ኧኸ እናንተ የክርስቶስ የሆናቹ ሰዎች.. እናንተ ምርጦች.. አምላክ የባርያን መልክ እስኪይዝ በሥጋ እስኪወለድ ድረስ የወደዳችሁ ያፈቀራችሁ ክቡራን.. እንዴት ናችሁልኝ.. ማን እንደ ኢየሱስ ሊያፈቅረን ይችላል.. ለእርሱም ለባህሪ አባቱ ለአብም ሕይወትን ለሚሰጥ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን።
የአምላክን በሥጋ መወለድ ሳስብ በጣም ከሚያስገርመን ነገር ውስጥ አንዱ የቅድስት ድንግል ነገር ነው። ስለ እርሷ ሳስብ በጣም ነው የሚገርመኝ ክርስቶስን.. ሁሌም ከልጅነቴም ጀምሮ የማውቀው ደጋግሜም የምሰማው ነገር ቢሆንም ለጭንቅላቴ ግን እንደውም ክብደቱ እየጨመረ ይሄዳል..
ሲደጋገም ቀላል ካልመሰለን በቀር ቆይ አምላክን በሥጋ በማኅጸን መያዝ ምንድር ነው ይሄ.. አምላክን ወልዳው በእቅፏ ይዛው ፊቱን በስስት ማየት እንደምን ያለ ነው.. ጡቶቿን አውጥታ መግባዋለች እኮ.. አቅፋው መዋልስ ቆይ ሁሉም ነገር እኮ ያስገርማል የምር.. ፊቱን እየሳመች የገላውን ጠረን እያሸተተች ማሳደጓስ.. መቼስ ዶሴቲክ መናፍቅ ካልሆንህና ሥጋውን ካልተጠራጠርህ እንደማንኛውም ሕጻን ከእናቱ ጋር ግንኙነት አለው..
ገና ከመውለዷ ልጇን ሊገድሉባት እንደ ሆነ ስትሰማ ያገኛትስ ሃዘን ትካዜ.. በስስት ስታየው አስቡት.. ከዚያም ልጇን ይዛ ወደ ግብጽ በበረሃው መሰደዷስ.. ወላዲተ አምላክ.. የኔ እመቤት.. ልጇ ወዳጇ ኢየሱስን ባቀፈ እጇ ትቀፈን የኔ የተወደደች እናት.. በልጇ በኢየሱስ መንገድ እንድንሄድ ጸሎት ልመናዋ ይርዳን..
ጌታ ኢየሱስ በልባችን የሚወለድበት መልካም ቀን ይሁንልን..
@Apostolic_Answers
ዛሬ የተቀበልሁት መጽሐፍ በጣም ፒስ ነው..
እስልምናን በደንብ የማጥናት ፍላጎቱ አለኝ እና ጥናትም ከጀመርሁ ትንሽ ቆየሁ (ያው ትንሽ ብንቀራፈፍበትም) እና እስልምናን ሳጠና በተለመደው እስልምናን በሚተቹ ተባራሪ በሆኑ ምንባባት ብቻ ሳይሆን ከሥር ከመሠረቱ አጀማመሩን እና ራሱ የቁርአንን መረዳት ማጥናቱን ነው የመረጥሁት..
እናም በ "ነቢዩ" ሙሃመድ የሕይወት ታሪክ እና ወደ ነቢይነቱ እንዴት እንደ መጣ እና ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ያለውን ነገር በማጥናት ነው የጀመርሁት.. እና እያጠናሁም ነው..
ከዚያም ወደ ቁርአኑ ስሻገር ቁርአኑን በጥልቀት ለመረዳት ጥሩ መጽሐፍ ያስፈልገኝ ነበር.. እና ለእርዚህ ደግሞ የእስልምና እና የታሪክ ምሁር በሆነው የኦርቶዶክስ ጽሐፊ(a former catholic) ሮበርት ስፔንሰር የተዘጋጀው "the critical qur’an…” የተሰኘው መጽሐፍ በጣም ያስፈልገኝ ነበር.. እና አስፈልጎኝም አልቀረም እጃችን ገብቷል ይልሃል😁😁
ቡሩክቲሻ ጥብሷ😁😁 አመሰግናለሁ.. እሷ ናት ራሴው ልገዛው ያሰብኩትን ራሷ ገዝታ ከሃገረ ኢንግላንድ የላከችልኝ
በትንሽ እውቀት ላለመታበይ.. ይልቁንም ትሁት እንድንሆን ወይም ገና ብዙም እንዳላወቅን እንድናውቅ ከሚረዱን ነገሮች ውስጥ አንዱ የጥንት ሊቃውንት ቅዱሳን አባቶቻችንን ጽሑፍ እና አሁንም ድረስ ያሉ ግን ደግሞ ስኮላርሊ የሆነ ጽሑፍ የሚጽፉ ጸሐፍትን ሥራ ማንበብ ነው..
