ከምንደባደብ ይቅር በቃ😁😁 ብቻዬን አልችላችሁም ታውቃላችሁ😁😁 በዛ ላይ ደግሞ የኛ ድብድብ የቤተ ክርስቲያኒቱን ምርጥነት ምናልባት አዳዲስ ለሚመጡ ሰዎች እንዳይጋርድም ይብራ.. ያው ምኑንም ሳያውቁት በድክመት ማለት ነው
ያው ዋናው ነገር እኛ ነገሮችን እንዴት እንመልከት የሚለውን ቀስ በቀስ ማስተካከልና ኦርቶዶክሳዊ ማድረግ ነው.. አልፎ አልፎ ግን እንሄድበታለን😉😉
ስለ ድብርት ምናምን ገብረ ኢየሱስ ከተባለው ጀለሴ ጋር እያወራን ነበር እና ምን አለኝ.. የሚደብሩ ነገሮች ገጥመውን ድብርት ውስጥ ልንገባ እንችላለን.. ግን ደግሞ ስለ ኢየሱስ ስናስብ ያንን ድብርት ሊያሸንፍ የሚችል አንዳች ደስታ ውስጣችን እየተመላ ይመጣል..
በተለይ ጌታችን በሁሉ የሚገኝ ከመሆኑ አንጻር ከአንተ አጠገብም እንዳለ ስታስተውል የእርሱን presence feel ስታደርግ አሳብህ ሁሉ ከድብርትህ ተነስቶ ወደ እርሱ መሸጋገር ይጀምራል..
አንዳንዴ እየጸለይክም ራሱ መሃል ላይ የእርሱን ከጎንህ ሆኖ በሚያሳሳ በፍቅር ዓይን እያየህ እንደሆነ ሲሰማህ ድንገት እጅህን አፍህ ላይ አድርገህ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ ብቻም ሊሆን ይችላል ጸሎትህ..
አንዳንዴ ግን በድካም ውስጥ ምናምን ሆነን ከመንፈሳዊው ነገር ርቀን እንዲህ ያሉ ነገሮችን ላናስተውልና ላናስብ እንችላለን ግን ደግሞ ቀስ በቀስ ለማደግና ከጌታ ጋር ለመኖር መሞከር.. ከቅዱስ ቁርባን አለመራቅ ይገባል.. ጌታ ደግሞ በጣም ረዳት ነው..
እንዲህ አለኝ እንግዲህ.. ለማንኛውም እናመሰግናለን ብሮስኪ.. አንድ ቀን ላይቭ እንጋብዝሃለን ግድ ነው😁😁
@Apostolic_Answers
በድጋሜ ሥራው ባላችሁኝ መሠረት..
ግን በጌታ ፈታ ልንልበት እንጂ ሰውን ለማናደድ አይደለም ማርያምን😁😁
መሃል ላይ ኤርሚንም አካተትኳት ሎል
አንዷ ፕሮቴስታንት “ጓደኛዬ ነገር” የነ ኤርሚያስንና ትዝታውን ነገር አይታ ምን ብትለኝ..?? ክርስቶስን የኔ አሳብ አይደለም ራሷ ያለችኝን ቃል በቃል ነው ማስቀምጥላችሁ😁😁
“ያጡት የጎደለባቸው ደስታና ውስጣዊ ሰላም አለ መሰለኝ.. ከኦርቶዶክስ ሲወጣ ኦርቶዶክስን እሚሳደብ.. ወንድ የናቃት ከዛ ወንዶችን ሁሉ ለበቀል እምትሳደብ አስቀያሚ ፌሚኒስት ነው ሚመስሉኝ 😏”
😂😂 ይሄ ከባድ ነው የምር.. እግረ መንገዳችሁን ቆንጂት እንድትመለስ ጸልዩላት.. ሃሪፍ ግን ደግሞ የተመታች ፕሮቴስታንት ናት ሎል
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና እንዲህ አለው፦ አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ፡ ና፥ ተከተለኝ።”
[ማርቆስ 10: 21]
ጌታችን ለድሆች በመስጠት በሰማይ መዝገብ ማግኘት እንደሚቻል በራሱ አንደበት ነገረን.. ስለዚህ በተቻለን አቅም ከፍቅር በመነጨ መልኩ ትንሽም ብትሆን ለድሆች ማካፈልን አንርሳ.. መጽሐፍም እንደሚለው “ለድሃ የሚሰጥ ለ እግዚአብሔር ያበድራል”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ኮመንት ላይ የቅዱሳንን ስም ስለጻፍክ የምን በረከት ነው ምታገኘው.. ኧረ አትጃጃሉ በጌታ..
