ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል
“በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።”
[ማርቆስ 8: 38]
ከላይ ከፍ ብሎ እንደተቀመጠው ጌታችን አስቀድሞ “በኋላዬ ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ብሎ ነበር.. እናም ዝቅ ብሎ “በእኔና በቃሌ የሚያፍር..” አለ..
በዚህ በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በጌታ አለማፈር ማለት ጌታ ጌታ ማለት ሳይሆን መስቀሉን ተሸክሞ እርሱን ደግሞ መከተል ነው.. ይህም በሕይወት ነው.. ዝሙትን እና ሌሎችንም ክደን ፈተናውንም ተቋቁመን ዓለምን እምቢ ብለን ጌታን ስንከተል በእርሱ አላፈርንም ማለት ነው.. ዓለም ይሸለኛል የሥጋን ፈቃድ መፈጸምን መርጬ የኢየሱስ ቃል ግን ምንም ነው ብንል ግን ያኔ በጌታ አፍረናልና የሰው ልጅ(ኢየሱስ) በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእኛ ያፍርብናል..
ስለዚህም በጌታችንና በቃሉ የምናፍር አንሁን.. ለመመስከርም ለመኖርም..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እንኳን ደስ አላችሁ..
ኦርቶዶክስ አቃብያነ እምነት እና ፕሮቴስታንት አቃብያነ እምነት እግር ኳስ ግጥሚያ ይኖረናል በቅርቡ..
ሎል😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተባለው ምስባክ
“ምድርኒ ወሀበት ፍሬሃ፤
ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ።
ወይባርከነ እግዚአብሔር፤
ወይፍርህዎ ኵሎሙ አጽናፈ ምድር።”
[መዝሙር ዳዊት 67: 6-7]
በግእዝ አጨናነኳችሁ አ..?? አይዞን እኔም ምስባክ ላይ በአማርኛ ሲሉት ስሰማ ጥቅሱን ይዤው ነው😁😁
“ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።”
ከዝናብ በኋላ ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች.. እንዲሁ ከእግዚአብሔር በረከት ወይም ጸጋ በኋላ ከምድር የተዘጋጀን እኛ ደግሞ ፍሬን እንሰጣለን.. ሰው ጌታችን ኢየሱስ ከሚሰጠው ከሕይወት ውኃ ሳይጠጣ ፍሬን ማፍራት አይችልም.. እኛ ደግሞ ከዚህ ውኃ ጠጥተናልና እንደ ምድረ በዳ እሾህና አመኬላን እንደሚያበቅል ምድር አንሁን.. ከኃጢአት ሁሉ እየራቅን ከጸጋው የተነሳ ፍሬን እናፍራ..
“እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
አንዲት እህት እያለቀሰች አሁን በስልክ አወራችኝ..
የቤቱ ታላቅ ወንድም ፕሮቴስታንት ሆነባቸው እና ቤት ውስጥ የነሱን መዝሙር ምናምን እየከፈተ እናትየዋን በጣም ያስቸግራቸው ነበር እና ያለቅሱ ምናምን ነበር.. እና እቺ እህትየዋ ለካ የኛን ቪዲዮዎች እየላከችለት ላይቭንም እንዲሁ ምናምን ነገር.. ከዛ የሆነ ቀን ላይቫችንን እያየ ከዛ ለእህቱ ደወለላት እና እንደተሰማው ምናምን አወራት አሁን በንስሐ ተመለሰ.. ይኸው አሁን የመጨረሻ ደስ ብሏት በቃ እያለቀሰች ነው ራሱ ያወራችኝ.. ጌታ ይመስገን.. የእናት ጸሎት ልጅንም ይረዳል..
@Apostolic_Answers
“ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል”
[ሐዋ 14:22]
ከሥጋ ምኞት መከልከል ይህ መከራ ነው.. በዓለም ብልጭልጭ ተጠላልፎ ከመውደቅ መሸሽ ዓለምን እምቢ ማለት መከራ ነው.. ለክርስቲያን መከራው መስቀል ነው..
