እግዚአብሔር አምላካችን "እኔ ሊቅ ነኝና እናንተም ሊቃውንት ሁኑ" ሳይሆን ያለው "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" ነው ያለው
ስለዚህ ሁላችንም ለቅድስና ተጠርተናል.. ሊቅነቱም አስፈላጊ ነው ግን ለሁላችንም አይደለም.. ክርስትና ቅድስና ነው..
@Apostolic_Answers
እንኳን ለ "ቅዱስ ቫለንታይን" ቀን አደረሳችሁ🤭🤭
አሁን አ እንዴ የምሰማው.. ለካስ ዛሬ February 14 የቫለንታይን ቀን ሲባል ቫለንታይን ለካስ ጥንታዊ ቅዱስ አባት ነው.. እና የሱ መታሰቢያ ቀን ነው.. ያው ግን ሰዎች አያይዘው የፍቅር ቀን ምናምን ብለውም ያከብሩታል..
ለማንኛውም ሲጣራ በዝች እለት ነበር አክሊልም የተወለደው.. እና የልደት ቀኔ ነው ዛሬ🤪🤪
እድሜያችን ቆሰው.. ይመቸው😁😁
እህቶች ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁልኝ.. የጌታችን ጸጋና ሰላም አይለያችሁ..
ከዚህ ቀደምም ጽፌ ነበር.. አንዳንዴ በጣም በሚያስደነግጥ መልኩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ "የንስሐ አባት" አልያም ደግሞ "መምህር" ተብለው ግን ደግሞ ሴቶችን የሚያስቸግሩና ወደአልተገባ ነገር ውስጥ የሚገቡ ሴሰኞች እንዳሉ መሰማት እየተጀመረ ነው..
ይህ ነገር በአደባባይ ሲነገር አስቀያሚው ነገር ደገኛ አባቶቻችንን ሁሉ በእዚህ ዓይነት ጥርጣሬ እንዳናያቸው ነው.. ይህንን ታሳቢ በማድረግና ከንስሐ አባቶቻችን ጋር ያለንን መልካም መንፈሳዊ ግንኙነት እያጠነከርን.. ምናልባት ድንገት ከላይ እንዳልነው ያለ አስፃያፊ ነገር ሲከሰት ደግሞ እንዲሁ መታለፍ የለበትም..
የድምጽ ወይም የምስል ማስረጃን በመሰብሰብ ለቤተ ክርስቲያን መክሰስ.. ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሕግም ማቅረብና ጥሩ ቅጣት እንዲያገኝ ማድረግ.. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችም ይህንን ነገር መከታተል..
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ
ወደ ሮሜ 1
3-4፤ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
አጋጣሚ ሰሞኑን "ወንጌል ስለ ማን ነው?" በሚል በቲክቶኩ መንደር ላይ ትንሽ ክርክር ነበር መሰል..
ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ወንጌል እንደተለየ ይናገራል.. ይህም ወንጌል ደግሞ አስቀድሞ በነቢያቱ አፍ የተነገረ ሲሆን እርሱም ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ነው..
ስለዚህ ወንጌል ምንድር ነው..?? ወንጌል የምስራች ቃል ማለት ነው.. ይህም የምስራች ቃል በአጭሩ እንዲህ የሚል ነው:
- ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ(ይጠበቅ የነበረው መሲሕ) የእግዚአብሔር ልጅ ነው
- እርሱ በሥጋ ከዳዊት ዘር(ከእመቤታችን) ተወለደ ስለሁላችን ሞቶ ተነሳ
- ሁላችን ደግሞ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን.. ለኃጢአት ከመንበርከክ ነፃ ወጥተን በጸጋው እርሱን ወደ መምሰል እናድጋለን
ስለዚህም በአጭሩ ወንጌል ስለ ኢየሱስ እና ስለ እኛ ነው.. ስለ እሱ ሲሆን እንደሚያድን ስለ እኛ ሲሆን በእርሱ እንደምንድን.. እዚህ ውስጥ እንግዲህ ብዙ ነገር አቅፎ እንደሚይዝ ግልጽ ነው.. ለምሳሌ በእዚህ በመሲሑ በኩል የተገለጠውን ሁሉ አምኖ መቀበል ሊሆን ይችላል..
