አንዱ ወዳጄ የድቡን ኬዝ ከሰማ በኋላ ምን አለ..
እየደረሰ ያለውን ጥፋት ከቀረፍን በኋላ ግን የእህቶቻችንን ልብ ያስሸፈተውን ድብ በግል የምናናግረው ነገር ይኖራል አንሰማውም የምር..
@Apostolic_Answers
ፌሚኒስት እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ እህቶች(ምናልባት ወንድሞችም) አንዳንዴ የሚጠቀሟቸው ቃላት በጣም አደገኛና ወንድን በማኅበረሰብ ውስጥ በጣም እንደ አውሬ እንዲታዩና ፀረ ወንድ አስተሳሰብ ቀስ በቀስ እያደገ እንዲሄድ ሊያደርግ የሚችል ነገር ያለ ይመስላል..
ይሄ ደግሞ እህቶች ለወንድ ጥላቻ እንዲኖራቸው ያደርጋል ብዬ አስባለሁ.. ለምሳሌ አንድ ወንድ እና ሴት ቢቸገሩ አንዲት ሴት ማንን ትረዳለች..?? “ደግሞ ለወንድ” ብላ አትተወውም እሱን..?? እና ወደዚህ እንዳናመራ በጣም በጥንቃቄ ቢሆን.. እና መፋቀርን የሚያጠፋ መርዝ እንዳይሆን.. ያው በአንዳንዶች ችግሮች ምክኒያት
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?”
[ሉቃስ 1:43]
5 ነጥቦች😊😊
1. “የጌታዬ እናት” ብላለችና ኢየሱስ ጌታ ነው.. ይህም ጌትነት በሌሎች ክፍሎች ላይ እንደተነገረው “የጌቶች ጌታ፣ አንድ(ብቸኛ) ጌታ” እንደመሆኑ ስለሆነ አምላክነቱን ያሳያል..
2. እመቤታችን የጌታ እናት መባሏ የአምላክ እናት መባሏ ነው.. ያው ከላይ እንዳልነው ለኢየሱስ ጌታ ሲባል አምላክነቱን ስለሚያሳይ.. ስለዚህም እመቤታችን የአምላካችን እናት ናት ቃልን በሥጋ ጸንሳዋለችና
3. የአምላክ እናት እንደመሆኗ እመቤታችን ያላት ታላቅ ክብር:— ቅድስት ኤልሳቤጥ ምንም እንኳ “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ” እንደነበረች ይኸው ወንጌል ቢናገርም.. እግዚአብሔርም ታላቅ ተአምርን ቢያደርግላትም.. እመቤታችን ወደሷ ስትመጣ ግን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” አለች.. የእመቤታችን ክብር ከእርሷ በጣም በእጅጉ ይበልጣልና..
4. ይህ ጌታ የኤልሳቤጥ ጌታ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነውና ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን “የጌታችን እናት” ይላል.. ስለዚህም በክብር እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች..
5. በቅድስት ኤልሳቤጥ ላይ የወረደው መንፈስ በትህትናዋ ተገልጧል.. መንፈስ ቅዱስ የትሕትና መንፈስ ነው.. “ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ አይገባኝም” አስባላት..
ስለዚህ እኛም ይህ ትህትና በሕይወታችን ውስጥ ይታይብን ዘንድ ይገባል.. ጌታችንም “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሑት ነኝና” ብሏል.. ትሑት ሰው የእግዚአብሔርን ድንቆች በሕይወቱ ውስጥ ያያል.. በነገር ሁሉ የእግዚአብሔርንም እርዳታ አያጣም..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የጌታ ተአምር ለሙስሊሞች
ሙስሊምም ፕሮቴስታንትም ወንድም እህቶቻችን በንግግር ብናሳስዝናችሁ ይቅርታ..
https://vm.tiktok.com/ZMrGQtM6R/
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሁንም ሰሞኑን እመቤታችን ተገለጠች እየተባለ ነው.. እና ግን ግብጽ በጣም ደስ የሚሉት የምርም ተገልጣለች ወይስ መስሏቸው ነው የሚለውን ራሷ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥብቅ የሆነ ምርመራ አድርጋበት ከዛ ታሳውቃለች እንጂ እንዲሁ ኦፊሻል አይደረግም..