እንደዚህ ዓይነት ሥራዎችን ባየሁ ቁጥር እኔ የሚሰማኝ ይህ ነው😁😁
እያነበብሁ ካለሁት ጸዴ ሥራ ውስጥ አንዱን ልጋብዛችሁ:
“Christology and the council of Chalcedon” by fr. Shenouda m. Ishak..
ነገረ ክርስቶስ ላይ በኦሬንታል ኦርቶዶክስ በኩል በጣም ሃሪፍ ሆኖ የተዘጋጀ.. አዘጋጁም በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በተደረገ ውይይት ላይ የተገኙ ቴዮሎጂያን ናቸው..
መልካም ቀን
አንዳንዴ ቅዳሴ ላይ ለ 2 ወይም 3 ሰዓት ያህል መቆም ሊያደክም ይችላል..
እና ያኔ አሳቤ ውስጥ የሚመጣው.. የኔ ኢየሱስ ገና በጠዋቱ በአርብ እለት በምድራዊ ንጉሥ ፊት ለፍርድ ቆሞ ነበር.. ከዚያም አውጥተው የሮማ ወታደሮች ራሱ ላይ የሾህ አክሊል አድርገው "ንጉሥ ሆይ" እያሉ እየዘበቱበት ከዚያም ተፉበት.. በመቃን ደግሞ ፊቱን መቱት(የኔ ኢየሱስ ፊቱን በመቃን ተመቷል).. በብዙ ተገርፎ ተንገላትቶ ከዚያም መስቀልን ተሸክሞ ወደሚሰቀልበት ሥፍራ ደግሞ ሄደ..
ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በእርዛው መስቀል ላይ ደግሞ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው በዛ ስቃይ ውስጥ ለሦሥት ሰዓት ያህል ቆየ.. ያውም ርቃኑን.. ለሚሰቅሉትም "አባ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" አለ
እና ይህንን መከራውን ስናስብ ቅዳሴን ቆመን እንድናስቀድስ ያበረታናል.. መከራውን እንደው እንድናስብም ያደርገናል..
ያው ግን በጣም ችግር ከሆነ እንደው እያረፍንም ቢሆን እናስቀድስ ከቅዳሴ አንቅር..
በሉ ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ😊🤗
@Apostolic_Answers
በአንድ ወቅት ፃድቃኔ ስሄድ እዛ በሚኖረኝ ቆይታ የማነበው ነገር ከመጽሐፍ ቅዱሴ ጋር ገድለ ጊዮርጊስን ይዤ ነበር የሄድሁት..
እና ከጾም በሁዋላ አመሻሽ ላይ ቁጭ ብዬ የቅዱስ ጊዮርጊስን ገድል ማንበብ ጀመርሁ.. ያው መጽሐፍቱን ለሕይወታችን መጠቀም ስላለብን..
እና ይህንን ያየ አንዱ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው..?? "ምግብ ተበልቶ ይገለጣል ወይ..??" አንዳንድ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ያለው የእነርዚህ መጽሐፍት ምልከታ በጣም የተለጠጠ ነው.. አሁን ይሄ በቃ ስህተት ቢያይ እነርዚህ መጽሐፍት ላይ ልቡ ይሰበራል ክርስትናውን ይጠራጠራል..
