አፍጥኑት አፍጥኑት
በውስጥ የማወራበትን ቴሌግራሜን ላጠፋው ስለሆነ ወደ ቤተ ክርስቲያን መመለስ ፈልጋችሁ ያወራችሁኝ እና ግን ያላናገርኳችሁ አልያም የሆነ ለብቻችሁ የማስተምርበት ቻናል ውስጥ ካላካተትኳችሁ ኑና አስታውሱኝ ትንሽ በውስጥ ጠፋ ከማለቴ በፊት
በውስጥ ብቻ ነው ትንሽ ምጠፋው ያልኩት🙄🙄 ያው ብዙ ሰው አላወራም ነው
የክርስቶስ ምስክር ቅዱስ ሚናስ ላይ ማላገጥ እና መሳደብ የሰይጣን ልጅነት ነው.. ሰማእቱ በዘመኑ ከበጉ ደም የተነሳ አባታቸውን ሰይጣንን ድል ስለነሳው አሁን ልጆቹ ለአባታቸው ይቆሙለታል.. ሳያስቡት የሚናገሩትን አያካትትም.. እነሱ ሰነፎች ናቸው.. በስንፍናቸው ሳያስቡት ሰይጣንን እያስደሰቱ ያሉ
ይህንን የጋዲን ቪዲዮ ብዙ ሰው ጋር እንዲደርስ አድርጉት 😊😊
https://vm.tiktok.com/ZMkFBgUka/
አባታችን ስለ እኛ ከተናገሩት..
ሚዲያው ላይ የክርስቶስን ነገር በሚናገሩት ሁሉ ስም አሜን ብያለሁ.. እግዚአብሔር እርሶንም ባሉበት በጤና ይጠብቅልን
በጣም ደስ የሚል አዲስ ዝማሬ አሁን ተለቀቀ.. ሁላችሁም እንድታደምጡት ጋበዝኳችሁ.. በዛውም ዩትዩቡን subscribe አድርጉ
https://youtu.be/wOp6KefwHok?si=KHiYfK0ooVCLzx0v
በ2 ወር ከምናምን ቀን ውስጥ ብቻ 100 ሺህ ጨምረን 400 ሺህ ገባን🤭🤭
በሉ በዚህ አያያዛችን ብዙ ቦታ መድረሳችን ነው.. ጌታ ይመስገን😁😁 ጌታ ብቻውን ሚከብርበት ያድርግልን
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ጋይስ.. በምስሉ ላይ ምትመለከቱት ጌች የሚሰራው ኤሌክርትሪክ ነክ ነገር ላይ ነው..
እና ከቆጣሪ በኋላ መስመር ዝርጋታ ከፈለጋችሁ፣ የኤሌትሪክ መስመር ብልሽት ካገጠማችሁ... ጥሩት።
የኤሌትሪክ ሠራተኛ የሚፈልጉ ድርጅቶችንም ካወቃችሁ አለን ብሏችኋል..
አትርሱት ፕሊስ እሺ.. አስሰሩት
ቴሌግራም ላይ በዚ @Getute21 ታገኙታላችሁ
አንድ “አንባቢ” የምትሉት ሰው ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከወጣ የሚወጣበት ምክንያት ብዬ የማስበው..
1. አንባቢ የሚመስል ግን የማያነብ ነው.. ማለትም ከመጽሐፍ ቀዱስ የሆነች የሆነች ጥቅስ ያውቃል በምልአት ግን ከመጽሐፉ ጋር ትውውቅ የሌለው..
2. ከአባቶችም ያው እንደሚታወቀው በየ ርእሱ ላይ እንዲሁ በየ ኢንተርኔቱ የሚዘዋወሩ አንዳንድ quotations በመሰብሰብ እሷንው በመናገር ብቻ እንጂ ከዛ በዘለለ የአባቶችን ነገር ለማንበብ የማይሞክር
3. አልያም ደግሞ እንደው የሚያነብ ብቻ እንጂ ከቅዱስ ቁርባን የማይሳተፍ ከሆነ..
ሳስበው እኔ ይሄ ይመስለኛል
ከምንደባደብ ይቅር በቃ😁😁 ብቻዬን አልችላችሁም ታውቃላችሁ😁😁 በዛ ላይ ደግሞ የኛ ድብድብ የቤተ ክርስቲያኒቱን ምርጥነት ምናልባት አዳዲስ ለሚመጡ ሰዎች እንዳይጋርድም ይብራ.. ያው ምኑንም ሳያውቁት በድክመት ማለት ነው
ያው ዋናው ነገር እኛ ነገሮችን እንዴት እንመልከት የሚለውን ቀስ በቀስ ማስተካከልና ኦርቶዶክሳዊ ማድረግ ነው.. አልፎ አልፎ ግን እንሄድበታለን😉😉
ጌታ ሆይ አንተ ለራስህ አድርገኸናል፤
በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ልባችን እረፍት የለውም
የአውግስጢኖስ ኑዛዜ 1፡1
@christo_kentrikos
@christo_kentrikos
👆👆 ከኢክቲስ ላይ የተወሰደ
ኧረ ገብረ ኢየሱስ ቻናሉን ከፍቷል.. ደስ ብሎኛል የምር.. በሉ ከታች ባለው ሊንክ ጆይን አድርጉት.. እንደሚጠቅመን በጣም እርግጠኛ ነኝ..
