ?ሲሉን አይይ ምንም ቸኮሌት ብቻ ስጡን የምንልበት አመት ይሁንልህ![🤭]
ብቻ ደስተኛ ነኝ አንተ በመኖርህ ብዙ ጠቅመከኛል ብቻ ጌታ ከእናቱ ጋር እና ከቅዱሳኑ ጋር ሁሌም ካንተ ጋር ይኑር መልካም በአል አሜን የማይነበብ ፊርማ!እንዱ ለአክሊለ ሰማዕት(አኬ) ከላከው የተወሰደ ይመቾት❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ለማንኛውም ሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ😊🤗
ሰንበት ት/ቤት ዛሬ የዶግማ ኮርስ ፈተና ፈትኛቸው🤦♂️🤦♂️
ሙሉውን ደረቅ ጥያቄ ነበር እና በጣም ከብዷቸው ይኸው መልስ መስጫውን በነጠብጣብ አድርገው መስቀል ሰርተውበት ሰጡኝ😭😭
እኔም ጥያቄውን ረስቼው የሰሩትን የመስቀል ምልክት ውበት እያየሁ ማርክ እየሰጠሁ ነው😭😭 (ደግሞ ስቀልድ ነው😁😁)
ግን ክርስቲያኖች አስተምህሮዋችንን በደንብ ልንማር ልናውቅ ይገባል
"ለእናትህ ሁለተኛ ልደትን ከውኃዎች የሰጠሃት ልጅ ሆይ"
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ : በእንተ ልደተ ክርስቶስ : hymn 11
ለእናቱ ሁለተኛ ልደት የሰጠ ልጅ😊😊
@Apostolic_Answers
አንዱ ወዳጄ "ሃሪፍ ዐቃቤ እምነት ነኝ ብለህ ታስባለህ ብሮ" ብሎ ጠየቀኝ..
አዲስ ነው እዚህ መሰለኝ.. ያው ከዚህ ቀደምም ስለተናገርኩ.. እኔ መምህርም ዐቃቤ እምነትም የምባል አይደለሁም.. ወደፊት ሃሪፍ ዐቃቤ እምነት የመሆን ፍላጎቱ አለኝ ጌታ ይርዳኝ..
ለጊዜው ግን በስሱ የምናውቃትን ከክርስቲያን ወንድም እህቶች ጋር ማውራት እንጂ ሌላ ምንም የለም😁😁
አንድ በጣም የሚያስፈራና የሚያሳፍርም ነገር😳😳
እግዚአብሔርን እንደ ጠላት ማየት
የሆነ ነገርን በጣም ከወደድን እና ያ ነገር ደግሞ በእግዚአብሔር ያልተወደደ ከሆነ.. እግዚአብሔር ከዛ እንድንርቅ ከሆነ ፍላጎቱ እና እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ከምንወደው በላይ ያንን ነገር ከወደድን እግዚአብሔርን የምናይበት መንገድ "ከምንፈልገው ነገር የሚነጥለን ጠላታችን" አድርገን ነው..
ከዛም ያ ሰው ከሁለት አንዱን መምረጥ ግድ እየሆነበት ሲመጣ.. ከእግዚአብሔር ይልቅ ያንን በእግዚአብሔር የተጠላውን ነገር ይመርጥና እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ እየተወ ይሄዳል..
እግዚአብሔር ይጠብቀን ከዚህ.. ብዙ በእግዚአብሔር የተጠሉ ነገሮችን እናደርግ ይሆናል.. ክርስቲያን ግን ከነዛ ነገሮች ለመውጣት ይታገላል እንጂ ጭራሹኑ በእግዚአብሔር ላይ የበላይ አያደርግም..
ኃጢአት ብቻ አይደለም.. ከጌታ የሚያርቅህ ጉዋደኛ እና ቤተሰብም ቢሆን ከኢየሱስ ሊበልጡብን አይገባም..
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:
"ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም.."
[ማቴ 10:37]
@Apostolic_Answers
እስቲ አንድ ጊዜ ቸኮላት በሉ..
"በሉ" እንጂ "ብሉ" አላልኩም..
ማን እንደላከልኝ አልናገርም.. ያው ሄዳቹ ለእኛም ላኪልን እንዳትሏት ሎል.. እህታችን ግን ለአገልግሎቱ መፋጠን ያደረግሽው ቀላል አይደለም ሎል😝😝 አይ ግን አመሰግናለሁ የምር አንቺ **😊🤗 ደግሞ ዘጭ ነው😁😁