ኧ ምርጦች.. ዛሬ ልንጀምር ነው የግእዝ ንባብ ምናምን.. እና በጣም ደስ ብሎኛል እኔ ራሱ በደንብ ትኩረት ሰጥቼ ልማር ነው..
ስለዚህም ዛሬ ማለትም አርብ ከምሽቱ 2:30 መግቢያ ይኖረናል.. ያው ላይቭ ነው
የት..?? እዚው ቻናል ላይ..
@Apostolic_Answers
መንፈሳዊ ነገር ላይ ትንሽ መስራት ስትጀምሩ የሚደብረው ፓርት ምን መሰላችሁ..
ቤት ውስጥ "አባ" ምናምን እያሉ ሙድ ለመያዝ ይሞክራሉ እና እኔ ደግሞ ቤት ውስጥ ስሜ አቢ ነው እና አስቡት "አባ አቢ" ስባል😭😭 አባቢ ሎል
እና ደግሞ ዛሬ በጠዋቱ ከቅዳሴ ተመልሰን ስለ ገነት እና ስለ ሲዖል እያወራን አንዷ ምን ብላ ሙድ ብትይዝብኝ..??
"እኔ እንደሆነ የአቢ ጺም ላይ ተንጠልጥዬም ቢሆን ገነት እገባለሁ"
😭😭 ኡፍፍ
የምር ሙድ አትያዙብን😁😁
https://youtu.be/b8t-2LzU5uE
ዩትዩባችንን እስቲ የተወሰነ መንቀሳቀስ እንዲጀምር እናድርገው እና በሰፊው በአዳዲስ ኮንተንቶች ብቅ እንላለን👍👍
ኧ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች(ኅሩያነ እግዚአብሔር)..
ግእዝ ቀላቀልኩባችሁ..?? አይዞን እንግዲ ልመዱት🤭🤭
ለማንኛውም መልእክተ ዮሐንስ.. ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት በግእዝ ልንማር ነው እዚው ቴሌግራም ላይ በሳምንት ሦስት ቀን..
መማር የምትፈልጉ የገብረ ሥላሴ መዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ በአክሱም ማተሚያ ቤት የታተመው ቢኖራችሁ መልካም ነው..
ቀኑን አሳውቃችሁዋለው.. በዚው ሳምንት እንጀምራለን
ግእዝ መጣንልሽ🥴🥴
@Apostolic_Answers
ዛሬ ከአንድ ጉዋደኛዬ ጋር ነበርኩ እና ሚስቱም(gf) አብራው ነበረች እና ምግብ እየበላን ነበር..
ሙሉ ሰዓቱን እሱ እሷን እያጎረሰ እሷ ደግሞ እሱን እያጎረሰችው ነበር.. አንድም እንኳን ለራሳቸው አልጎረሱም..
ምንድን ነው እንዲ መጃጃል..?? ኧረ ወዲያ
.
.
.
.
.
እኔን ግን መሃል ቤት አስቡኝ😭😭 ፑር አክሊል
በኢየሱስ ምልጃ(ጸሎት) እና በቅዱሳን ምልጃ መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት
ቅዱሳን በቃ እንደኛው መጸለይ ብቻ ነው.. ጸልየው እግዚአብሔር ፈቃዱ ከሆነ ልመናቸው ተቀባይነት ይኖረዋል.. የእርሱ ወዳጆች ናቸውና
የጌታ ጸሎት(ምልጃ) ግን ከደም ጋር የሆነ ነው.. ስለዚህም ዋጋውን እኔ ከፍያለሁ የሚል ሥልጣናዊ ንግግር እንጂ እንደ እኛ ምላሽን የሚጠብቅ አይደለም..
ሌላው ሁለተኛው ትልቁ ልዩነት.. የቅዱሳን ምልጃ ሰው ብቻ እንደ መሆናቸው የሚያቀርቡት ልመና ሲሆን..
ጌታ ኢየሱስ ግን ሲጸልይ ሰው ብቻ አይደለም ይልቁንም አምላክም ነውና ጸሎት ተቀባይም ስለሆነ ሥልጣናዊ ነው.. ስለዚህም እርሱን ሦስተኛ ወገን አማላጅ አያስብለውም..
@Apostolic_Answers
2ኛ ጴጥ 1: 15
"ከሞትኩም በሁዋላ እተጋለሁ” ይላል..??
👉በመጋቤ ብሉይ አእመረ
2:17 - ግእዙ ምን ይላል..??
8:15 - አንድምታው ምን ይላል..??
11:13 - ማጠቃለያ እና ምክር
ላይቭ ላይ ተጠይቀው የመለሱት ነው.. ይጠቅማችሁዋል
የቅድስት ሥላሴ ትምህርት አጭር ማብራሪያ..
