apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

መንፈሳዊ ወንድ እና ዓለማዊ ወንድ ልዩነቱ ምንድር ነው..??

ጥያቄ ይልሃል😉😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እንደው አንድ ነገር አስጨነቀኝ..

አንዲት የምቀርባት እህት አለች እና እዚህ ቴሌግራም ላይ አልፎ አልፎ ቢሆንም እናወራ ነበር.. ያው ከዛን ግን ቴሌግራም አጠፋሁ.. እና ስለዚህም በውስጥ ልናወራ አንችልም..

እና ምን..?? በዚህ በማናወራበት ሰዓት ላይ አንዱ በውስጥ ሄዶ እኔን መስሎ ያወራታል.. የሆነ እኔ በተደጋጋሚ የምጠቀማቸውን ቃላት እየተጠቀመ ምናምን ነው ያወራት screenshot አይቼ.. እና ለጅቷ ደስ የምትል
ምስኪን ልጅ ብትሆንም ከባባድ ኃይለ ቃል በመጠቀም እርሷን የሚያሳዝን ነገር ተናገራት እና አዘነች.. ይህ ሰው እኔንም እሷንም የሚያውቀን ሰው እንደሚሆን ግልፅ ነው እና ጥቂት ሰው ስለሆነ የምገምተው በቀላሉ ልደርስበት እችላለሁ.. ግን በጣም ነው ያስገረመኝ..

እና ለምን ነገርኳችሁ..?? እባካችሁን አሁን ላይ በውስጥ ማንንም አላወራም ማለት ይቻላል 3 ወይም 4 ልጆች አሉ እነርሱም ተደዋውዬም ያወራሁዋችሁ ናችሁ.. ስለዛ በኔ ስም የሚያወራችሁ እንዳይኖር..

ከዚህ በፊትም እንዲህ ተደርጎ እንደሆነ
እነጃ እንግዲህ.. እኔ ብዙ ጊዜ የምጠቀማቸውን ቃላት መጠቀሙ ደግሞ🤢🤮

አክሊል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሐዋርያዊ ወይም ቅዱስ ትውፊት ማለት ምን ማለት ነው..??

ትውፊት ማለት ቅብብሎሽ ማለት ሲሆን.. ቅዱስ ትውፊት ማለት ደግሞ በአጭሩ ቅዱስ የሆነ ቅብብሎሽ ሆኖ ከጌታ ለሐዋርያት ከዚያም ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ትምህርት ወይም የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ነው..

ስለዛ ቅዱስ ትውፊት ከራሱ ከጌታ ለሐዋርያት የተሰጠ ከዚያም የሚተላለፍ ነው.. ይሄ የሚተላለፈው ደግሞ ትምህርት ሃይማኖት ይባላል.. ስለዚህም ሃይማኖት የሆነ ነገርን ሃይማኖት ካልሆነው ትልቁ መለያም ይህ ነገር ቅዱስ ትውፊት ነው ወይስ አይደለም በሚለው ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይህን ያውቁ ኖሯል..??

በቤተክርስቲያን ውስጥ የእመቤታችንን ተአምር መስማት ቅዱስ ቁርባን እንደ መቀበል ይቆጠራል የሚል “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” የለም።

የቤተ ከርስቲያን አስተምህሮ የሚባለው ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብሎሽ እስከ ዛሬ የደረሰው ሐዋርያዊ ትምህርት ብቻ ነው።

ስለዛ አንዳንድ መጽሐፍት ላይ ከተለያዩ ነገሮች አንፃር የተፃፈው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ተደርጎ ይቆጠራል ማለት አይደለም።

“የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” ምን ማለት እንደሆነ ሁሉም ክርስቲያን ሊያውቅ ሊረዳ ይገባዋል

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኢየሱስን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ..

በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአካሉ ማለትም በቤተ ክርስቲያን እኖር ዘንድ.. እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ.. ራስ የሆነውን እርሱንም እመለከት ዘንድ


እግዚአብሔርን የማፍቀርና የመፍራት ውሎ ይሁንላችሁ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“የፕሮቴስታንት መዝሙር” ብዬ የሰራሁት ላይ ጥያቄ ያለው አሁን ላይቭ ነኝ ኑ ጠይቁኝ


https://vm.tiktok.com/ZM6REc38h/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የፕሮቴስታንት መዝሙር መስማት አይቻልም..?? ለምን..??


https://vm.tiktok.com/ZM6R5tUjY/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት..