“የማቴዎስ ወንጌል” ሲባል ለምሳሌ የጌታችን ወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ እንዳጸፈው ማለት ነው.. እና የጌታን ወንጌል ሲጽፍ ብዙ ነገሮችን ሲያነሳ እናየዋለን..
ስለዚህም ወንጌል ሲነሳ ስለ እመቤታችን ለምሳሌ አይነሳ ማለት ትልቅ ስህተት ነው.. በነቢያትም በሐዋርያትም የተባለላት ነገር ቀላል ስላልሆነ..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ነገረ ክርስቶስ ላይ በታሪክ ውስጥ በአባቶች ዘንድ ቴክኒካል የሆኑ ነገሮች ስላሉ ጥንቃቄ ይፈልጋልና በተለይ እኛ ሃገር ደግሞ የቃላት ውስንነት ይኖራል በጣም በዚህም ምክንያት ታሪካዊው ነገረ ክርስቶስ ሲጠና ትንሽ የሚያስቸግር ነገር ይኖራል..
እና ለአንባቢያን ብቻ የምትሆን አንድ ነገር ልናገር.. ነገረ ክርስቶስ ላይ "ከሁለት አካል" የሚለው አሳብ ላይ "አካል" የሚለው ምንድር ነው..?? የሚለውን መመርመር ይገባል.. ኬልቄዶንያውያኑ ሁፖስታሲስን እና ፕሮሶፖንን ሁሌም አንድ አድርገው ለ አካል(individual, ማንነት) ይሰጡታል.. ያው ፕሮሶፖን እንደዛ ነው.. ሁፖስታሲስ ግን ሁሌም individual(አካል) እንደማለት ሳይሆን የሆነ ባህሪ ቢኖር ያ ባህሪ የተገለጠበት ነገር(individuated የሆነበት አይደለም) ያ ነው ሁፖስታሲስ ብዙውን ጊዜ ነገረ ክርስቶስ ላይ.. ስለዚህም ማንነት(አካል) የሌለው ነገርም ባህሪ ይኑረው እንጂ ሁፖስታሲስ ይሆናል ማለት ነው.. ለምሳሌ ዲንጋይ..
ነገረ ክርስቶስ ላይ እኛ ሃገር "ከሁለት አካል" ስንል "አካል" ያልነው ፕሮሶፖንን ሳይሆንን ሁፖስታሲስን #ይመስለኛል.. ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይቼው possible የሆነ ያገኘሁት እና አሁን የደረስሁበት ነገር ይሄ ነው..
ዛሬ ከያረጋል ጋር ተገናኘን.. እና ከአንድ ሰዓት በላይ ቁጭ ብለን አወራን.. ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ በአካል ሳገኘው..
እንደው ፈተና እንዳላበዛበት ስሙን ሳነሳ ግን በቃ የምር ጌታ ብዙ እድሜን ሰጥቶት ከዚህም በላይ ብዙ ይጠቅመን ዘንድ በጸሎታችን ልናስበው የሚገባ ሰው..
ከእርዚህ ቀደም አዲስ አበባ ያላችሁ ልጆች በሞላችሁት ፎርም መሠረት ስልካችሁን ከዛ ላይ ወስጄ ለእያንዳንዳችሁ አንድ የኛ ብቻ የሆነ የቴሌግራም ቻናል ሊንክ እልክላችኋለሁ.. ያው በአንድ ቀን ሁላችሁም አይደርሳችሁም ታገሱኝ.. ከዛ እዛው ላይ እንጀምረዋለን.. አንዳንድ ነገሮችን ሼር እንደራረጋለን ምናምን..
Читать полностью…የአንዱ ሥግው ቃል ኢየሱስ double consubstantiality
"አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ብሎ እግዚአብሔር ተናገረለት
አዳም አምላክነት ሽቶ ሲወድቅ የወደቀውን እርሱን ለማንሳት ደግሞ ያንንው ሥጋ እግዚአብሔር "ቃል" መጥቶ ነሣውና ከራሱ ጋር አዋሐደው። በእርዚህም ያ "ቃል" የነሣው የአዳም ሥጋ "ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" [ከሦስቱ አካላት እንደ አንዱ ሆነ] የሚለው ቃል መፈጸሚያ ሆነ።
ታድያ ግን የማንረሳው ነገር ሥጋ በተዋሐደው ቃል በኩል እንዲህ ሲነገርለት.. ቃል ደግሞ በተዋሐደው ሥጋ በኩል ከእኛ ከሰዎች እንደ አንዱ እንደ ሆነም ጭምር ነው። ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ "ተንከተም" በተሰኘ መጽሐፋቸው ገጽ 256 ላይ እንዲህ ሲሉ ያስቀምጡታል፡
"ይህ ነገር ድንቅ ነው! ፈጣሪ እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ከራሱ ጋር አዋሕዶ ከራሱ ጋር አስተካከለው፤ ከእኛ በነሣው ሥጋ ምክንያት ከእኛ ጋር እኩል ሆነ ማለትም ከፍጡራን እንደ አንዱ ሆነ።"
ስለ እርዚህም አምላክ እንደ መሆኑ ከአብ ጋር አንድ ነው፤ ሰው እንደ መሆኑ ከእኛ ጋር አንድ ነው[ከኃጢአት በቀር]። እርሱ ኢየሱስ ግን ሁሌም አንድ ነው።
@Apostolic_Answers
ሰላም ለእናንተ ይሁን.. እንዴት አደራችሁ👊😁
አንድ ጥቅስ ላጋራችሁ
"[ኢየሱስ] ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ::" [ማር 1:35]
መምህራችን ኢየሱስ የተግባርም መምህር ነውና በማለዳ ተነሥቶ ገና በሌሊቱ ወደ ምድረ በዳ ሄዶ ይጸልያል..
ያው እኛም በጠዋት ተነስቶ መጸለይን.. እንደው ከልባችን ሆነን ቢያንስ አባታችን ሆይን እና የልባችንን ምስጋናን ማቅረብን እና ደግሞ በጊዜ መነሳትን ብንለማመድ መልካም ነው..
ስለዛ ይህንን የምናነብ ሁላችን ቀናችንን ቢያንስ በአባታችን ሆይ ጸሎት እንጀምር..
መልካም ቀን😊😊
ይኸው አንዱ ጀለስ ደግሞ ክላስ ውስጥ "በቫለንታይን ቀን ለመወለድ ምን አነሳሳህ..??" የሚል ጥያቄ በመሰንዘር ነፍሴን እያስጨነቃት ነው ሎል
በነገራችን ላይ የተወለድኩት 1996 feb 14 ነው.. ያው for your more information lol
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ..
ወደ ገላትያ 4
23፤ ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።
አብረሃም ከአጋር ኢስማኤልን ወለደ.. ከሣራ ደግሞ ይስሐቅን ወለደ.. ከባሪያዪቱ ከአጋር የተወለደው እንደ ሥጋ ነው ይህም እንደ ማንኛውም ሰው አጋር መጸነስ የምትችልበት ሁኔታ ላይ ሆና የተወለደ ነው.. ሣራ ግን እንደ ሥጋ መውለድ በማትችልበት ጊዜ ወለደች.. የወለደችውም እንደ እግዚአብሔር የተስፋ ቃል መሠረት ነው.. ልጅ ትወልዳለች ብሏልና እርሱ.. ስለዚህም በዚህ የተስፋው ቃል ተወልዷል..
እንደ ሥጋ የተወለደው የባሪያዪቱ ልጅ ወራሽ አልነበረም.. ወራሹ የተስፋ ቃል ያለው "የጨዋይቱ ልጅ" ነው..
ይህ ነገር ምሳሌነቱ አጋር የኦሪት ወይም የሕግ ምሳሌ ስትሆን.. ሕግ ደግሞ ጸጋ እስኪመጣ እንደ ሞግዚት ሆና የጠበቀች ናት እንጂ በራሷ ለውርስ የምታበቃ አይደለችም.. ሣራ ደግሞ የወንጌል የጸጋ ምሳሌ ናት.. አሁን በኢየሱስ በኩል ጸጋ ተገልጧልና ከጸጋ በታች ሆንን..