በዘይቱን ያኔ የተገለጠችውንም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ የሆኑ ሳይቀር ተሳትፈውበት ነበር ጉዳዩ ላይ.. እና ጥንቃቄዋ ደስ ይላል
@Apostolic_Answers
“አቤቱ አንተ አባታችን ነህ”
የምርም እግዚአብሔር አባታችን ነው እኛም ልጆቹ ነን.. ያውም ኢሳይያስ እንዳለው ያለ ዓይነት ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ በኩል የሆነ ልጅነት..
“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ”
እናመሰግንሃለን..
አንዷ ጥብስ ምን አለችኝ..
“ያለ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት የለም” ብለን ተከራክረን ተከራክረን ከዛ እንተኛለን እኛም አንቆርብም.. አለችኝ
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅዱስ ምስጢር መካፈል ላይ ትልቅ የሆነ መነቃቃት ያስፈልጋል.. የተሰሩ ካቴድራሎች ሁሉ በቆራቢዎች መሙላት አለባቸው.. አይመስላችሁም..??😁😁
ለዚህ ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንወጣ.. ንስሐ ገብተን በመቁረብ እንጀምር.. በሉ ሰላም እደሩልኝ..
አንዱ ወዳጄ ዛሬ ቅዳሴ ላይ አግኝቶኝ.. እና ያው ቅዳሴው አልቆ ስናወራ ምን አለኝ.. “ቆንጂት” የምትለው ለካ ከጳውሎስ ኮርጀህ ነው እያለኝ ነው😆😆
“ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።”
[ቲቶ 2: 4-5]
እኔ እንኳን አላስበውም ነበር😁😁
ቁርአን ተጠብቋል አልተጠበቀም ከማለትህ በፊት ገና ከጅምሩ የፈጣሪ ቃል መሆኑን በምን አወቅህ..??😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrbQdjr9/
ይቅርታ አድርግልኝ እንግዲህ አቡ..
በአደባባይ የተናገርከው ስለሆነ
በአደባባይ መለስኩልህ..
https://vm.tiktok.com/ZMrqNVHBW/
የቅዱሳንን ምልጃ ማን ይቀበላል ማን ደግሞ አይቀበልም..??
የሚቀበሉት:-
1. ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ(ኦርቶዶክሱም ካቶሊኩም አሲሪያኑም)
2. ፕሮቴስታንት(እንደ ሉተራን ያሉት.. ያው የሰዎችን invocation ግን ይቃወማሉ)
በአጠቃላይ ይህንን የማይቀበል በጥንት ቤተ ክርስቲያን አባቶች የተወገዘ ነው.. ለምሳሌ የጄሮም against vigilantius ሥራ ይነበብ
የማይቀበሉ:-
- እስላም እና ጴንጤ(ኦንሊ ጂሰሶችን ጨምሮ)
እስላም ወይም ጴንጤ ካልሆንክና የኢየሱስ ከሆንክ የቅዱሳንን እገዛ በተለይም የእመቤታችንን ተጠቀም በጣም ይረዳሃል
@Apostolic_Answers
ዮሐ 15:2 ላይ በግሪኩ “ፍሬ ማያፈራውን ያስወግደዋል” የሚለው የለም..??😭😭
https://vm.tiktok.com/ZMrVeNP6M/
አንዳንዴ እንዲሁ በልምድ ከሚባሉ ነገር ውስጥ..
“ኢየሱስ በምድር ሳለ አልማለደም ምልጃን አላቀረበም”
እስከማውቀው ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ አትልም.. አሁን ላይ እየማለደ(እየጸለየ) ባይኖርም በሥጋው ወራት ግን ጸሎትና ምልጃን አቅርቧል.. በቲክቶኩ መንደር አንዲት እህት ባለማወቅ ከብዙ ጊዜያት በፊት “እመቤቴን ሰው ናት ልትሉ ነው እንዴ” እያለች ስትከራከር አስታውሳለሁ.. ካላት ፍቅር አንጻር ያው ባለማወቅ የሌለውንም መናገር ነው ይሄ..
