እንደተለመደው ዛሬም ቪዲዮ ስለቅ መሸብኝ.. እስቲ ሼር ቅብርጥሴ አድርጉት ሰው ጋር ሳይደርስ አይቅር ያው ባይጠቅምም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMFtLJ4TE/
ታቦት የክርስቶስ ስጋ እና ደም መሰዊያ ለመሆኑ ፤ በብሉይ ኪዳኑ ታቦት ላይ መሠረትነት ያለው ቢሆንም በአገልግሎት ይለያያሉ ብላ ቤተክርስትያን ለማመኗ የ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌን article መመልከት በቂ ነው
Читать полностью…ማኅበሩ በሕይወት መኖሩ መልካም ነው😁 በዚህ ዓይነት እነ ጴጥሮስም ተመልሰው ቢመጡ የሚቀበሏቸው አይመስለኝም አንዳንዶቹ
https://vm.tiktok.com/ZMFbTfFNN
#ማጣቀሻዎች
፩. The sacrament of thr incarnation of our lord chapter 7፡63
፪. St. Ambrose theological and dogmatic works page 217
፫. አቡሊናርዮስ (አቡርዮስ) የሎዶቂያ ጳጳስ የነበረ ሰው ሲሆን የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ጓደኛ የነበረ እና ስለ ነቂያው የእምነት ድንጋጌ አጥብቆ የተጋደለ ሰውም ነበር ቅዱስ ጄሮምም ከእርሱ ተምሮ እንደነበር ይነገራል {F.r tadros y.malaty apanaromic view of patristics in the six centuries page 154} ቢሆንም የክርስቶስ ፍፁም የሰውን ነፍስ አልነሳም የሚል እንግዳን ትምህርት በቤተክርስቲያን ስላመጣ በሁለተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ {Universal council} በቁስጥንጥንያ ትምህርቶቹም እርሱም ተወግዟል።
፬. The sacrament of thr incarnation
of our lord chapter 7፡63
፭. የአበው ጽሑፎች በዙውን ጊዜ ለሕዝብ የሚሰጡ ትምህርቶች {Oration,lecture,sermon} ናቸው በኋላ ነው ወደ ጽሑፍ የሚገለበጡት
፮. Life of st. Ambrose 18
፯. ይህ ምንፍቅና አርዮስ ዘመም {Neo arianism} ልንለው እንችላለን የክርስቶስን ከአብ ጋር መተካከል ቢያምኑም ነገርግን ለእርሱ ይገዛል ብለው ያምናሉ {F.r tadros y.malaty apanaromic view of patristics in the six centuries page 201}
፰. The sacrament of thr incarnation of our lord chapter 1፡3
፱. ብናጥስ{ኖቫትያን} የሮም ቤተክርስቲያን ቄስ የነበረ ሲሆን ከሃይማኖት አደጠው ለተመለሱ የሚደረገውን የንስሀ ጥምቀት {Re baptism} የተቃወመ ሲሆን በወቅቱ በነበሩት በቅዱስ ቆጵርያኖስ በቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘእስክንድርያ በቅዱስ ዲዮናስዮስ ሮም ምላሽ የተሰጠው ቢሆንም ባለመመለሱ በሮም በተደረገ አከባቢያዊ ጉባኤ {Local council} ትምህርቱም እርሱም ተወግዘዋል።{የታኅሣሥ ፲፱{19} ስንክሳር}
ዶናተስም የዚህ ምንፍቅና አቀንቃኝ ነበር
፲.The sacrament of thr incarnation of our lord chapter 2፡13
... ይቀጥላል
@orthodoxdigitallibrary
በሰላም ነው ግን ሰሞኑን በየቦታው የሆነ ሰውን እያፈመስነው ያለነው..??😁😁
ኧረ በጌታ ለእንደዚህ አይነት ልጆች እኛው ሶሻል ሚዲያው ላይ መልስ እንስጣቸው ያን ያህል ቦታ መስጠት አያስፈልግም እንደው..