ወደ ቆላስይስ 1
15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።


እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ በልጁ ፈጠረ.. የተፈጠረ ነገር ሁሉ በኢየሱስ ከተፈጠረ መቼስ የኢየሱስን አምላክነት ግልፅ አድርጎ ያሳያል..

ባይሆን የሚገርመኝ ግን በልጁ ፈጠረንና.. ይህ ፍጥረቱ ሲወድቅ ደግሞ በዛው በልጁ አደሰው ፈወሰው.. ለዛ ነው ዝቅ ብሎ እንዲህ የሚለው..


ወደ ቆላስይስ 1
19-20፤ እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።


መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኢትዮ ቴሌኮም ደግሞ አንዳንዴ ይሰግጠው አ እንዴ..

እኔ እንደ ወረደ በትኩሱ የሚያስፈልገኝ በዚ በጉንፋን ሰዓት ሻይ ምናምን እንጂ ዘፈን አይደለም ትላለህ🤧🤧

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቲክቶክ ላይ የፎሎወሮቼ ብዛት በከተማ..

ሻሼ ይልሃል😁😁 እዚም አላችሁ ግን..??😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እግዚአብሔር መናቅ ነው እየተለማመድን ያለነው..??

https://vm.tiktok.com/ZMjEbKr9F/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የተመታ ጉንፋን😆😆


ይመቸው😤

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት


ወደ ሮሜ 5
10፤ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን


ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ በራሱ ድኅነት ነው.. ይህንን እርቅ ያገኘነው ደግሞ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ሞት እንደሆነ ይነግረንና ከታረቅን በሁዋላም በሕይወቱ እንደምንድን ይናገራል..

ኢየሱስ ሕግን ሁሉ ፈጸመ በቅድስና ኖረ.. የክርስቲያንም ግብ ይህንን ኢየሱስን መምሰል ነው.. እርሱን መስለን ደግሞ በቅድስና መኖርን እንድንችል ራሱ ኢየሱስ በእኛ ይኖረላል..

ኢየሱስ በእኛ የሚኖር ከሆነና የእርሱ ሕይወት ደግሞ የቅድስና ከሆነ እንግዲያውስ ከእርሱ የተነሳ እኛም የቅድስና ሕይወትን እየኖርን ራሱን ኢየሱስን ወደመምሰል እናድጋለን..

ይህ ድኅነትን መፈጸም ይባላል.. ድኅነታችንን የምንፈጽመው በእኛ በሚኖረው በክርስቶስ ሕይወት ነው.. ድኅነቱን የፈጸመ ሰው ደግሞ ይድናልና "በሕይወቱ እንድናለን" አለ..

"በሕይወቱ እንድናለን" ያለው በሞቱ ከታረቅን 👉በሁዋላ በማለት እንደሆነ ይሰመርበት..


መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"ለሰዎች የምትሰጠው ምንም ነገር ባይኖርህ..

ሞቅ ያለ ፈገግታ እና መልካም ቃልን ስጣቸው.. ፍቅርን ስጣቸው.. መልካምነትን ስጣቸው.. የማበረታቻ ቃልን ስጣቸው.. ልብህን ስጣቸው"

[አቡነ ሽኖዳ]

ሰዎችን በማሳዘን ፈንታ ሁሌም ይህንን ብናደርግ ኢየሱስ በእኛ እንዳለ ያኔ ይታወቃል..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወዳጆቼ እባካችሁን እባካችሁን.. ስልኬ ላይ ካርድ የምትልኩ.. አመሰግናለሁ ግን እባክህን ከዚህ ድርጊትህ ተቆጠብ😁😁

የድምጽም የኢንተርኔትም የዓመት ያልተገደበ(unlimited) ጥቅል ስላለኝ ምንም አይጠቅምም መላካችሁ..

ስልኬ ላይ ማታ የገባ ካርድ አለ ለዛ ነው የምጽፈው.. ያው ላኪው ማን እንደሆነ ስላላወቅሁ እዚሁ ተናገርሁ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቅዱሳንን በብዙ ለምን እናከብራለን..??


https://vm.tiktok.com/ZM6YSrCSj/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል


የዮሐንስ ወንጌል 9
2፤ ደቀ መዛሙርቱም፦ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
3፤ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ክፍል ሲያብራራ እንዲህ ይላል:

[ወላጆቹ ሃጢአት ስለሰሩ አይደለም.. በወላጅ ሃጢአት ልጅ አይቀጣም ሕዝቅኤልም እንደሚለው.. እርሱ ራሱም ሃጢአት ሰርቶ አይደለም.. ገና ሳይወለድ ሃጢአት አይሰራምና..