ለማንኛውም እኔ በመንፈሳዊ ሕይወቴ እንዳድግ የሚጠቅሙኝን አነባለሁ ከዛ በተረፈ ሳነብ ግን ስህተት እና አርቴፊሻል የሚመስሉ ነገሮችን ሳልቀበል እንዲሁ አልፋቸዋለሁ
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዲህ ይላል፡- "ቴዮሎጂን ማውራት ለሁሉም የተሰጠ አይደለም ፤ ቴዮሎጂ እንዲሁ ቀላል የሆነና ያለ ድካም የሚገኝም አይደለም.. ቴዮሎጂ ለሁሉም ሰው ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ንባብ እንዳለው ለተመሰከረለትና ከምንም በላይ ደግሞ የሥጋና ነፍሱን ንጽሕናም ለሚጠብቅ ነው"
[On God and Christ, The Five Theological Orations and Two Letters to Cledonius: 1st oration, 3]
ስለ ሥላሴ እና ነገረ ክርስቶስን ሳጠና የተገነዘብኩት ይሄንን ነው.. በጣም ጸሎትና መረጋጋት ይጠይቃሉ አንዳንድ ነገሮች.. እና ደግሞ እንዲሁ ተባራሪ እውቀት ብቻ ላለው ለእኔ ቢጤ እንዲሁ በግልጽ ለመናገር የሚያስቸግሩም አሉ.. ጎርጎርዮስ የሰጠው አንድ ምሳሌ አለ፡ ጸሐይን ቀና ብለን በዓይናችን ማየት ይከብደናል.. ያው እንይ ካልንም ዓይናችን ጉዳት ውስጥ የሚገባ እንጂ ጸሐይን የምናይ አይደለንም.. ልክ እንዲሁ ጥልቅ ቴዮሎጂ የሚሰጠው በንባብ ብዙ ለገፉና እግዚአብሔርም ለረዳቸው እንጂ ለሁላችንም አይደለም..
ያው ግን ለድኅነት የሚያስፈልገንን እውቀት ከያዝን በቂ ነው.. ዋናው ደግሞ በዛ እውቀት መንፈሳዊ ሕይወታችንን አሳምረን ክርስቶስን መስሎ መኖር.. አለቀ።
@Apostolic_Answers
በስተመጨረሻም
ክርስቲያናዊ የሆነ ግሩፕ አያስፈልገንም ጋይስ..?? ማለት ከሶሻል ሚዲያው በዘለለ መሬት ላይ ያለ አካላዊ ጓደኝነት ምናምን.. እየተገናኘን ትንሽ የእግዚአብሔርን ቃል የምንማማርበት የምንጸልይበት የምንዘምርበት.. ከዛ ደግሞ ወደ ንስሐ እና ቅዱስ ቁርባን የምናድግበት..?? ስለዚህም ግሩፑ ሕይወቱን ክርስቲያናዊ አድርጎ ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ምናምን ብላችሁስ አርቃችሁ አታስቡም..?? ስለዛ ክርስትናችንን ከጥቅስ ደግሞ ወደ ሕይወት ብናሳድገው..
ዲየግ ይህ አሳብ የእናንተም ከሆነ.. እንዲህ ያለ community ቢኖረን ብለን አሰብን.. እና ግን በአንዴ ሰው ሁሉ ግር ብሎ ከተቀላቀለ ትንሽ ያዝጋል.. ስለዛ ለጊዜው ፍላጎቱ ላላችሁ አዲስ አበባ ያላችሁ ልጆችን ብቻ መዝግበን አውርተንበት ልንጀምረው አስበናል።
ስለዚህም አዲስ አበባ ያላችሁ ልጆች ብቻ ከታች የማስቀምጥላችሁን ፎርም ትሞላላችሁ..
ስሙን ለጊዜው ሐዋርያዊ ቤተሰብ ብለነዋል🤭🤭 ያው አብረን እናወጣዋለን እሱን😁😁
ውረድ ውረድ..??😂😂
ኧረ የሆነ ሰው ገና ከመሄዱ ፕሮቴስታንቱንም ላርም እያለ ነው😆😆
የምር ግን የጀለስን ያህል ድፍረት ቢኖረኝ.. ይመቸው😁😁
በሰዎች ተገፍቼ ጴንጤ ሆንሁ የሚሉ ሰዎች ግን የምር ያሳዝኑኛል..
በመጀመሪያ ደረጃ ግፊቱ በትልልቅ አባቶችም ደረጃ ጭምር ከሆነ ሰውዬው ድካም ሊኖርበት ስለሚችል ከቤተ ክርስቲያን ሊገፋና ሊወጣ ይችል ይሆናል..
ነገር ግን ሲጀመር ሰውዬው ክርስትና የገባው እና በሞቅታና በስሜት የማይመራ ዓይነት ከሆነ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቢገለል ራሱ ለምሳሌ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለምን አይሄድም..??
እንደው ብዙ ቢርቅ ራሱ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን የተማረ ሰው ቢያንስ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን ያያል እንጂ በምንም ተአምር ሰው ጴንጤ ሊሆን አይችልም..
