2ቆሮ 5:20 - "እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ" ወይስ "እንደሚማለድ"
"ለ" ወይስ "ል"..??😁😁
https://vm.tiktok.com/ZM2gpry2H/
"እንዳትበድል ድንግልን ከእናቷ ሆድ ጀምሮ #የጠበቃት መንፈስ ቅዱስ.. እንዳትረክስም ያነፃት ለወልድ ዋህድም ማደሪያ ያደረጋት እርሱ ነው::"
አባ ጊዮርጊስ : አርጋኖን ዘእሑድ 1: 18
እመቤታችን ከማህጸን ጀምሮ የተጠበቀች ናት.. የተጠበቀችውም ኃጢአት ከመስራት ወይም ከመበደል ነው.. ስለዚህም እመቤታችን ምንም ኃጢአት ያላደረገች እጅግ ንጽሕት ናት.. ንጽሕናዋም ልክ ሄዋን ሳትበድል በፊት እንደ ነበራት ያለ ንጽሕና ከዚያም በላይም ይሆናል..
ይህ በየትኛውም ኦርቶዶክስ አሃት አብያተ ክርስትያናትም በመለካውያንም በሁሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት ዘንድ ይታመናል..
አምላክን በሥጋ የወለደች ናትና ስለ ክብሯም ሲናገሩ ለምሳሌ አንድ አሌክሳንደር ሽሜመን የተባሉ መምህር አንድ በስፋት የሚጠቀሙበትን ጸሎት በመጥቀስ እንዲህ ይላሉ: "ከኪሩቤል ይልቅ የከበረች: ከሱራፌልም ይልቅ በማይነጻጸር ደረጃ ክብርት"
[celebration of faith vol 3: the Virgin Mary]
ይህ አሁን ከአባ ጊዮርጊስም አድርጌ የፃፍኩት ጽሑፍ ሁለት መልእክቶችን ያዘለ ነው.. ሁለተኛው አሳብ የገባችሁ ሰዎች እስቲ ትንሽ ጥናት አድርጉበት..
ለማንኛውም መልካም የጌታ ቀን (ሰንበት)
"ወደ ልጅሽ በጸለይሁ ጊዜ ብቻዬን የምዘነጋ አልሁን.. አንቺም ከእኔ ጋር ሁኚ እንጂ.."
አርጋኖን ዘእሑድ 3:10
@Apostolic_Answers
ወደ ፊልጵስዩስ 4
1፤ ስለዚህ፥ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ ደስታዬና አክሊሌ የምትሆኑ ወንድሞቼ ሆይ፥ እንዲሁ በጌታ ቁሙ፥ ወዳጆች ሆይ።
የጳውሎስ መልእክታት ላይ ንግግሩ ውስጥ ፍቅሩን ስለሚያሳዩ ብዙ ጊዜ ሳታስቡት ፈገግም ብላችሁ ምናልባት እምባም እያቀረረ ዓይናችሁ አልፎ አልፎ መጽሐፉን እንድታቅፉትም እያደረገ ነው የሚያስነብባችሁ😁😁
አዳሜ ተነስተሽ ቁርስ እየበላሽ ይሆናል.. አክሊል ግን ጉዙ ላይ ነው እና ከናዝሬት ወደ አሰላ ታክሲ ውስጥ ነው😭😭
ግን ደግሞ አያሳስብም በጠዋት ተነስተሽ ፍርፍር ላይ የሰፈርሽ ሁላ አሰላ ላይ ክትፎ ወይም ቁርጥ በመብላት እበቀልሻለሁ🤪🤪
ሁለት ሰዎች ተቃወሙኝ.. "ተአምረ ማርያምን ጠቅሰህ ያንን ታሪክ ስህተት ነው እንዴት ትላለህ ለአንተ ይህንን ሥልጣን ማን ሰጠህ" አሉኝ..
አንዱ እንዲህ አለ፡ "ያ ክፍል ላይ ያለው ንስጥሮስ በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘው ንስጥሮስ ሳይሆን ሌላ ንስጥሮሳዊ ነው"
ሁለተኛውም ተነስቶ፡ "ዮሐንስ አፈወርቅ የተባለው ሌላ ዮሐንስ ነው" አለኝ
እኔም ይህንን አሰብኩ፡ እኔ የተቃወምኩትን ሁለቱም ተቃውመውታል ስለዚህም ንስጥሮስን ሌላ ንስጥሮሳዊ ሰው ወይም ደግሞ ዮሐንስ አፈወርቅን ሌላ ዮሐንስ አድርገውታል.. ስለዚህም እኔ የማልቀበለውን እነሱም አይቀበሉትም..
