በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ደጋግመን ኃጢአት የሰራንባቸውንና የምንሳነፍንባቸውን ጊዜያት ለበጎ እንጠቀማቸዋለን:
እኛ በጌታ እርዳታ ስንበረታ በሌሎች ኃጢአትና ስንፍና ቶሎ ከመፍረድ ይልቅ እንድናዝንላቸው ያደርገናል.. ይህ ደግሞ ለእነርሱ ወደ መጸለዩ ይመራናል..
ስለዛ እኛ ራሳችን ደግሞ ምን ያህል ደካሞች እንደሆንን አንርሳ.. ምንም ከፍ ብንል በጌታ ነውና ልንኮፈስ አንችልም..
ጌታ ያሳድገን(በመንፈስ)
@apostolic_answers
የዝሙት አሳብ እኔ ሳልፈልገው ይመጣብኛል ከዛም ወደሱ እሳባለሁ.. ምናልባትም ከሃሳብም ዘልዬ የሆኑ ነገሮችን አደርጋለሁ.. ልክ ሲያልፍ መጸጸት እጀምራለሁ..
ምን ላድርግ..??
1. ሚስት ከሌለህ በጭራሽ ስለ ግንኙነት አታስብ
2. የምታየውን ነገር በጣም ምረጥ.. ፊልም የምታይ ከሆነ ፊልሙ ወደ እንደዚህ አይነት ሙድ ውስጥ የሚከት ነገር በፍጹም ሊኖረው አይገባም.. ትንሽ እንኳን ካለው በቃ አእምሮህ ላይ ተቀምጦ ለወደፊትህም ሌላ ፈተና ይሆንብሃል.. ስለዛ ገና ከጅምሩ አሳቦቹ እንዳይመጡ ተከላከል
3. አንተ ባትፈልገውም አዎ አሳቡ ሊመጣ ይችላል ግን ደግሞ ለዛ አሳብ ተባባሪ አትሁን.. አልወድቅም ብለህ በማሰብ ወይም ማሰቡ ብቻ ችግር የለውም ብለህ ተዘናግተህ በአሳብ ወደዛ አትወሰድ.. ይልቁንም ገና አሳቡ ሲመጣ ራስህን በሌላ ነገር ቢዚ አድርግ..
4. ፈተናው በጣም የከበደ ሲመስልህ የጌታን የስቅለት ስእል እያየህ እንዲህ ብለህ ተናገር፡ "አዎ ፈተናው ብርቱ ነው.. አንተ ግን ከፈተናዎችም ሁሉ በላይ የበረታህ ነህ" ስለዚህም የመስቀሉን ኃይል ትታጠቃለህ
5. ጦርነት ሜዳ ውስጥ ነህና ሁሌም ክርስቶስ በአንተ ኖሮ እንዲዋጋልህ ፍቀድለት.. እርሱ በአንተ ይኖር ዘንድ ንስሐ እየገባህ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ደጋግመህ ተሳተፍ.. ሁሌም አጫጭርም ቢሆን ጸሎት አድርግ..
እና ደግሞ ብቻችሁን አትሁኑ ከሰው ጋር መቀላቀል ምናምን ፒስ ነው
ጌታ ይርዳን
@Apostolic_Answers
ጠዋት ላይ ነው አሉ..
አቡ እና ጋዲ ቁርስ አብረው ነው የበሉት.. ያው እነ አቡ ጋር ስላደሩ..
አቡ እንቁላል ነበር ሰርቶ ያበላው እና አቡን ማን ቢሉት..??