ነገ እለቅላችሁዋለው ቲክቶክ ላይ ሙሉ ቪዲዮውን😊🤗
Stay tuned ትላለህ😁😁
@Apostolic_Answers
የክርስትናን ትምህርት ለማስተማር የሚሞክር ሰው እነዚህ ላይ ቢያተኩር እላለሁ:
1. ቅዳሴ አለመቅረት እና የጸሎት ሰው
2. አንባቢ አንባቢ አንባቢ
3. ትምህርትን የሆነ ሰው ስለተናገረው ብቻ ማስተጋባት ሳይሆን ሐዋርያዊ ትውፊትን መከተል.. ይህም ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብሎሽ ውስጥ የሚታይ ትምህርት
4. ሁሌም ራስን ከፍ አድርጎ ለማሳየት ሳይሆን ክርስቶስን ከፍ ለማድረግና አካሉን ለማነጽ መስራት.. ስለዚህም ክርስቲያን ወንድም እህቶችን በማገዝ መንፈስ መንቀሳቀስ
5. ሌላ የሚያስተምሩ ክርስቲያን ወንድሞች ውስጣችንን የሚረብሹት ከሆነና በእነሱም ላይ ክፋትን(ምናልባትም envy) ካሰብን ጊዜ ሳናጠፋ ለዛ ሰው መጸለይ መጀመር.. ለዛ ሰው ስንጸለይ የቀደመው ስሜታችን ተለውጦ እንደውም መውደድ ማፍቀር እንጀምራለን
6. ስለ መምህራን ሁሉ መጸለይ..
7. 1, 2, 3 ይሰመርባቸው
"መጠን.."
ነገረ ማርያም ላይ ትልቁ ትምህርት ወላዲተ አምላክ የሚለው ነው..
ከዚህ ውጪ immaculate conception ምናምን የሚል ትምህርት ዘመን አፈራሽ በግለሰቦች የተጀመረ ነው..
አንዳንዴ ፕሮቴስታንቶችን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ክርስቲያኖችንም ስለ ቅዱስ ትውፊት ምንነት በሚገባ ማስተማር ያለብን ይመስለኛል
የሆነ ሰው ሁለት ማስተርሱን በአንዴ ሰራ ይልሃል.. ደስ ይላል በጣም
እና his last word:
“አሁንም ዓለም ከሚደርስበት አድርሽኝ: ሁዋላ ደግሞ በልጅሽ በወዳጅሽ በስተቀኝ እንድቆም አድርጊኝ" [አርጋኖን ዘረቡዕ 2:7]
አሜን በነገር ሁሉ የእመቤታችን አጋዥነት አይለህ.. እንኳን ደስ አለህ😊😊
ከዝሙት ለመራቅ አእምሮ ላይ መስራት የመጀመሪያው መንገድ ነው..
ለምሳሌ ከአንዲት ሕፃን ልጅ ጋር ብትተኛ ምንም ነገር ሊፈጠር አይችልም.. የማይፈጠርበት ምክንያት ደግሞ ገና ከጅምሩም አሳቡ አእምሮህ ውስጥም በጭራሽ ሊመጣ ስለማይችል ነው..
ሕጻናትን እንደፈለግህ ብታጫውታቸው ብታቅፋቸው ብትስማቸው ምናምን ከእነርሱ ጋር ሲሆን አንተም ውስጥህ እንደ እነርሱ ንጹህ ነው.. ስለዛ ምንም ነገር አታስብም..
ይሄንን ነገር ግን ካደገች ሴት ጋር ለማድረግ ብትሞክር መጨረሻህን አስበኸዋል..??😭😭
ተወው አታስበው አታስበው
ይህ የሚሆንበት ምክንያት ግልፅ ነው አእምሮህ እንደነዚህ አይነት ነገሮችን ማሰብ ስለሚጀምር ነው(ታሳፍራለህ ማን lol) ያው በዛ ደረጃ ሲጀመርም መጃጃል ባያስፈልግም በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚኖሩን ግንኙነቶችም ግን እንዳንፈተን አእምሮዋችን እንደዚ አይነት ነገር ቀድሞ እንዳያስብ መከላከል.. ድንገት ቢያስብ ራሱ ወዲያውኑ ኢየሱስን መስቀል ላይ ሆኖ ማሰብ..
አንዳንዴ እንደዚ አይነት ነገር እንዳይፈጠር ከመፍራት የተነሳም ማሰብ ሊጀመር ይችላል.. እንዳልኳችሁ ኢየሱስን መስቀል ላይ ሆኖ አስቡት..
በጣም ከባድ ፈተና የዝሙት ፈተና ነው.. ጌታ ኢየሱስ ለሁላችንም ኃይልና ማስተዋልን ያድለን
@Apostolic_Answers
ቪዲዮ መስራት አዝግ ነገር ነው በጣም.. ጭራሽ ከፊታቹ ሰው ቆሞ ደግሞ በቃ ዝገት ነው..