👇👇
@christo_kentrikos
@christo_kentrikos
👆👆
እህቱ ከፕሮቴስታንት ተመልሳለት ስሜታዊ ሆኖ ቪዲዮ እየሰራ መሆኑ ነው.. እና ግን ስሜን ማን ብሎ እንደጠራው ስሙ😭😭
ትዝታው የሥራህን ይስጥህ ሎል
ጆ የሚሉት አንድ ግምብ ፊት ፕሮቴስታንት አለ.. ያው አንዳንዴ ቢያዝግም የምወደው ደስ የሚል ወንድም ነው እስካየሁት..
እና ከእነሱ ግሩፕ ላይ ይሄንን ነገር ሰው ልኮልኝ አልቻልኩም😁😁 “ፕሮቴስታንት ነህ..??” ተብሎ አንዱ ተጠይቆ ለማረጋገጥ “እስቲ አክሊል ልክ አይደለም በል” እያሉት ነው😆😆 ያው ለጫወታው ነው ያሉት ግን ያስቃል😁😁
ቲክቶክ መጠቀም የማትፈልጉ አልያም በተለያየ ምክንያት ለጊዜው መግባት የማትፈልጉ..
ሔና የሚሰራቸውን ቪዲዮዎች እና እኔም የምለቃቸውን.. እዚሁ ቴሌግራም ላይ ቀጥታ ቪዲዮውን ለማግኘት ከታች ያለውን ቻናል ጆይን በሉ..
@enochenok16
@enochenok16
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:
“ደቀ መዛሙርቱም፦ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።”
[ዮሐንስ 9: 2-3]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ክፍል ሲያብራራ ከሚያስቀምጣቸው ነጥቦች ውስጥ:
1. አዎ በወላጆቹ ሃጢአት ምክንያት አልታወረም.. ሕዝቅኤልም ይህንን ይናገራል በወላጅ ሃጢአት ልጅ አይቀጣምና.. እርሱ ራሱም ሃጢአትን ስላደረገ አይደለም አዎን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ እንጂ..
2. ታድያ እንዲሁ ታውሮ መኖሩ አምላክን ኢፍትሃዊ አያስብለውምን..?? የሚል ሰው ቢኖርም ገና ከጅምሩ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውስ እርሱ አይደለምን..?? የዓይኑን ብርሃን ዘግይቶ ቢሰጠውስ አምላክ ይወቀሳልን..?? ይልቁንስ ኋላ ላይ ዓይኑን ሲያበራለት አብሮ የልቡንም ዓይን ያበራለት አይደለምን..??
ዓይን ኖሮም ኢየሱስን ካላየ ምኑን ዓይን ሆነው ነው.. ጌታችን በክፉ ነገሮች የታወረውን ዓይናችንን ይፈውሰው.. እርሱን የምናይና በእምነት በፊቱ የምንሰግድለትም ያድርገን
መልካም የጌታ ቀን
—————————————-
@Apostolic_Answers
አንዱ የነፈሰበት ፕሮቴስታንት የተናገረውን ሰማሁ..
ቆይ ጥንት ላይ ገና እመቤታችን ሳትመጣ አስቀድሞ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ተስላ ነበር የሚል ነገር በአስተምህሮ ደረጃ እኛ ጋር አለ እንዴ..??
የለም። የተለያዩ መጽሐፍት ላይ የሚገኙ ጽሑፎች ሁሉ እየተወሰዱ አስተምህሮ አይደረጉም.. እንዲህ የሚመስል ነገር ብታገኝ እንድትቀበልስ ትገደዳለህ..?? አትገደድም። ሳትቀበል የማለፍ መብትህ የተረጋገጠ ነው😁😁 ያው ሌላ ትርጉም ካለውም ትሰማለህ..
በማያስጨንቅ አትጨነቅ.. አርፈህ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እወቅ.. እንዴት መመላለስ እንዳለብህ ሥርዓቷን እያየህ እየጠበቅህ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበልክ ኑር
@Apostolic_Answers
አንድ እዚሁ ሚዲያ ላይ የተወሰነ እቅበተ እምነት ላይ የሚሰራ ፕሮቴስታንትን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋብዤው እና ቅዳሴ ላይ ተገኝቶ ነበር..
እና ምን አለኝ.. የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ በጣም ብትሰራ በጣም በርካታ ፕሮቴስታንቶችን መማረክ የምትችል ይመስለኛል አለኝ.. አዎ እኔም ይመስለኛል በጣም በቀላሉ በከተማውም በገጠሩም መሰብሰብ ትችላለች..
ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ምርጥ ናት.. አንዴ ብድግ ብላ አንዳንድ ነገሮች ላይ እርምጃ ብትወስድ በቃ..
እንደው የምመኘውን ልንገራችሁና ትንሽ ደግሞ እንደባደብ በጽሑፍ..??😁😁 ይቅር ካላችሁ ይቀራል ሎል
ፕሮቴስታንቲዝም ሳያስነቃ ፍጹም ከኢየሱስ የሚያርቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ይሄ ትምህርታቸው ነው
https://vm.tiktok.com/ZMkd6pgwJ/
ፕሮቴስታንቶች መሰዊያው ወይም የጌታ ጠረጴዛ ቅዱስ ነው.. ለጌታ ሥራ የተለየ ነው እያሉን ነው😁😁 እምነታቸው ሆኖ ሳይሆን ያው ከክርስቲያኖች ጥያቄ ለማምለጥ እንደሆነ እናውቀዋለን እንረዳዋለን😁😁
ጋዲ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMketGygc/