በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
2ኛ ጴጥ 1: 15
"ከሞትኩም በሁዋላ እተጋለሁ” ይላል..??
👉በመጋቤ ብሉይ አእመረ
2:17 - ግእዙ ምን ይላል..??
8:15 - አንድምታው ምን ይላል..??
11:13 - ማጠቃለያ እና ምክር
ላይቭ ላይ ተጠይቀው የመለሱት ነው.. ይጠቅማችሁዋል
አንዳንድ ክርስቲያኖች መጠቀም ማቆም ያለባቸው ጥቅስ
https://vm.tiktok.com/ZM2rNoxn7/
የቅድስት ሥላሴ አጭር ማብራሪያ
ሼር ይደረግ
https://vm.tiktok.com/ZM26Tb8v6/
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ..
ነገ እለቅላችሁዋለው ቲክቶክ ላይ ሙሉ ቪዲዮውን😊🤗
Stay tuned ትላለህ😁😁
@Apostolic_Answers
[ራእይ 21: 7]
ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።
ይህንን የተናገረው አብ ወይስ ጌታ ኢየሱስ..??
'ኢየሱስ አባት ነውን..??' በሚል ርዕስ ለሰራሁት ቪዲዮ ፕሮቴስታንት ጸሐፊ ጳውሎስ ፈቃዱ ምላሽ ብለው የጻፏትን አነስ ያለች ጽሑፍ ተመለከትኩና ጥቂት ነገር ልልበት ወደድሁ..
ጳውሎስ ካነሳቸው አሳቦች ውስጥ አንዳንዶቹን እርስ በእርስ የሚጋጩ(self contradictory) ሆነው አግኝችያቸዋለሁ.. ወደ እነሱ አሳቦች ምናልባትም በቀጣይ የምመጣበት ሲሆን አሁን ግን በራእይ 21፡ 7 ላይ ያለው ቃል ላይ የተናገረውን በማስቀመጥ ለእርሱ ጥቂት ምላሽ ልስጥ፡
ጳውሎስ እንዲህ አለ፡
"ያየሁት ቪዲዮ 'ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል' የሚል ጥቅስ ከራእይ 21፥7 ጠቅሷል። ለመሆኑ ይህን የተናገረው አብ ነው ወይስ ወልድ? በማለት አስቀድሞ ማጥናት ተገቢ ነው። ከፍ በማለት በቁጥር 5 ላይ “በዙፋንም የተቀመጠው” የሚለው ለዚህ መልስ ይሰጠናል። “በዙፋኑም የተቀመጠው” የሚለው አገላለጥ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ አብን የሚገልጥ ስለ መሆኑ ቢያንስ ራእይ ምዕራፍ 5ን መመልከት በቂ ነው። ክርክርን ለማሸነፍ ሲባል ብቻ ጥቅስን ከዐውዱ አፋትቶ መውሰድ የትም አያደርስም።"
እንደ ጸሐፊው ገለጻ ከሆነ "ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።" በማለት የተናገረው አብ እንደሆነና ይህንን ጥቅስ ደግሞ ኢየሱስ አባቴ ነው ለማለት መጥቀስ ለእርሱ "ክርክርን ለማሸነፍ ሲባል ብቻ ጥቅስን ከዐውዱ አፋትቶ 'እንደ' መውሰድ" ነው..
እንግዲያውስ ከቁጥር 5 ጀምሮ ያለውን አብረን እያነበብን እንመልሳለን.. ወደ መልሱ እንዝለቅ
[ራእይ 21፡5] "በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፡ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፡ አለኝ።"
1. "በዙፋኑ የተቀመጠው" የሚለው አገላለጽ ለአብ በሌላ የራእይ መጽሐፍ ክፍል ላይ ስለተሰጠ 21ኛው ምእራፍ ላይም ይህ አገላለጽ ቢመጣ ለኢየሱስ አይሆንም ማለት ስሁት ሙግት ነው.. Appeal to probability fallacy ይባላል ይህ.. ያውም ደግሞ ሌሎች የራእይ መጽሐፍ ክፍሎችንም ያለማስተዋል ነገር የሚታይበት ነው..
ለምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ እዚሁ የራእይ መጽሐፍ[3፡21] ላይ እንዲህ አለ፡ "እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ"
ስለዚህ በዙፋኑ የተቀመጠው ኢየሱስም እንደሆነ ይናገራል.. ከዚህም የምንረዳው ዙፋኑ የአብም የኢየሱስም እንደሆነ ነው.. ለዛም ነው በሌላ የራእይ ክፍል[22፡1] ላይ እንዲህ የሚል ቃል የምናገኘው፡ "በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወት ውኃ ወንዝ አሳየኝ"
ስለዚህም ይህ የእግዚአብሔር ዙፋን የበጉም ዙፋን ከመሆኑ አንጻር ራእይ 21፡5 ላይ "በዙፋኑም የተቀመጠው" የሚለውን አገላለጽ እንደው ለአብ ብቻ ነው የሚለውን የጳውሎስ ፈቃዱን አሳብ ያርቀዋል.. በነገራችን ላይ ቁጥር 3 ላይም እንዲህ ይላል፡ "..የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርሷ ውስጥ ይሆናል"
2. "ጻፍ አለኝ" ፡- እዚሁ ቁጥር 5 ላይ ይህንን ቃል የተናገረው በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ከሆነ እንግዲያውስ ዮሐንስን "ጻፍ" እያለ ሲያነጋግር የነበረው ከመልአክ እና ከጌታችን ኢየሱስ ውጪ ኧረ ማን ነው..?? አብ ተገልጦ "ጻፍ" ሲለው ነበር..?? ግልጽ ይመስለኛል..
እስቲ ደግሞ ወደ ቁጥር 6 እንሂድና እንጨርስ፡
[ራእይ 21፡6] "አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።"
1. "አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ" የሚለው አገላለጽ በራእይ መጽሐፍ ከማን እንደሚመጣ እናውቀዋለን..
ለምሳሌ የመጀመሪያው የራእይ መጽሐፍ[1፡8] ላይ እንዲህ ይላል ጌታ ኢየሱስ፡ "...አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ቁጥር 17 ላይም፡ "ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ"
የራእይ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምእራፍ ላይ ብቻ ሳይሆን መደምደሚያ ምእራፍ[22፡13] ላይም ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡ "አልፋና ዖሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ"
እንግዲህ ይህ የመጨረሻው ጥቅስ ማለት ከተነሳንበት የራእይ መጽሐፍ ክፍል ቀጥሎ ያለ ምእራፍ ነው..
እዚህ ላይ እንዲሰመርልኝ የምፈልገው በራእይ መጽሐፍ ላይ "እኔ ነኝ" እያለ እነዚህን ቃላት ሲናገር የምንመለከተው ጌታ ኢየሱስን ብቻ እንጂ አብን አለመሆኑን ነው
2. "ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።" ይህንን ቃል ስንመለከት መቼስ ወዲያው ትዝ የሚለን ዮሐንስ 7፡37 ነው.. ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ጮኸ፡ "ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ" እዛው ዮሐንስ 4፡10 ላይም ሳምራዊቷን ሴት "ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት" ተብሎለታል.. ኧረ ይህ ብቻም አይደለም እዚሁ የራእይ መጽሐፍ ቀጣዩ ምእራፍ[22፡17] ላይም እንዲህ ይላል፡ "መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ። የሚሰማም ና ይበል። የተጠማም ይምጣ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።"
ስለዚህም ራእይ 21 6 ላይ "ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ" ያለው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ እንደሆነ አመላካች ነው።
ከዚያማ ቁጥር 7 ላይ አባታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡
"ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።"
ገና ድል ስንነሣ ነው ልጅ የምንሆነው..?? የለም በጥምቀት ልጅ ሆነናል ያ ግን ፍጻሜውን የሚያገኘው ድል በመንሣት ውስጥ ይሆናል።
አዎን ክርስቲያኖች የኢየሱስ ልጆች ነው።
ይቀጥል ይሆናል..
@Apostolic_Answers
ይቅርታ ቀልድ አበዛው ግን..
አሁን ከልደት ጋር ሆነን እና ሻይ አዝዞ.. "ዝንጅብል ይኑረው" ሲል ይሁን አልኮ.. "ሻይ ቅጠል አይኑረው" ሲል ተወዛገብኩ.. ከዛ ግን ምን ቢል..?? ....... "ስኳር አይኑረው"😭😭 አልቻልኩም ጋይስ..