የሥጋን ምኞቱን እየፈጸመ የሚኖር፤ የዓለም ወዳጅ እርሱ የመስቀል ጠላት ነው።
ስለዛ መከራን እንታገስ.. “በሥጋ መከራን የተቀበለ እርሱ ኃጢአትን ትቷልና” እንዲል ጴጥሮስም(1ጴጥ 4:1) አይዞን የእግዚአብሔር ጸጋው አጋዣችን ነውና በእርሱ ተደግፈን ጌታችንን ብቻ እየናፈቅን እንኑር..
ሰላም ዋሉልኝ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች
@Apostolic_Answers
የአዲስ አበባን ታቦት ክብር በግደለው ሁኔታ ባወጣው..??
ዌል ጥያቄ ለጴንጤዎች.. የጌታ ጠረጴዛ(ማዕድ) አላችሁ..?? ካላችሁ አሳዩን..
https://vm.tiktok.com/ZMhdYLtgo/
አሜሪካ ያላችሁ እንዴት ናችሁ.. SPOT በሚል ስም የሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን የኛ ነው አ..?? ከሆነ ጥንቃቄ ቢደረግ.. አሁን የተናገራችሁት: “faith alone saves(justifies), but faith that saves is not alone” የሚለው አገላለጽ ቃል በቃል የተወሰደው ከJohn Calvin antidote to the council of Trent 6ኛው ሴሽን 11ኛው ካነን ላይ ከመለሰው ላይ ነው.. ጥንቃቄ ቢደረግ ለክፉም ለደጉም..
አይቼው ማለፍ ስላልፈለግሁ ነው.. ጌታ ከእነርሱ ጋር ይሁን..
@Apostolic_Answers
ቀለል ያለ ዲቤት አድርጋችሁም እንዲህ ስታለቅሱ ምትከርሙ ከሆነ ወይ ማትተዉት ዲቤቱን.. ሰለቸን እኮ ሎል
ተመልከቱ የፋላሲ መአት እና የኛም መልሶቻችን😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMhjjGR8b/
አንድ የፕሮቴስታንት “ነቢይ” ጀለስ ነገር አለኝ እና ይመቸው “ገራሚ ሚስት እንደምታገባ ታይቶኛል” አለኝ😁😁 አልቻልኩም በቃ አንተ የምርም ነቢይ ነህ አልኩት ሎል..
እስቲ ዛሬ ማታ በጸሎታችሁ አስቡት የጌታ ጸሎትን እንዲጸልይ ነግሬዋለሁ.. “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ” የሚለውን..
@Apostolic_Answers
አመሰግናለሁ ግን አይገባም ነበር በእውነቱ ከሆነ..
በጣም በተቻለኝ አቅም charitable ሆኜ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ልብ ላይ እንደሚሰራ በማሰብ ተወያይቻለሁ..
ምናልባት ለጥያቄና መልስ ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆንንና ሰዓት መግደልን እዛ አስተውያለሁ እሱን አስተካክለን ሃሙስ ደግሞ እንገናኝ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”
[ማቴዎስ 11: 11]
1. ከሴቶች ከተወለዱ መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም ተባለ.. ይህም ነቢይ እንደመሆኑ ነው.. ጌታችን ከየትኞቹም ነቢያት እንደማያንስ መሰከረለት ማንም የሚበልጠው የለም በማለት.. አንድም የዮሐንስን ለየት የሚያደርገው ነቢይነት እንደ ሌሎቹ ስለ ጌታ የተናገረ ብቻ ሳይሆን አይቶታልም.. ጭራሽ አጠመቀው..
2. “በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል” ተባለ ይህም እንዲህ ያለ ክብር ያለው ዮሐንስ ገና ወደ ሐዲስ ኪዳን ስላልተሸጋገረ በሐዲስ ከሁሉ የሚያንሰው ዮሐንስን ይበልጣል ተባለ.. ይህ በክርስቶስ የሆነውን ሐዲስ ኪዳን ክብር ያሳያል.. የክርስቶስ መሆን በራሱ በብሉይ ኪዳን ካለው ትልቅ ነገር ያስበልጣልና ነው..