ስለዚህም የእግዚአብሔርን ጸጋ የጣሉ ከሕግ በታች ብቻ ሆነው ለመቀጠል የወሰኑ አይሁዳውያን እነርሱ የባርያይቱ ልጆች ሆነው አይወርሱም.. ክርስቲያኖች ደግሞ ከጸጋ በታች ሆነን "እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን" ስለዚህም ወራሾች ነን..
"ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።" በማለት የሚናገረው ይሄንኑ ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
በፕሮቴስታንቱ ዶግማ የሆነውን ካልሆነው መለየት እንደማይቻል ያውቁ ኖሯል..??
ካላወቁ አሁን ያውቃሉ ሎል
https://vm.tiktok.com/ZM6vDVprj/
ኧረ የኔስ ቅሌት በዛ😭😭
ከቅዳሴ መልስ ቁርሴን በልቼ ተመልሼ ሰንበት "ለማስተማር" ሄጄ ነበር.. እና በጣም ደስ ይላሉ ተማሪዎቹ ግን እያስተማርኩ እያለ የሆነ ምሳሌ ልሰጥ ፈልጌ አትሮንሱ ላይ ስልኬን አስቀመጥሁ..
እና አትሮንሱን ምን ብዬ ብጠራው..?? ጠረጴዛ😭😭 እና "ጠረጴዛው ላይ ስልኬን ባስቀምጥ" እያልሁ ነበር.. አፈርኩ ተሸማቀኩ አጠርኩ የምር
አርፌ አስቀድሼ ብቻ ብውልስ😁😁
የእመቤታችንን እረፍቷን ማሰባችን በጣም መልካም ነው.. ወደ ካቶሊኩ ዓለም የተወሰነ ውዝግብ አለ ሞታለች አልሞተችም ከሚለው ጋር በተያያዘ.. ያው immaculate conception ከሚለው ትምህርታቸው ጋር ተያይዞ ጥቂቶች ሳትሞት ነው ያረገችው የሚሉም ስላሉ ማለት ነው.. እነርሱ ጋር ዶግማ የሆነው ማረጉዋ ነው..
እመቤታችን ምንም ኃጢአት ያላደረገች ፍጽምት ንጽሕት ብትሆንም እንደማንኛውም ሰው የአዳም ዘር ናትና ሞት ለእርሷም የሚገባ ሆነ.. ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ግን ሥጋዋን በመቃብር ሊተወው አልወደደም እና ወደ ሰማይ አፍልሶታል..
እመቤታችን ባለችበት ሆና አሁንም ስለ ደካሞች ስለ እኛ መጸለይን አታቋርጥብን.. እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች..
ቅድም ነበር መዝሙር እየዘመርሁ ለቅቄ ሁሉም "ገፉኝ" እና ከዝማሬ አገልግሎት ተገፍቼ ቀጥታ የመጀመሪያውን ሲንግል ዘፈኔን ለቅቂያለሁ
አቀናባሪው ዮናታን ነው እኔን ምንም እንዳትሉኝ😁😁
ለ10 ደቂቃ የምትቆይ ፖስት😆😆
ድብርብር ያላችሁ ትመስላላችሁ.. እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሎል
ጌታችን ኢየሱስ የግዝረትን ሕግ ፈጽሟልን..?? አሳባችሁን ለማወቅ የተጠየቀ ጥያቄ😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከጳውሎስ እና ወንጌላት ውጪ ካሉ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት
1ኛ ዮሐንስ 4
1፤ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
"ሐሰተኞች ነቢያት" ያለው ምንፍቅናን የሚያስተምሩትን ነው.. እና "መንፈስ" ያለውም ያው የስህተት ትምህርታቸውን ሲያስተምሩ የተነዱበትን መንፈስ ማለት ነው.. ስለ እርዚህም መንፈስን ሁሉ አትመኑ ሲል የምትሰሙትን ትምህርት ሁሉ አትመኑ እንደማለትም ነው.. ምናልባት አስተውላችሁ ከሆነ እናንተ ጋርም ይኸው የመጽሐፍ ክፍል ከነበር የተነበበው.. "መንፈስን ሁሉ አትመኑ" የሚለውን "ትምህርትን ሁሉ አትመኑ" ብለው ነው ያነበቡት..
መናፍስት ከእግዚአብሔር ከሆኑ በአጭሩ ከሐዋርያዊ ትምህርት ጋር አይጋጩም.. የእውነትን መንፈስ ከስህተት መንፈስ በእርዚህ እንለየዋለን.. ሐዋርያዊው ትምህርት ደግሞ ሐዋርያዊት በሆነችው በዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን እንጂ ሌላ በየትም የለም.. ቅዱስ ሄራንየስም እንዲህ ይላል: "እውነታው ያለው በዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" [against heresies 4:1]
ከዚህ አንፃር የስህተትን መንፈስ ከእውነተኛው መለየት ቀላል አይመስላችሁም..??🤪🤪
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እንዴት አደራችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች..
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤
በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
[መዝ 34፡8]
የእግዚአብሔርን ቸርነት የሚቀምሰው እርሱ መታመኛውን እግዚአብሔርን ያደረገ ነው.. እግዚአብሔርን የሚፈራ የሚወድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅድስና ሕይወት የሚመላለስ እርሱ ቸርነቱን ይቀምሳል..
እግዚአብሔርን የመፍራትና የማፍቀር ብሎም በእርሱ ብቻ የምንታመንበት ቀን ያድርግልን..
መልካም ውሎ እናንተ ክቡራን የእግዚአብሔር ልጆች.. ከወርቅና እና እንቁ ይልቅ በከበረ በክርስቶስ ደም የተገዛችሁ ውዶች..
@Apostolic_Answers
የኢየሱስ ደም ብቻ ከኃጢአት ያነጻናል ወይስ ሌላ ከኃጢአት የማንጻት ብቃት ያለው ነገር አለ..??
የቅዱሳን ምልጃ ወይም የራሳችንም ጸሎት ቢሆን (ለምሳሌ ከኃጢአቴ አንጻኝ ብለን የምንጸልየው) ወይም ደግሞ ንስሐም በሉት ሁሉም የበጉ ደም እንዲያነጻን የሚደረጉ ተማጽኖዎች ናቸው..
ጥምቀት ራሱ ብንል በጥምቀት ውስጥ የኢየሱስ ደም አለ ነው ስለእርዚህም በመንፈስ ቅዱስ አሠራር በእርሱ እንታጠባለን እንጂ ጥምቀት እና የኢየሱስ ደም ሁለት የተለያዩ የኃጢአት ሥርየት የሚሰጡ መንገዶች ሆነው አይደለም።
"የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።" [1ዮሐ 1፡7]
@Apostolic_Answers
አሜሪካ..??🙄🙄
ማን ነበር ሊልካት ያሰበው የቤተ ክርስቲያን ሰው..?? የምር በጣም ነው የምትደብሩት.. ሙዳችሁ ይከብዳል.. ይኸው እኔ አለሁ አ እንዴ.. ምንድን ነው እንደዚህ አድሎ መፈጸም😏😏 በነገራችን ላይ እዘምራለሁ ራሱ የምር.. እስቲ ሞክሩኝ😝😝
ቆንጂት ግን ይመቻት😁😁 እንጃ ልጅነትም ደግሞ ያለ ይመስላል በእርግጥ
ኧረ ጋይስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ፕሮቴስታንቶች ወደ ክርስትና እየመጡ/እየተመለሱ ነው..
እንደው ጌታ ክርስቶስን ነው የምላችሁ.. አመጣጣቸው እስኪያስገርመኝ ድረስ ነው.. ሄደው የነበሩ አገልጋዮችም እንዲሁ በገፍ ነው እየተመለሱ ያሉት..
እግዚአብሔር ይመስገን.. ክርስትና ኢትዮጵያ ውስጥ በእጅጉ ሊለመልም ይመስላል.. ያው በልማድ ብቻ ሳይሆን በእውቀት እና በሕይወትም..
እንጸልይ እንጸልይ.. ጌታ ይሰበስባቸው ዘንድ
@Apostolic_Answers