እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤
-> በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ
መዝ 27:4
እስልምና እና ኢየሱስ
1️⃣ ቁርአን ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፡
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡" (3፡185)
ስለዚህም ሁሏም ነፍስ ትሞታለች
2️⃣ይኸው ቁርአን ደግሞ በሌላ ሥፍራ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል ፡ "..«ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም.... ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡"(4:157-158)
እዚህ ላይ እንግዲህ የኢየሱስን አለመሰቀልና አለመገደል ይናገራል.. ይልቁንም ደግሞ ሳይሰቀል ሳይገደል አላህ ወደራሱ እንደወሰደው(እንዳነሳው) ይናገራል.. ስለዚህም ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀረ
እና ምን..?? አትሉኝም..?? ካላችሁኝማ ዲየግ ወደ ሙግቴ ልግባ ሎል..
- ነፍስ ሁሉ ሞትን ትቀምሳለች
- ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀርቷል
- ስለዚህም ኢየሱስ "ነፍስ ሁሉ" ተብሎ ከተገለጸው የሰው ዘር አይመደብም።
ከዚህ ቀደምም ለማሳየት እንደ ሞከርነውም ኢየሱስ በእስልምና በዘር ደረጃ ጭራሽ የአዳም ዘርም አይደለም ያስብለዋል የሚለውን ሌላ ማሳያ ይሆናል (ስለዚህም ፍጹም ሰውነቱንም ይክዳል አምላክነቱን ብቻ ሳይሆን ማለት ነው)
ምናልባት ግን ኢየሱስ ተመልሶ መጥቶ ሞትን ይቀምሳል የሚል ሰው ካለ.. ከቁርአን በግልጽ ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣና እንደ ሚሞት የተነገረበትን ክፍል ቢሰጡን..
ቁርአን ላይ አጥተው ምናልባት ወደ ሃዲሳቱ ጎራ ለማለት ከሞከሩ ደግሞ ቁርአኑ ለእስልምና ትምህርት በቂ አይደለም ለማለት ያስደፍረናል ማለት ነው።
@Apostolic_Answers
ሰባኪ ነኝ ዘማሪ ነኝ ምናምን በሚለው ውጭ ያሉ እህቶችን ገንዘብ የምትፈልጥ ከሆነ የምር በቃ ፍልጥ ሰገጥ ነህ🤝
በቃ የምታገለግል ከሆነ አርፈህ አገልግል.. አንቺም ደግሞ አገልጋይ ነኝ ላለ ሁሉ ሳንቲም አትላኪ.. በተለይ አረብ ሃገራት ምናምን ያላችሁ.. ሠራ ሠራ ጠርቀም ጠርቀም አድርጋችሁ ተመለሱ እንጂ አታባክኑ.. ምክንያት እየፈጠሩ ሳያስነቁ ለመንጠቅ ምናምን የሚሞክሩ ስለሚኖሩ..
ያው ምንም ነገር ያለ አግባብ አይሁን ለማለት እንጂ ንፉግነትንም እያስተማርኩ አይደለም..
ቆይ ጽሑፍ እንዳይረዝምብኝ ቀጣይ ደግሞ ከእህቶች ጋር ስላለን ቅርበት እናወራለን🤭🤭 ወይስ ይብራ..?? "ይቅር አይነገር" የሚል ካለ ተበላ😬😬
@Apostolic_Answers
ወሳኝ ነጥብ ትላለህ..
የሆነ ነገር ለማድረግ ስንነሳ በዛ ነገር ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት እንደፍራለን..??
ለምሳሌ ሚስት ኖራህ እርሷን ወደ ጎን አድርገህ ሌላ ሴት ጋር ለመሄድ(በሌላ አማርኛ cheat ለማድረግ) ብታስብ.. በዚህ ጉዳይ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??
እሺ አንድ ሰው ላይ ክፋት ለመስራት ለመነሳት ብትሞክር እዚህ ሥራህ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??
ለምሳሌ እነርዚህ ነገሮች ላይ ጌታችንን ለማሳተፍ ጭራሽ አትደፍርም.. መቼስ እንደው አንደኛውን ካልናቅኸው በስተቀር..
