የመሢሁን መምጣት ይህም የአጋንንት መንግስት ፈርሶ የጌታ መንግስት የመምጣቱን መልካም ዜና እንደ መስማት የሚያስደስት ምን አለ..?? ነቢያት ሁሉ ይህንን ይጠብቁ ነበር.. የጌታን መወለድ..
ይህንን መልካም ዜና ደግሞ የነገረን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ነበር.. የምር ቅዱስ ገብርኤል የጌታውን ልደት ማብሰሩ ለእርሱ ክብሩ ነው.. ይህንን የምስራች ይዞልን የመጣውን ገብርኤልን አለመውደድ አለማፍቀር አንችልም..
በቅዱስ ገብርኤል በኩል የልጅህ የኢየሱስን የመምጣት ዜና የነገርከን እግዚአብሔር ሆይ ለአንተም ለልጅህም ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል.. ቃልህን ለሚጠብቀው ለገናናው መልአክህም ምስጋና ይገባል..
መልአኩ ዛሬም በሕይወታችን በኑሮዋችን ውስጥ የጌታን መምጣት የሚያበስረን ይሁንልን.. በምልጃው አይለየን
@Apostolic_Answers
ዛሬ ማታ 3:00.. ኢየሱስ አምላክ ነው.. ለሙስሊም ወንድም እህቶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው
https://vm.tiktok.com/ZMFWnCHL8/
ጌታችን ኢየሱስ የወደቀውን አለም የፈወሰውና ከውድቀት ያወጣው እንዴት ነው..?? ወደ ወደቀው አለም ገብቶ ወይስ ከወደቀው አለም ራቅ ብሎ..??
አካላዊ ቃል የመጣው ወዳልወደቀው ሥጋ ወይስ ወደ ወደቀው ሥጋ..??
ከቃል ጋር ተዋሕዶ የቃልን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ አምላክ የተባለው የወደቀው ሥጋ ወይስ ያልወደቀ ሥጋ..??
ጌታ ቢረዳኝና ቢፈቅድ ሌላ ከዚህ የሚቀድሙ ነገሮች ካልተደራረቡብኝ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአባቶች ትምህርት አድርገን ሰፋ ያለ ነገር እናወራባቸዋለን..
#ቤተክርስቲያን_ምን_ትላለች..??
@Apostolic_Answers
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡
ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!
ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን!
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት!
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት!
የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው!
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!
ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ — በእንተ ምሴተ ልደት