እና እናንተ ሰዎች ግን እንዴት አደራችሁ ምናምን.. በሉ መልካም ውሎ😁😁
@Apostolic_Answers
በጣም ይቅርታ ኢትዮ ቴሌኮም.. እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዋዜማን አእላፋት ዝማሬ ቀድሞ ቀጠሮ አስያዘን..
ባይሆን እስቲ ቀጣይ ዓመት ሞክሩ😬😬 ofc እሱንም ቢሆን ተወዳጅ ዘማርያንን ይዛችሁ😁😁
ሐዋርያዊ ቤተሰብ ብለን አዲስ አበባ ብቻ ያላችሁትን መዝግበን ነበር ግን በጣም በዛችሁ ካሰብኩት በጣም ራቀ.. ስለዛ ለመጀመሪያው ግንኙነታችን እንዲሁ የማውቃችሁን ብቻ ልደውልላችሁ እና እንገናኛለን..
እና የምንገናኝበትን ቦታ ወስንን እዛ አጥቢያ ከሞላችሁት ውስጥ ደግሞ ራንደምሊ የተወሰናችሁት ጋር እደውልላችሁዋለሁ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል እና የመልእክት ክፍል ውስጥ:
የዮሐንስ ወንጌል 10
9፤ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።
"በሩ እኔ ነኝ" አለ ጌታ ኢየሱስ.. የድኅነት በር.. የሕይወት በር እርሱ ብቻ ነው.. በራሳችን ስላልቻልን በእርሱ በኩል ወደ መንግስቱ እንቀላል ዘንድ የተዘጋጀልን በር.. በእርዚህ በር ስንገባ ደኅንነታችንም የተጠበቀ ነው ምክንያቱም እረኛው ምንደኛ(ተከፋይ ቅጥረኛ) ሳይሆን እኛ የራሱ በጎች ነንና.. ስለዚህም ተኩላ ሲመጣ ጥሎን የሚሸሽ አይደለም..
በእረኛው በርነት ወደ መንጋው ከተቀላቀልን ከእኛ የሚጠበቀው ከፊታችን ያለውን እረኛ መከተል ብቻ ነው.. ይህም በሕይወትም ጭምር ነው.. ስለ እርዚህም ዛሬ ቅዳሴ ላይ በተነበበው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላይ እንዲህ ይላል:
1ኛ ጴጥሮስ 2
21፤ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
22፤ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
23፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
24፤ #ለኃጢአት_ሞተን_ለጽድቅ_እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።
25፤ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ #እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
መስቀላችንን ተሸክመን እረኛችን ኢየሱስን በሕይወት እንከተል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ስሟት እቺን ቪዲዮ.. ምናልባት ትጠቅማችሁ ይሆናል ብዬ ነው..
መላሽ:- መምህር ገ/መድኅን
ጥያቄ:- ክርስቶስ ፍጡርም ፈጣሪም ነው..??
ለሙሉ ምላሹ ይህንን ሊንክ ይጫኑ ፦
https://youtu.be/gqBMl71lQEA?t=456
ፕሮቴስታንቱ: ድነሃል አሁን..??
ስፒሮስ: አዎ ድኛለሁ.. ደግሞም ድኀነቴን እፈጽማለሁ
ፕሮቴስታንት: አሁን ብትሞት የት ነው የምትገባው..??
ስፒር: እሱን ስሞት ጠይቀኝ😎😎
😁😁 ይመቸው ስፒር.. ያው ስትሞት የሚፈጠረው ነገር ድኅነትህን በመፈጸም እና ባለመፈጸም ላይ ስለሚወሰን መሆኑ ነው
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል..
ወደ ሮሜ 13
11፤ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
የሚገርም ቃል.. ባመንንበት ሰዓት ስንጠመቅ ድነናል ወደ አዲሱ ሕይወት መጥተናል.. ከዚያ በሁዋላ ግን እንዳንዘናጋ.. መዳናችንን መፈጸም አለብንና.. "ከእንቅልፋችሁ ተነሱ" ይላል.. ምክንያቱም ደግሞ "ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና" ይላል..
አንዴ ካመነ በሁዋላ የሚያንቀላፋ እርሱ በጌታ ፍርድ ወንበር ፊት ሲገለጥ ድኅነቱን ያጣዋል ምክንያቱም አልፈጸመውምና.. አንዴ ካመነ በሁዋላ የሚነቃ እርሱ ግን ከጌታው የዘላለምን ሕይወት ይቀበላል(አንዴ ሲያምን በጥምቀት ያገኘው ያ ሕይወት ፍፃሜውን ያገኛል)
እንዴት ከእንቅልፍ እንነሳ የሚለውን እዛው ጋር አስከትሎ ከታች እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል:
ወደ ሮሜ 13
12፤ ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
13፤ በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
14፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።
ሥራ ለድኅነት አያስፈልግም የሚሉ ሰዎችን ጌታ ልባቸውን ይክፈት..
ወደ ኤፌሶን 5
14፤ አንተ የምትተኛ ንቃ፡ ከሙታንም ተነሣ፡ ክርስቶስም ያበራልሃል።
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ኢየሱስ በሥጋው አምልኳል ወይስ አላመለከም..??
አሁን ደግሞ መከራከሪያ ርዕስ ይህ ሊሆን ነው መሰል.. ብዙም ባልተረዳነው ነገር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ከምንል እኛ ራሳችን አርፈን በፍጹም ልባችን እግዚአብሔርን ብናመልክ አይሻልም..??
ገድላት ድርሳናት ተአምራት ውስጥ ጭራሽ ታሪኩ ያልተፈጸመ ነገርም ሊገባ ይችላል.. ያም ሆነ ይህ ዋናው ነገር እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ማወቅ ነው..
ያው እቺ የምትጻፈው እንዲ ሰው ሲተኛ በሌሊት ነው😁😁
እግዚአብሔር አብ ለኢየሱስ አባቱም አምላኩም ነው..??
ይህንን ለመመለስ ኢየሱስ ምንድር ነው የሚለውን ማወቅ በቂ ነው.. እርሱ ሥጋ የሆነ ቃል እንደመሆኑ አምላክም ሰውም ነው.. ሥጋው የተፈጠረ እንደመሆኑ አምላክ አለው.. ተዋሕዶ የሥጋን ፍጡርነት አላጠፋውም
አብ የኢየሱስ አምላክ ሲባል እንደ ቃልነቱ ሳይሆን ሥጋ እንደመሆኑ የተነገረ ነው.. ስለዛ ለሥግው ቃል ኢየሱስ - አብ አምላክም አባትም ይባላል..
ግን ደግሞ ሥጋ በጊዜ ውስጥ የመጣ ስለሆነ ይህንን ስንናገር በክብር እና በፍርሃት ይሁን..
ካስፈለጋችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስም ከአባቶችም ማየት እንችላለን..
አስባችሁት ታውቃላችሁ ቅዱስ ጳውሎስ አሁን በሥጋ በሕይወት ቢኖር እና በኢትዮጵያ ወዳለችው ቤተ ክርስቲያን መልእክት ቢጽፍ ምን የሚጽፍ ይመስላችኋል..??
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ ጳውሎስ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ በኢትዮጵያ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
.......... ብሎ ይጀምርና😁😁 ከዛስ ምን ምን ያነሳ ይሆን እስቲ ኮመንት.. የኔን ምናልባት ቀጣይ😁😁
ከላይ ያለውን ጽሑፍ ሳታነቡ ፎርሙን አትሙሉ.. ፈታ ያለ community ነው የሚሆነው ግን ደግሞ በመንፈሳዊ ሕይወት የማደግ ፍላጎቱ ያለን ብቻ ብንሆንና በአካል መገኘት ሲኖርበትም የሚገኝ ዓይነት ሰው ቢመዘገብ ፒስ ነው..
ፎርሙ እነሆ👇👇👇
https://forms.gle/3XunfRq7cmjq6rmT8
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
የዮሐንስ ወንጌል 1
51፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ፡ አለው።
“በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ” አለ ጌታ ኢየሱስ.. መላእክት በኢየሱስ ላይ የሚወጡና የሚወርዱ ከሆነ በሚወጡበት በዛ በሰማይ አለ በሚወርዱበትም በምድር ደግሞ አለ.. ይላል አውግስጢኖስ.. በሰማይም በምድርም ያለ ነው ነው አሳቡ..
መልካም የጌታ ቀን
@apostolic_answers
https://vm.tiktok.com/ZM66eWxJm/
ፕሮቴስታንት የማልሆንበት ዋናው ምክንያት..
በጌታ ኢየሱስ ላይ ያለን እርግጠኛነት ፕሮቴስታንቲዝምን እንዳንቀበል ያደርገናል