ባይሆን ግን መጽሐፈ ምስጢር ላይም ያለው ራሱ ንስጥሮስና ራሱ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲሆን ይህንን ተቃውመው የራሳቸውን ሌላ ታሪክ ሲመሰርቱ ለእነርሱስ ሥልጣኑን ማን ሰጣቸው..??
ወይስ ሥልጣን የምንጠየቀው እኛ ብቻ ነን😭😭
👉አንዱን የታሪክ ስህተት ለማዳን ሌላ የፈጠራ ታሪክ ክርስቲያኖችን መመገብ መልካም አይደለም
@Apostolic_Answers
አንተ እዚ የሎጥን ቤት በር ሲገፉ የነበሩት ሰዎች ስማቸው ማን ነው እያልክ ትወዛገባለህ በጎን ግሩሜ ቴዮሎጂውን ጨርሶ ተመርቋል..
ግሩሜ እንኳን ደስ አለህ ብሮዬ.. ደስ ብሎኛል😊🤗
እና ደግሞ የጌታን መንግስት(ቤተ ክርስቲያንን) በእውነት እና በፍቅር የምታገለግልበት ያድርግልህ
ተአምረ ማርያም ላይ በሰራሁት ላይ አንዳንድ ለማጣመም ለሞከሩ ፕሮቴስታንቶች.. እስቲ ጠረጴዛውን ወደ እነርሱ እናዙረው..
https://vm.tiktok.com/ZM2m3s6jV/
"የተራበ ሆድ ለምግብ እንደሚቸኩል
ክርስቶስ ደግሞ ይቅር ለማለት ይቸኩላል"
አርጋኖን ዘእሁድ 2: 7
አይ መታደላችን.. እንደ ኢየሱስ ያለ ሩኅሩኅ ይቅር ባይ አምላክ ባይኖረን አልቆልን ነበር የምር..
ችግሩ ደግሞ የስግጥናችን ስግጥና ይቅርታ ለመጠየቅ ንስሐ ለመግባት አንነሳሳም ብዙ ጊዜ..
ንስሐ እንዳለ ሆኖ ስትጸልይም : "አባ በድያለሁ ይቅርታ አድርግልኝ.." በለው..
መልካም ቀን😊🤗
2ቆሮ 5:20 - "እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ" ወይስ "እንደሚማለድ"
"ለ" ወይስ "ል"..??😁😁
https://vm.tiktok.com/ZM2gpnNks/
ተከታታይ የክርስትናውን ትምህርት መማር የምትፈልጉ ግን ደግሞ ያልተመዘገባችሁ ወይም ጭራሽ ያልሰማችሁ tiktok የማትጠቀሙ ልጆች @aklilabi የሚለውን ተጫኑና join በሉት እስከ ማታ ባለው ጊዜ ውስጥ አወራችሁዋለው [ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር]
ሊንክ ያልላኩላችሁ ብቻ
እስቲ ላስቸግራችሁ.. የአንዲት እህቴ ሪሰርች አካል የሆነ Survey ነገር ነው እና ጥያቄዎቹን ቲክ ቲክ አድርገን submit እናድርግላት..
ወደ 300 ሰው ያስፈልጋታል እና ከ300ው አንዱ አንተ/ቺ ይሁኑ ትላለህ😁😁
------------------------------------
ሊንኩን ተጭነው ይግቡ
👇👇👇👇👇
https://forms.gle/3nCQa3CzVHgcHaQR8
ያላደለው ጣት "hi kongo” ብሎ እየጻፈ ሰውን ያነጉላል🤪🤪
የአንዳንዱን ደግሞ ጥበብ እይ በና😊😊 አመሰግናለሁ ሳሚ ወንድሜ😊🤗
መልካም እለተ ሰንበት ደግሞ
ንስጥሮስ ወይስ ንስጥሮሳዊ ሊቀጳጳስ..??
ተአምረ ማርያም[48] ላይ የሰራሁትን ቪዲዮ ተከትሎ አንድ ወንድሜ ያ የተአምር ክፍል የታሪክ ተፋልሶ እንደሌለበት አድርጎ ፌስቡኩ ላይ የጻፈውን በግሩፓችን ላይ አስቀምጠውት አየሁ..
ያው ወዳጄ ቀጥታ ፌስቡኩ ላይ ስለሆነ የፖሰተው እኔም እዚው ላይ ትንሽ ነገር ልበልበት እሱ ከሰጠው አሳብ ጋር በተያያዘ፡
የወንድሜ አሳብ በአጭሩ እንዲህ የሚል ነው፡ —ክፍሉ ላይ "ንስጥሮስ" የተባለው ራሱ ንስጥሮስ ሳይሆን ይልቁንም ቀደም ሲል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የነበረ ሌላ ንስጥሮሳዊ አሳብ ያለው ሌላ የቁስጥንጥንያ ሊቀጳጳስ ነው.. ንስጥሮስ መባሉም ከምንፍቅናው መመሳሰል ነው—
መልካም 3 ነጥቦችን ላስቀምጥ፡
1. ይህ አሳብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የሌለው የራሱ የወንድሜ ግምታዊ አሳብ ብቻ ነው
2. ይህ የተአምር ክፍል ከአባ ጊዮርጊስ መጽሐፈ ምስጢር ጽሑፍ ላይ የተካተተ እንደሆነ ጽሑፉ ያመላክታል.. እናም ይኸው ታሪክ በመጽሐፈ ምስጢር የጌና ንባብ(ምዕራፍ 4) ላይ የተቀመጠ ሲሆን "ንስጥሮስ" ተብሎ የተጠራው ግለሰብ ራሱ ንስጥሮስ እንደሆነ ያስቀምጣል፡
ማስረጃ..??
እዛው መጽሐፈ ምስጢር ክፍል ቁጥር 10 ላይ እንዲህ ይላል፡
"ከዚህ በኋላ ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስለ እርሱ #በኤፌሶን ተሰበሰቡ ወደ ጉባኤያቸውም ጠርተው ስለ ስህተቱ ገሠጹት....... እርሱ ግን እምቢኝ አላቸው በመንፈስ ቅዱስ አፍ አንድ ሆነው #አውግዘው ከቤተ ክርስቲያን ለዩት..... በመንበረ ጵጵስናውም ስለ ሃይማኖት ቀናተኛ የሆነ የቤተ ክርስቲያንም ዓምድ የሆነ #መክስምያኖስን አስቀመጡት"
ከዚህ የምንወስደው ሁለት ነገር
ሀ. በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘው ራሱ ንስጥሮስ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ እናውቃለን
ለ. በመንበረ ጵጵስናውም መክስምያኖስን አስቀመጡት ብሎናል.. መክስምያኖስ(St Maximianus) ደግሞ በቁስጥንጥንያ ራሱን ንስጥሮስን ተክቶ ሊቀጳጳስ የሆነ ሰው ነው [Fr shenouda ishak: christology and council of chalcedon, pg 55]
3. ሦስተኛውና የመጨረሻው ነጥቤ ግን ወንድሜ ያነሳው አሳብ "ተአምር ውስጥ ስህተት ልጊኝ አይችልም" ከሚል ቅድመ እሳቤ በመነሳት ይመስላል ምክንያቱም ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ ከመሞከር ይልቅ እንደው በቃ ልክ ነው ብቻ ብሎ ለሱ ደግሞ ግምታዊ አሳቦችን መስጠት ነው..
ደግሜ የምለው እንደዚህ ያሉ ነገሮች ክርስቲያኖችን ሊያስጨንቁ አይገባም.. የትኛውም የገድላት ሆነ የተአምራት መጽሐፍት የእምነታችን መሠረቶች አይደሉም.. ለኅይወታችን የሚጠቅሙ እንጂ.. ስለዛ ለኅይወት በሚጠቅሙን መንገድ እንጠቀማቸው እንጂ እንደው እዛ ላይ ባለ ጽሑፍ ሁሉ ብዙ አንጨናነቅ..
@Apostolic_Answers
"የሴትን ኃፍረት የሳመ አፈወርቅ ተባለ" የሚለው 👉የተአምረ ማርያም ክፍል ላይ 2 ሃሳቦች አሉኝ
https://youtu.be/dHQn1v9DgNs
"ለሰዎች ምንም የምትሰጠው ከሌለህ፣ ሞቅ ያለ ፈገግታ እና ደግ ቃል ስጣቸው.. ፍቅርን ስጣቸው ፣ ርህራሄን ስጣቸው፣ የማበረታቻ ቃል ስጣቸው፣ ልብህን ስጣቸው።"
አቡነ ሽኖዳ 3ተኛ
@TnshuaBetechrstian
👆👆👆👆
እናንተ ተወዳጆች እስቲ ተቀላቀሏቸው