ነገር ግን ይህ የሆነው “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው” ታድያ ግን እዚህ ላይ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል.. “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ እውር ተደረገን..??” የሚል.. ታድያ ግን ገና ከጅምሩ ካለመኖር ወደ መኖርስ ያመጣው እርሱው አይደለም..?? እውር ሆኖ በመኖሩስ በሁዋላ ላይ የልቡም ዓይን እንዲበራ ምክንያት አልሆነለትም..?? እያዩ የማያዩ አሉና(እንደ ፈሪሳውያኑ) ]



ዓይን ራሱ ጌታ ኢየሱን ካላሳየህ ምኑን ዓይን ሆነው..??

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንድ ጊዜ ግን በጣም የሚገርሙኝ ዓይነት ሰዎች አሉ😁😁

ለምሳሌ ከላይ በጻፍኩት ላይ "የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ" ምን ማለት እንደሆነ ገልጪያለሁ ይህም ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብሎሽ የመጣ እንደሆነ ተናግሪያለሁ.. ከዚህም አንጻር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲነገሩ የሚሰሙ ነገሮች ሁሉ በዚህ አስተምህሮ ውስጥ የሚጠቃለሉ ናቸው ማለትም እንደማይቻል ማለት ነው።

ታድያ ግን ተአምሩ ላይ ያለው ስህተት ነውም አይደለምም አላልኩም.. እኔ ርዕሴም እርሱ አልነበረም.. ብቻ ግን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አይደለም ነው።

ታድያ ግን እንዲህ ተብራርቶ ተቀምጦም አንዱ ይመጣና "ያወዛግባል😭" ይላል.. ጥሩ ነው ያወዛግብህ ሂድና ትልልቅ መምህራንን ጠይቅ የአባቶችንም መጽሐፍት አንብብ.. አንተ እንዳያወዛግብህ ተብሎ አንዳንድ ነገሮች ምንም ትምህርት አይሰጥባቸው አይባልም።

[በነገራችን ላይ ተአምሩ ላይ ያለው ነገር እውነት ይሁን አይሁንም እኔ አላውቅም.. ስለዛ እውነትም ሃሰትም አላልሁም.. ስለዚህ ጉዳይ ምንም አላወራሁም እዚህ ላይ እውቀቱ ስለሌለኝ]

የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ማለት የክርስቶስ ትምህርት ማለት ነው።

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ተከከታታይ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት መማር የምትፈልጉ ሰዎች እንዳላችሁ አሁንም እየነገራችሁን ስለሆነ አሁንም ለአዳዲሶች አዘጋጅተናል.. ከዚህ በፉት ያልተመዘገባቸ‍እሁ ብቻ ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉ


/channel/+3nFiHrKdDQ82ZTVk

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለእሼ ተዘመረ..??😬😬


https://vm.tiktok.com/ZM684Ljkc/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት


ወደ ዕብራውያን 12
28፤ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤

29፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


የማይናወጥን መንግስት እንቀበላለን አዎ.. ስለምንቀበል ምን እናድርግ..?? በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ..

ይህንን ባናደርግስ..??

"አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው"

ይቀጣል ወይም ያጠፋል ነው በብሉይ እንዲህ እንደተባለ:

ኦሪት ዘዳግም 4
23፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።

24፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።


መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ዲያቆኔ አንተን ባየ ዓይኔ ሌላ ለምኔ"

በተለይ እህቶች እቺን ዜማ የምትሏት የማንን ልብ ለመስበር ነው..??

አንሰማችሁም!


ከ ዲያማ(ዲያቆን ያልሆኑ ማህበር)

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንተ ፍዘዝ እኔ በገና እየተለማመድኩ ነው🤪🤪 አሁን ገና ነው ደግሞ እቺን የተለማመድኳት😁😁

ጣቶቼ ሲያምጹብኝም እያየሁ ነው.. በተለይ ቀለበት ጣት😁😁

ቆይ ቀጣይ ሳምንት እልክላችሁዋለሁ ምን ያህል እንደምሻሻል😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቀሲስ ዶር ዘበነ ለማ በጣም ደስ የሚሉ የምወዳቸው ሰባኪ ናቸው.. ከተወሰኑ አመታት በፊት ወደ እኛ ሰፈር አካባቢ በሚገኝ አንድ ደብር መጥተው ሲሰብኩ በአካል ተገኝቼ ነበር እና በጣም ደስ ይላሉ.. እግዚአብሔር አብዝቶ ይርዳቸው..

እንዲሁ እንደ እኛ ሲጨቃጨቁ ብቻ መዋል ሳይሆን ክርስቲያኖችን ለማገዝ እየደከሙ ያሉ ይመስለኛል..