👉ስለዛስ ምን..?? የሆነ ነገርን ስናደርግ የምናደርገውን ነገር በዚህ እንመዝነው.. እዚህ ላይ ኢየሱስን ለማስገባት ያስደፍረኛል..?? እንበል.. የማያስደፍር ከሆነ ከዛ ነገር እንራቅ ምንም ይሁን ምን
ኢየሱስ የሕይወታችን መልኅቅ
@Apostolic_Answers
አይ ያረጋል.. በጣም ነው የምወደው የምር.. ጌታ አብዝቶ ይርዳው.. እውቀት ማስተዋል ጥበብን አሁንም ያብዛለት..
ይህንን ስል ያው ምንም ሊሳሳት የማይችል የክርስትና ልኬት ነው እያልኩም አይደለም.. ያው እርሱም በተደጋጋሚ እንደሚናገረው እንኳን አንድ ግለሰብ ሲኖዶስም ይሳሳታል(እዚህ ላይ ግን እኔ የማውቀው ሎካል ሲኖድ እንጂ አለም አቀፋዊ ሲሆን አይሳሳትም.. እርሱም አለም አቀፋዊውን አላለም)
እንደው ስም መጥራት ዝገት ሊሆን ይችላል ግን መምህር ያረጋል : ብርሃኑ አድማስ እና የኔታ ገብረ መድኅን ያው በተመለከትኩት ልክ በጣም ነው የምወዳቸው..
እናንተም ልክ እንዲሁ የምትወዷቸው መምህራን ይኖራሉ.. ማንንም ስትሰሙ ግን ከጥንት በመጣው በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሚዛንነት ሊሆን ይገባዋል..
@Apostolic_Answers
የአንዲት የጸነሰች ሴት ምራቅ ወደ ሌላኛዋ ሴት ገብቶ ያችኛዋ እንድትጸንስ ምክንያት ሆነ..??
አንዲት በጣም ጎበዝ እህቴ ድርሳነ ዑራኤልን ጠቅሳ ይህ ታሪክ እጅግ ከባድ እንደሆነ አነሳች እና ትንሽ አወራን እና ያወራነው ትንሽዬ ናት ግን ከጠቀማችሁ ጠቅለል ያለውን ነገር ልስጣችሁ..
በቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት ውስጥ ለአእምሮ የሚከብዱ ተአምራትን ብናገኝ እንዲሁ ትክክል ነው አይደለም እያሉ ሲከራከሩ ከመዋል ትክክል ከመሰለህ በእምነት "በእውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን..??" ብለህ ተቀብለህ እለፍ
አይ አልቀበልም ካልክ ደግሞ ያው በመቀበል ባለመቀበል ላይ ድኅነትህ ስለማይመሰረት እንዲሁ ሳትነቅፍ እለፈው.. ነቅፈኸው ምናምን ድንገት ግን የምርም የእግዚአብሔር ተአምር ቢሆንስ..?? ተበላህ ማለት አይደል..
ሰው ለጸሎት እና ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ጊዜ ቢሰጥ መልካም ነው.. ያው እንዲሁ ይሄኛው ተአምር ትክክል ነው ይሄኛው አይደለም ምናምን እያለ ፈራጅ ሆኖ ቁጭ ብሎ ሲከራከር ከሚውል ማለት ነው።
ያው ትምህርት ነክ ነገር ቢሆን ቀላል ነው በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መዝነኸው ታልፋለህ.. ተአምር ሲሆን ግን ይለያል.. ለአእምሮዬ ከባድ ነው ብለህ ብትነቅፍ ያ ተአምር ግን የምርም የእግዚአብሔር ሊሆን ስለሚችል ካልተቀበልክ አልተቀበልክም ነው ቢያንስ ግን አትንቀፍ ነው።
ያው ከእኛ በዘለለ የአንድ መምህርንም ትምህርት ሰማሁና ከሰማሁትም አንጻር አካፈልኳችሁ
@Apostolic_Answers
ለዩኒቨርሲቲ እና high school ተማሪዎች የሰጠሁዋችሁን የቤት ሥራ አሁን አስገቡልኝ🤪🤪
@aba_abi ላይ ላኩልኝ እስከ ነገ ድረስ
የቤት ሥራ ለዩኒቨርሲቲ እና Highschool ተማሪዎች
ትምህርት ቤቶች ላይ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሥራ ይጠበቅባታል..