ስለዛ ይህንን ክብር አስጠብቆ መኖር አስፈላጊ ነው.. በሕይወታችን ሁሉ የክርስቶስ እንደመሆናችን መኖር..
@Apostolic_Answers
ዮሐዴ ኑሮ ምርር ሲለው አንትሽ ጋር ይደውልና.. 📞 “እስቲ አንዴ በቴስታ👨🦲 ብለኸኝ ወይ ገላግለኝ ከዚ ኑሮ”
“መልካም የመላጦች ቀን” እያላችሁ ሳምንቱን ሙሉ አታዝጉን🙄🙄
ስሙ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች.. የጌታ ወዳጆች.. ጠዋት ስንነሳ ብዙ ጊዜ ስልካችን አጠገባችን ስለሚቀመጥ እርሱን እናነሳና ሳናስበው ስልካችን ላይ ጊዜ አባክነን ቀናችንን እንጀምራለን.. ግን እንዲ ብናደርግስ.. ያው እኔ ሞክሬው በጣም ደስ የተሰኘሁበት..
ማታ ስንተኛ መጽሐፍ ቅዱሳችንን አጠገባችን አድርገን እንተኛና ልክ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ያው በቅዱስ መስቀል ምልክት አማትበን የጌታችንን ስም መጥራት.. ከዛ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማንሳት እና መሳም.. ከፈለጋችሁም እቀፊት የእግዚአብሔር የአባታችሁ ቃል ስለሆነ.. ከዛ አንድ ምእራፍም ትሁን ግማሽ ምእራፍ ደስ ያላችሁን ክፍል አንብቡ በናንተ ምርጫ.. ከዛም ስለ ቃሉ አመስግኑና ትንሽም ቢሆን ጸልዩ.. አባትችን ሆይን እና የልባችሁንም ብቻ ብትሆን እንኳ.. ከዛ ቀስ በቀስ እናድጋለን..
ከዛ ከጸሎት በኋላ ስልካችሁን ማየት ይፈቀዳል😁😁 ያበደ አ..?? ሞክሩት ፕሊስ
@Apostolic_Answers
እናንተስ..??😁😁
የኃጢአት ወይም ክፉ የሆነ አሳብ ድንገት ሲመጣባችሁ ምታደርጉት ነገር አለ..?? የእኔን አሳውቃችኋለሁ ቆይ ግን አንዱ ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ:-
እንዴት እንደለመደብኝ ባላስታውስም እጄ ባለበት ቦታ እዛው እንዳለ በጣቶቼ በቅዱስ መስቀል ምልክት አደርጋለሁ ከዛ ደጋግሜ የጌታን ስም እጠራለሁ.. አለኝ
እናንተስ..??
በአዲስ ዘመን.. አዲስ ሕይወትን ያላብሻችሁ.. ስለ እናንተ ስለ ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ.. ልባችሁ ለቃሉ ክፍት ስለሆነ.. ጌታን ስለምትወዱት.. ቤተ ክርስቲያኑን ስለምታፈቅሯት.. በመንፈሳዊው ነገር ለማደግ ቢያንስ ጉጉቱ ስላላችሁ.. እግዚአብሔር ይመስገን.. ሁላችንን በዚህ አዲስ ዓመት ደግሞ በፍቅሩ ያሳድገን..
@Apostolic_Answers
2016 እንዴት አለፈ ብዬ አሰብኩና.. መቼስ እግዚአብሔር ይመስገን.. ግን በብዙ ስንፍና.. በዘዋሪነት(መዞር አልወድም ነበር😁😁).. በብዙ መውደቅ እና መነሳት.. በታላቅ የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት..
2017 ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ኢየሱስን በልብ ይዞ ፍሬያማ የመሆን ዘመን ያድርግልን.. እግዚአብሔርን መውደድ ማፍቀር የሚበዛልን አመት.. አባ ገ/ኪዳን እንዳሉት በክርስቶስ የመደሰት አመት ይሁንልን