apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ተመልሰናል🤪🤪

https://vm.tiktok.com/ZMjRyyXaA/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የፕሮቴስታንት መዝሙር የዘመረችው እህታችን በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ገዳም ውስጥ ነው የተደበቀችው አሉ😬😬

እመቤቴን በጣም ነው ያነደደችሽ ግን በቃ አፉ እንበላታ😬😬

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በመንፈሳዊ ሕይወትህ ስትደክም

በደከምክባቸው በእነዚህ ወቅቶች ላይ ራስህን መግዛትና ከኃጢአት መራቅ ሲያቅትህ አስተውለህ ይሆናል.. ይህም ከጌታ ተለይተህ ብቻህን ማሸነፍ እንደማትችል ያስተምርሃል..

ስለዚህም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ሕይወት ስትመለስና የመንፈስ ፍሬዎች ሊታዩብህ ሲጀምሩ እንዳትኮፈስና ሌሎች ደካሞች ላይም እንዳትፈርድ ያደርግሃል..

ምክንያቱም አንተም ያሸንፈከው ኃይልን በሚሰጥህ በክርስቶስ እንጂ በራስህ እንዳልሆነ ታውቀዋለህና.. ስለዛ ለእነርሱም እንድታዝንላቸውና እንድትጸልይላቸው ያደርግሃል..

ጌታ ሁላችንን ያበርታን..

ደግሞ እንኳን አደረሳችሁ.. መልካም ቀን😊🤗

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እስቲ ልጠይቃችሁ.. ኮመንት ላይ አሳውቁኝ..

በክርስቲያኖች እና በፕሮቴስታንቶች መካከል ያለ የትምህርት ልዩነት.. ለእናንተ ትልቁ ልዩነት የምትሉትን አንድ ወይም ሁለቱን ብቻ ጻፉልኝ😊😊

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በአማራ ክልል አካባቢ ያሉ ወንድም እህቶቻችን አባት እናቶቻችን እንደምታውቁት በብዙ መከራ ውስጥ እያለፉ ነው እና እስቲ እንደው እንጸልይላቸው በጌታ.. ምስኪን ሕዝብ.. ከጦርነት ወደ ጦርነት.. እግዚአብሔር በቃ ይበላቸው.. እንደው ስንጸልይ አንርሳቸው ለማለት ያህል ነው..

አይዟችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጌታችን ይመጣል ለዘላለምም ከእርሱ ጋር እንኖራለን

ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩት ግን አሁን ላይ እርሱን የወደዱት ናቸው.. "ወንድም ጌታ ይወድሃል" ማለት ብቻ ሳይሆን አንተስ ጌታን ትወደዋለህ ወይ ነው..

እወደዋለሁ ካልክ እንግዲያውስ ቃሉን ጠብቅ.. ለመዳን ተጠመቅ ካለህ አሜን በል.. ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የራሱ ሥጋና ደም እንደሆነ ከነገረህ አሜን በል.. አይ ካልክ በቃ ገና አልወደድኸውም..

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለንም ወደ ቅዱስ ምስጢር እየቀረብን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ካላጠነከርን ትእዛዙን ካልጠበቅን እርሱን መውደዳችን በምን ይታወቃል..??


"ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።"
[1ቆሮ 16: 22]

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤

-> በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ

መዝ 27:4

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እስልምና እና ኢየሱስ

1️⃣ ቁርአን ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፡
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡" (3፡185)

ስለዚህም ሁሏም ነፍስ ትሞታለች

2️⃣ይኸው ቁርአን ደግሞ በሌላ ሥፍራ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል ፡ "..«ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም.... ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው፡፡"(4:157-158)

እዚህ ላይ እንግዲህ የኢየሱስን አለመሰቀልና አለመገደል ይናገራል.. ይልቁንም ደግሞ ሳይሰቀል ሳይገደል አላህ ወደራሱ እንደወሰደው(እንዳነሳው) ይናገራል.. ስለዚህም ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀረ

እና ምን..?? አትሉኝም..?? ካላችሁኝማ ዲየግ ወደ ሙግቴ ልግባ ሎል..

- ነፍስ ሁሉ ሞትን ትቀምሳለች
- ኢየሱስ ሞትን ሳይቀምስ ቀርቷል
- ስለዚህም ኢየሱስ "ነፍስ ሁሉ" ተብሎ ከተገለጸው የሰው ዘር አይመደብም።

ከዚህ ