ትላንት ደግሞ አንድ ፕሮቴስታንት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደተጨመረ ነግሪያችሁ ነበር እና ግን አጠፋሁት ለልጁ ጥሩ ላይሆን ስለሚችል..
እና ግን ፎቶው ላይ ፊቱ ባይታይም ኮፕቲክ እንደሆነ ግን ያስታውቃል መሰል😁😁 እና ምን ልላችሁ ነው ያው እኔ ኢትዮጵያዊም ስለሆንኩ እናም በሌሎችም ምክንያቶች በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠመቁ ነው ምፈልገው.. እና የትላንቱም ልጅ በቃ እዛ በጣም ስለፈለገ እምቢ አለኝ😁😁
ግን ደግሞ እዛም መጠመቅ ምትፈልጉ ፕሮቴስታንቶች በጣም ደስ እያለኝ ይዠያችሁ እሄዳለሁ.. እናም የጥምቀታችሁ ቀን አብሪያችሁ ነኝ😁🤗
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:
“ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።”
[ዮሐንስ 1: 9]
ከቁጥር አንድ ጀምሮ ስለ “ቃል” ይናገራል እና ዓለማት የተፈጠሩበት ያ አካላዊ ቃል ወደ ዓለም እንደ መጣ ይናገራል.. “ሁሉ በእርሱ ሆነ” በማለት እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ በቃሉ(በልጁ) እንደ ፈጠረ ይናገራል..
እናም ይህ ዓለም ደግሞ በሃጢአት ምክንያት ጨለማ ውስጥ ገባ እጅግ ከባድ ጨለማ ውስጥ.. ይህ ጨለም ለሺህ ዓመታት የነገሠ ጨለማ ነው.. ብዙ ደጋግ አባቶቻችን ሁሉ በዚሁ ጨለማ ውስጥ ኖሩ.. እነርሱ ራሳቸው ይህንን ጨለማ መግለጥ የሚችሉ ብርሃን ሊሆኑ አልቻሉምና..
ከዛም በዘመን ፍጻሜ.. ጨለማ የማያሻንፈው ለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛ ታላቅ ብርሃን ተገለጠ.. እርሱም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው.. ዓለም በልጁ ተፈጠረ.. ዓለም በልጁ ዳነ ከጨለማ ወጣ
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የዛሬው ስንክሳር
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታሕሣሥ ዐሥራ ስምንት በዝች ቀን የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የቲቶ ሥጋ አቅራጥስ(crete) ከሚባል ሃገር ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ የፈለሰበት መታሰቢያ ሆነ..[ተጨማሪ ታሪክ ከስንክሳሩ ላይ ታገኛላችሁ አንብቡ]
በቅዱስ ቲቶ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን
@Apostolic_Answers
አሁን በዚህ ዘመን ሱሪ የምትለብስ እህት ቅዱስ ቁርባን መጥታ እንዳትቀበል እንደሚል ዓይነት የግንዛቤ እጥረት ያለበት ብቻ ሳይሆን በሽታም ጭምር ያለበት ሰው ማን አለ በስመ አብ.. ለራሱ የሃጢአት ክምር ተሸክሞ በሌሎች ሰዎች ጥቃቅን ነገሮች ላይ አፉን የሚያላቅቅ ሰው..
ጌታ ስለ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ሲናገር እንዲህ ይላል:
“እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።”
[ማቴዎስ 23: 24]
@Apostolic_Answers
ከቅዱስ ቁርባን እኮ መካፈል እፈልግ ነበር.. ግን ቀሚስ ብቻ ልለብስ ነዋ.. ለሚሉ እህቶች እና ኃጢአት ብሰራስ ለሚሉ ሁሉ
https://vm.tiktok.com/ZMkrT7opD/
😁😁 እየጸፍኩ እያለ ይሄ ሰውዬ እንዲህ ያወረኝ ጀመር.. እና የምርም ገላገለኝ በቃ እንዲህ ዓይነት ነገር ከፈለጋችሁ ከእርሱ ጋር አውሩ.. እኔ ፈታ ብዬ ልኑርበት ትላልህ ሎል
የሱን አካውንት ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉት..
@christo_kentrikos
@christo_kentrikos
እኔ ያው መምህራንን መናገር አልወድም ሃይማኖትን የሚንድ ካልሆነ.. እና ቅድም በለቀኩት ቪዲዮ የደበራችሁ ካላችሁ ይቅርታ..
ግን መምህርም ልክ አይመስሉኝም.. እንዲሁ መተቸት ላይ ናቸው በቃ በስመአብ.. ባለፈው ታቦት ሌላ መሰዊያ ሌላ አሉ.. ደግሞ ዛሬ እንዲሁ ሌላ ነገር.. እና እየበዛ መሄዱ እንዲህ ዓይነት ነገር ምንም ደስ አላለኝም..
አዝናለሁ ግን ይሄንን ስል ማርያምን.. ያው ለብዙ ዘመን ከመድከማቸው የተነሳ መተቸት ራሱ ይከብዳል.. ግን ደግሞ ትንሽ..
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:
ወደ ሮሜ 3
24፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
25፤ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው..