መድኃኒታችን ኢየሱስንም በምድርም አልማለደም ማለትን ልክ እንደዛች እህታችን ነው ማየው.. ምክንያቱም ለጌታ ያለን ፍቅርና ክብር የሚታየው እንዲሁ በመሸፋፈን ሳይሆን እንዳለ ያለውን በመቀበል ነው.. ጸለየ ቢባል ምን ይከብዳል ሞቷል እንኳ እየተባለ..
ያው ግን የ እርሱ ጸሎት እንደ ማንኛውም ሰው ጸሎት አይደለም ምክንያቱም:
1. እርሱ ሲጸልይ ሰው እንደመሆኑ ቢጸልይም እንኳ እርሱ ግን ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክም ነው.. ስለዚህም የጸለየው ሥግው ቃል ነው..
2. ሲጸልይ ከታላቅ መስዋእት ጋርም ነው ይህም የራሱን ሥጋ አንዴ ለዘላለም በማቅረብ ነው.. ይህም ሥጋ የአምላክ(የቃል) ሥጋ ነው
ያው ለማስታወስ ያህል ብቻ እንጂ ይህ ይጠፋችኋል ብዬ አይደለም
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“ይህንም ብሎ፡ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና፡ ብሎ ጮኸ።”
[ዮሐንስ 11:43]
ከሞተ አራት ቀን ወደ ሆነው “ይሸታል” ወደተባለው ሙት ጌታችን መጥቶ አስነሳው.. መግነዙን ፍቱት አለ.. እና አባ ሲያስተምሩ ምን አሉን በኃጢአት ብትተሳሰሩ እንኳ ጌታን ተስፋ አድርጉት እርሱ ከታሠራችሁበት ማሰሪያ ፈትቶ ነጻ ያደርጋችኋል.. እርሱን ብቻ ተስፋ አድርጉ.. የሞተውን አበቃለት የተባለውን እንኳ አስነስቷልና..
እርሱ የትኛውንም ልብ ሳይጸየፍ በልዩ ፍቅሩ በዛ ሊኖር ይመጣልና እናንተ ደግሞ ጌታን የሚቀበል ልብ ይኑራችሁ.. ጌታችሁ የልባችሁን በር ዘወትር ያንኳኳልና ክፈቱለት እርሱ ይግባ..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እንደዚህ ያለ ታላቅ ሃጢአት ሲደረግ ከቤተ ክርስቲያንስ ምን ይጠበቃል..??
አቤት ቅዱስ ጳውሎስ አሁን ቢኖርና በኢትዮጵያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ቢጽፍ ምን ይል ይሆን
https://vm.tiktok.com/ZMrtWXWep/
የሰው ቅርጽ ያለው የሆነ ነገር ነው.. አላውቅም ምን እንደሆነ.. ግን ሰው እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ.. እንደ “ሰው” በክብር ባይሞት.. በምድርም ፍርድ አለና
Читать полностью…ቤተ ክህነቱ ሪፖርት እያስደረገብኝ የሚከታተለኝ ሰው ቀነሰብኝ እያለ ነው ኤርሚያስ😆😆
ማይ ብራዘር ገድላት ተዓምራት ስትል አሁን ሰዉ ስቆብህ ነው ሚያልፈው.. ተስፋ አድርገው ሚዲያ ላይ የመጡት እሱን ነበር ግን አልተሳካም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrswWqMA/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የሌሎች መልእክታት ክፍል
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።”
[1ኛ ጴጥሮስ 4: 3]
የክርስትና አንዱ አዋጅ ይህ ነው.. በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት ይኑራችሁ.. ክርስቶስ ስለ ኃጢአት ለእናንተ የሞተው ኃጢአታችሁ ይቅር እንዲባል ብቻ ሳይሆን ይልቁን እናንተም ደግሞ ለኃጢአት ሞታችሁ ለጽድቅ እንድትኖሩ ነው ነው.. ይህም ከአሕዛብ ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወጥተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ነው..
ራስን መግዛት ላይ በጣም መስራት አለብን.. በአንዴ ላናድግ እንችላለን ግን የጠራን ጌታ የታመነ ነውና በትንሹ እንታመንለት.. በድርጊት ከሚሰሩ ኃጢአቶች እየተቆጠብን ስንመጣ እርሱ ደግሞ ጥቃቅን የሚባሉትንም እያስተወን ይመጣል.. ቀስ በቀስ እርሱን እስክንመስል ያሳድገናል.. ለዚህም ነውና እርሱ እኛን መስሎ በሥጋ የተገለጠው..
በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንም.. ዛሬ የወደቅን የሰነፍን ተስፋ እንደሌላቸው የምንረሳ አይደለንም.. መደገፊያችንን ልኡል እግዚአብሔርን ተደግፈን እንነሳለን.. ጌታችን እስከ ሞት ድረስ ወዶን ፍቅሩ እዛ ላይ ያበቃም አይደለም ደግሞ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦም በነገር ሁሉ እያገዘን ይቅርም እያለን ያሳድገናል..
ጌታችን አሳዳጊያችን ነው.. በጸጋው ሁላችንን ያሳድገን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
በጌታ ላይ እንዲህ መቀለድ..??
በእርግጥ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለ ጥምቀት እነርሱ እንዳሉትም “ረጠብ.. ራስ” የሚባልበት ብቻ ነው.. በዚህስ ልክ ብለዋል
https://vm.tiktok.com/ZMrqcEbLf/
እመቤታችን ያው ለኮፕቲኮች(ግብጽ ኦርቶዶክሶች) በጣም ትገለጥላቸዋለች.. እንደምታውቁት በዚህ ዘመን እንኳን ቅርብ ጊዜ ላይ በዘይቱን ለብዙዎች ለሙስሊሞችም ጭምር በተደጋጋሚ በዛው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በብርሃን መልክ ተገልጣለች.. ጭራሽ አንዳንድ የተወሰነ ጥራት የጎደላቸው ቢሆኑም የተነሱ ፎቶዎች እና የዓይን እማኞች አሁንም ድረስ አሉ.. እና ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር እንዳደረገችላቸው በተደጋጋሚ እንሰማለን
እና ይሄንን ያስትዋለች አንዷ ጓድኛዬ ምን አለችኝ "ኮፕቲኮችን ትወዳቸዋለች"😁😁 አዎ እነርሱም በጣም ይወዷታል.. እኛንም ትወደናለች ምንም ጥያቄ የለውም ግን ልባችንን ከክፋት መልሰን ብቻ "በልጅሽ በኢየሱስ መንገድ እንድንሄድ እርጂን" እያሉ እርዳታዋን መጠየቅ ነው..
አንዳንዴ ሰይጣን ይህንን የነሱን ጸሎት እገዛ እንዳናገኝ "ቀጥታ ራሱን ጌታን መጠይቅ አልችልም እንዴ?" በሚል አሳብ ይህንን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደውን መተጋገዝ እንድንረሳና እንድንተው ያደርገናል። አዎ ጌታችንን ቀጥታ እናነጋግረዋለን.. ሐዋርያት "ጸልዩልን" እያሉ ሌሎችን ክርስቲያኖችን የጠየቁት ግን ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ይህ መተጋገዝ ያለውን ቦታ ስለተረዱት ነው
@Apostolic_Answers
ጾም ገባ ደስ ይላል በጣም.. ይሄንን ወቅት በጣም ልንጠቀምበትና ምግብን ስንራብ ትህትናን እየተላበስን ክርስቶስን የምንራብበት የእመቤታችንን እገዛ የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባዋል..
Читать полностью…ከ18 አመት በታች የሆናችሁ ባታነቡት ፒስ ነው ለክፉም ለደጉም
"friends with benefit" የሚባል የአሕዛብ ልምምድ ታውቁ ይሆን..?? ያው ሁላችሁም ባይሆንም ብዙዎቻችሁ ታውቁት ይሆናል.. ወንድ እና ሴት ኖርማል ጓደኛማቾች ይሆኑና ቀስ በቀስ እዛው ጓደኝነት ላይ sexual ነገሮችን(ግብረ ሥጋ ግንኙነትና የመሳሰሉትን) ምናምንም ይጨምሩበታል ያው ባልና ሚስት ለመሆን አያስቡም ፍላጎቱም አይኖራቸው ይሆናል ግን ደግሞ ዝሙትና መዳራትን ይፈጽማሉ..
