የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ንግግር አሁን አይደል እንዴ የምሰማው..
መጀመሪያ ነገሩ አናደደኝና ትንሽ ቆይቶ ግን አሳቀኝ.. ምንም ideaው በሌላቸው ነገር ላይ ነው እንዴ የሚናገሩት.. ሕግ ማስከበሩ ላይ ብቻ ይበርታ መንግስት እንጂ የራሷን ጉዳይማ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይተውላት..
ምን ጉድ ነው ጋይስ.. ማለቴ መግለጫው😁😁
@Apostolic_Answers
ተወዳጆች እንግዲህ እስቲ ደግሞ ልናስቸግራችሁ ነው..
1. ከEnglish ወደ አማርኛ አጠር አጠር ያሉ ጽሑፎችን በመተርጎም ልታግዙን የምትችሉ ልጆች ካላችሁ ብታሳውቁኝ እንደው ደስተኛ ነኝ.. ያው ጽሑፎቹን እኛው ነን የምንሰጣችሁ..
2. እንዲሁም ደግሞ ከአማርኛ ወደ ኦሮሚፋም መተርጎም የምትችሉ ልጆች..
3. ወደ ትግረኛም ልትተረጉሙ የምትችሉ
ተዘጋጁ እስቲ በቅርቡ በውስጥ እንድታወሩኝ አደርጋለሁ
ያው ክርስቲያን ወንድም እህቶች ብቻ
@Apostolic_Answers
አንድ አካል ሁለት ባህሪ..??
አንዳንድ ሰዎች ክርስቶስ "አንድ አካል" ነው ሲሉ የሰውነቱ አካል የለም የመለኮት ብቻ እንጂ በማለት ይህ አንድ አካል የመለኮት ብቻ ነው ይላሉ..
አካል ማለት ማንነት ስለሆነ ክርስቶስ ሁለት አካል እንደሌለው ግልጽ ነውና ዘላለማዊ ከሆነው ከቃል አካል ውጪ ሆኖ ሁለተኛ የሰው አካል ሊኖር አይችልም የለምም ታድያ ግን አስቀድሞ በነበረ ዘላለማዊ የቃል አካል ጋር አብሮ የሰውነትም አካል ተዋሕዶ አንድ ሆኗል ነው እንጂ አንድኛው የጠፋ ሆኖ አይደለም
የሰውነት አካል የለውም ማለት የሰው ማንነት የለውም እንደማለት ነው ይህም ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንትም ያወገዘችው የዶሴቲዝም ምንፍቅና ነው
@apostolic_answers
ደጋግሜ ባየው ልጠግበው ያልቻልኩት intro ቪዲዮዋችን
በነገራችን ላይ ይህንን ሁሉ የሰራው አላዛር የሚባል ወንድሜ(ወንድማችን) ነው.. ላዛሩስ ብሮዬ የምር ጌታ ያክብርልን..
የዛችን ልጅ ጸባዩዋን ችለህ መስራትህ የሚደንቅ ነው🤣🤣
ቤተ ክርስቲያንን ያሳያል ብለን እናስባለን
ከላይ -ሐ (ሐዋርያዊ)
ከታች -መ (መልሶች)
ተደርጎ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ተሰርቷል..
አዲሱን ሎጎዋችንን 12 ሰዓት ሲል የምንቀይረው ይሆናል.. በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በYT በአዲስ አቀራረብ ለመምጣታችን መግቢያ ቪዲዮ ይለቀቃል😬😬
Читать полностью…የእመቤታችን ንጽሕናና ቅድስና ሔዋን ከመወደቋ በፊት ያላትን ንጽሕና የሚያሳይ ነው.. ምንም አይነት እንከን የማይገኝበትም እንደሆነች አምናለሁ.. ምንም እንኳን አንዳንድ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህንን በማይደግፍ መልኩ የጻፉ ቢኖሩም(እሱን ወደ ፊት ሰፋ ያለ ነገር አዘጋጅቼ አሳያችሁዋለው) በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ያለው እምነት ግን እመቤታችን ከፍጥረታት ተወዳዳሪ ሊገኝላት የማትችል ናት..
ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ከእመቤታችን ንጽሕና ጋር በተያያዘ እንዲህ ይላል፡
"በትሕትናዋ፣ በንጽሕናዋ፣ በቅድስናዋ እና መልካም በሆነው ፈቃድዋ በእርሱ ተመረጠች.. ከእርሷ የተሻለ ቢኖር ያንን ደግሞ በመረጠ ነበር.."
(homilies concerning the blessed Mary: homily 1: sec 6 on the annunciation)
ታድያ ግን ያዕቆብ ዘስሩግ ይህንን ሲናገር ከሌሎችም ጋር በማነጻጸር እሷ የተሻለች የሆነችው ለእግዚአብሔር ባላት መታመን እንደሆነ ያሳያል እንጂ ገና ከጅምሩም ለእርሷ ከሌሎቹ የተለየ ሥጋ አስቀድሞ ስለተዘጋጀላት ወይም ደግሞ ከአዳም ዘር ተለይቶ አስቀድሞ ለብቻዋ የቀረ ሥጋ ሆኖ እንዳልሆነ ግልጽ ያደርገዋል.. እንዲያማ ቢሆን ንጽጽሩንስ ምን አመጣው ገና ከጅምሩ የተለያየ ሥጋ ተሰጥቷቸው ያስብላል..