1. ድኅነት የሆነልን እንዲሁ በጸጋው እንጂ አስቀድሞ በኛ መልካም ነገር ታይቶ አይደለም.. ስለዚህም ማንም አይመካም ከሥራ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥጦታ ነውና..
- ሥራ ያስፈልጋል ምንለው አንዴ ከዳንን በኋላ ድኅነቱን ለመፈጸም ጸጋውን በመጠቀም ፍሬ ቢስ ሳንሆን የቅድስና ሕይወትን መኖር ነው..
2. ይህንን ጸጋ ደግሞ ያገኘነው በክርስቶስ ቤዛነት ምክንያት ሲሆን እንዲሁ ዝም ብሎ ሰውን ሁሉ አዳነ አይባልም.. ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ የተገለጠ ቢሆንም ሰዎች ግን ይህንን ለማግኘት አስቀድመው ማመን አለባቸው.. “እርሱንም በእምነት የሚገኝ አድርጎ አቆመው” የሚለው ለዛ ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች.. የዩትዩብ አካውንታችን ከታች ያለው ነው እና እስቲ ሰዎች ጋር ምናምንም እንዲደርስ አድርጉ
apostolicanswers1" rel="nofollow">https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
የዩትዩብ አካውንታችንን ቀጥታ ከቲክቶክ ላይ ሄዶ ሰብስክራይብ ለማድረግ sign in አድርጉ እያለ ስለሚያስቸግር ቀጥታ በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ቤተሰብ ሁኑን እዛ ላይም
ጭራሽ እንዲህም ብለው ነበር🙄🙄 ኢክቲስ በቃ የፕሮቴስታንቱን እኔ አለሁ አንተ እኛ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው መንገድ የዘጉት ላይ ሂድባቸው😁😁
👇👇
/channel/Christo_kentrikos/11
—————-
እንደሚታወቀው ዓላማችን ሰዎች እምነታቸውን እንዲያውቁ እና በእግዚአብሔር ቤት ጸንተው እንዲኖሩ.. ብሎም ደግሞ ጌታን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናፈቅረውና ተስፋ እንድናደርገው ከዛ ቀጥሎ ደግሞ ሰዎችን ወደ ክርስትና ለማምጣት በፍቅር መማማር ነው..
እና ደግሞ በዚህም ጉዳይ እግዚአብሔር እጅጉን አብዝቶ እየረዳን ነው.. መልካም አሳቦቻችንን ሁሉ የሚያከናውንልን አምላካችንን እናመሰግነዋለን
ግን ደግሞ ምንድነው መሰላችሁ አንዳንዴ ከሥር ከሥር እያሉ በጣም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አስከባሪ መስለው ግን ደግሞ ሳያስቡት የቤተ ክርስቲያን ጠላት የሚሰራውን የሚሰሩ አንዳንዶች አሉ.. የክፋታቸው ክፋት እኛን ተሐድሶ እንደሆንን ለማስመሰል ይጥራሉ.. እሱ እንደማያዋጣ ሲያውቁ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስም ሰዎችን ለማወክ ይሞክራሉ.. ጌታ ይርዳቸው.. ከስህተታቸው ቢመለሱ ለራሳቸው መልካም ነው..
መልካም አሳብ ያላችሁ ወንድም እህቶቼ ግን ከኔ ጉድለት ሲታይ ብዙ ችግር ሊኖርብኝ ስለሚችል እባካችሁን እንደው በጌታ ቀርባችሁ ንገሩኝ.. ፍቅራችሁን በእርሱ አያለሁና.. እና እንደምወዳችሁ ደግሞ ታውቃላችሁ 😁🤗
@Apostolic_Answers
የቅዱሳን የሕይወታቸውን ታሪክ ወይም ገድላቸውን ጭራሽ ባናገኝ ግን የክርስትና ሕይወት በጣም ተራራ ሆኖብን ለመጋደል አንነሳሳም ነበር የምር.. የገድል ፊልም ስናይ እንዴት ነው የቅድስና ሕይወትን የምንናፍቀው..
ጌታ ሆይ ስለ ቅዱሳንህ እናመሰግነሃለን..
ሃጢአት በመስራት ሰው ድኅነቱን አያጣውም የሚለውን የፕሮቴስታንት አስተምህሮ በእግዚአብሔር ቃል ስናፈራርሰው መቋቋም ያቃታቸው አንዳንድ ልጆች “አይ እኛም እኮ እንደ እናንተ ነው ምናምነው” ብለው ሲመጡ ሳይ ትንሽ ፈገግ ያደርገኛል..
ፕሮቴስታንቶች ያው ድብልቅልቁ የወጣ አስተሳሰብ ነው ያላቸው ድኅነት ላይ.. አንዱ በሃጢአት ድኅነት ይታጣል ሲልህ ሌላኛው አይታጣም ይልሃል.. አንዱ እምነት ብቻ ስል ጥምቀትንም አግልዬ ነው ሲል ሌላኛው ይመጣና አንተ እውር ጥምቀትን ማግለል አይቻልም ይለዋል ሎል.. አንዱ ዳግም ውልደት(በ irresistible grace) ከእምነት ይቀድማል ሲል ሌላው ደግሞ በእምነት ነው ምንወለደው ይላል..