Highschool ላይ እንዲሁም በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትልቅ ሥራ እንደሚጠበቅብን ግልፅ ማሳያዎች አሉ.. በሌላ ቤተ እምነቶች እና በዓለማዊነት የሚወሰዱ ክርስቲያን ወንድም እህቶቻችን ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም..
እናም የቤት ሥራው ምንድን ነው..
1. በሌላ ቤተ እምነቶች የሚሠሩ ሥራዎች ባስተዋላችሁት ልክ ምን ይመስላል
2. ትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የክርስቲያኖች(ኦርቶዶክስ) እንቅስቃሴ ምን ይመስላል
3. ክርስቲያኖች በእምነት እንዲጸኑ እኛ ጋር ቢኖር ወይም ቢደረግ ብላችሁ የምትመኙት..
ይህንን መልሱና ከዛም ነገ እንድትልኩልኝ አድራሻዬን አስቀምጥላችሁዋለሁ
"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"
"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"
"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"
ዲ/ን ያረጋል
የሮም ካቶሊክ እና ማርያም
- 16ኛው ክ/ዘመን ጉባኤ ትሬንት ላይ እመቤታችን ምንም አይነት ኃጢአት እንዳልሰራች ገልጸዋል.. (ሁሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት ያምናሉ ይሄንን)
- በ1854 immaculate conception የሚል ትምህርት (እመቤታችን አዳም ከወደቀ በሁዋላ ከእርሱ ያልተገኘች የሚያስመስል ትምህርት) ዶግማ አደረጉ.. ይሄን ዶግማ ባያደርጉት መልካም ነበር.. በየትኛውም ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት በኢትዮጵያውያም ጨምሮ እንዲህ ያለ ዶግማ የለም.. ካቶሊክም ዶግማ ካደረገችው 160 አመቷ አካባቢ ነው
- በ1950 ደግሞ የእመቤታችንን እርገት ዶግማ አደረጉት(እኛ ጋር ዶግማ አይደለም) ግን ሌላ አወዛጋቢ ነገር አለ እዚህ ላይ.. ጉባኤው ላይ የተወሰነው እንዲህ በሚል ቃል ነው: "የምድራዊ ሕይወቷ ዘመን በተጠናቀቀ ጊዜ በሥጋና ነፍስ ወደ ሰማይ ተወሰደች" ምኑ ነው የሚያወዛግበው..?? እመቤታችን ስትወሰድ እንደ ማንኛውም ሰው ሞታ ከዛ ተነስታ ነው ወይስ እንዲሁ ሳትሞት የሚል ጥያቄ ያስነሳል..
ያው አዳም ከወደቀ በሁዋላ ከእርሱ እንዳልተገኘች የሚመስል ነገርን አስቀድመው ስለደነገጉ "ሞታለች" የሚለውን ቃል በዶግማ ውስጥ ማካተቱን የፈሩት ይመስላሉ.. እና ነገረ ማርያም ሲለጠጥ ወደማይወጡበት ችግር ውስጥ ይገባሉ..
እኛ ጋር ዶግማችን ሁሉ ከክርስቶስ ጋር መገናኘት አለበት.. ስለዚህም ነገረ ማርያም ላይ ዶግማው "ወላዲተ አምላክ" መሆኗ ነው.. ይህ ነገረ ክርስቶስም ስለሆነ.. ከዚህ በተረፈ ድንግልናዋ እና ንጽህናዋ ክብርዋ በምልጃ አጋዥነቷ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ትምህርቶች ናቸው.. ምክንያቱም አባቶቻችን በተለይ ስለ ድንግልናዋ ጥብቅና ሳይቀር ቆመውለት አስተላልፈውልናል.. ሲቀጥል አምልኮዋችን ውስጥም አሉ..
@Apostolic_Answers
በግላችሁ ጸሎት ስታደርጉ ቤተክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ ሆኖ ግን ፍሌክሰብል ሁኑ.. ለምሳሌ አንድ ወዳጄ አባታችን ሆይን ሲጸልይ ብዙ ጊዜ የሚያደርገው አባታችን ሆይን 3 ያደርግና(ቅድስት ሥላሴንም እያሰበ) ከዛም እመቤታችን የሚለውን(በሰላመ ቅዱስ ገብርኤልን) አንዴ ያደርጋል..