ሁኔታዬን አይቶ ጭራሽ ምን ቢለኝ..?? : "ስኳር ትወዳለህ..??" 😭😭ኡፍፍ
አሁን የሰለቸኝ ነገር
መንገድ ላይ ሆኜ ዝናብ ዘንቦ.. ከእርሱ ደግሞ ለማምለጥ የምሮጠው ሩጫ😭😭
መኪና ግዙልኝ አላልኩም ደግሞ😁😁(ብትልስ..??😝😝)
አይ ግን ሩጫው እናንተም ጋር አለ..??😁😁
ፕሮቴስታንቶች ሳያስቡት እንዴት የማርያም ጠላት እንደሚሆኑ
https://vm.tiktok.com/ZM2RnNa2Q/
ስሙ ምርጦች..
በቅርቡ ተከታታይ የክርስትና ትምህርት መስጠት ልንጀምር አስበን ነበር(የት እንደሚሰጥ ምናምን አልናገርም አሁን🤪)
እና ትምህርቱን የምሰጠው በጽሑፍ እና በድምጽ ነው እና ድምጹ ብቻውን እንዳይሆን ይልቁንም አብሮ የሚታይ አኒሜትድ ቪዲዮ ነገር ቢኖረው ሃሪፍ ይሆናል..
እና እስቲ በቪዲዮ ኤዲቲንግ ልታግዙን የምትችሉ ልጆች ካላችሁ አውሩኝ @aklil1 ላይ😊😊
ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ይማልዳሉ..??
https://vm.tiktok.com/ZM2hLhCu5/
የምግባራት ሁሉ እናታቸው ጾም ደረሰች! በጥቂቱ እንታመንባት ዘንድ ዕርገትን እና በዓለ ጰራቅሊጦስን ተክትላ ፆመ ሐዋርያት ጠበቀችን ። ላለመጾም "ይህ ጾም እኮ እንደ ዓብይ ጾም አይደለም" ፣ "ብዙ ሰዎች አይጾሙትም" የሚል ምክንያት ይኖርህ ይሆናል ፤ ሰዉ ችላ ስላልው ግን ጾሙን እንዳላሳነሰው ፣ ግዴታህንም እንዳላስቀረው እወቅ እንደውም ለምቾት የሚጋብዝህ ፈተና በበዛበት በመጾምህ ዋጋህን ጨመረው እንጂ!
የምትፆማት ፆም ምትጠቅም ትሁን ድሃን እያስጨነቅክና እያስለቅስክ ፣ የሰውን ገንዝብ እይቀማህ ፣ እየደበደብክና እየገደልክ ፣ በልብህ ቂም በቀልና ሽንገላ ይዘህ አይሁን እንዲህ ስላለው እግዚአብሔር "እኔ የወደድሁት ፆም ይህ አይደለም" ይላል(ኢሳ 58) ። ይልቅ ፆምህ ከምጽዋት እና ከጸሎት ጋር ትሁን ። የሚመፀውት ነገር ግን የማይጾም ሰው ስለ ጠገበ የተራበን ይንቃል፤ ስለጽድቅ የተራቡት ግን ሚበሉትን አጥተው ለተራቡት ያዝናሉ። የሚፆም ነገር ግን የማይመፀውት ገንዘቡን ለማትረፍ ንብረቱን እንደሚሰስት ባለ ጸጋ ነው ፤ የሚመፀውት ግን የማይፀልይ ሰው ደግሞ ጸሎት ምን ያደርግልኛል እንደሚል በገንዝቡ ነብሱን ያዳነ እንደሚምስለው ሰው ነው ። ስለዚህ በየዕለቱ ምሳህን ለተራቡ ስጥ፣ የተጠሙትን አጠጣ ፣ የተራቆቱትን አልብስ ፣ እንግዶችን ተቀበል ፣ የታመሙትን ጠይቅ ፣ የታሰሩትን ጎብኝ ፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ቅዳሴ አቅርብ ።
