እዚህ ንግግራቸው ላይ ብዙ ሲቃወማቸው አየሁ.. ቤተ ክርስቲያናችንን ካላወቅን ለሁሉም ነገር ተቃዋሚ ብቻ ነው ምንሆነው እና ቢያንስ እዚህ ያለው ጀማ ይህንን ይወቅ..
ምግብ ሃይማኖት አይደለም ፍትሐ ነገሥቱንም ማየት ይቻላል.. ከጥንቱ የ እስራኤል ባህል ምናምን አንጻር አድርገን እዚህ ኢትዮጵያ አንበላም እንላለን እንጂ ሃይማኖት አይደለም ይሄ
@Apostolic_Answers
እኔ እንደው 10ም 20ም ሰው ጠብቄ ቪዲዮ እለቃለሁ በሆነች ደቂቃ ውስጥ የሃገር ሕዝብ መጣ ያው ክርስቲያኖችም ምናምን ስለሚመጡ.. አርፌ ቪዲዮዌን ፕራይቬት አደረግሁ😁😁
የመጡትን እስቲ ቀስ እያልኩ አያለሁ😁😁
ለጳውሎስ ፈቃዱ.. በትላንቱ ላይ ለተሰነዘረው “ነቆራ” አስተያየት እና ከአባቶች አንጻር ለተናገረው ደገኛ ነገር ደግሞ reflection ነገር
https://vm.tiktok.com/ZMh4gtDvQ/
በድጋሜ የተለቀቀ ለተሻለ ነገር
የተወሰኑ ልጆች ፈልጌ ነበር..
1. በእቅበተ እምነት ዙሪያ ክርስቲያን ወንድም እህቶቻቸውን ማገዝ በጣም በጣም በጣም የሚፈልጉ
2. እድሜያቸው ከ19-22 የሆኑ (ስለዛ ልኮረኩማቸው የምችላቸው😁😁)
3. ከዓለማዊ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የክርስትና እና ተያያዥ መጽሐፍትን ለማንበብ ጊዜ የሚኖራቸው
4. ኢንግሊዥ ላይ ጥሩ የሆነ ማንበብ እና በደንብ መረዳት የሚችል..
5. የተወሠነ የክርስትና ትምህርት ያወቀ
6. አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ያሉ
ይህንን የምታሟሉ ብቻ ከታች ባለው ሊንክ ይግቡ
/channel/+xi4Mk6JR_ZVmMTZk
👆👆
ዛሬ ከቅዳሴ ስወጣ ሰንበት ት/ቤት የማውቃት እህቴ እዛው በር ላይ ስጦታ ሰጠችኝ.. ትንሽዬ ሳይዝ ያላት ፍሬም ነገር ናት እና ስእል እንደሆነ ግልጽ ነው.. እና በቃ የእመቤታችን ጌታን አቅፋ በሆነና ጠረጴዛዬ ላይ ባስቀመጥኩት እያልኩ ሄጄ ቤት ደርሼ ስከፍት የጌታ ነው..
ስኬች ነገር ነው በእጅ የተሳለ.. በጣም ነው ደስ የሚለቅ በተለይ ስኬች የተደረገ መሆኑ.. በጣም አመሰግናለሁ ቤዙሻ😊🤗 ሌላ ዓይነት የተለመደ ትልቅ ምናምን ቢሆን እዛው አብረን ቤተ ክርስቲያን እንሰጠው ነበር ሎል
የሆነ ወቅት ላይ የመዝሙር እና የስበከት ማእበል አስነስተው ከዛም ግርር ብለው ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ሰዎች.. የወጡበትን ምክንያቶች ስሰማ በጣም ነው ያሳዘነኝ..
1. ብዙዎቹ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን ተምረው አልኖሩም.. ስለዚህም የሆነ ሰው ሳያስነቃ የፕሮቴስታንት ትምህርትን ያስተምራቸዋል.. ለምሳሌ “ጥምቀት አያድንም” አይላቸውም ግን ደግሞ ያድናል እያለም አያስተምራቸውም.. ክርስቲያናዊውን በግልጽ ሳይቃወም ፕሮቴስታንታዊውን ብቻ ያስተምራቸዋል..
2. የተማሩት ሰዎች ደግሞ የሆነ ሰዓት ላይ በአንድም በሌላም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነቋቆር ሲኖርና ትንሽ መወቀጥ ሲጀምሩ እየተገፉ ይሄዳሉ..
