በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
አይ ጽጌ ሥጦታው😊😊 አስተማሪዎቹንም እዩዋቸው
https://vm.tiktok.com/ZMFmCgf5a/
ደግሞ እስቲ ፕሮቴስታንቶችን እንጎብኝ🤪
https://vm.tiktok.com/ZMFfdE8nF/
ከሥጋዋ ሥጋ የሚባል ታሪክ የለም..??
https://vm.tiktok.com/ZMFUtBYCY/
"መሠዊያው መከራው ነው" ይልሃል😁
https://vm.tiktok.com/ZMFUhrrFY/
ወይኔ ደግሞ ሳላወራችሁ.. በጌታ ካሁን በሁዋላ ጦርነት የለም አሉ.. ኧረ በእግዚአብሔር እንዴት ነው ደስ የሚለው.. ያለቁት ዘመዶቻችን ሁሉ እጅጉን ቢያሳዝኑንም ከአሁን በሁዋላ መቆሙ ግን የምር ደስ ብሎኛል.. እንኳን
ደስ አላችሁ😘😘
የኢየሱስ ሥጋ መሠዊያ ነው ይለናል ብሮ ደግሞ
https://vm.tiktok.com/ZMFDsXYAS/
ቁርአን የኢየሱስን ፍፁም አምላክነቱን ብቻ ሳይሆን 👉ፍፁም ሰውነቱንም ይክዳል
https://vm.tiktok.com/ZMFDyPS9u/
ራሱ አስመስሎ ራሱ መርገም እንዴት ይስማማል..??
https://vm.tiktok.com/ZMFSXWeoU/
ሴቶችና "የንስሐ አባት"
እሺ ባለፈው ያቋረጥኩትን ዛሬ ላውራችሁ.. እንደምታውቁት አንዳንድ "ካህናት" በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው የፕሮቴስታንቶችን አጀንዳ የሚያስፈፅሙ አሉ.. ምናልባት ይህንን የሚያደርጉት ኃይማኖትን በማጣመም ሊሆን ይችላል..
አሁን ግን ክርስቲያኖችን ከቤተ ክርስቲያን የማባረሪያ አዲስ ስልት የሚመስል ነገር እያስተዋልን ነው.. ይህንን በጥናት ደረጃ ለጊዜው 100% እርግጠኛ ባልሆንም ድርጊቱ ግን ስላለ ጥቂት ነገሮችን ልበላችሁ..
አዲስ አበባን ጨምሮ ተለቅ ተለቅ ባሉ እንደ ሐዋሳ ባሉ ከተሞች ላይ እጅግ ተመሳሳይ ነገር እየተፈጠረ ነው.. "ምንድን ነው እሱ..??" አትሉኝም.. እሺ ልዝለቅ ወደ ዋናው ጉዳይ:
ጥቂት የሚባሉ "ካህናት"(አንዳንዶቹ ላይሆኑም ይችላሉ) እጅጉን የምንወዳቸውን የንስሐ አባቶቻችንንም እንዳናምንና ብሎም ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ጥለን እንድንጠፋ በየከተማው ትልቅ የሆነ ግፍን ይሰራሉ..
ይህ ሥራቸው በየቦታው በጣም ተመሳሳይ ከመሆኑ አንፃር የሆነ ኮርስ የወሰዱ ነው የሚምስሉት
ሥራቸው:- ሴት ክርስቲያኖችን የንስሐ ልጅ አድርገው ይወስዱና ከዚያም እጅጉን አስነዋሪ በሆነ መልኩ መካሪ መስለው sexual የሆኑ ነገሮችን ደጋግመው ያወሯቸዋል.. ስለ ፆታዊ ግንኙነት መምከሩ ሳይሆን ችግሩ ይልቁንም ሁሌም ከዚህ ጋር በተያያዘ ረጅም ወሬ ማውራቱ ነው.. በዚህም አይበቃም ይልቁንም ከእሕቶች ጋር ፆታዊ ነገር ወደ መፈፀም ያመራሉ.. ይህንን ሲያደርጉ ደግሞ አንዳንዴ በድፍረት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንደሆነ ይናገራሉ.. ሌላው ደግሞ ይህንን ሲያደርጉ ነውራቸው እንዳይታወቅ "ለማንም ሰው አትናገሩ" ይላሉ.. ይህ ሴራቸው ሲጋለጥ ደግሞ ሰዎች አዝነው እንዲተዉአቸው የሚያደርጉ ትወናዎችን ያሳያሉ..