እናንተም እንዲ አድርጉ ሳይሆን ወደ ጌታ በደንብ እንዲያቀርባችሁ እያደረጋችሁ ጸልዩ..
በተለይ በሆነ መጽሐፍ ብቻ መጸለይ ሳሆን በልባችሁ ያለውን አውሩት እግዚአብሔርን.. ካስተዋላችሁት የልባችሁን ማውራት ስትጀምሩ የአሳብ መበተን ራሱ ብዙም አይታይም..
እና ውዳሴ ማርያም: ዳዊት እና ዮሐንስ ወንጌል እንደ አቅሚቲ ማድረግ
የመጨረሻ መልስ😁😁 አዲስ ለሰራው ቪዲዮ..
ያው አዲስ ቪዲዮ ከሰራ ምን እንጠብቃለን..?? አዲስ ስህተት ደግሞ ሎል.. በሉ ስህተት ሳርም አልኖርም😁😁
5
እዚህ ላይስ ምንም አልጽፍም ሎል..
ማንንም belittle ላደርግ አልፈልግም ግን ያው ልጁ ቪዲዮውን የሰራበት መንገድ ራሱን የሆነ ወንበር ላይ ባስቀመጠ መልኩ ስለሆነ ምን ያህል በስህተቶች የታጨቀ ቪዲዮ እንደሰራ ላሳየውም ስለሚገባ ነው
ክፍል- 3
"ዮሐንስ የተባለው ራሱ ዮሐንስ አፈወርቅ ከሆነ የተአምር ክፍሉ 👉ስህተት ነው" (በወንድማችን)
እንግዲያውስ ራሱ መሆኑን እኔ በማስረጃ አሳይሃለው..
ስለዛ welcome 🤝 እንበል..??
መግቢያ - ክፍል 1
ከተአምር ክፍሉ ጋር የተገናኘ ነው.. ማየት የማያስፈልጋችሁ ሰዎች አትዩ.. ያው ተከታታይ ቪዲዮዎች ነው የሚሆኑት ትንሽ ሰዓት እያረፍን
ጌታችን የእኛን ባህሪ የነሳውና የተዋሃደው ሊፈውሰው ነው..
ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዲህ ይላል..
“ያልነሳውን አላዳነውም: ከመለኮቱ ጋር የተዋሐደው እርሱ ግን ድኗል:: ግማሽ አዳም ብቻ ወድቆስ ቢሆን(ነፍሱ ቀርታ ሥጋው ብቻ ቢሆን ውድቀት የገጠመው) እንግዲያውስ ክርስቶስም የሚነሳውና የሚያድነውም ግማሹን ሊሆን ይችላል.. ነገር ግን ሙሉ ሰውነቱ(ባህሪው) ከወደቀ ግን እንግዲያውስ ከሙሉ የወልድ ባህሪ ጋር ሊዋሐድ እና ሙሉ በሙሉ ሊድን ይገባዋል::”
[ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ : መልእክት ወደ ክሊዶንዩስ (To Cledonius the Priest Against Apollinarius)]
@Apostolic_Answers
ትእቢት ላስቸገረው ትሕትናን ለሚፈልግ ሰው ፍቱን መድኃኒት የሆነ ጸሎት.. ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም.. ሉቃስ 1 ላይ ያለው ወላዲተ አምላክ የጸለየችው ማለት ነው..
የሉቃስ ወንጌል 1
47፤ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
በዚህ የሚጀምረው ጸሎት..
ይህ ጸሎት ቅድስት ድንግል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወክላ የጸለየችው ጸሎት ይመስላል.. ያው ጸሎቱ ከእመቤታችን ውጪ በግለሰብ ደረጃ ለአንተ አይመጥን ይሆናል ለቤተ ክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያን ግን ኖርማል ነው.. አንተ ደግሞ የዛች ቤተ ክርስቲያን አባል ነህ እንኳን ደስ አለህ😁😁
ስለዚህም እንዲሁ እመቤታችን እንዲህ አለች ብሎ የመድገም ነገር ብቻ ሳይሆን አንተ ራስህ ደግሞ የቅድስት ቤተክርስቲያን አባል መሆንህን እያሰብክ በጣም ተረጋግተህ ከወላዲተ አምላክ ጋር ጸልየው..
በዚህ ውስጥ ወይ ትእቢት እየተሸነፈ ትሕትና እያየለ ይሄዳል ወይ አንተ ተሸንፈህ ጸሎቱን ከልብ ለመጸለይ ይደብርህና ትተወዋለህ
@Apostolic_Answers
መንፈስ ቅዱስ
ጌታ ኢየሱስ ሲያርግ "ሌላ አጽናኝ" ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች ተጥለን ነበር..
ቤተ ክርስቲያንን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሁላችን ተበትነን ነበር
በክርስቶስ የተሰራውን የማዳን ሥራ በእኛ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ያድሰን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ኖሮ በኢየሱስ የተሠራውንም የማዳን ሥራ ባላገኘንና በሞት ውስጥ በቀረን ነበር
በደከመን ጊዜ ያበረታን ዘንድ በበደልንም ጊዜ ወደ ንስሐ ይመራን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ለኃጢአት ባርያ ሆነን በቀረን ነበር
ቅዱሳንን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ራሱን ክርስቶስን እንዲመስሉ ለፈተናዎች ሁሉ ያስጨክናቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ክርስቶስንስ መምሰል ከየት መጥቶ
ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ያስጨክነን.. ለእርሱ ምስጋና ይሁን.. አሜን😊
@Apostolic_Answers
10,000 ገባን ለካ😝😝 በስንት ጊዜው😁😁
ቴሌግራም በጣም ቀርፋፋ ነው ግን ደግሞ በጣም cool ነው.. ልክ እንደኔ ማለት ነው😎😉 ሎል🤭🤭 የምር ግን ቴሌግራም በጣም ደስ ይላል..
ቲክቶክ በጣም በጥንቃቄ ካልተያዘ ራስን ማጥፊያ ቦታ.. ተመልካቾቹን ብቻ ሳይሆን የሚያገለግሉ ልጆችም የጸሎት እና የማንበቢያ ጊዜያቸውን ይሻማል በጣም..
ቴሌግራምም ጥንቃቄን ይፈልጋል በእርግጥ..
ብቻ ጸልዩ አንብቡ እደጉ ምናምን🤪🤪
የሴት ጓደኛ(ፍቅረኛ ትላለህ😁) ያለችህ ወንድሜ ስለ ኢየሱስ ታወራታለህ..??
ትዝ ይለኛል ከትንሽ ጊዜ በፊት አንድ ጓደኛዬ እንዲህ ብዬ ስጠይቀው ሳቅ እያለ "ምን እንድትጠላኝ ነው..??" ብሎኝ ነበር.. እና ልክ በጊዜው የማይጠበቅ መልስ ስለሆነ አስቆኝ ነበር.. በእርግጥ እሱም እንደ ቀልድ ነው ያለኝ.. አሁን እንደውም እሷ ናት ስለ ኢየሱስ የምትነግረው ሎል
ግን ደግሞ የምርም እንዲህ ያሉ ነገሮች የሚፈጠሩ ከሆነ ከባድ ነው.. አንዳንዶቻችን ጭራሽ ስለ ኢየሱስ መወራት ሲጀመር የምንደነግጥም አለን.. ይህንን ስም ሲሰማ ሊደነግጥና ምቾት ሊነሳው የሚገባው ጠላታችን ዲያቢሎስ ብቻ ነው.. ስለ ኢየሱስ በየቦታው ልናወራ ይገባል.. ልናወራ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን ልንኖረውም ይገባል
ቆንጂት ከጓደኞችሽ ጋር ሆነሽ ስለሆነ ወንድ ለማውራት ካላፈርሽ ስለ ኢየሱስ ማውራት ጭራሽ ሊያሳፍርሽ አይገባም
ብሮዬ አንተም እንዲሁ.. በተለይ ጓደኛ ካለችህ አውራት ስለ ኢየሱስ ለሌሎች ጓደኞችህም አውራቸው.. ከራቁህ ይራቁህ.. የኔ ኢየሱስ የምደራደርበት አይደለም እንበል..
አለም እኮ ቀስ በቀስ በጌታችን ኢየሱስ እንድናፍር እያደረገችንም መሰለኝ..
ሕይወታችን ኢየሱስ ነው
@Apostolic_Answers
መስቀል መድኃኒታችን ነው..??😬😬
"መስቀል" ስንል ምን እያልን ነው የሚለውን እኛን ጠይቁን ፕሊስ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቻችን..
መስቀል ስንል እንደው የሆነ የተመሳቀለ እንጨትን ብቻ የማሰብ ጉዳይ አይደለም.. ይልቁንም እዛ መስቀሉ ላይ የኛ ኢየሱስ እጆቹን ዘርግቶ ምን ያህል እንደሚወደን፤ የአጋንንትንም ራስ ሲቀጠቅጥ፤ በነገሮች ሁሉ ኃይል ሲሆነን ሲያሳየን ይታየናል
ስለዚህም መስቀል ስንል እጹ ብቻውን ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ነው የምናየው.. "መድኃኒት" ካልነው እንግዲያውስ መስቀል ማለታችን እጹ ብቻውን ሳይሆን ኢየሱስንም አብረን ስለምንለው ነው።
ቅዱስ መስቀል ኃይላችን ነው.. የክርስቶስ መስቀል ምርኩዛችን ነው። የክርስቲያኖች ትልቁ አርማችን ምልክታችንም ነው..
አንዳንድ ሰው ጊዜ ሰጥቶ "የኢሉሚናቲ የሰይጣን ምልክት" እያለ ያወራል.. ያውም ምንም በማያውቀው ነገር.. ስለ ክርስቲያኖች ምልክት ስለ ኢየሱስ መስቀልስ ጊዜ ሰጥተህ ታወራለህ ወይ..??
የኢየሱስ መስቀል ስንል ስለ እንጨቱ ብቻ እያልን አይደለም.. ይልቁንም እዛ እንጨት ላይ የኔና የእናንተ ጌታ ኢየሱስ ክንዶቹን ዘርግቶ እለተ ዐርብ ላይ ያለውን ያንን ነው የምንናገረው።
በመስቀሉ አናፍርም.. በእርሱም የምንሰብከው የተሰቀለውን ክርስቶስን ነውና
@Apostolic_Answers
ስትጸልይ ምንድን ነው የሚያጣድፍህ..?? እስቲ ረጋ በል..
ባክህን እኔም እንደዛው ነኝ😭😭 አንዳንዴማ ለራሴውም የምጸልይ አይመስልም እኮ.. የሆነ በቃ ይህንን ማንበብ ወይም ማለት አለብህ ብቻ ተብዬ የተገደድኩ ይመስል እሷን ለመጨረስ ያህል ፈጠን ፈጠን ማለት.. በተለይ ለሆነ ጉዳይ ከቸኮልክማ ተው😁😁
ስትጸልይ ቅዱሳኑ ከአንተ ጋር እንዲሆኑ ትፈልጋለህ.. ግን ቅዱሳኑ እንዳንተ በሩጫ ሲጸልዩ አስበው.. ለምሳሌ በጸሎተ እግዝእትነ ማርያም(የማርያም ጸሎት) ልትጸልይ ቆመህ መቼስ እመቤታችንም አብራህ እንድትጸልይ ትጠብቃለህ.. እና የእርሷ እርጋታ አለ.. ያንተ ግን ጥድፊያ.. እመቤታችን ተረጋግታ እንደምትለው ብትለው ሃሪፍ ነው..
አባታችን ሆይን ስትጸልይ እያንዳንዱን ቃልና ሃረግ በጣም በእርጋታ በለው.. ያኔ ወደ እግዚአብሔር በጣም ያቀርብሃል
ስትጸልይ ከአባትህ ጋር እየተገናኘህ ነው.. አባትህ ደግሞ አምላክህም ነው.. ስለዛ ረጋ በል👊😊
@Apostolic_Answers
ፊራ ከባድ ሰው.. ጌታ ይመስገን
ታናሽ ወንድማችን ነው(በእድሜ).. እኔ እንኳን የማውቀው ከ2 አመት አካባቢ በፊት "ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ አገልግሎት" በሚል ስም ተከታታይ የክርስትና ትምህርት የምሰጥበት ቻናል ላይ ጀምሮ ይመስለኛል..