ለምን ይህንን አነሳሁ..??

ስህተት ከሰው አይጠፋምና ምናልባት ስህተት ቢናገሩ ያችን አጉልተው ለማሳየት ደፋ ቀና የሚሉ ብዙ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶች ስላሉን ያ ነገር ጭራሽ እኛ ላይ መምህሩን ወደ አለመስማት እንዳይመራን ያሰጋል..

በቴዮሎጂው ዓለም የቱ ጋር እንዳሉ አላውቅም ግን ቢያንስ ስብከታቸው በጣም ደስ የሚል ክርስቲያኖችን የሚያጽናና የሚያጸናም ነው እና ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ ቢሰሙ መልካም ነው..

እና ደግሞ መናገር እንደሚገባው ስለ እርሱ(ስለ ወንጌል) በግልጥ ይናገሩ ዘንድ ደግሞ እኛም እንጸልይላቸው[ኤፌ 6:20]
ለሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መምህራኖቻችን እንጸልይ..

ዛሬ ብዙም በማልወደው ርእስ ተከሰትኩ😁😁

በሉ መልካም ውሎ እኔም ሶፍቴን ላንሳ🤧🤧 [ጉንፋን😁]

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ምናልባት ያላሳወቅኋችሁ ሰዎች ካላችሁ የግል ቴሌግራም አካውንቴን ዲሊት ብዬው ነው.. ለትንሽ ጊዜ ከግሩፑም እወጣለሁ[ዛሬ አለሁ ነገ ነው የምወጣው] ግን ግሩፑ ላይ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ስላሉ ግሩፑ ላይ ከመጠየቅ ወደ ኋላ እንዳትሉ.. እኔም ቶሎ ለመመለስ እሞክራለሁ..

እዚህ ቻናሉ ላይ ግን አለሁ..

አንዳንድ የማደርጋቸው ነገሮች ስለተደራረቡብኝ ነው ቶሎ fix አደርጋትና እናዝጋለን ማለቴ እንማማራለን ትላለህ ሎል..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ስሙ ሰዎች የገና(የጌታችን ልደት) ጾም ሊገባ ነው ለካ.. በጣም ደስ ይላል የምር.. በተለየ ሁኔታ ልደቱን የምናጣጥምበት ወቅት ነው..

ጾሙ ከመግባቱ በፊት ታድያ ንስሐ ያልገባን እንግባ እናፍጥነው እናፍጥነው..

ያው ከጾሙ በፊት በርገር መብላቱም እንዳለ ሆኖ ትላለህ ሎል(ይሄ ለሆዳሞች ነው😁😁)

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እግዚአብሔር በሕይወታችን ጣልቃ አይገባም..??

https://vm.tiktok.com/ZMjKXvemf/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አስበኸዋል "ብንሄድ ይሻለናል" ብለህ ፖስተህ ወደ ሲዖል ብትሄድ😬😬

እዛ ሄደህ ደግሞ "ብንመለስ ይሻለናል" ሲያስብልህ ያለው ሁኔታ.. ችግሩ መመለስም አይቻልም እንጂ🥴🥴

ከዚህ ሁሉ ግን የምርም ብንሄድ ይሻለናል.. ወደ ቅዳሴ.. ከዓለም ያጣነውን ደስታ በጌታ እውነተኛ ደስታ ሆኖ እናገኘዋለን.. ሐዋርያው ጳውሎስ "በጌታ ደስ ይበላችሁ" አለ። ከዓለም ያጣነውን ሰላም ከጌታችን እናገኘዋለን..

ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡ "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ.. እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ያለ አይደለም"

ለማንኛውም ነገ ቅዳሴ በስንፍና እንዳንቀር.. ሰላም እደሩልኝ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መዝሙረ ዳዊት 40
1፤ እግዚአብሔርን ቆይቼ ደጅ ጠናሁት፥
እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።


"ቆይቼ ደጅ ጠናሁት" ማለት በትእግስት ብዙ ጠበክሁት ማለት ነው.. ስለዛ እግዚአብሔርን በትእግስት እንጠብቀው.. መልካሙን እግዚአብሔር ያድርግ


እግዚአብሔር መልካም ነው

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መልካም ሥራ የምንሠራው ስለ ዳንን ነው ወይስ ለመዳን..??

ስለ ሁለቱም ነው.. እንዴት እንደሆነ ይመልከቱ😊😊

https://vm.tiktok.com/ZMj3x47vw/

Читать полностью…
Subscribe to a channel