በጾም ጊዜ ከምግብ ብቻ አትከልከል ፤ የሚፆም ሰው ሆዱ ብቻ ሳይሆን የአካል ክፍሉ ሁሉ ይፁም ፡ አንደበትህ ሰውን ከማማት እና ከመስደብ ይፁም ፣ አይንህ ሴትን ከመመልከት ይፁም ፣ ጆሮህ ዘፈን እና ጨዋታን ከመስማት ይከልከል፣ ራስህ ጸጉር ከመሰራት ይፁም(🤭 ያላችሁን ማለቴ ነው።) ፣ እጅህ የሰውን ገንዘብ ከመውሰድና ከመማታት ይፁም በዋናነት ግን ልቦናህ ከ ሽንገላ ፣ ከቂም ፣ ከቁጣ እና ከመታበይ ይፁም ልብ እምቢያለውን አካላት ሊያደርጉ አይችሉምና ።
ጥቂት ነገር ማግኘት እምብዛም ባያስደስትም በቀን 3 ጊዜ እንመገብ የነበርን ሰዎች ግን ተርበን በምንመገባት አንድ መብል መደሰትን እንማራለን ጾም በትንሽ ነገር ሀሴት ማድረግን ትሰጠናለች(እውነተኛ ደስታ ቅርባችን ሲሆን ነው።) ፣ የስጋ ንጽህናን ፣ የነብስ ቅድስናን ፣ መራራትን ፣ ራስን መግዛትን ንብረታችን እናደርግባታለን ። ብቻ ለሁሉም በጥቂት ታምነንበት በብዙ ይምንሾምበት መልካም የፆም ጊዜ ይሁን🤍 ።
***
Sources
¹ ርቱዐ ሃይማኖት
² Seneca letter 18
አንዱ በውስጥ "አንዳንዴ የሚሰማኝ ስሜት" ብሎ የላከልኝ😊😊
ጌታ በእጅጉ እንደሚቀበልህ ውስጥህ ሲያውቀው እና የሆነ ደስታ ውስጥ ሆነህ..
ከዛ ደግሞ እርሱ እንደዛ እየተቀበለህ አንተ ግን እርሱን ደጋግመህ እንደበደልከው ደግሞ ትዝ ሲልህ.. እንደዛም ሆኖ ግን ምን ያህል እንደሚያፈቅርህ ውስጥህ ሲመሰክርልህ.. ደስታ እና ሃዘን ተደባልቀው ሌላ ታሪክ
አንዳንዴ ባለሁበት ቦታ በቃ ዝም ብዬ አመሰግንሃለው ጌታ ሆይ.. እወድሃለው እለዋለው..
ያው ከዚ ጋር ተያይዞ የጠየቀኝ ምንም አይጠቅማችሁም እቺን ብቻ ልስጣችሁ
ሮሜ 6 እና የፕሮቴስታንቱ ውዝግብ
https://vm.tiktok.com/ZM22pAb5t/
አንድ ፊልም አየሁ(አትፍረዱብኝ😊)
እና ፊልሙን እያየሁ ስለ ባልና ሚስት አሰብኩ.. እንደ አዲስ ጋብቻ ምንድነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ.. ማለት በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት በጣም ከሌላው ግንኙነት ሁሉ የተለየ ነው ሊሆን የሚችለው.. ከወንድምህ ጋር ያለህ ግንኙነት ከአብሮ አደግ ጓደኛህም ጋር ሊኖርህ ይችላል ቅርርብነቱ ፍቅሩ ምናምን..
ግን በባልና በሚስት መካከል ያለው ፍቅር በእጅጉ የተለየ ነው.. በእጅጉ የተለየም ሊሆን ይገባዋል.. በውበት እና sexual በሆኑ ነገሮች ላይ ሊመሠረት አይገባውም.. ምክኒያቱም የወጣትነት ውበት የሆነ እድሜ ላይ እየጠፋ ይመጣል.. sexual ነገሮችም የሆነ ሰዓት ላይ ጣእማቸው ይጠፋ ይሆናል.. እና የዛን ጊዜ ቁሺው ልትል ነው ወይስ ሌላ ወጣት ጋር ልትሄድ..??
