ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷልና።”
[ሉቃስ 1: 47]
እመቤታችን ስትናገር ጸሎቴን ወይም ጽድቄን ተመልክቷል ሳይሆን “የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷል” አለች.. ይህም ዝቅ ማለትን ነው.. ይህ ታላቅ ትህትና ነው.. አያችሁ የኔ ተወዳጆች ሰው ትህትና ሲኖረውና በመንፈስ ደሃ በሆነ ቁጥር እግዚአብሔር ደግሞ አብዝቶ ጸጋውን ይሰጠዋል ከፍ ከፍም ያደርገዋል..
ዲያቢሎስን አስታውሱት.. የወደቀው በትእቢት ነበር.. ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ኤጲስ ቆጶስ ሹመት ሲናገር ምን ዓይነት ሰው መሾም እንዳለበት ሲናገር እንዲህ አለ:
“በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።”
[1ጢሞ 3: 6]
የትህትና መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ) ትእቢትን ብቻ ሳይሆን የውሸት ትህትናዎችንም ሁሉ ከልባችን አውጥቶ እውነተኛ ትህትናን በልባችን ይሙላ.. መንፈስ ቅዱስ ይርዳን
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እስቲ ይሄን ቪዲዮ ሼር አድርጉት.. ለሰው ሚያዳርሰው ከሆነ አሁን ይዞታል በጣም
https://vm.tiktok.com/ZMrv7MDGk/
እስቲ እንሞክረው ዝም ብለን.. ያው ለሰው አላጋራውም እያለ ነው ቲክቶክ.. ጠምዶኛል ሰሞኑን😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrvANhPb/
አንዱ ወዳጄ የድቡን ኬዝ ከሰማ በኋላ ምን አለ..
እየደረሰ ያለውን ጥፋት ከቀረፍን በኋላ ግን የእህቶቻችንን ልብ ያስሸፈተውን ድብ በግል የምናናግረው ነገር ይኖራል አንሰማውም የምር..
@Apostolic_Answers
ፌሚኒስት እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ እህቶች(ምናልባት ወንድሞችም) አንዳንዴ የሚጠቀሟቸው ቃላት በጣም አደገኛና ወንድን በማኅበረሰብ ውስጥ በጣም እንደ አውሬ እንዲታዩና ፀረ ወንድ አስተሳሰብ ቀስ በቀስ እያደገ እንዲሄድ ሊያደርግ የሚችል ነገር ያለ ይመስላል..
ይሄ ደግሞ እህቶች ለወንድ ጥላቻ እንዲኖራቸው ያደርጋል ብዬ አስባለሁ.. ለምሳሌ አንድ ወንድ እና ሴት ቢቸገሩ አንዲት ሴት ማንን ትረዳለች..?? “ደግሞ ለወንድ” ብላ አትተወውም እሱን..?? እና ወደዚህ እንዳናመራ በጣም በጥንቃቄ ቢሆን.. እና መፋቀርን የሚያጠፋ መርዝ እንዳይሆን.. ያው በአንዳንዶች ችግሮች ምክኒያት
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?”
[ሉቃስ 1:43]
5 ነጥቦች😊😊
1. “የጌታዬ እናት” ብላለችና ኢየሱስ ጌታ ነው.. ይህም ጌትነት በሌሎች ክፍሎች ላይ እንደተነገረው “የጌቶች ጌታ፣ አንድ(ብቸኛ) ጌታ” እንደመሆኑ ስለሆነ አምላክነቱን ያሳያል..
2. እመቤታችን የጌታ እናት መባሏ የአምላክ እናት መባሏ ነው.. ያው ከላይ እንዳልነው ለኢየሱስ ጌታ ሲባል አምላክነቱን ስለሚያሳይ.. ስለዚህም እመቤታችን የአምላካችን እናት ናት ቃልን በሥጋ ጸንሳዋለችና
3. የአምላክ እናት እንደመሆኗ እመቤታችን ያላት ታላቅ ክብር:— ቅድስት ኤልሳቤጥ ምንም እንኳ “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ” እንደነበረች ይኸው ወንጌል ቢናገርም.. እግዚአብሔርም ታላቅ ተአምርን ቢያደርግላትም.. እመቤታችን ወደሷ ስትመጣ ግን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” አለች.. የእመቤታችን ክብር ከእርሷ በጣም በእጅጉ ይበልጣልና..
