8ኛው ሺህ🙄🙄
ትላንት በነበረን የጴጥሮስ መልእክት ጥናት እና የጌታን ዳግም የመምጣት ተስፋ ጉዳይ ላይ ስናወራ የጌታ መምጫው ዘመንም ሆነ ቀን እንደማይታወቅ ተናግሬ ነበር.. ስለዚህም 8ኛው ሺህ የሚባለውም በቤተ ክርስቲያን ደረጃ የተሰጠ ሳይሆን አንዳንዶች ያሉት እንደሆነ ማለት ነው..
የኔ ተወዳጆች ይህ የመምጫው ዘመን ወይም ቀናት ከሁለችንም የተሰወረ ነው.. በቃ እግዚአብሔር ሰውሮታል ምን ይደረግ እንግዲህ.. አይደለም ለሰዎች ለመላእክትም ሰውሮባቸዋል.. ከሰዎች መካከል አምላክን በሥጋ የወለደች እመቤታችን እና 3ኛ ሰማይ ድረስ የተነጠቀ ቅዱስ ጳውሎስ ዝም ካሉ.. ከቅዱሳን መላእክትም ቅዱስ ሚካኤልና ገብርኤል ዝም ካሉ እኛም ዝም ብንል..
ወደ ራሽያ አካባቢም የጌታ መምጫ 7ኛው ሺህ ነው ምናምን ሲሉ ነበር ይባላል አሁን አርፈው ተቀመጡ መሰል 8ኛው ሺህ ገባባቸው ሎል😁😁
ጌታችንም እንዲህ አለ:
“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የሚያውቅ የለም..”
@Apostolic_Answers
ምን ያህል ፕሮቴስታንት ወደ ክርስትና መጣ..?? ዌል ከራሳቸው እንስማ መልሱን
ለቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMkXWXVQJ/
ለኢንስታግራም
https://www.instagram.com/reel/DFYCV8IodnE/?igsh=eXI2YmM3eXF0YW9u
አፋጣኝ
ትላንት ከዲያቆን ያረጋል ጋር እያወራን ነበር እና “መድሎተ ጽድቅ” መጽሐፍን ወደ ኢንግሊዘኛ የመተርጎም አሳብ አለ እንደ ፕሮጀክት ተይዞ..
እናም ይህንን የመተርጎም ሥራ ሊሰራ የሚችል ኢንግሊዘኛ ላይ በጣም ፍሉዌንት የሆነ(ቢሆን ውጭ የሚኖር) ሰው እና ስለ ክርስትና ትምህርት የሚያውቅ ሰው ካለ እስቲ በውስጥ አናግሩኝ @aklil101 ላይ..
እና ደግሞ በክፍያ ነው አዎ🙄🙄
😁😁አባ ጆሳያህ ትሬንሃም ይባላሉ ከፕሮቴስታንት ወደ ኦርቶዶክስ የተመለሱ በጣም የተወደዱ መምህር ናቸው..
ይሄን የሰራኸው ሰው ታሳፍራለህ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMkCfNCce/
ዛሬ በጣም ልቤን የነካውና እንደው ክርስቶስን ያለማጋነን የሆነ እምባዬን ያመጣው ነገር.. አንድ ትልቅ መምህር ለጸሎት የእኛን የክርስትና ስም ጠየቀ እና እመቤቴን በጣም ደስ ይላልም በጣም ደግሞ ልብን ይነካልም.. ደግሞ ሌላም አንድ በጣም የምወደው መምህር እንደዛ ሲያደርግ አይቼ ነበር እና በስመአብ..
ክርስቶስ በሚያውቀው በእናንተ ጸሎት እና በጌታችን ርህራሄ ብቻ ነው የምንቀጥለው.. ጌታን ደግሞ ስለ ሁላችሁምም እናመሰግነዋለን
መልካም አዳር😊🤗
ላካፍላችሁ መሰለኝ የምር..