የጌታ ኢየሱስ ወገኖች ሆይ.. እንደምታውቁት በእኛ ዘንድ እንዲህ ያለ ነውር ይቅር እና ሊጋቡ የወሰኑ እንኳ በምስጢረ ጋብቻ አንድ ሳይሆኑ እንዲህ ያለ ነገር አይደረግም.. ለዛም ነው ክቡር ጳውሎስ "መጋባት ክቡር ይሁን" ካለ በኋላ "መኝታውም ንጹሕ ይሁን" የሚለው። ከመጋባት ወጪ ያለ "መኝታ" ሁሉ ርኩሰት ነው.. ቀጠል አድርጎ ሐዋርያው፡ "ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።" ይላል..
ስለዚህም እናንተ የተመረጣችሁ በዋጋ የተገዛችሁ የእግዚአብሔር ውድ ልጆች ናችሁና እንዲህ ባለው የአሕዛብ ርኩሰት ውስጥ ወድቃችሁ አትገኙ.. ስለ ዝሙት ወይም መዳራት(ዝሙት ቀስቃሽ ድርጊቶች) ራሱን ችሎ በሌላ ርእስ እመጣበታለሁ ሌላ ቀን.. ከእናንተ ግን ምናልባት እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ ያለ ቢኖር እርሱ አሁን ይቅርታ ጠይቆ ወይም ጠይቃ ያቁም.. የሥጋ ምኞታችንን እንመርጣለን ወይስ ከሙታን የተነሣውን ለዘላለምም ከእርሱ ጋር የሚያኖረንን እስከ ሞት ድረስ የወደደንን ጌታ..?? አሁን ይምረጥ/ትምረጥ.. ይሄ ቀስ ተብሎ ይተው የሚባልም ኃጢአት አይደለም..
"አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና"
[ገላ 6፡7]
ጌታ በዚህ ኃጢአት ውስጥ ላሉ ወንድም እህቶቻችን ምህረትን ያድርግላቸው እርሱን መውደድን ይስጣቸው መውጫውን መንገድ ያመልክታቸው
@Apostolic_Answers
አንዱ ወዳጄ አሁን ምን አለኝ..
መጸለይ በጣም እስኪከብድኝ ድረስ እሳነፍና.. አንዳንዴ ‘ኧረ ቢያንስ አባቶችን ሆይ ልበል’ ብዬ እቆምና ግን ደግሞ ሳላስበው በቦታው የጌታ መገኘት እየተሰማኝ በጣም ደስ የሚል ከስንት አንድ ጊዜ የሚያጋጥመኝን ዓይነት የጸሎት ጊዜ ኖሮኝ እጨርሳለሁ..
መላእክት በፊቱ የሚሰግዱለት ታላቁ አምላክ እርሱ ዝቅ ብሎ የኔን ድምጽ የኔን አሳብ እያየ እንደሆነ ሲሰማኝ ዝም ብዬ የኔን ድካምና የእርሱን ፍቅር፣ ትእግስት፣ ምህረት፣ ቸርነት እያሰብኩ ‘አመሰግንሃለው እወድሃለው አባ’ ብቻ እለዋለሁ..
እና ደግሞ ነገረ ቤተ ክርስቲያን ላይ “የቅዱሳን ኅብረት” የሚለውን አሳብ ከማወቅ በዘለለ እየተረዳሁት ስመጣ የእመቤታችንንና የቅዱሳኑን አጋዠነት በበለጠ መጠቀም ጀመርሁ.. የቅድስት ድንግል ጸሎቷ ይደግፍህ አንተንም
———————————————
ደስ ይላል ስለዛ እኛም በትንሹ እንታመን እግዚአብሔር ደግሞ ቀስ በቀስ በብዙ ይሾመናል.. መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers
👆👆👆👆
አንድ ወንድማችን ለቆንጂት ቀለበት አድርጎላት መሆኑ ነው.. እና ደስ የሚል ጊዜ ነበረን..
እና ይህ ወንድማችን ቀለበት ሊያደርግላት ሲል አቡ ምን መዝሙር ቢጋብዝ ጥሩ ነው..??
“የማደርገውን አላውቅም”😭😭