እና የምለው ሲጠፋኝ😭😭
ከ 9 ወር አካባቢ በፊት ነበር😁😁
የምግባራት ሁሉ እናታቸው ጾም ደረሰች! በጥቂቱ እንታመንባት ዘንድ ዕርገትን እና በዓለ ጰራቅሊጦስን ተክትላ ፆመ ሐዋርያት ጠበቀችን ። ላለመጾም "ይህ ጾም እኮ እንደ ዓብይ ጾም አይደለም" ፣ "ብዙ ሰዎች አይጾሙትም" የሚል ምክንያት ይኖርህ ይሆናል ፤ ሰዉ ችላ ስላልው ግን ጾሙን እንዳላሳነሰው ፣ ግዴታህንም እንዳላስቀረው እወቅ እንደውም ለምቾት የሚጋብዝህ ፈተና በበዛበት በመጾምህ ዋጋህን ጨመረው እንጂ!
የምትፆማት ፆም ምትጠቅም ትሁን ድሃን እያስጨነቅክና እያስለቅስክ ፣ የሰውን ገንዝብ እይቀማህ ፣ እየደበደብክና እየገደልክ ፣ በልብህ ቂም በቀልና ሽንገላ ይዘህ አይሁን እንዲህ ስላለው እግዚአብሔር "እኔ የወደድሁት ፆም ይህ አይደለም" ይላል(ኢሳ 58) ። ይልቅ ፆምህ ከምጽዋት እና ከጸሎት ጋር ትሁን ። የሚመፀውት ነገር ግን የማይጾም ሰው ስለ ጠገበ የተራበን ይንቃል፤ ስለጽድቅ የተራቡት ግን ሚበሉትን አጥተው ለተራቡት ያዝናሉ። የሚፆም ነገር ግን የማይመፀውት ገንዘቡን ለማትረፍ ንብረቱን እንደሚሰስት ባለ ጸጋ ነው ፤ የሚመፀውት ግን የማይፀልይ ሰው ደግሞ ጸሎት ምን ያደርግልኛል እንደሚል በገንዝቡ ነብሱን ያዳነ እንደሚምስለው ሰው ነው ። ስለዚህ በየዕለቱ ምሳህን ለተራቡ ስጥ፣ የተጠሙትን አጠጣ ፣ የተራቆቱትን አልብስ ፣ እንግዶችን ተቀበል ፣ የታመሙትን ጠይቅ ፣ የታሰሩትን ጎብኝ ፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና እና ቅዳሴ አቅርብ ።
በጾም ጊዜ ከምግብ ብቻ አትከልከል ፤ የሚፆም ሰው ሆዱ ብቻ ሳይሆን የአካል ክፍሉ ሁሉ ይፁም ፡ አንደበትህ ሰውን ከማማት እና ከመስደብ ይፁም ፣ አይንህ ሴትን ከመመልከት ይፁም ፣ ጆሮህ ዘፈን እና ጨዋታን ከመስማት ይከልከል፣ ራስህ ጸጉር ከመሰራት ይፁም(🤭 ያላችሁን ማለቴ ነው።) ፣ እጅህ የሰውን ገንዘብ ከመውሰድና ከመማታት ይፁም በዋናነት ግን ልቦናህ ከ ሽንገላ ፣ ከቂም ፣ ከቁጣ እና ከመታበይ ይፁም ልብ እምቢያለውን አካላት ሊያደርጉ አይችሉምና ።
ጥቂት ነገር ማግኘት እምብዛም ባያስደስትም በቀን 3 ጊዜ እንመገብ የነበርን ሰዎች ግን ተርበን በምንመገባት አንድ መብል መደሰትን እንማራለን ጾም በትንሽ ነገር ሀሴት ማድረግን ትሰጠናለች(እውነተኛ ደስታ ቅርባችን ሲሆን ነው።) ፣ የስጋ ንጽህናን ፣ የነብስ ቅድስናን ፣ መራራትን ፣ ራስን መግዛትን ንብረታችን እናደርግባታለን ። ብቻ ለሁሉም በጥቂት ታምነንበት በብዙ ይምንሾምበት መልካም የፆም ጊዜ ይሁን🤍 ።
***
Sources
¹ ርቱዐ ሃይማኖት
² Seneca letter 18
አንዱ በውስጥ "አንዳንዴ የሚሰማኝ ስሜት" ብሎ የላከልኝ😊😊
ጌታ በእጅጉ እንደሚቀበልህ ውስጥህ ሲያውቀው እና የሆነ ደስታ ውስጥ ሆነህ..
ከዛ ደግሞ እርሱ እንደዛ እየተቀበለህ አንተ ግን እርሱን ደጋግመህ እንደበደልከው ደግሞ ትዝ ሲልህ.. እንደዛም ሆኖ ግን ምን ያህል እንደሚያፈቅርህ ውስጥህ ሲመሰክርልህ.. ደስታ እና ሃዘን ተደባልቀው ሌላ ታሪክ
አንዳንዴ ባለሁበት ቦታ በቃ ዝም ብዬ አመሰግንሃለው ጌታ ሆይ.. እወድሃለው እለዋለው..
ያው ከዚ ጋር ተያይዞ የጠየቀኝ ምንም አይጠቅማችሁም እቺን ብቻ ልስጣችሁ