ያው ግን የኔ ሃሳብ ነው😬😬
@apostolic_answers
እስቲ ይሄንን ቪዲዮ ሼር ምናምን እንዳርግ ከመሸ ስለለቀቅነው ብዙም ሰው ጋር ላይደርስ ስለሚችል
https://vm.tiktok.com/ZMFs6toDE/
page 62
ውይይቱን ካያቹት ሜሎስ ደጋግሞ " ቤተክርስትያን ታቦት የብሉይ ኪዳኑ ራሱ እንጂ ብላ ምታምነው የሀዲስ ኪዳን አምልኮ የሚፈጸምበት መሠዊያ ነው አትልም " ለማለት ማስረጃ ሲያደርገው የነበረው መጽሀፍ ፤ actually እንደዚህ ይላል ።
ታድያ ይሄ ማለት ወይ መጽሀፉ እንዲህ እንደሚል እያወቀ ለሀሰት ማስረጃነት ተጠቅሞበታል ፤ ወይ ደግሞ ተገቢውን research አልሰራም ።
የመጽሐፍ ርዕሰ = በእንተ ሚስጢረ ሥጋዌሁ ለእግዚእነ {The sacrament of the incarnation of our lord}
ጸሐፊ= ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን
የተጻፈበት ጊዜ = ፫፻፹፩{፫፹፪}{381{382}} ዓ/ም
ይዘት = ነገረ ክርስቶስ
#መግቢያ
፧
፩.፩ የመጽሐፉ ስያሜ
የመጽሐፉ ጸሐፊ ቅዱስ አምብሮስ "Mystery of our lord's incarnation"{De incarnationis dominicae sacramento} ብሎ ሲጠራው [፩]
የቅዱሱን ታሪክ የጻፈው ጳውሊኖስ እና ቄሳዴሮስ "The incarnation of our lord" ሲሉት ሌሎች ደግሞ "Against apollinarsts" {መድፍነ አቡሊናርዮሳውያን} ይሉታል [፪] እንዲህም ያሉት መጽሐፉ ለአቡሊናርዮስን [፫] ምንፍቅና ምላሽ ስለሰጠ ይሆናል።
፧
፩.፪ ምክንያተ ጽሑፍ
መጽሐፉ ከOn the faith {De fide} On the Holyspirit {De Spiritusancto} በኋላ ሦሥተኛ የዶግማ ሥራው ነው {ስለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ያብራራበት} መጽሐፍ ነው።
፧
"ነገርግን ምንላርግ? በየቀኑ አዳዲስ ጥያቄዎች ይመጣሉ... ለተቃውሞ ገደብ {ልክ} ከሌለው ለምላሽስ እንዴት ገደብ {ልክ} ሊኖረው ይችላል?" [፬] በማለት ሊቁ ይህን መጽሐፍ እንዲያዘጋጅ ያደረገው አምስት ጥራዝ ባለው በOn the faith{ De fide}መጽሐፍ ምላሽ የሰጣቸው የመድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ፍፁም አምላክነት ለሚክዱት ለአርዮስ ተከታዮች የማያባራ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ምእመናነ ክርስቶስን በእምነት ለማፅናት ነው።
፧
አንድም ታሪኩን ያዘጋጀው ጳውሊኖስ ስለ መጾሐፉ መዘጋጀት ምክንያት የንጉሥ ግራትያን ዘቦች {እልፍኝ ከልካይ} የሆኑ ሁለት አርዮሳውያን ስለ ጌታችን ሥጋዌ ጥያቅ ጠየቁ በበነገታውም በቤተክርስቲያን ተገኝተው ቅዱሱ ምላሽ እንዲሰጣቸው እና በትምህርቱ ለመሳተፍ ቃል ገብተው ስለ ነበር ለእነርሱ ምላሽ ለመስጠት መጽሐፉ እንደተጻፈ ይናገራል።
ነገርግን ሊቁ ቃሉን አክብሮ በሚስጢረ ሥጋዌ ላይ ትምህርት ሰጥቶ በመጽሐፍ መልክ ቢጻፍም [፭] አርዮሳውያኑ ግን ቃላቸውን ሽረው በትምህርቱም ሆነ የጠየቁትን ጥያቄ ምላሽ ለመስማት አልተገኙም[፮] ነበር በዘመኑ አርዮሳውያን በእነ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ በእርሱም ላይ መከራዎችን አድርሰውበታል።
የተለያዩ የስም ማጥፋት ወሬዎችንም በእርሱ ላይ ይነዙ ነበር።
፧
፩.፫ አጠቃላይ የመጽሐፉ ባህርይ
መጽሐፉ የሚያጠነጥነው በነገረ ክርሰቶስ ለተነሱ ምንፍቅናዎች ምላሽ መስጠት ላይ ነው።
መልስ ከተሰጣቸው የምንፍቅና አይነቶች ውስጥ አርዮሳዊነት እና አቡሊናርዮሳዊነት ሰፊውን ቦታ ሲወስዱ መንፈቀ{ተረፈ} አርዮሳዊነት[፯] አውጣኪያዊነት እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል።
፧