3. ሲገፉ ደግሞ ሲጋቱ የኖሩት የፕሮቴስታንትን ትምህርት ስለነበረ ወደ ፕሮቴስታንቱ መሄድ ይቀናቸዋል.. እነዛም አለሳልሰው ይጠሯቸዋል..
የክርስትናን ትምህርት ጭራሽ እንዳልተማሩ የሚያሳየው ቢያንስ ከፕሮቴስታንት በፊት ማየት የሚችሉት ቤተ ክርስቲያን ነበር.. ለምሳሌ.. የግብጽን ለምን አላዩም ነበር..?? ኦሬንታልን ቢተዉ ራሱ ኢስተርንን እንዴት አላዩም እላለሁ.. ይህንን ሁሉ ባላየ አልፈው ወደ ፕሮቴስታንት ከሄዱ በቃ ገና ከጅምሩ ክርስትናን አልተረዱትም ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል..
አሁን መለስ ብለው ቢያስቡበት.. ጌታ ይርዳቸው ያሳዝኑኛል..
@Apostolic_Answers
ዛሬ እመቤታችን ናት.. እሰቲ አንድ ሽልማት ያለው ጥያቄ ልጠይቃችሁ
የጌታን ልደት ይዞ ሲናገር እንዲህ ያለው ማን ነው..??
"በወንጌል የተጻፈውን ከልብህ ብታምን ወደ ራስህ ሕይወት ታስገባዋለህ.. የኢየሱስን ልደት የራስህም ታደርጋለህ.. ጌታ በአንተ ውስጥ ዳግም ሲወለድ በድንግል ማርያም እቅፍ ታርፋለህ የእርሷ ውድ ልጇም ትሆናለህ"
ለምን ላስጨንቃችሁ እኔው ልንገራችሁ.. ጋሽ ሉተር ናቸው.. በረከታቸው አይደርባችሁና እርሳቸው ስለ እመቤታችን የተናገሯቸውን አንድ ቀን በሰፊው እናያለን.. በዛም ውስጥ ፕሮቴስታንቶች ለእመቤታችን ያላቸው ክብር ቀስ በቀስ በሚገርም ሁኔታ እንዴት እየቀነሰ እንደሄደ እናያለን
ኧረ አንዳንድ ሰው ግን በጌታ.. Monophysitism ምናምን ላይ እርግጠኛ ነኝ ዶር ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ልጅ የተሻለ ያውቃሉ..
ሁሉንም አውቃለሁ እንደማትሉ አስባለሁ አላለም😁😁 ሳያስበው በጣም የኢየሱስ ጠላት የሆነ ልጅ
https://vm.tiktok.com/ZMhxG75wN/
“ነይ ማርያም” ስላላችሁ ከኢየሱስ እኩል አደረጋጅኋት ብሎ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሃሰትን ለሚያስነግረው የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ
https://vm.tiktok.com/ZMhgrtmm1/
ወንድም ኤርሚያስ ምን አለ..?? ሎል
አክሊል ጋር 1500 ሰው ምናምን ላይቭ እየገባ ያለው 40 ዶላር እየከፈሉ ፕሮሞት እያደረጉለት እንደሆነ ምስጢሩን ሰምተናል እያለ ነው😁😁
እንደዚ ምታደርጉ ሰዎች ፍቱ በ40ዋ ዶላር ዝም ብለችሁ ኑ ጥሬ እንብላበት ሎል
እግዚአብሔር አምላካችሁ የሆነላችሁ እናንተ የተለያችሁ ምርጥ ሕዝቦች.. ይመቸን በስመአብ ጌታ ይመስገን የምር “አባ” ብለን የምንጠራው አምላክ ነው ያለን..
“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ..”
[ሮሜ 8: 15]
@Apostolic_Answers
ዩትዩባችንን ድጋሜ ማንቀሳቀስ አስቤ ዛሬ ቪዲዮ ልቀርጽ ካሜራዬን ከቦርሳ ውስጥ ላወጣ ስል ቦርሳ ውስጥ እቺን ቲንሽዬ ወረቀት አየኋት..