4. ይህ ጌታ የኤልሳቤጥ ጌታ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነውና ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን “የጌታችን እናት” ይላል.. ስለዚህም በክብር እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች..
5. በቅድስት ኤልሳቤጥ ላይ የወረደው መንፈስ በትህትናዋ ተገልጧል.. መንፈስ ቅዱስ የትሕትና መንፈስ ነው.. “ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ አይገባኝም” አስባላት..
ስለዚህ እኛም ይህ ትህትና በሕይወታችን ውስጥ ይታይብን ዘንድ ይገባል.. ጌታችንም “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሑት ነኝና” ብሏል.. ትሑት ሰው የእግዚአብሔርን ድንቆች በሕይወቱ ውስጥ ያያል.. በነገር ሁሉ የእግዚአብሔርንም እርዳታ አያጣም..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የጌታ ተአምር ለሙስሊሞች
ሙስሊምም ፕሮቴስታንትም ወንድም እህቶቻችን በንግግር ብናሳስዝናችሁ ይቅርታ..
https://vm.tiktok.com/ZMrGQtM6R/
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሁንም ሰሞኑን እመቤታችን ተገለጠች እየተባለ ነው.. እና ግን ግብጽ በጣም ደስ የሚሉት የምርም ተገልጣለች ወይስ መስሏቸው ነው የሚለውን ራሷ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥብቅ የሆነ ምርመራ አድርጋበት ከዛ ታሳውቃለች እንጂ እንዲሁ ኦፊሻል አይደረግም..
በዘይቱን ያኔ የተገለጠችውንም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ የሆኑ ሳይቀር ተሳትፈውበት ነበር ጉዳዩ ላይ.. እና ጥንቃቄዋ ደስ ይላል
@Apostolic_Answers
“አቤቱ አንተ አባታችን ነህ”
የምርም እግዚአብሔር አባታችን ነው እኛም ልጆቹ ነን.. ያውም ኢሳይያስ እንዳለው ያለ ዓይነት ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ በኩል የሆነ ልጅነት..
“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ”
እናመሰግንሃለን..
አንዷ ጥብስ ምን አለችኝ..
“ያለ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት የለም” ብለን ተከራክረን ተከራክረን ከዛ እንተኛለን እኛም አንቆርብም.. አለችኝ
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅዱስ ምስጢር መካፈል ላይ ትልቅ የሆነ መነቃቃት ያስፈልጋል.. የተሰሩ ካቴድራሎች ሁሉ በቆራቢዎች መሙላት አለባቸው.. አይመስላችሁም..??😁😁
ለዚህ ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንወጣ.. ንስሐ ገብተን በመቁረብ እንጀምር.. በሉ ሰላም እደሩልኝ..
አንዱ ወዳጄ ዛሬ ቅዳሴ ላይ አግኝቶኝ.. እና ያው ቅዳሴው አልቆ ስናወራ ምን አለኝ.. “ቆንጂት” የምትለው ለካ ከጳውሎስ ኮርጀህ ነው እያለኝ ነው😆😆
“ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።”
[ቲቶ 2: 4-5]
እኔ እንኳን አላስበውም ነበር😁😁
ቁርአን ተጠብቋል አልተጠበቀም ከማለትህ በፊት ገና ከጅምሩ የፈጣሪ ቃል መሆኑን በምን አወቅህ..??😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrbQdjr9/
በቁርአንህ ማፈር ከጀመርክ ነው መዋሸት የምትጀምረው.. እውነቱን ነግረህ ሰውን እስላም ማድረግ ስለማትችል..
በብሉይ ኪዳን ያሉ ውጊያዎችን እንዴት እንያቸው ከሐዲስ ኪዳን አንጻር
https://vm.tiktok.com/ZMrvbnrj3/
እንኳን ለእመቤታችን ፍልሰተ ሥጋ በሰላም አደረሳችሁ
የእመቤታችን ፍልሰተ ሥጋዋ እንዴት እንደተከናወነ ባናውቅም ያው እንደ ካቶሊክ ለጥጠን ዶግማ ባናደርገውም.. በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ግን የሚታመንበት ትምህርት ነው..
በስፋት የሚሰጠው እይታ ያው ጌታችን ሞቶ በመነሳት የትንሳኤያችን በኩር ነው.. ስለዚህም ሁላችንም ደግሞ ሞተን አንቀርም እንነሰላን.. ይህንን ነገር እኛ የምናገኘው በትንሳኤ ሰዓት ኋላ ላይ ነው.. ይህንን እኛ የምናገኘውን ነገር ለእመቤታችን ቀድሞ ሰጥቷታል ነው..
መልካም በዓል
@Apostolic_Answers
እንደዚህ ያለ ታላቅ ሃጢአት ሲደረግ ከቤተ ክርስቲያንስ ምን ይጠበቃል..??
አቤት ቅዱስ ጳውሎስ አሁን ቢኖርና በኢትዮጵያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ቢጽፍ ምን ይል ይሆን
https://vm.tiktok.com/ZMrtWXWep/
የሰው ቅርጽ ያለው የሆነ ነገር ነው.. አላውቅም ምን እንደሆነ.. ግን ሰው እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ.. እንደ “ሰው” በክብር ባይሞት.. በምድርም ፍርድ አለና
Читать полностью…ቤተ ክህነቱ ሪፖርት እያስደረገብኝ የሚከታተለኝ ሰው ቀነሰብኝ እያለ ነው ኤርሚያስ😆😆
ማይ ብራዘር ገድላት ተዓምራት ስትል አሁን ሰዉ ስቆብህ ነው ሚያልፈው.. ተስፋ አድርገው ሚዲያ ላይ የመጡት እሱን ነበር ግን አልተሳካም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrswWqMA/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የሌሎች መልእክታት ክፍል
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።”
[1ኛ ጴጥሮስ 4: 3]
የክርስትና አንዱ አዋጅ ይህ ነው.. በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት ይኑራችሁ.. ክርስቶስ ስለ ኃጢአት ለእናንተ የሞተው ኃጢአታችሁ ይቅር እንዲባል ብቻ ሳይሆን ይልቁን እናንተም ደግሞ ለኃጢአት ሞታችሁ ለጽድቅ እንድትኖሩ ነው ነው.. ይህም ከአሕዛብ ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወጥተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናደርግ ነው..
ራስን መግዛት ላይ በጣም መስራት አለብን.. በአንዴ ላናድግ እንችላለን ግን የጠራን ጌታ የታመነ ነውና በትንሹ እንታመንለት.. በድርጊት ከሚሰሩ ኃጢአቶች እየተቆጠብን ስንመጣ እርሱ ደግሞ ጥቃቅን የሚባሉትንም እያስተወን ይመጣል.. ቀስ በቀስ እርሱን እስክንመስል ያሳድገናል.. ለዚህም ነውና እርሱ እኛን መስሎ በሥጋ የተገለጠው..
በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንም.. ዛሬ የወደቅን የሰነፍን ተስፋ እንደሌላቸው የምንረሳ አይደለንም.. መደገፊያችንን ልኡል እግዚአብሔርን ተደግፈን እንነሳለን.. ጌታችን እስከ ሞት ድረስ ወዶን ፍቅሩ እዛ ላይ ያበቃም አይደለም ደግሞ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦም በነገር ሁሉ እያገዘን ይቅርም እያለን ያሳድገናል..
ጌታችን አሳዳጊያችን ነው.. በጸጋው ሁላችንን ያሳድገን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
በጌታ ላይ እንዲህ መቀለድ..??
በእርግጥ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለ ጥምቀት እነርሱ እንዳሉትም “ረጠብ.. ራስ” የሚባልበት ብቻ ነው.. በዚህስ ልክ ብለዋል
https://vm.tiktok.com/ZMrqcEbLf/