ጣጡስ ያለው ቅድስት ታቲያናን ነው.. ሮማዊት ናት
ጀማሪ ጴንጤ ትዝታው ሳሙኤል..
ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድመለስ ታቦት መፈለጥ አለበት እያለ ነው.. በዚህ ንግግሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ምን ያህል የክርስቶስ ጠላት እንደሆነ ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZMhK6pAxr/
———
በጋሻው ጌታ ይርዳህ ወንድሜዋ.. እባክህን በድጋሜ አስብበት ብዙ ስህተት ውስጥ ነህ..
ሐዋ 2:38 ላይ ያለው ጥምቅት በውኃ ሚፈጸመው ጥምቀት አይደለምን..??
https://vm.tiktok.com/ZMhwAmv76/
አንዱ “ሉተራን ነኝ” የሚል ወንድም በሃዋዝ መመለስ እንዳዘነ ሰምቼ ትንሽ ያስቃል😁😁
አስበችሁታል ምስጢራትን ሙሉ በሙሉ ከካደ ቤተ እምነት ወጥቶ ቅዱሳት ምስጢራት በትክክል ወደሚፈጸምባት ቤተ ክርስቲያን መምጣቱ ሉተራኑን ሲያስለቅሰው ሎል.. እንደውም ለእውነተኛ ሉተራኖች ሊያስደስት ነበር የሚገባው.. ምክንያቱም በእነርሱ አስተሳሰብ አንድነት ያላቸው ከእኛ ጋር ስለሆነ.. ያው እነርሱ ምስጢራት ላይ በጣም እናምናለን ስለሚሉ..
ግን እውነተኛ confessional ሉተራኖች ብዙም የሉም እኛ ሃገር.. ውስጣቸው ያለው ጴንጤያዊነት ሳያስቡት ፈንቅሎ ይወጣባቸዋል😁😁
ቤተ ክርስቲያን በጣም ጥንቁቅ ከመሆኗ የተነሳ ሕጻናትን ስታጠምቅ እና ከጌታ ጋር መኖር እንዲጀምሩ ስታደርግ የክርስትና አባት ወይም እናት እንዲኖራቸው ታደርጋለች..
ይህንንም የምታደርገው ሕጻናቱ ከፍ እያሉ ሲሄዱ በእምነት እንዲያድጉ እና እምነታቸውንም እንዲያውቁት አስተምረው እንዲያሳድጉ ነው.. ስለዚህም እነዛ አባት ወይም እናት የሆኑት ሰዎች ለማስተማር ቃል ይገባሉ እዛው የጥምቀቱ ሰዓት..
በጣም ደስ የሚለኝ ደግሞ እኚ የክርስትና አባት እና እናት ሕጻኑን ወክለው እምነታቸውን እንዲመሰክሩ ሲደርግ የሚመሰክሩት ጸሎተ ሃይማኖትን ብቻ ነው.. “ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ…” ብሎ ጀምሮ “…በሙታንም ትንሳኤ አምናለሁ” እስከሚለው ድረስ ያለውን ማለት ነው..
@Apostolic_Answers
አሰልቺ በሆነው ሚዲያ ላይ እንደዚህ ዓይነት ቪዲዮዎችን ሳይ የሚጠብቁ ሰዎች እንዳሉ ያስታውሰኛል.. እና ሃላፊነት እንዲሰማኝ ያደርገኛል..
ግን fan የሚለውን ቃል ቀይሩልኝ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMh3mJfxk/
ሐዋዝዬ ወንድሜ በድጋሜ እንኳን ደህና መጣህ.. የምትወደው ኢየሱስ ያስፈጽምህ..
ጳውሎስ ፈቃዱ ደግሞ ምን አድርጉ ነው ሚሉን..??🙄😭
https://vm.tiktok.com/ZMh3eT2Jy/
አንድ እዚሁ ሚዲያ ላይ የተወሰነ እቅበተ እምነት ላይ የሚሰራ ፕሮቴስታንትን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋብዤው እና ቅዳሴ ላይ ተገኝቶ ነበር..
እና ምን አለኝ.. የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ በጣም ብትሰራ በጣም በርካታ ፕሮቴስታንቶችን መማረክ የምትችል ይመስለኛል አለኝ.. አዎ እኔም ይመስለኛል በጣም በቀላሉ በከተማውም በገጠሩም መሰብሰብ ትችላለች..
ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ምርጥ ናት.. አንዴ ብድግ ብላ አንዳንድ ነገሮች ላይ እርምጃ ብትወስድ በቃ..
እንደው የምመኘውን ልንገራችሁና ትንሽ ደግሞ እንደባደብ በጽሑፍ..??😁😁 ይቅር ካላችሁ ይቀራል ሎል
ፕሮቴስታንቲዝም ሳያስነቃ ፍጹም ከኢየሱስ የሚያርቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ይሄ ትምህርታቸው ነው
https://vm.tiktok.com/ZMkd6pgwJ/
ፕሮቴስታንቶች መሰዊያው ወይም የጌታ ጠረጴዛ ቅዱስ ነው.. ለጌታ ሥራ የተለየ ነው እያሉን ነው😁😁 እምነታቸው ሆኖ ሳይሆን ያው ከክርስቲያኖች ጥያቄ ለማምለጥ እንደሆነ እናውቀዋለን እንረዳዋለን😁😁
ጋዲ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMketGygc/
ሽልማት ያለው ጥያቄ.. ምርጫ ነው መልሱ..
?? ወጣቶች ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን ምንድን ነው..??
ሀ. የጌታችን ሥጋና ደም
ለ. ሀ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም
ነጻ ሲሆን ርካሽ እንዳይመስለን.. ነጻ የሆነው ምንም ብናደርግ ዋጋውን ስለማንችለው ነው.. ስለዚህ ደግሞ ጌታ ይመስገን.. እንደ ቅዱስ ቁርባን ክቡር ነገር ምን አለ.. አይቅለልብን..
@Apostolic_Answers
ዌል ዌል😁😁
በሕይወት መጽሐፍ ስሙ የተጻፈ ሰው ስሙ ከዛ መጽሐፍ ላይ የማይደመሰሰው ድል ከነሣ ነው.. ልክ ጌታችን ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን አባት መልእክትን ሲያስተላልፍ በሰርዴስ ስላሉ ሰዎች ሲናገር እንዲህ እንዳለው:
“ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም..”
[ራእይ 3: 5]
——————//////—————-
“ወርሻለሁ.. ገብቻለሁ ወደ እረፍት” የሚል ንግግርም በጣም ጥንቃቄ ይፈልጋል.. መጽሐፍ እንዲህ ይላል:
“እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። “
[ዕብራውያን 4: 11]
ወደ እረፍት ለመግባት እንትጋ ነው ሚለው.. “ወርሻለሁ” የሚለው ላይም መጽሐፍ የሚለው ወራሾች ነን(እንወርሳለን) ነው እንጂ “ወርሰናል አለቀ” የሚል ዓይነት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አይቼ አላውቅም..
“ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።”
[ራእይ 21: 7]
@Apostolic_Answers
ምናልባት የሐዋዝን “በሕይወት መዝገብ ጻፍከኝ” የሚለውን መዝሙር አለመስማት ያልቻላችሁ ሰዎች ካላችሁ.. መዝሙሩ ውስጥ ስህተት ብለን ከሐዋዝ ጋርም ያሰብነውን ክፍል ቆርጬ አውጥቼ ለቀክሁላችሁ..
ሐዊ ካየው ግን “እንደገና እስኪሰራ አትታገስም እንዴ” ማለቱ አይቀርም.. ምክንያቱም በድጋሜ ሊሰራው አሳቡ አለው.. ጌታ ይርዳው
እና ደግሞ መሳሪያዎቹም ይሄ አሁን የለቀኩላችሁ ይሻላል ከመድረክ ሥራው ይልቅ😁😁
@Apostolic_Answers
“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።”
[ፊልጵስዩስ 1: 21]
ቢኖር ክርስቶስን ያገለግላል ክብር ነው.. ቢገድሉትም ጌታን በመከራው መስሎት ወደ ዘላለም እረፍትና ክብር ይሸጋገራልና ለእርሱ ጥቅም ነው..
@Apostolic_Answers
ዶር ተስፋዬ ሮበሌ ስለ ማርያም የሚያምኗቸው 12 ነገሮች እና የኛ ትዝብት
https://vm.tiktok.com/ZMhTQ6jkt/
—————
ኢየሱስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ አላለም.. ስለዚህ አምላክ አይደለም ለሚሉ ሙስሊሞች የተሰጠ መልስ..
በጌታ አካውንቱን ፎሎው ማድረግና ቪዲዮውንም ሼር ምናምን ማድረግ እንዳትረሱ.. በጣም ጠቃሚ ወንድም ነው.. አረብኛም ጎበዝ ነው..
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMh31UCp7/
👆👆