በቅዱሱ ዘመን አርዮሳዊነት እና መንፈቀ{ተረፈ} አርዮሳዊነት ያየለበት እና ቤተክርስቲያንን የፈተነበት ስለነበር አብዛኞቹ የቅዱሱ የዶግማ ጽሑፎቹ ለእነርሱ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው።
በመጽሐፉ ውስጥ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እግረ መንገዳቸውን አብረው ተተርጉመዋል።
የቅዱሱ የአመላለስ ዘዴም በመጀመሪያ የመናፍቃኑን ሀሳብ ካነሳ በኋላ ምላሹን ከመጽሐፍ ቅዱስ በማምጣት በአመክንዮ አስደግፎ ማስቀመጥ ነው።
፧
ሊቁ የግሪክ ቋንቋ የተማረ ላቲናዊ ቢሆንም በዚህ መጽሐፍ በግሪክ ቃላት ያሉ የነገረ መለኮት መግለጫ ቃላትን {Theological terminologies} ያብራራል ይተነትናል።
፧
፪.የመጽሐፉ የውስጥ ክፍል በጥቂቱ ሲተነተን
መጽሐፉ አስር ምዕራፍ ያለው ሲሆን የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሀሳብ በስሱ ለማየት እንሞክራለን።
፧
ምዕራፍ ፩
ይህን የመጽሐፉን ክፍል መግቢያ {introduction} ማለት ይቻላል።
በዚህ ክፍል ቅዱሱ የአቤል እና የቃየንን መሥዋዕት መሠዋት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኅብረ አምሳላዊ ትርጓሜን ይተረጉማል።
የቃየንንም መሥዋዕት ከመናፍቃን ጋር ያገናኘዋል የቃየን መሥዋዕት እግዚአብሔርን አላስደሰተውምና ነው ይህንንም ሊቁ እንዲህ ያብራራዋል "ቃየን መሥዋዕቱ እግዚአብሔርን እንዳላስደሰተ አወቀ እግዚአብሔርም “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች — ዘፍጥረት 4፥7 አለው ግን የቱ ጋር ነው ወንጀሉ? ጥፋቱ የቱ ነው? በመሥዋዕቱ አይደለም ነገርግን የመሥዋዕቱ መባእ የቀረበበት የእዕምሮ ሁናቴ ነው።" ይላል [፰]
፧
ማለትም እግዚአብሔር መሥዋዕቱን ያልተቀበለለት መሥዋዕቱን ንቆት አልነበረም ነገርግን መሥዋዕቱ የቀረበበትን መንገድ ነው ማለቱ ነው።
የቃየን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ሞገሥን እንዳላገኘ እንዳላስደሰተ ከቤተክርስቲያን ኅብረት የተለዩ የመናፍቃንም ሃይማኖት እግዚአብሔርን አያስደስተውምና።
የመናፍቃን አገልግሎት እምነት በቤተክርስቲያን ውስጥ አይደለምና ነው።
፧
ምዕራፍ ፪
በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ለቃየን የተናገረው የግሳጼ ቃል ማለትም {“መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች
— ዘፍጥረት 4፥7} አስተምህሮአቸውን ከተለያዩ የፍልስፍና ትውፊቶች ለቃረሙት በግብር ቃየንን ለመሰሉት ለአውናምዮሳውያን {መንፈቀ{ተረፈ}አርዮሳውያን} ለሰባልዮሳውያን፣ለጸረ-መንፈስቅዱስ{Pneumatomachi {ለመቅደንዮሳውያን}}፣የክርስቶስን አካል ቤተክርስቲያንን ለከፈሉ ለብናጥስ{ኖቫትያን} እና ዶናተስ [፱] እንዲሁም ለአቡሊናርዮሳውያን እና መሰል መናፍቃን እንደሚገባ ይናገራል።
፧
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ፫፡፬{3፡4}ን ዋቢ በማድረግም እንዲህ ይላል "ስለዚህ ማንም ከዘላለማዊ ንጉሥ መኖሪያ ከእናት ቤተክርስቲያን እቅፍ እንዳይለየን እንጠንቀቅ ልክ በመኃልየ መሓልይ እንዳለችው ነፍስ"[፲]
፧
ምዕራፍ ፫
በዚህ ክፍል ላይ የዮሐንስ ወንጌል ፩፡፩{1፡1}ን የሚያብራራበት {የሚተረጉምበት} ክፍል ነው።
ወንጌላዊው እንደ አሳ አጥማጅነት ሳይሆን እንደ ሰው አጥማጅነት {ሐዋርያት አሳ ማጥመድ ትተው ሰው ያጠምዱ{ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ያቀርቡ ዘንድ}በጌታ እንደተሾሙ ልብ ይላል} በመንፈስቅዱስ ተቃኝቶ መናገሩን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መናፍቃን የልብ ጆሯቸውን ዘግተው እንደሚሰሙት እና ተጨማሪ ጉዳዮችን ይዘረዝራል።