ጋብቻ ማለት ለሆነ እድሜ ክልል ያህል ብቻ እንደሆነ ካላሰብነው በቀር በእነርዚህ ላይ ሊመሠረት አይችልም.. ይህ ማለት ግን ውበት አያስፈልግም እያልኩ ወይም ደግሞ ምንም ቼክ አታድርግ ምናምንም አይደለም😊😊 ያው መሠረት አይሁኑ ነው.. በጋብቻ ውስጥ ያለ መኝታም ደግሞ ፒስ ነው(🤭iykwim lol)
ባልና ሚስት መካከል አንዳቸው ለምሳሌ cheat አደረጉ የሚባለው ከሌላ ሰው ጋር የሆነ ነገር የጀመሩ እንደሆነ ነው.. ግን ደግሞ ወንዱ ለምሳሌ አግብቶም ግን ደግሞ ምንም እንኳን በተግባር ምንም ባያደርግም ሌላ ሴትን ቢመኝስ..?? ያ ጋብቻ ምን ያህል አስቀያሚ እንደሚሆን አስቡት..
የክርስቲያን ጋብቻ በጣም ውብ ነው.. ባልና ሚስት አንድ ሲሆኑ በአሳብም በመንፈስም ሊሆን ይገባዋል.. እንደዛ ሲሆን ፍቅሩ ምናምንም እየተለየ ይሄዳል.. አርጅተው ምናምን ራሱ በፍቅር ይተያያሉ ምክኒያቱም በሁለቱ መካከል ያለው ሥጋዊ intimacy ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ጭምር ነው..
ይሄ እንዲሆን ግን በሁለቱ መካከል ኢየሱስ ሊኖር ይገባዋል.. ሁለቱም ለጌታ ትልቅ ፍቅር ሊኖራቸው ይገባል.. ያኔ ወንዱ እንደ ኢየሱስ ሴቲቱም እንደ ቤተ ክርስቲያን ይሆናሉ.. የሚወለዱትንም ልጆች እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ክርስቶሳውያን..
ምንድነው ዛሬ የጻፍኩት😁😁 ብቻ መልካም ውሎ ምናምን
@Apostolic_Answers
ኢየሱስ አባት አይደለምን..??
ኦንሊ ጂሰስ Vs ፕሮቴስታንት
https://vm.tiktok.com/ZM2LqfgKv/
👉ዛሬ አንዲት እህታችን ከፕሮቴስታንት ወደ ክርስትና ተመልሳለች ጌታ ይመስገን..
እና ግሩፓችን ላይ "ለምን ወደ ክርስትና/ኦርቶዶክስ ተመለስሽ..??" ተብላ ተጠይቃ "እንደው አጠር ያለ መልስ" ብላ የፃፈችው Screenshot ነው ፎቶው..
ክርስቶሳዊቷ እህቴ ፍቅርተ ሥላሴ.. ዛሬ ጌታን እርሱን ክርስቶስን ለብሰሽዋል.. ሐዋርያውም ገላ 3:27 ላይ "የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችሁታል" እንዲል..
እናም በሕይወትሽ ሁሉ ይህ የጽድቅ ልብስ ይታይብሽ.. ጌታ ከአንቺ ጋር ይሁን..
@Apostolic_Answers
አንድ ወንድሜ የንስሐ አባቱን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩልኝ አላቸው.. "ጌታ እርሱን መውደድ ማፍቀርን እና መፍራትንም እንዲሰጠኝ ጸልዩልኝ"
"ጌታ ሆይ አንተን መውደድን ማፍቀርን ስጠኝ.. ለክርስቲያን ወንድም እህቶቼ ሁሉም አንተን እንዲያፈቅሩህ ስጣቸው"
ወድጄዋለው ጸሎት ውስጥ እንጠቀመው😊🤗
@apostolic_answers
የጠዋት ልምድ😉😉
1️⃣ ልክ ከእንቅልፋችን ስንነሳ(ምድረ እንቅልፋም🤪) - ምንም ነገር ከመናገራችን በፊት እንደነቃን በቅዱስ መስቀል ምልክት እናማትብ..
2️⃣ ማታ ስንተኛ ስልካችንን ዘግተን እንተኛና ጠዋት ስንነሳ የጠዋት ጸሎት(ቢያንስ አባትችን ሆይ) ሳንል በፊት አለመክፈት..
እስቲ ከነገ እንጀምረው ምርጦች💪😊
🤣🤣 እናንተ አድክሞች
"መምህር ምላሱን አያወጣም"
እኔ ግን መምህር አይደለሁም ስለዛ መብቴ ነው ተረዱኝ😝😝