እናማ አምና 12ኛ ክፍል ተፈትኖ 609 ነበር ያመጣው.. እና ከዚያም ፈተና ተፈትኖ አልፎ መንግስት የሰጠውን ዱባይ ሄዶ የመማር እድል አገኘ..
ስለ ሁሉም ነገር እምላከ ተክለሃይማኖት ይመስገን.. ጻድቁ አሁንም በአማላጅነቱ አይለይህ.. እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳህ
እንኳን ደስ አለህ ብሮ..
ሰላም ለእናንተ ይሁን የኔ ተወዳጆች
ያው ባለፈው ግእዝ ጀምረን ነበር.. እና በአንዳንድ ምክንያት እዚ ማካሄድ ስላልቻልን.. እኔም ስላልተመለስኩ መምህራችን ጴጥሮስ በሌላ በሱ ቻናል ላይ የሚቀጥለው ይሆናል..
ይጠቅማችሁዋልና እንደው በጌታ ሳትረሱት ከታች ባለው ሊንክ join በሉት
@geazlekulu
@geazlekulu
👆👆👆👆👆👆
6
በዚ ደረጃ ስህተቶቹን ከማሳይ አቅርቤው አንዳንድ ነገሮችን ባሳየው ባግዘው ምናምን መልካም ነበር ግን ፈራጅ ሆኖ ስለመጣ ለመታገዝም ምቹ አይደለም..
አንዳንዶቻችሁን ግን ይቅርታ በተደራራቢ ቪዲዮዎች አዛኳችሁ😝😝 በቃ አንድ የመጨረሻ ብቻ አቀብላችሁና እንጨርሳለን🤪🤪
ክፍል - 4
"ሊቃውንትን አልጠየቀም" እያለ እኔን ሲወቅስ ነበር
ይሄንን ያየሁ እኔም በቃ ይሄ ልጅ እንደው ለማስረጃ ወደ ሊቃውንቱ ይሮጣል ብዬ ሳስብ እሱ ግን surprise አደረገኝ.. ወደ ኢንሳይክሎፒዲያ ሮጦ🏃🏃
ግን ኢንሳክሎፒዲያውም ሊረዳው አልቻለም😭😭
አዝናለሁ ግን ዛሬ ቀን ላይ ኔትዎርክ ሰርቶልኝ ቲክቶክ ለአንድ ጉዳይ ስገባ አንድ ቪዲዮ ላይ ሜንሽን ተደርጌ አየሁ እና ሳየው በቃ እንዲሁ ላልፈው አልቻልኩም.. ያዘንኩትም የተአምረ ማርያሙ ጉዳይ ላይ ስለሆነ ነው..
ቪዲዮውን የሰራው ልጅ ታላቁ ጂብሪል የሚባል ክርስቲያን ወንድም ነው.. በእርግጥ መልስ የሚያስፈልገው አይነትም አይደለም.. ከተመልካቾች ሳይድ እንዲሁ 10 ደቂቃ ሙሉ የባከነበት.. ቪዲዮውን ለሰራው ደግሞ ምናልባትም 10 ቀንም የደከመበት ይሆናል😁😁
ግን ደግሞ ያቀረበበት መንገድ disrespectful ብቻ የሆነ ሳይሆን እንዲሁ misleading ስለሆነም እና ደግሞ Wikipedia ላይም ኤዲት አድርገው የነሱን አሳብ እንዲደግፍ ሲሉ እንዳስገቡም አስተዋልኩ.. እሱንም በማስረጃ አሳያችሁዋለው.. ይህ ደግሞ በእውነት አሳፋሪ ነው..
ካሁን በሁዋላ መልስ ስሰጥ ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእንደነዚህ አይነት አጭበርባሪዎችም ነው.. አጭበርባሪ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት Wikipedia ላይ ሳይቀር ያለ reference በማስገባታቸው ነው..(ማንኛው እንዳደረገው 100% አላውቅ ይሆናል ግን ተደርጉዋል)
ቲክቶክ ላይ ባይሆንም እዚው ቪዲዮ አስቀምጥላችሁዋለሁ
ስለዛ ከወዲሁ ብዙዎቻችሁን ይቅርታ እየጠየኩ ለአንዳንዶች መማሪያ አደርገዋለው.. ስለዛ ማየት የማትፈልጉ እባካችሁን እንዳታዩት