በፕሮቴስታንቱ መልካም ሥራ ለመዳናችን እንደ ማረጋገጫ(evidence) ይሆናል እንጂ ከዘላለም ሕይወት ጋር ግን ግንኙነት የለውም ነው ተብሎ የሚታመነው..
❓ ምናልባት ግን የዘላለም ሕየወታችንን እንዳናጣም መልካም ሥራ መስራት አለብን የተባለት የእምነት መግለጫ ካላችሁ እዚሁ ኮመንት ላይ አስቀምጡና እንየው😁😁
@Apostolic_Answers
“እዚሁ ቲክቶክ ላይ ጌታ ኢየሱስን የካዱ ብዙዎች አሉ” እያለን ነው.. ያው ከጴንጤ የወጡ ለማለት ነው..
እውነት ነው በጣም ብዙ አሉ ጴንጤን ጥለው የወጡ እነርሱ እንኳን የሚያውቋቸው.. ግን የካዱት ሌላ ኢየሱስን ነው.. ከዛም በሐዋርያት የተሰበከውን ተቀበሉ
በ16 ቀን ውስጥ 100k ፎሎወርስ..??🙄🙄
Dec 9 ነበር 400k የገባነው.. ይኸው Dec 25 ደግሞ 500k ገባን🤭🤭
ጌታ ጉባዔያችንን ይባርክ.. ዋናው የቁጥር መብዛት ሳይሆን መማማሩና ወደ ጌታ መቅረቡ ነው..
@Apostolic_Answers
ስሙ ጋይስ አምና ያወራኋችሁን ነገር በቅርቡ ብናደርገው ብዬ አሰብኩ..
ምንድን ነው እሱ..?? የሆነ መንፈሳዊ ፕሮግራም አዘጋጅተህ ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ወንድም እህቶች ምሳ ጋብዘሃቸው ወንጌል ብትሰብክላቸው..
1. አምላካቸውን እንዲያውቁ ስለ አምላካቸው ምንነገርበት
2. ከዛ የመጽናኛ ስብከት ስለ ዘላለማዊ መኖሪያቸው ቢነገራቸው ስለ ተስፋቸው ኢየሱስ ምናምን
ያው የምናዘጋጅ ከሆነ ሳንቲም ትንሽ ትንሽ አጋጭተን ነው ምናዘጋጀው.. ለአዳራሽ ለስፒከር ለዲኮር ለምሳ ምናምን.. አንተው ተወጣው እሱንም አትሉኝም መቼስ ሎል..
ምን ይመስላችኋል..??
አንድ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጨመር ቢፈልግ.. የግድ ገድላት ተአምራትን ሙሉ በሙሉ መቀበል አለበት..??
አዳዲስ ሰው በመጣ ቁጥር እነርሱን ለማስረዳት ሲባል ደጋግሞ ይሄንን ነገር ማንሳት ትንሽ አድካሚ ነው ያው ጭቅጭቅም ስለሚኖርበት😁😁
ትንሽ ወቀጣ ያስፈልገኛል ሰሞኑን.. ሚዲያው ላይም ስለበዛሁ ሎል😁😁
1. ገድላትን ማንበብ ለሕይወታችን ለተጋድሎ ስለሚያግዙን ማንበብና መጠቀም አስፈላጊ ነው..
2. ነገር ግን በገድላትም ሆነ ተአምራት ውስጥ ያለውን ሁሉ የግድ መቀበል አለብህ የሚባል ነገር የለም.. ለምሳሌ እኔ በሚጠቅመኝ መልኩ እጠቀምባቸዋለሁ.. ግን ደግሞ ማልቀበላቸውም ነገሮች አሉ.. ይሄ ግን ከክርስትና አያስወጣኝም..
3. ገድላት ተአምራት ከተጻፉበት ዘመን አንጻርም አንዳንዴ በጣም ግነታዊ ነገሮች ሊገኙበት እንደሚችሉ አምናለሁ..
4. ቤተ ክርስቲያኔም ይህንን ሙሉ በሙሉ ካልተቀበልክ የኔ አትሆንም አትለኝም.. አንድም አባትም እንዲህ ያለ አጋጥሞኝ አያውቅም እኔ..
5. አይደለም ገድላት እና ተአምራት.. የቅዱሳን ሊቃውንት አባቶቻችንን መጽሐፍት እንኳ ሙሉ በሙሉ ተቀበል አይባልም (እዚህ ላይ ቀጣይ እመጣበታለሁ በቀጣይ ጽሑፍ)
@Apostolic_Answers
ወንድማችንን ቮት አድርጉት.. ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑና ከዛም ወደታች s ቤት ስትደርሱ “sudik” የሚል አለ.. እናም እሱን ተጭናችሁ submit በሉት ከዛ ስልክ ቁጥራችሁን አስገብታችሁ የተላከላችሁን ኮድ በማስገባት ጨርሱ
https://www.tiktokcreativeawards.com/categories/16