እዩት እንግዲህ መምህራችን ጳውሎስ ሲመክረን..
“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።”
[ገላትያ 6: 1]
@Apostolic_Answers
ዌል ትንሽ ማብራሪያ ዋቄፈታ ላይ..
ቅዱስ ጳውሎስ የአቴና ሰዎችን እንዲህ አላቸው:
“..የአቴና ሰዎች ሆይ፥ እናንተ በሁሉ ነገር #አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ። የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ፦ #ለማይታወቅ_አምላክ፡ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።”
[ሐዋ 17: 22]
እነርሱ የማይታወቅ አምላክ ብለው የሚያመልኩት ጣኦትን ሊሆን ይችላል ግን እውነተኛው እርሱ ሳይሆን ይሄ ነው ብሎ ያሳያቸዋል ማለት ነው..
የዋቄፈታ ሰዎችም ደግሞ አይተውትም ሆኖ ድምጹን ሰምተውት የማያውቁት አምላክ አላቸው.. የሁሉ ፈጣሪ እንደሆነም ያስባሉ.. እንግዲያውስ ይህ ዓይነት ክብር የሚገባው ለእውነተኛው አምላክ የኢየሱስ አባት ነው.. ልጁ ኢየሱስም ከአባቱ እንደመገኘቱ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ ጌታ ነው..
እና በዚህ አምነው አምልኮዋቸውን እንዲያስተካክሉ እና ከፈጣሪያቸው ጋር እንዲገናኙ ጥሪ ማቅረብ ማለት ነው.. ያው በፍቅር እና በትህትና..
@Apostolic_Answers
ዌል እንግዲህ thank you for the 300k እና ዛሬ ማታ መጽሐፈ ሩትን እንማራለን ጌታ ከፈቀደ
https://vm.tiktok.com/ZMhhPykSF/
ያለ ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት ማስረዳት አይቻልም..
Textual criticism የሚሰራው እደክታባት እስከተገኙበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው ከዛ በፊት ስላለው ጽሑፍ እርግጠኛ የሆንነው በመንፈሱ እና በሙሽራይቱ ነው..
ከጌታ የተቀበልነው ሃይማኖትም ሆነ ቃለ እግዚአብሔር ተጠብቀው የሚኖሩት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ነው..
የራሳቸውን ሰው ሰራሽ “ቤተ ክርስቲያናት” ለማቋቋም ሲሉ የጌታ ቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆነው የተነሱ እነርሱ የጌታ መንግስት ጠላት ናቸው.. ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የጌታ መንግስት ናት..
@Apostolic_Answers
የመጨረሻ እና መዝጊያ ቪዲዮዬ ለፕሮቴስታንቶች..
እና
ለሙስሊሞች ጥሪ.. እነሱን ደግሞ እስቲ እንይ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMhrr7L4b/
ፕሮቴስታንቶች 66 ቀርቶ ከዛ ውስጥ 1 እንኳን የማይሳሳት ብለው የሚያሳዩን መጽሐፍ አይኖርም በነሱ አካሄድ.. ካለ በሉ አሳዩን😊😊
እንዴት እንደሆነ ተመልከቱ ቪዲዮውን
https://vm.tiktok.com/ZMhMVFstw/
ቀለል ያለ ዲቤት አድርጋችሁም እንዲህ ስታለቅሱ ምትከርሙ ከሆነ ወይ ማትተዉት ዲቤቱን.. ሰለቸን እኮ ሎል
ተመልከቱ የፋላሲ መአት እና የኛም መልሶቻችን😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMhjjGR8b/
አንድ የፕሮቴስታንት “ነቢይ” ጀለስ ነገር አለኝ እና ይመቸው “ገራሚ ሚስት እንደምታገባ ታይቶኛል” አለኝ😁😁 አልቻልኩም በቃ አንተ የምርም ነቢይ ነህ አልኩት ሎል..
እስቲ ዛሬ ማታ በጸሎታችሁ አስቡት የጌታ ጸሎትን እንዲጸልይ ነግሬዋለሁ.. “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ” የሚለውን..
@Apostolic_Answers
አመሰግናለሁ ግን አይገባም ነበር በእውነቱ ከሆነ..
በጣም በተቻለኝ አቅም charitable ሆኜ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ልብ ላይ እንደሚሰራ በማሰብ ተወያይቻለሁ..
ምናልባት ለጥያቄና መልስ ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆንንና ሰዓት መግደልን እዛ አስተውያለሁ እሱን አስተካክለን ሃሙስ ደግሞ እንገናኝ
ከፕሮቴስታንት ጋር በኅብረት ሆናችሁ እስልምና ላይ ለምትሰሩ እህቶቼ..
እናንተ የተወደዳችሁ ጀግኖች እህቶቼ በጣም ነው ማከብራችሁም ምኮራባችሁም.. ትጋታችሁ እና ተስፋ አለመቁረጣችሁ ያስደንቀኛል.. ጌታ በነገር ሁሉ ያግዛችሁ..