"መጋቤ እንቁላል"🤭🤭
ነፃ ፈቃድ እና
የፈጣሪ አስቀሞ ማወቅ
https://vm.tiktok.com/ZMYTvdoFX/
ሸሚዜን ስቆልፍ ትዝ ያለኝ ነገር😳😳
ያኔ ፍንዳታ እያለን ሸሚዛችንን ከላይ ያለችውን ብቻ ቆልፈን ከታች የምንተወው ግን ምን ጉድ ነው..??😬😬
የሆነ ቀንማ ትዝ ይለኛል ጥቁር ሸሚዝ ለብሼ እንደዛ ቆልፌ ነፋስ ሲመጣ አስቡት Batman🤦♂️🤦♂️
ጤነኞች አይገባችሁም ያው😁😁
"ለኃጢአቴ አንዴ ከተከፈለልኝ ለምን እጠየቃለው..??"😬😬
https://vm.tiktok.com/ZMYvPtvtH/
የኢየሱስ ጸሎት ስለ አንድነት
እና የፕሮቴስታንት ክፍፍል
https://vm.tiktok.com/ZMYW9mWBc/
ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተንሥአ እምዉታን
እኛስ ከሙታን የተነሳውን ክርስቶስን እንሰብካለን
1ኛ ቆሮንቶስ 15
3፤ መጽሐፍ እንደሚል፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥
4፤ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል፡ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥
5፤ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤
6፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤
7፤ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤
8፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ።
ዛሬ ማታ 3:30 ላይቭ.. "ቅድስት ሥላሴ"
https://vm.tiktok.com/ZMYptqsC7/
የሆነ ከክ/ሃገር የመጣ ሰው ቤት ውስጥ አጊኝቼ ስለ ክርስትና ጠየኩና..
በቃ አልቻልኩም😭😭 ኡፍፍ.. ደግሞ እኮ የመጡት ከሊቃውንት ሃገር ነው ትላለህ😁😁
አይ ግን የምር ግልፅ ነው ይቀረናል ማስተማር ላይ.. በሰሜኑም ጭምር ማለቴ ነው
እባካችሁን እንደዚህ አይነት ሰው ስታገኙ ባለቻችሁ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ:- ስለ ሥላሴ.. ስለ ኢየሱስ.. ስለ ቤተ ክርስቲያን እና ስለ ትንሳኤ ሙታን ንገሩዋቸው..
የኢየሱስ መካከለኛነት
እና የቅዱሳን አማላጅነት
https://vm.tiktok.com/ZMYv71suo/
"እምነት ብቻ"
ጴንጤ vs ማርቲን ሉተር
https://vm.tiktok.com/ZMYvJbhGL/
ሮሜ 8 34 እና የፕሮቴስታንቱ አለመስማማት
https://vm.tiktok.com/ZMY7RSY9n/
አይ ምግብ😁😁
አይ ኢየሱስ😊😊
ምግብ ሲርበን በጣም እንናፍቀዋለን እንወደዋለንም.. አንዳንዴማ ከምግብ ፍቅር የተነሳ በጾም ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ ይልቅ የሥጋን ምኞት እየፈጸምን ከጠዋት ጀምሮ እንበላለን..
ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ግን ጋይስ..?? ልክ ስንጠግብ ምናልባትም እንደው ምግብን ማየት ራሱ ሊደብረን ይችላል..
ጌታ ኢየሱስ ግን በቃኝ የማይባል የሕይወት ምግብ ነው.. በበላነው ቁጥር ጭራሽ የሚፈቀር ነው..
ጌታ ፍቅሩን በሁላችን ልብ ያፍስስ
@Apostolic_Answers
1ኛ ቆሮንቶስ 15
19፤ በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።
🤔🤔 እስክንሞት ካለችው ከዚች ሕይወት ውጪ ታድያ ሌላ ምን ተስፋ አለ..??
20፤ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት(የመጀመሪያ) ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።
😊🤗 ኦው ጌታችን ሞቶ አልቀረም ተነስቷል ስለዛ እኛም እንነሳለን.. ስለዚህም ክርስቶስን ተስፋ የምናደርገው በሚመጣውም ሕይወት ነው..
#ኢየሱስ.. ትንሳኤው ትንሳኤያችን ነው
ጲላጦስ፣ በርባን፣ እኛ እና #ጌታችን_ኢየሱስ
ይህ የይሁዳ ክፍል ገዢ የሚሆን በሮም ንጉስ(ቄሳር) ሥር የሚሰራ ምድራዊ ፈራጅ ጲላጦስ የክብር ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን በፊቱ ቆሞ ባየው ጊዜ ዝምታው እጅጉን አስደንቆታል.. በዛ ላይ ደግሞ ምንም እንከን አላገኘበትም ነበር.. ይልቁንም አይሁዳውያን በቅናት ተነሳስተው እንዳመጡትም ተረድቷል..
ጌታ የገሊላ ገዢ ወደሆነው ወደ ሄሮድስም ቢሄድ ምንም እንከን አልተገኘበትም..