በዚህ ውስጥ እነዚህ እሕቶች እምነታቸውን እንዲጠሉና ከቅዱስ ምስጢር(ሥጋ ወደሙ) እንዲርቁ ይሆናሉ.. ከዚያም ሙሉ በሙሉ የጌታን እምነት ይተዋሉ..
እሕቶች እንዲህ ያለ ሰው ድንገት ካጋጠማችሁ በግልፅ ለሰንበት ትምህርት ቤት የበላይ አካላት እና የዛ ሰው ልጆች ከሆኑ ሌሎች እህቶች ጋር በመነጋገር የሆነ ነገር ላይ ድረሱ.. ለህግ መስጠት ካለባችሁም አሳልፋችሁ ስጡ..
እንደውም ሰሞኑን እንዲህ ያለ ነገርን ለማድረግ ሲሞክር የተገኘን አንድ ሰው የዛው ደብር ሰንበት ተማሪዎች ናቸው መሰለኝ ክፉኛ መቱት አሉ😁😁🙊🙊 መቀጥቀጥ ጥሩ ነው አይደለም የሚለውን ብዙም አላውቅም እኔ😉😁 ያው ግን ቀጥታ ለሕግ አሳልፎ መስጠት መልካም ነው..
@Apostolic_Answers
+ ቅዳሴያዊ አምልኮ - liturgy +
ቅዳሴ(liturgy) leitourgia ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ነው ትርጉሙም የህዝብ-ተግባር ማለት ነው። ከ አምልኮ ጋር ተያይዞ ሲነገር ህዝቡ በአምልኮት ውስጥ በጋራ የሚፈጽሙት ተግባራ/የሕዝብ-ተግባር/ ግብረ ምዕመናን ያሳያል ለምሳሌ መንፈስ ቅዱስ በርናባስ እና ሳኦልን ለጠራኋቸው ስራ ለዩልኝ ብሎ የተናገረው እያመለኩ(Λειτουργούντων (Leitourgountōn)) ሊተርጊያ ላይ እያሉ ነው(ሐዋ 13፡2) ። አምልኮ ሁሉ ሊተርጊያ አይደለም አንድ አምልኮ ሊተርግያ ለመባል ምዕመናን በአንድነት የሚፈጽሙት ተግባር(ግብረ ምዕመናን) ሊኖር ይገባል ለምሳሌ እኔ ብቻዬን ተነስቼ ብሰግድ ሊተርጊያ አይባልም፤ ሁሉም ግን በጋራ አንድ ልብ ሆነው አሜን ብለው ቢናገሩ፣ ቢሰግዱ ወይም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ተሰጥዖ ቢመልሱ ሊተርጊያ ይሆናል ማለት ነው ። ሀኪሙ ሉቃስ እነ ጳውሎስ በቅዳሴያዊ አምልኮ ላይ እንደተመረጡ፣ የዘመነ ሐዋርያት ቤተክርስትያን አምልኮዋ ስርዓታዊ(liturgical) እንደነበረ በዚህ መልኩ ይነግረናል ።
ብዙ ሰዎች የዘመነ ሐዋርያት ቤተክርስትያን አምልኮዋ ስርዓታዊ ያልሆነ፣ spontaneous ፣ በግለሰቦች ቤት ይካሄድ የነበረ(መቅደስ የማይፈልግ) ፣ ግብረ ካህናት የህዝብ ተሰጥአ የሌለበት ፣ ግለሰቦች አብረው ተሰብስበው በጋራ የግል ጸሎትና ምስግና የሚያቀርቡበት አድርገው ያስባሉ ። ስርዓታዊ የቅዳሴ አምልኮ እና መቅደስ ምናምን ደግሞ የክርስትያኖች አምልኮ በጊዜ ሂደት develop ሲያደርግ ቆይቶ የመጣ ይመስላቸዋል። በደንብ ላጤነው ግን ቅዳሴያዊ አምልኮ በጊዜ ሂደት በdevelopment የመጣ ከሆነ "እንዴት ሆኖ ነው በምስራቅ በምዕራብ ፣ በአውሮፓ ፣በእስያ እና በአፍሪካ በተለያዩ ባህሎች ውስጥ ያሉ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ወደ አንድ አይነት ቅዳሴያዊ አምልኮ converge ሊያደርጉ የቻሉት? " የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ፤ እያንዳንዱ በያለበት እንደየባህሉ የየራሱን ስርዓታዊ አምልኮ develop ማድረግ ሲገባው ሁሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት ግን ተመሳሳይ መሠረታዊ ቅርጽ(homologous structure) ያለው ቅዳሴ ነው ያላቸው ይህ ደግሞ የሚያሳየን ገና ከስር መሰረቱ(ከዘመነ ሐዋርያት ቤተክርስትያን) አንድ አይነት አምልኳዊ ስርዓት ይዘው የተነሱ መሆናቸውን(same origin እንዳላቸው) ነው ።
በተጨማሪም እግዚአብሔር አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የሰጠው አምልኮ ስርዓታዊ ስለሆነ ከዚህ የምንረዳው እርሱ የሚፈልገው አምልኮ ስርዓታዊ እንደሆነ፣ ብሉይ ኪዳን ለሀዲስ ኪዳን ምሳሌ እና ጥላ እንደመሆኑ የሀዲስ ኪዳንም አምልኮ ይህንን የብሉይን እንደሚመስል(identical ባይሆም እንኳን) ነው ። ይህንን የሚክዱ ሰዎች አስተሳሰባቸው መርቅያኖሳዊ ፣ የብሉይ ኪዳኑ አምላክ ሌላ የሀዲስ ኪዳኑ አምላክ ሌላ የሆነባቸው ናቸው ። እግዚአብሔር ለሙሴ በምድር ላይ የመቅደሱን አምልኮ እንዲያቋቋም ሲነገረው አስቀድሞ በሰማይ ያለውን አምልኮ አሳይቶት ነው "በተራራው ላይ እንዳሳየሁህ ሁሉ እንደማደሪያውም ምሳሌ እንደእቃውም ሁሉ ምሳሌ ለኔ ትሰራለህ" [ዘጸ 25፡9] ። ስለዚህ በምድር ላይ በዘመነ ኦሪት ያቋቋመው አምልኮ በሰማይ ላይ ያለውን የሚመስል ነው ፤ እንዲህ ያለው ቤተመቅደስ(አደባባይ፣ ቅድስት፣ ቅድስተ ቅዱሳን) ፣ የብርሀን መቅረዝ ፣ መሰዊያ ያለበት አምልኮ በሰማይም ጭምር ያለ ነው እንደውም በምድር ላይ አስቀድሞ የተሰጠው በሰማይ ያለው ምሳሌ ነው ። ይህንን ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሳይቀር እንኳን ያነሳዋል "እነርሱስ(የኦሪት ካህናት) ሙሴ በተራራ ላይ ሳለ እንደተረዳው ለሰማያዊ ነገሮች ምሳሌ እና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ "[ዕብ 8፡5] የክርስቶስ(የሀዲስ ኪዳኑ) ግን ምሳሌ እና ጥላ ሳይሆን ሰማያዊው አገልግሎት እራሱ እንደሆነ ሲያሳስብ ደግሞ አምልኮ ይላል "እርሱም በመቅደስና በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ(λειτουργὸς (leitourgos)) ነው፤ እርሷም(ድንኳኒቱ) በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት"[ዕብ 8፡2] ማለትም ሙሴ በሰማይ ያለውን የማደሪያ ድንኳን እና ቅዱሳት ነዋያት አይቶ እነዛን የሚመስሉ(ለነዛ ምሳሌ የሆኑ) በምድር ላይ ሰራና ስርዓታዊ አምልኮ መሰረተ ክርስቶስ ግን በሰማይ ባለው ድንኳን እራሱ ሰማያዊ በሆኑት ቅዱሳት ነዋያት እዛ ባለው ስርዓት የሚያገለግል/ ሊተርጊያ የሚያስፈጽም/ ነው ። በዚህ መሰረት ጌታ "አብን በእውነት የሚሰግዱለት/የሚያመልኩበት ጊዜ ይመጣል" ሲል የተናገረው ቃል[ዮሀ 4፡23] ተፈጸመ የሀዲስ ኪዳን አምልኮ እነደነ ሙሴ በሰማይ ያለውን ስርዓት የሚመስል copy ፣ ጥላ ሳይሆን በሰማይ ያለው እራሱኑ ፣ ዐማናዊው ፣እውነተኛው ስለሆነ ።
በሰማይ ያለው አምልኮ ደግሞ ኢሳያስ እንዳየው(በ 6ተኛ ምዕራፍ) ሱራፌል አንዱ ለአንዱ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች " የሚለውን ተሰጥዖ ደጋግመው የሚሉበት ነው ። ዮሀንስ በራዕይ እንዳየው(4ተኛ ምዕራፍ) 4 ቱ እንስሳት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የነበረውና ያለው የሚመጣው ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ" የሚለውን ተሰጥኦ ቀንና ሌሊት ሳያርፉ ደጋግመው የሚመልሱበት ፣ 24ቱ ሽማግሌዎችም እየሰገዱ "ጌታችን አምላካችን ሆይ አንተ ሁሉን ፈጥረኻልና ስለፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሀል" እያሉ ተሰጥዖ የሚመልሱበት ሥርዐታዊ አምልኮ ነው ። ስለዚህ የሀዲስ ኪዳኑም እንዲሁ ያለ ስርዕታዊ አምልኮ ነው የሚሆነው መቅደስ ፣ ቅዱሳት ነዋያት ያሉበት ፣ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አንድ ቃልን የሚመልሱበት፣ የሚሰግዱበት ሊተርጊያ ነው፤ "ለአብ የሚሰግዱለት በመንፈስ የሚሰግዱለት ጊዜው አሁን ነው"[ዮሀ 4፡23] እንዲል ጌታ ስጋዊ ያልሆነ መንፈሳዊ መስዋዕት የሚቀርብበት ፣ ስጋዊ ድርጊት የቀረበት ፣ ለስጋ ፍላጎት የማንጨነቅበት መንፈሳዊ አምልኮ ነው ። በአጭሩ የሀዲስ ኪዳን አምልኮ የኦሪት አምልኮ የሚመስለው(ምሳሌው የሆነ) ፣ በቅርጽ(ስርዐታዊ በመሆን እና በመሳሰሉት) ከብሉይ ኪዳን አምልኮ ጋር ተመሳስሎ ሀዲስኪዳናዊ ምሉዕነት(የተፈጸመ መስዋዕትን፣ አማናዊነት) ያገኘ ምዕመን አንድ ልብ ሆነው የሚፈጽሙት ሊተርጊያ ነው ። ለዚህም ነው ሐዋርያት ስለ ስርዓታዊነቱ በየዕለቱ አንድ ልብ ሆነው በመቅደስ ተግተው ፤ እዛ ያለው መስዋዕት ግን ገና ስጋዊ የሆነ መንፈሳዊ ያለሆነ ስለመሆኑ ደግሞ መንፈሳዊ መስዋዕታቸውን(ቅዱስ ቁርባንን) በቤታቸው ያቀርቡ የነበረውየሐዋ 2፡46
"በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ በመትጋት፣ እንጀራውንም በቤታቸው በመቁረስ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር "
ኢሳ ከፍጥረት ሁሉ ተለይቶ ለብቻው 👉"የአላህ ቃል" የተባለው በዚህ ምክንያት ነው
https://vm.tiktok.com/ZMFD7QHqh/
ኧረ ደግሞ አንድ ጨዋታ.. አሁን ላይ "ልሳን" ተብሎ እንግዲህ ከ100 አመት ወዲህ በኦንሊ ጂሰሶች(በሥላሴ የማያምኑ) እና በጴንጤዎችና አንዳንዶች ጋር የሚታየውን አጋንንታዊ ልምምድ በመቃወማችን እኛን ምን ቢሉን ጥሩ ነው..
"በመንፈስ ቅዱስ የማያምኑ"😁😁
እነዚህ ሰዎች የሚሉን "መንፈስ ቅዱስ" ደግሞ ፈገግ ያደርጋል ሥላሴ ሃሰትም ነው ትክክልም ነው ይላል..
ለእነርሱ "ቅዱስ" በመተመሰለባቸው መንፈስ አዎ አናምንም.. ጌታ ኢየሱስ በላከው መንፈስ ብቻ እንቻ እናምናለን እርሱም ለዘላለም ከሙሽራይቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጋር ነው
@Apostolic_Answers
በነገራችን ላይ አንድ የሆነ ላይብረሪ ነገር ውስጥ የሚቀመጥ ስለሆነ የምትፈልጉት ካለ ሄዳቹ ታነባላችሁ.. የት ቤተ ክርስቲያን ላይብረሪ እንደሚሆን እናሳውቃለን
Читать полностью…