ለማንኛውም እመቤታችን አሁን ለእኛም ምሳሌ የምትሆነን ከእኛው ጋር ተመሳሳይ በመሆኗ ነው.. ካልሆነ ግን እንደኛው ያለ ሥጋን ካልያዘች በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ እንደ ምሳሌም ልንይዛት አንችልም..
@Apostolic_Answers
ልክ እንደ ቤተ መንግስት ከአማራም ከኦሮሚያም ከትግራይም ከሌሎችም ተብሎ እየተቆጠረ ጳጳሳ ይኮናል እንዴ..?? ሰማያዊቷን ቤተ ክርስቲያን የምታገለግለው ሰማያዊ ሆነህ ብቻ እንጂ ኦሮሞ ወይም አማራ ስላልክ አይደለም.. ኧረ እንደው ሼም ነው እንዲህ ባልን ቁጥር የመንግስት አካላት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዳልሆንን ያስሳብቅብናል.. ጳጳስትን እኮ የሚሾመው መንፈስ ቅዱስ ነው አንተ ማን ነው በሥጋ ዘር መዳቢ አድርጎ የወከለህ..??
በኦሮሚፋ አልተሰበከም ያለ በቃ መስበክ መስራት እኮ ነው.. እንዲሁ ሽፋን የሚመስል ነገር ብቻ ማንሳት ምንድን ነው..?? መቼስ አትስበክ የሚል የለም..
ሁሉም ነገር ፖሊቲካ ይመስላል.. በፖለቲከኞች መንፈስ ውስጥ ተሆኖ ቤተ ክርስትያንን መምራት አይቻልም..
ቤተ ክርስትያንን የሚመራው እኮ የሆነ ክልል መንግስት ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው.. በዚህ ጊዜ የትም አካባቢ ያለ ክርስትያን በጸሎትም በሃሳብም አንድ ሊሆን ይገባዋል..
እንዲያ ከሆነ ደግሞ እኔ ያን ያህል ትልቅ ችግር እንደሚፈጠር አይሰማኝም.. መንጋውን የሚያውከው ይለይና ልባም የኦሮሚፋ ተናጋሪ ወንድሞቻችንና አባቶቻችን በቋንቋውም የበለጠ ወደ መስራት ይገባሉ..
ጌታ ሕዝቡን ይጠብቅ
@Apostolic_Answers
#ኢየሱስ የሚለውን ስም ስንጠራ እንዲሁ በአንደበታችን የማለት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በልባችን ይዘነው በማስተዋል ውስጥ ሆነን ከእኛ ጋር እንዳለ እያሰብን በእምነት እንጥራው..
@Apostolic_Answers
🚩 በቤተክርስቲያን መጻሕፍት ውስጥ የቤተክርስቲያን አባቶች ከክርስቶስ፥ ከቅድስት ድንግል ማርያም እና ከቅዱሳን ጋር ተያይዞ ትክክለኛ እምነት በሌለው ሰው ላይ ያስተላለፉት እርግማን ይገኛል።
ተሃድሶዎችና ሌሎች የቤተክርስቲያን ተቺዎች ግን እነዚህን ቃላት በመጥቀስ "..የኦርቶዶክስ መጻሕፍት ተራጋሚ ናቸው፥ ለድንግል ማርያም ስዕል ያልሰገደ ይጥፋ በማለት ይራገማሉ፥ በእርግማን የተሞሉ መጻሕፍት ናቸው፥ ተራጋሚ መጻሕፍት እንዴት እውነት ሊሆኑ ይችላሉ...ወዘተ" ሲሉ ይሰማሉ። ይህንንም ሀሳብ እንደ ትችት ያቀርቡታል
የእግዚአብሔር ቃል ግን እንዲህ ይላል 👇
"ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን #የማይወድ ቢኖር #የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:22)
"ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል #የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ #የተረገመ ይሁን።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 1:8)
ታዲያ....መጽሐፍ ቅዱስንም በእርግማን የተሞላ ተራጋሚ መጽሐፍ ነው ሊሉት ነው??? 🤔🤔
ከጌታ በራቅን ቁጥር.. ከዚህ ቀደም አልፈን የመጣናቸው አለማዊነት ሁሉ ይናፍቁንና ይማርኩን ይጀምራሉ..
እንደ ምህረቱ እንጂ እንደ እኛ ስንፍና አይሁንብን..
ከጌታ ሊያርቁን የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ከእኛ እንለይ..
መልካም ሰንበት(የጌታ ቀን)
@Apostolic_Answers
አዲሱን ሎጎዋችንን 12 ሰዓት ሲል የምንቀይረው ይሆናል.. በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በYT(ዩትዩብ) በአዲስ አቀራረብ ለመምጣታችን መግቢያ ቪዲዮ ይለቀቃል😬😬
@apostolic_answers