ካሜራውን እዚው ቴሌግራም ላይ የማውቃቸው የቅርብ ጓደኞቼ ነበር የሰጡኝ.. እና ባግ ውስጥ እቺን ጽሑፍም አድርገውልኝ ነበር.. በርግጥ በሰዓቱ የጻፈችውን ልጅ አሁን ላይ አጥተናታል በሕይወት የለችም😁😁
በሉ ለዩትዩብ ቪዲዮ ልቅረጽ.. ጠብቁ ከሰሞኑ መለቀቅ ይጀምራል
መምህር ጳውሎስ ፈቃዱ ቅዱስ ቁርባን ላይ “አማናዊ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም ብለው ያስተማሩ አባቶች አሉ” ብሎ ጽፎ ሰው ላከልኝ አሁን😁😁
ዌል ዌል ዌል🥴🥴 የተጠቀሱ አባቶችን ራሳቸውን ይዘን እንያ.. ነገ ወይም ቀጣይ ላይቭ ይገባበታል.. stay tuned😎😎
ፌሚኒስቶች አካሄዳችሁን አስተካክሉ ጥላቻን ሳትዘሩ ሥሩ ሲባሉ.. ይመጡና:
“መጀመሪያ እናንተ ሥሩና ከዛ ትተቹናላችሁ” ይላሉ😁😁 መጀመሪያ እናንተ ሥሩ የሚሉት እንግዲህ ለእነርሱ ሥራ ማለት ወጥቶ ሚዲያ ላይ ጥላቻን መዝራት ነው.. ሚዲያ ላይ ባይወጡም እንኳ ወንዶች ሁሌም በተግባር የሴቶች ጠባቂ ናቸው.. ስለዛ ሰራተኞች ናቸው..
ውስጣቸው ተጎድቶ ምናምን ይሆናል ሚዲያ ላይ ሚመጡት ግን እነርሱ ላይ በደረሰው ነገር ምክንያት ጥላቻን መዝራት በፍጹም የተገባ አይደለም.. ጥላቻውን ለራሳቸው ይዘው ጥፋት እንዳይደርስ ብቻ ማሳወቅ ያለባቸውን ያሳውቁ ነው..
ፌሚኒዝም የጥላቻ እና የመለያየት አቀንቃኝ ከሆነ እንግዲያውስ የቤተ ክርስቲያንም(የኅብረቱ) ጠላት ነው.. ይህንን ያልኩት ጥላቻን ለሚዘሩት ብቻ እንጂ ለሰላማዊዎቹ አይደለም
@Apostolic_Answers
“ፌሚኒስት” ተብለው ሚጠሩት.. ሁሉም ሳይሆኑ እነዛ ከወንድ ድብ ይሻላል እያሉ አሰልቺ ወሬ ሚያወሩትን ማለቴ ነው.. እነዛ ኮመንት ሳይቀር እየወሰዱ ሲሰዳደቡ ሚውሉት በጣም ንቀት ያለባቸው.. አወራራቸው ራሱ ሰውን እንዲሰማ የማይጋብዝ አዎ እነሱን ብቻ..
እዚህ ሚዲያው ላይ ፕሮፋይላቸው ላይ ጥሩ ያልሆነ አስጊ ነገር ተገኘባቸው መሰለኝ አንዷ ወጥታ ፕሮፋይሌን አጠኑብኝ እና ለመብቴ ድምጽ ሁኑኝ ስትል ሰማኋት.. ከማህበረሰቡ መልካም አኗኗር የወጣ ነገር እየተገኘ ከሆነ መብቴን አስከብሩልኝ ሚባለው አደገኛ ነው..
ያም ሆነ ይህ እንደዚህ ዓይነት አሰልቺ ነገር ውስጥ ምትገቡ እህቶች እንደው ለክፉም ለደጉም ራሳችሁን ጠብቁ ከእንዲህ ያለው አካሄድ.. ስትሳተፉ ከሰላማዊ እና ፍቅር እና ትህትና ካለው ጋር ብቻ ይሁን
@Apostolic_Answers
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል : አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ : የካቲት 1993: ገጽ 105
አንዳንድ ሰዎች እስላም እኮ አይደለም ሚባለው ሙስሊም ነው ይላሉ..
ዌል በኛ ሃገር አጠራር እስላም ይባላል.. ተረዱኝ😁😁
አሁን እስልምና ላይ የለቀኩትን አስጠፍተውብኛል😁😁
ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቼ ናፈቁኝ የምር😭😭
እስቲ ትንሽ ቆርጠን እንልቀቀውና እንሙክር ድጋሜ..??😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።”
[ማቴ 21: 43]
ጌታችን ኢየሱስ በሚያስተምርበት ወቅት የወይን አትክልት ገበሬዎችን ምሳሌ አድርጎ ያስተማረበት ክፍል ነው.. በዚህም ምሳሌ ውስጥ እንደተገለጠው የወይን አትክልት የተከለ አንድ ጌታ ነበር እናም ለገበሬዎች አከራይቶት ይሄዳል.. የወይኑ አትክልትም ፍሬን የሚያፈራበት ጊዜ ሲቀርብ ፍሬን እንዲቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ..
ገበሬዎቹ ግን ፍሬን ከመስጠት ይልቅ የሚላኩትን የጌታውን ባሮች ሁሉ ደበደቡ ወገሩ ገድሉም.. በኋላ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ላከባቸው.. በልጁ በወራሹም ላይ ተመሳሳዩን አደረጉ ገደሉት..
ይሄንን ምሳሌ ይነግራቸውና እንግዲህ የአትክልቱ ጌታው በመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ላይ ምን ያደርግባቸዋል..?? ብሎ ራሳቸው ፈሪሳውያንን ጠየቃቸው.. እነርሱም ሲመልሱ ክፉዎቹን ገበሬዎች ያጠፋቸዋል.. የወይኑንም አትክልት ፍሬን ለሚሰጡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጡታል አሉት..
ጌታችን ግን ይህንን የተናገረው ስለራሳቸው ነበር.. በየዘመናቱ እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን ነቢያትን ባርያዎቹን ላከ.. አይሁዳውያን ግን የነቢያቱን ቃል አይሰሙም ነበር.. በኋላም ብቸኛ ልጁን ላከ.. ልጁንም አልተቀበሉም.. ልጁ ኢየሱስን ባለመቀበላቸው ምክንያት ወደ ውጭ ተጣሉ.. የወይን አትክልቱም ለሌሎች ገበሬዎች ማለትም ለሐዋርያትና ከዛም በኋላ ለሚነሱ መምህራን ተሰጠ..
አሁን ላይ ልጁን በካዱ በአይሁዳውያን ዘንድ የእግዚአብሔር መንግስት የለችም.. የእግዚአብሔር መንግስት ያለችው በእኛ ዘንድ ናት.. በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ናት..
ከዚች መንግሥት ውጪ የሆነ ሰው ኢየሱስ ንጉሡ ያልሆነለት ሰው ነው.. ከዚች መንግሥት ውጪ ያለ እርሱ የእግዚአብሔርም አይሆንም.. ጌታ ፍጻሜያችንን በዚች መንግሥት ያድርግ..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
“በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2: 8
መልካም ውሎ😊🤗
@Apostolic_Answers
በተደጋጋሚ ቅድስት ሥላሴ ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች ውስጥ..
1 + 1 + 1 = 1 ..??😭😭
https://vm.tiktok.com/ZMhQXtMXR/
እንደ ጀማሪ ፍቅረኛ ስንቴ እየጻፍኩ አጠፋሁ.. ሲረዝምብኝ ወይም ምን ይሰራል ይሄ ምናምን እያልኩ😁😁
አሁን ራሱ አጠፋሁ😭😭 በሉ ሰላም ዋሉ😭😭
ደግሞ ኖርማል ነገር እየጻፍኩ ነው ያጠፋሁት ምንም አይደለም.. ፍቅሬን ልገልጽላችሁ ምናምን አይደለም🙄🙄
ስለ እኔ አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ስሰማ.. እንደው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ነው ያለው እና ሰዎችንም ሊያጠፋ ነው እያሉ ሲጽፉ አየሁ.. ጥቂት ነጥቦችን ላስቀምጥ
1. ምናልባት አንዳንዱ ፕሮቴስታንቶች በፊት ከቤተ ክርስቲያን የወጡት እንዲህ ባለ በለብ ለብ እውቀት የተጠቁ ሰዎች ግፊት ይሆናል ብዬ አሰብሁ.. ያው የራሳቸውም ድክመት እንዳለ ሆኖ
2. “በአንዲት ቅድስት አለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የሚለውን ጸሎት ላይ ከማለት በዘለለ አብዛኞቹ ምኑንም የተረዱት አይመስልም..
3. ሰዎች እኔ ላይ እንዲደገፉ አላደረግም.. ጌታቸውን እና ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲወዱ እምነታቸውን እንዲያውቁ ብቻ ነው ጥረቴ.. ስለዚህም እኔ ብቀር እቀራለሁ.. ኤታባቴ😁😁
4. ግድ የሚላችሁ ጥቃቅን ጉዳዮች እንጂ የነፍሳት ጉዳይ አይመስለኝም.. ለዚህ ግን ያው ይቅርታ..
5. እዋዳችኋለሁ ግን አታብዙት🤪🤪
@Apostolic_Answers