ከአሕዛብ ወገን የምትሆነው የጲላጦስ ሚስትም በህልም ስለ ክርስቶስ እጅግ መከራ ስትቀበል እንደነበርና ይህንን ጻድቅ ሰው እንዳይፈርድበት ወደ ገዢው ላከችበት..
ጲላጦስ ጌታን ሊፈታው ወድዷል.. ስለዚህም አንድ ሃሳብ አቀረበ.. በፋሲካ በዓል አንድ ወንጀለኛ ይፈታላቸው ነበርና ክርስቶስን ከአንድ እጅጉን ከታወቀ ነፍሰ ገዳይ ዘራፊ ወንበዴ ጋር አቅርቦ ማንን ልፍታላችሁ..?? አላቸው.. ምናልባትም የበርባንን ጨካኝነት ከማወቃቸው አንጻር እሱን ላለማስፈታት ሲሉ እንኳን "ክርስቶስን ልቀቀው" እንዲሉት በማሰብ ነበር..
እነርሱ ግን በካህናት አለቆች ተመክረው ያንን ከተማን ያወከውን ሰው በርባንን ፍታልን ሲሉ ለሁሉ እረኛ ሆኖ የሚያረጋጋውን ኢየሱስን ስቀለው አሉት..
ያንን የሰውን ምግብ የሚዘርፈውን ዓይን ያጠፋውን ሰው የገደለውን ፍታልን አሉት.. ሙታንን ያስነሳውን ቢርባቸው ምግብን አበርክቶ ያበላቸውን ቢታወሩ አይናቸውን ያበራላቸውን ዲዳ ቢሆኑ መስማትም ቢሳናቸው የፈወሳቸውን ጌታን ግን ስቀለው አሉት..
አሁንም ድረስ ግን ጲላጦስ ገርፎ ብቻ ሊለቀው ፈልጎ ነበር.. የካህናት አለቆች ግን ይህንን የጲላጦስን ሁኔታ በተረዱ ጊዜ "ይህንስ ብትፈታው #የቄሣር_ወዳጅ_አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው፡ እያሉ ጮኹ።"
Reflection
#ሦስት_ነጥቦች፡
1⃣ በርባን እኛን ሁላችንን ይወክላል.. በበደላችን በሞት የታሰርን ስንሆን ነጻ የወጣነው በክርስቶስ ሞት ነውና..
2⃣ ሕዝቡ ሁሉ ክርስቶስን ስቀለው በርባንን ፍታው አሉ.. አሁን ላይም ክርስቲያኖች ስለ ሥጋ ሲያስቡ የሥጋንም ፈቃድ ሲፈጽሙ በርባንን ይፈቱታል ክርስቶስን ይሰቅሉታል.. #በጽድቅ_ጎዳና_የሚመላለሱ እነርሱ ግን የመንፈስን ፈቃድ እየፈጸሙ #በርባንን_ሰቅለው_ክርስቶስን_ያዙ.. ስለዚህም በርባናዊነትን አስወግደን ክርስቶሳዊነትን ሁሌም እንላበስ
3⃣ ጲላጦስ በስተመጨረሻውም ቢሆን "የቄሳር ወዳጅ" አይደለም ላለመባል ሲል ክርስቶስ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጠ.. አሁንም ሰነፎችና ደካሞች ሌላን ሰውን ለማስደሰትና ወዳጆች ለመባል ሲሉ ከክርስቶስ ኢየሱስ ፊታቸውን አዞሩ.. ሰዎችንም ላለማስከፋት ስለ ክርስቶስ ከማውራት ወደኋላ አፈገፈጉ..
@Apostolic_Answers
ከአንድ ሰው ጋር እያወራሁ ነበር.. እና ሁሉም ነገር እኮ መልካም ነበር..
ግን መሃል ላይ..
"ተሃድሶዎች መስቀል ያለበት ነጠላ ይለብሳሉ ምንድን ነው ልዩነታችን ታድያ" አለችኝ😭😭 ኡፍፍ ሃዘን ላይ ተቀምጫለሁ አሁን
"እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ" ወይስ "እንደሚማለድ"..??😬😬
https://vm.tiktok.com/ZMYpg926b/