ታድያ ግን የኔ ተወዳጅ እህቶች ይህንን ሥራ ስትሰሩ ዋናው አላማችሁ ከእስላሞቹ ጋር መጨቃጨቅ እና እነሱን ማሳፈር ሳይሆን ነፍሳትን መማረክ እና ወደ ጌታ መንግሥት ማምጣት ነው.. በዚህ ውስጥ በተለይ አሁን የሚታወቁ ለቤተ ክርስቲያን ግልጽ ጥላቻ ካለባቸው ጴንጤዎች ጋር ኅብረት ማድረግ ማለት ክርስቲያኖችን ለጥፋት ማዘጋጀት ነው..
በቅንነት አይታችሁ እንዲህ የምታደርጉ እህቶች ብትቆጠቡ እንደው ከይቅርታ ጋር.. እወዳችኋለሁ.. ደግሞ ጌታ ቢረዳኝ እስልምና ላይ እንደ አቅሜ ላግዛችሁ ዝግጅቴንም እየጨረስኩ ነው..
ክርስቲያኖች እናንተም አንዳንድ እህቶች እንዲህ ያሉ ፕሮቴስታንታዊ ነገሮችን ሲለቁ አትተባበሩ..
@Apostolic_Answers
አንድ ወዳጄ አሁን እንዲህ አለኝ:
ኢሬቻ የዋቄፈታ “ሃይማኖት” ሥርዓተ አምልኮ ነው ይባላል ያው የተለያዩ ባህላዊ ነገሮችንም ቢይዝም ማለት ነው..
እንዲያ ከሆነ እዚህ ቦታ ላይ ክርስቲያን ምናልባት ከተገኘ ሊገኝ የሚገባው:
“ይህ እናንተ ዓለምን የፈጠረ ‘ዋቃ’ የምትሉት የማታውቁት አምላክ የጌታችን ኢየሱስ አባት ነው.. ሁላችንን ከሞት ያድነን ዘንድ ልጁን ላከው.. እርሱም ስለሁላችን ሞቶ ተነሣ.. ስለዚህ እኛም ሞተን እንደማንቀር እርግጥ የሆነ ተስፋን ሰጠን.. ከሞት ታመልጡ ዘንድ በልጁ በኢየሱስ እመኑ..”
ብሎ ለመናገር መሆን አለበት አለኝ.. እንዴት ነው ያስማማል..??
@Apostolic_Answers
መቃብር ቦታ አስተዋዋቂ ሆነ ደግሞ ይሄ ጀለስ😆😆 ግን መጨረሻዋን እዩአት ጥሩ መልእክትም አላት..
ፎሎው ምናምን አድርጉት እስቲ ጥሩ ያስተምራል.. ስለ መቃብር የሚያወራው አልፎ አልፎ ብቻ ነው ሎል..
https://vm.tiktok.com/ZMhreWW9J/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል
“በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።”
[ማርቆስ 8: 38]
ከላይ ከፍ ብሎ እንደተቀመጠው ጌታችን አስቀድሞ “በኋላዬ ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ብሎ ነበር.. እናም ዝቅ ብሎ “በእኔና በቃሌ የሚያፍር..” አለ..
በዚህ በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በጌታ አለማፈር ማለት ጌታ ጌታ ማለት ሳይሆን መስቀሉን ተሸክሞ እርሱን ደግሞ መከተል ነው.. ይህም በሕይወት ነው.. ዝሙትን እና ሌሎችንም ክደን ፈተናውንም ተቋቁመን ዓለምን እምቢ ብለን ጌታን ስንከተል በእርሱ አላፈርንም ማለት ነው.. ዓለም ይሸለኛል የሥጋን ፈቃድ መፈጸምን መርጬ የኢየሱስ ቃል ግን ምንም ነው ብንል ግን ያኔ በጌታ አፍረናልና የሰው ልጅ(ኢየሱስ) በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእኛ ያፍርብናል..
ስለዚህም በጌታችንና በቃሉ የምናፍር አንሁን.. ለመመስከርም ለመኖርም..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እንኳን ደስ አላችሁ..
ኦርቶዶክስ አቃብያነ እምነት እና ፕሮቴስታንት አቃብያነ እምነት እግር ኳስ ግጥሚያ ይኖረናል በቅርቡ..
ሎል😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተባለው ምስባክ
“ምድርኒ ወሀበት ፍሬሃ፤
ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ።
ወይባርከነ እግዚአብሔር፤
ወይፍርህዎ ኵሎሙ አጽናፈ ምድር።”
[መዝሙር ዳዊት 67: 6-7]
በግእዝ አጨናነኳችሁ አ..?? አይዞን እኔም ምስባክ ላይ በአማርኛ ሲሉት ስሰማ ጥቅሱን ይዤው ነው😁😁
“ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።”
ከዝናብ በኋላ ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች.. እንዲሁ ከእግዚአብሔር በረከት ወይም ጸጋ በኋላ ከምድር የተዘጋጀን እኛ ደግሞ ፍሬን እንሰጣለን.. ሰው ጌታችን ኢየሱስ ከሚሰጠው ከሕይወት ውኃ ሳይጠጣ ፍሬን ማፍራት አይችልም.. እኛ ደግሞ ከዚህ ውኃ ጠጥተናልና እንደ ምድረ በዳ እሾህና አመኬላን እንደሚያበቅል ምድር አንሁን.. ከኃጢአት ሁሉ እየራቅን ከጸጋው የተነሳ ፍሬን እናፍራ..
“እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers