ጾም በረሃብ የመሰቃየት ጉዳይ አይደለም..
ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በመብል ብቻ አይደለምና.. ጾም እንደ ክርስቲያንነታችን ከሥጋዊ ነገሮች ጥገኝነት በቻልነው አቅም ተላቀን መንፈሳዊው ነገር ላይ የምንደገፍበት ነው..
ሥጋዊ ነገሮች ለምሳሌ ጊዜን በፊልም ብንጨርሰው አሁንም እዛው አለማዊ ነገር ላይ ተንጠልጥለናል.. እና ደግሞ ሰውን ከማስከፋትና ኃጢአቶችንም ከማድረግ እንራቅ
በተቻለን አቅም ሁሉ ኢየሱስን እያሰብን እንዋል.. የሆነ የሆነ ሰዓት ላይ አጫጭር ጸሎቶችን እንጸልይ..
ለምሳሌ ፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ
ይሄማ የጾም ጸሎት ጊዜ በመንፈሳዊ ሕይወታችን አንድ ደረጃ ከፍ የምንልባት ናት.. ግድ ነው💪💪
መልካም ጾም ጸሎት
@Apostolic_Answers
————————
ኧረ በለው.. እድሜ ግን ይቆሰው የለ እንዴ.. ለማንኛው "ቱዴ" የካቲት 6 ነው.. በሥጋ የተወለድኩበት ቀን😁😁 በእርግጥ ዋናው ልደታችን እንደ አዲስ የተፈጠርንበት የተጠመቅንበት ቀን ቢሆንም ለሱም ግን አስቀድሞ በሥጋ መወለድ ይጠይቃልና ጌታ ለክብር ወደዚህ አለም ስላመጣኝ አመሰግነዋለሁ.. ለመጣሁበት አላማ ደግሞ ያኑረኝ
Feb 14 1996
የካቲት 6 1988 (womb escape day)🤪🤪
አዲስ ነገር ከሌለ.. በ5 ግን አስባችሁታል.. ያ ሁሉ ሕዝብ.. ጌታ ሆይ በምንም አጋጣሚ እንዲ ወጥተን አናውቅም እና የዛን ቀን ሌላ ታሪክ ነው.. በዛ ላይ ደግሞ ስንዘምርበት ኡፍ🤗🤗
ብቻ የጌታ ፈቃድ ይሁን
9:00
ተንስኡ ለጸሎት
ይህች ሰዓት ጌታችን ኢየሱስ ቅድስት ነፍሱ ከቅዱስ ሥጋው የተለየችበት ስለዚህም የሞተበት ሰዓት ናት.. ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ
በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ጌታን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ
@Apostolic_Answers
"በመንፈሳዊ ሕይወቴ በእጅጉ ደክሚያለሁና መፆሜንም እንጃ" ላለኝ አንድ ወንድሜ.. ምናልባት ለሌሎችም ከጠቀመ በሚለው:
ምናልባት ላታስተውለህ ትችላለህ ግን ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ለመመለስ አንድ ጥሩ ስቴፕ ላይ ነህ.. ይህም መድከምህን አምነሃል.. ሰው መድከሙን ካላወቀ ብርታትን አይናፍቅም.. ይህ ብቻ ሳይሆን በደከምክባቸው በእነዚህ ወቅቶች ላይ ራስህን መግዛትና ከኃጢአት መራቅ ሲያቅትህ አስተውለህ ይሆናል.. ይህም ከጌታ ተለይተህ ብቻህን ማሸነፍ እንደማትችል ያስተምርሃል ስለዚህም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ሕይወት ስትመልስና የመንፈስ ፍሬዎች ሊታዩብህ ሲጀምሩ እንዳትኮፈስና ሌሎች ደካሞች ላይም እንዳትፈርድ ያደርግሃል.. ምክንያቱም አንተም ያሸንፈከው ኃይልን በሚሰጥህ በክርስቶስ እንጂ በራስህ እንዳልሆነ ታውቀዋለህና.. ስለዛ ለእነርሱም እንድትጸልይላቸው ያደርግሃል.. ይህንን የምልህ አሁን ያለህበት ሁኔታ ወደ መልካም ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት የምትገባበት መነሻህ ነውና ነው..
ይህ እንዲሆን ግን ወደ ክርስቶስ መስቀል መመልከት ተገቢ ነው.. ጌታ የሞተው ማንም ሰው እንዳይጠፋ ነው.. የጌታችን ደም ከኃጢአት ሁሉ የሚያነፃና የሚያድስ ነው.. ግን ደግሞ አስበው በሆነ ውድቀት ውስጥ ስለሆንክ አይ ይቅርብኝ ወደ አምላኬ አልመለስም ብትል ጌታን ምን ያህል እንደምታሳዝነው.. ኃጢአት ስትሰራ ታሳዝነዋለህ አልመለስም ስትል ግን ሞቱን ከንቱ ታደርገዋለህ..
ወደ መስቀሉ የምንመለስበት ቀኑም ሰአቱም አሁን ነው.. ለእኛ ያለን አምላካችን ብቻ ነውና ወደ እርሱ እንጠጋ በእርሱም እንኑር..
በጌታ ፊት ቁምና ለእኔ ያልከኝን ለእርሱም ንገረው: "ጌታ ሆይ ልቤ ደንድኗል ዘልዛላ ሆኚያለሁ.. ሁሉም ነገር ከብዶኛል" በለው.. አያይዘህም "ጌታ ሆይ መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ.. ዘመኔን እንደ ቀድሞ አድስ" በለው.. "ያለ አንተ ምንም ማድረግ አልችልምና ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር መኖርን ስጠኝ" በለው..
በዚህ እምነት ውስጥ ሆነህ አጫጭር ጸሎቶችን ጸልይ.. ለምሳሌ አባታችን ሆይን እና ደግሞ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ዎክ እያደረክም ሊሆን ይችላል ይህችን አጭር ጸሎት እየደጋገምክ ጸልይ: "ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ"
"ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ"
ድንግልንም ንገራት: "በልጅሽ በኢየሱስ መንገድ እንድሄድ እርጂኝ" በላት ትረዳሃለችም
@Apostolic_Answers
ግጭቱ ያለው በምእመናኑ መካከል ሳይሆን በምእመናኑ እና "ሕግ አስከባሪ" ተብለው በተቀመጡት መካከል እንደሆነ ነው እያየን ያለነው..
በኦሮሚያ ክልል ያለው ምእመኑ ግን እንዴት ደስ እንዳለኝ የምር.. እነ ይቴ ጭሷን(አሁን ጰጵሳለች አሉ😁😁 አንተ እዚ ፍዘዝ ይቴ ጰጵሳለች) ሕዝቡ አንቀበልም ብለው እየሞቱ ነው..
ስለዚህም ሕዝብ ከሕዝብ ጋር አይደለም ግጭቱ
@Apostolic_Answers
ንስሐ መግባት እንዲሁ "ኃጢአት ሰርቻለሁ" ብቻ ማለት ሳይሆን እያንዳንዱን ኃጢአታችንን መዘርዘርም ይጠይቃል..
ሰው ታምሞ ወደ ህክምና ሲሄድ እውነተኛ ፈውስን ማግኘትን ከፈለገ "ታምሚያለሁ" ብቻ ሳይሆን የሚለው እያንዳንዱን የህመሙን ምልክቶች ይዘረዝራል..
እንዲሁ ደግሞ በመንፈሳዊ ህመም ውስጥ ሆነን ከኃጢአት በሽታ መፈወስን የምንፈልግ እኛ እያንዳንዱን ኃጢአታችንን በመዘርዘር ከሁሉም ልንፈወስ ይገባል..
እና ደግሞ ንስሐ መግባት አያስፈራም.. እግዚአብሔር ያውቀዋል ከእኛ የሚፈልገው ኃጢአት ማድረጋችንን አምነን እንድንናዘዝና ይቅርታ እንድንጠይቀው ነው..
የንስሐ አባቶቻችን ሰዎች ናቸው እነሱም ራሳቸው ፈተናን ያውቁታል ይወድቃሉ ይነሳሉ ስለዛ ምንም ልንፈራ አይገባም
ባይሆን ንስሐ የምንገባው ጌታን ስለምንወደው ከእርሱ ጋር አብረን እንድንኖር ስለዚህም ከቅዱስ ምስጢርም እንድንካፈል ነውና ከንስሐ በሁዋላ ወደ ቅዱስ ቁርባን run🏃🏃♀️
@Apostolic_Answers
ኧረ የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ እነ አካለ ወልድ የትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለጊዜውም ቢሆን እንዳይገቡ ታግደዋል አሉ😁😁
ስሰማ ሳላስበው የሚገርም ሳቅ ነው የሳኩት🤭🤭
ጌታ ይመስገን እስቲ ነገ ደግሞ እንሰማለን
የግድ መሞት ላይጠበቅብን ይችላል በነገራችን ላይ
የማቴዎስ ወንጌል 10
16፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ 👉እባብ ልባሞች(ብልህዎች) እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
ይቅርታ ተወዳጆች ግን ስሜታችንን ብቻ ሳይሆን ጭንቅላታችንንም ልንጠቀም ይገባል.. ስለዚህም ምንም ክርስቲያን ሳይሞትብን ተጽእኖ መፍጠር የምንችልባቸውን መንገዶች መመካከር መልካም ነው..
ሰው ቤቱ ቁጭ ብሎ "ሂዱ" ምናምን ብሎ ወደ ጦርነቱ ሰውን ሲጠራና በቦታው ላይ ሲገኝ ተመሳሳይ አይደለም ውጭ እና አዲስ አበባ ላለን ሰዎች ቀላል መስሎ እንዳይታየን እፈራለሁ..
ስለዛ እስከ የካቲት 5 በተቻለን አቅም ራሳችንን እንጠብቅ.. ምንም ምክንያትም አንስጥ እላለሁ
ኧኸ ኧኸ.. ይኸው እኛ ደብር አሁን ምሽት ላይ ብዙ ሰው መጥቶ ጸለይን አሁን ደግሞ ጧፋችንን ለኩሰን ልንዘምር ነው.. በመከራ ውስጥ ሆነን እንዘምራለን..
ደግሞኮ ስንጸልይ ስለራሳችን ብቻ አይደለም.. ስለ ሚያሳድዱንም ጭምር እንጂ.. ምክንያቱም ባለማወቅ(ክርስቶስን) ይህንን ያደርጋሉና..
@Apostolic_Answers
6:00
ተንስኡ ለጸሎት
ይህች ሰዓት ጌታችን ኢየሱስ የተሰቀለበት ሰዓት ናት.. አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር ይሰቀል ዘንድ እርሱ ስለሁላችን ተሰቀለ..
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ጌታን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ
የምንችል ደግሞ ወደ ቅዳሴ እንሂድ