አሁን በዚህ ሰዓት ከመሸ አንድ ወዳጄ ይሄንን ይዞልኝ መጣ.. የሃገር ልብስ እና ኩታ(ደብል ነጠላ) ነው.. ሁለቱም በጣም ነው ሚያምሩት ደውሉላቸው ምናምን ስትፈልጉ በተለይ ኩታው በጣም ነው ደስ የሚለው.. የለኝም ነበር ደግሞ ሎል
እና ግን በዝች ወቅት ውስጥ ስድስት የሃገር ልብስ ነው የተሰጠኝ እና እስቲ በኔ ቁመት እና በኔ ቀጫጫነት ልክ ለሆናችሁ ላካፍላችሁ እንዴ የተወሰነውን..??😁😁
ኧረ እቺን ነገር ሌላም ሰው ሲላት አየሁና አልቻልኩም😆😆
ማርያምን በጣም ቶሎ ቶሎ እገባለሁ.. ጋይስ እኔ ከእናንተ ጋር መማማሬ ምናምን ለኔ በረከቶቼ ናችሁ እና እንደ ሥራ አይደለም ለኔ ይሄ..
ለዛሬ ግን በጊዜ ተኙ ሎል
እነሆ የመጀመሪያው የኢንስታግራም ቪዲዮ.. በዛውም ትክክለኛውን አካውንታችንን አጋሩ
https://www.instagram.com/reel/DE4fFyrI5Fk/?igsh=MXEzeG44ZTVhYmd3ZQ==
አይ በጋሻው አይ ፕሮቴስታንት
“ኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ ሃጢአተኛ ነበር አብ ኢየሱስ ላይ ተኮሰበት ቀጣው” ይሉናል
https://vm.tiktok.com/ZMkmGumwf/
“4ኪሎ ያለው ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወለሉ ላይ ሆን ተብሎ የመስቀል ምልክት ተደረገበት ጊዜው ከባድ ነው 👉ኢሉሚናቲ ምናምን”
እንዲህ እያሉ የሚያዝጉ ሰዎችን የሰማሁ እኔ ፎሎወራችን 666 ሆኖ ሳየው ይኸው ድንጋጤ ውስጥ ነኝ😭😭
ለማንኛውም የቻላችሁ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አትቅሩ ዛሬ የካቴድራሉ ምርቃት ስለሆነ
ዛሬ ደግሞ ትንሽ ወንድሞችን እንቀጥቅጥ ለምን እህቶችን ብቻ ሎል
መጽሐፈ ምሳሌ 6
32፤ ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤
እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
33፤ ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥
ስድቡም አይደመሰስም።
ካላገባሃት ሴት ጋር ምታመነዝር ከሆነ አእምሮ የጎደለህ ነህ እያለህ ነው ቃሉ.. ኧረ ወራዳም ብሎሃል እና ደግሞ ለዘላለም ማይደመሰስ ስድብ ነው በአንተ ላይ ያለው.. በዚህም ነፍስህን ታጠፋለህ ይልሃል..
እንዲህ የጎደለ አእምሮ ይዘን እንዳንኖርና ነፍሳችንንም እንዳናጠፋ ጌታ ይጠብቀን.. የሳትንም ጌታ በምህርቱ ይቀበለን ዘንድ ንስሐ እንግባ..
@Apostolic_Answers
ከዚህ ቀደም እንዳልነው ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድኅነት እንደሌለ እርግጥ ነው የሚያድነው ጥምቀትም ያለው በዛችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ በሌላ የለም
ይህንን ነገር ቅዱስ ቆጵርያኖስ ሲያብራራ ከሚጠቀማቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ኤፌሶን 5 ነው
ወደ ኤፌሶን 5
25-26፤ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
ነጽታ የተቀደሰችው ቤተ ክርስቲያን ናት ከቤተ ክርስቲያን ውጪ መንጻት መቀደስ የለም ይህም ደግሞ የሆነው “በውኃ መታጠብ እና ከቃሉ ጋር” ነው። በውኃ መታጠብ ደግሞ ጥምቀት ስለሆነ የሚታይ አገልግሎት ነው ስለዚህም የሚታየውን ይህንን አገልግሎት ምትፈጽመውም የተፈጸመላትም የምትታይ ቤተ ክርስቲያን እንዳለች ልብ ይሏል።
መቼስ ይህች ቤተ ክርስቲያን ጭራሽ በጥምቀት ውስጥ መንጻት የለም የሚሉ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች አይሆኑም አይደል? አንባቢም ሆነህ ፕሮቴስታንት ከሆንክ ምናልባት በጌታ ሰዓት እንደነበሩ ነቢያትን እንደሚያነቡ ግን እንደማይረዷቸው ፈሪሳውያን ሆነሃል ማለት ነው።
“አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል”
[ከኢክቲስ የተወሰደ]
@christo_kentrikos
👆👆
ቅዳሴ ላይ ካህኑ እጁን ታጥቦ ውኃውን ይረጫል..
ፕሮቴስታንቶች ቤተ ክርስቲያናችሁን በሃይማኖት እና በአምልኮ(ቅዳሴ) ጉዳይ በተቹ ቁጥር የጥንቷን ቤተ ክርስቲያንን ነው የሚተቹት.. ምን ያህል ከጥንቱ የተለዩ አዳዲስ ከልቶች እንደሆኑም እዩበት
ለቲክቶክ ተጠቃሚያን
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMkCsWUV4/
ለኢንስታግራም ተጠቃሚያን
👇👇
https://www.instagram.com/reel/DFSIgmoo_Z2/?igsh=MWRvazBqN3RuZnViZA==
አንዲት ጓደኛዬ ከአንዱ ወንድም ጋር የፍቅር ግንኙነት ሊጀምሩ አስበው በምን ምክንያት ሳይሰራ ቢቀር ጥሩ ነው..??
በየ ሳምንቱ መቁረብ አልፈልግም ሲላት እምቢ አለች🤭🤭 አንዱ መስፈርት ቶሎ ቶሎ ትቆርባለህ ወይ የሚል እየሆነ ነው😁😁
ነሽኩር ረቢና😁😁
የክርስቶስ ጥምቀት - በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
ቤተ ክርስቲያንን ባወቅናት ቁጥር እየወደድናት ነው ምንሄደው
ለቲክቶክ ተጠቃሚያን
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMk91FHd4/
ለኢንስታግራም ተጠቃሚያን
👇👇
https://www.instagram.com/reel/DFA2-J9oT8S/?igsh=aWdjb2wxcGhwanBq
ጥምቀት ላይ አብዝተው ለሚያገለግሉ ወጣቶች
ለቲክቶክ ተጠቃሚዎች
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMkHrtwLd/
ለ ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች
👇👇😁😁
https://www.instagram.com/reel/DE9djIfoddD/?igsh=MWt0dzdxNTlvaHFocw==
————-
አንዳንድ ክርስቲያኖች 2 ነገር ሲናገሩ ሰማሁ
1. “አክሊል የክርስቶስ መስቀል ቢረገጥም ችግር የለውም ብሏል”😭😭 እነዚህ በጣም የታዘብኳቸው የሰውን አሳብ ሚያጣምሙ አልያም ለመረዳት አቅም ላይ ያልደረሱ ናቸው..
2. “አክሊል ኢሉሚናቲን እንደ ቀልድ እያየ ነው..” የናንተን የፈረንጅ “የጭራቅ ተረት” ከሆነ ይህንንስ እውነት ብላችኋል አዎ እንደ ቀልድ ነው ማየው😭😭
አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች 4 የጌቪን ኦርቱለንድን ቪዲዮዎች አይታችሁ እንደ አደገኛ ባታዝጉንስ..?? ሎል
Infallible መጽሐፍ ቅዱስን የምትሰጥህ infallible ቤተ ክርስቲያን ከሆነች.. ታድያ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተለያየ የመጽሐፍት ቀኖና ስላላቸው የትኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት infallible..?? የሚል የሚያስቅ straw man ይሰራሉ..
1. Infallible canon አለ ብለን መች ተናገርን..?? እንደ አካባቢው ሁኔታ እና እንደ አቀባበላቸው አብያተ ክርስቲያናቱ እነርሱ ጋር የደረሱትን መጽሐፍት ይይዛሉ.. ስለዚህም የቀኖና ጉዳይ ልክ እንደ ሃይማኖት ዶግማ ምናምን አይደለም.. ይሄ ከጥንትም አለ በአይሁዳውያንም ዘንድ አለ.. አንዳንድ የአይሁድ ማህበረሰብ የሚቀበሉት የመጽሐፍት ብዛት ከሌላኛው የአይሁድ ማህበረሰብ ይለያይ ነበር ጥንት ላይ.. ይሄንን በብዙ የአይሁድና የፕሮቴስታንት እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች ማሳየት ይቻላል.. ከዚህ በፊትም የተወሰነ አሳይቼ ነበር..
2. ራሱ እጅህ ላይ ያለው የዮሐንስ ወንጌል infallible መሆኑን infallible በሆነ ደረጃ ታውቃለህ ወይ ነው..?? ማለትም ፍጹም በማትሳሳትበት ደረጃ እርግጠኛ ነህ..?? እኔ አዎ ነኝ ምክንያቱም ከቸርች ነው የተቀበልኩት.. ሌላው ግን አንዱ ጋር የሆነ መጽሐፍ ኖሮ ሌላው ጋር ድንገት ባይኖር ራሱ አያሳስበንም ከላይ ባልኩት ምክንያት..
3. ሲቀጥል ቤተ ክርስቲያን infallible ናት ያልነው ሃይማኖት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ልትሳሳት አትችልምና ነው.. ይሄንን በተደጋጋሚ ተናገርን እኮ😁😁
4. ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ለተነሳው.. autocephalous church ከሆነች ገና 60 አመቷ ነው ከዛ አንጻር የመጽሐፍትን ጉዳይ በደንብ በራሷ ትውፊት መሠረት በጉባኤ ደረጃ ቀኖናውን ማወጅ ይኖርባታል ነው.. በዘመናት ውስጥ ይህንን ስላላደረገች የሷን መጠበቅ ይኖርብናል እስከዛው ግን ይኸው ባለው እንቀጥላለን.. ልክ እንደ ጥንቱ ማለት ነው
@Apostolic_Answers
ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወለሉ ላይ የመስቀል ምልክት አለ እና እዛ ቤተ ክርስቲያን አንመጣም የሚል አለ አሉ😁😁 እኔ በእርግጥ እንዲህ ያሉ ነገሮች አያስጨንቁኝም ሆን ብለው የመስቀል ምልክት እንደማያደርጉና ያንን እያሰቡም እንደማያደርጉም ስለማውቅ..
ባይሆን እንዲህ ማመጽ ከቻልን አይቀር እኔ ርእስ ልስጣችሁ😁😁 ከዚህ ቀደም ከ4 ወር በፊት ከጻፍኩላችሁ ውስጥ:
1. የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ዋናዎቹ 27ቱ እንደሆኑ ይታወቃል ከነዚህ ጋር የሚስተካከል መጽሐፍ መቼስ አይጨመርም ብዬ አስባለሁ.. ስለዚህም የቀሩት 8ቱ የሥርዓት መጽሐፍት ከምን አንጻር እንደሚታዩ በግልጽ ማሳወቅ
2. ብሉይ ኪዳን ላይ በፍትሃ ነገሥቱ አቆጣጠር ከሆነ “ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን” ብሎ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ይቆጥረዋል.. መቼስ ከክርስቶስ በኋላ ተነስቶ ግን ደግሞ ወደ ክርስትና እንኳ ባልመጣ አንድ “አይሁዳዊ” ያልዳነ ሰው የተጻፈ ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ አይሆንም ስለዛ ከምን አንጻር እንደሆነ ማሳወቅ
3. “መጽሐፈ መቃቢያን” ተብሎ ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ እውነተኛው መጽሐፈ መቃብያን እንዳልሆነ ይታወቃል.. ስለዚህም ትክክለኛውን ወደ አማርኛ መተርጎም
4. “ተረፈ ባሮክ” ከዚህ ቀደም ቀኖና ውስጥ የለም ብያለሁ.. ዋናው “ባሮክ” እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ በታሪክ ውስጥ ሁሉ የታመነ ነው.. ግን ደግሞ ይሄኛው “ተረፈ ባሮክ” እስካየሁት ድረስ በታሪክ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የማይታወቅ በእኛ ሃገርም በቀኖና ደረጃ ሲቆጠር አላየሁም.. ከኤርሚያስ ጋር የሚቆጠረው “ተረፈ ኤርሚያስ” እና “ባሮክ” እንጂ “ተረፈ ባሮክ” አይደለም.. እናም ምናልባት ሕትመት ውስጥ ሲታይ ቀኖና እንዳይመስል ቢወጣ እንደው ቀኖና እና ኅትመትን ለይቶ የማያውቅ ብዙ ስለሆነ..
@Apostolic_Answers
Another one😁😁
ጓደኞቻቸው ሳይቀር ነው ከሥራቸው ወደ ኦርቶዶክስ እየመጡ ያሉት ይኸው በራሳቸው ምስክርነት😁😁
ባለፈውም አንዱ “እዚ ቲክቶክ ላይ ብዙ ወደ ኦርቶዶክስ የሄዱ አሉ” ብሎ ሲናገር ታስታውሳላችሁ መቼስ😁😁
ለማብሸቅ አይደለም ማርያምን እሱ ጥሪያችን አይደለም.. ግን በቃ ጌታን ስለዚህ ነገር እንድናመሰግነው እና አሁንም አብዝተን እንድንወደው ነው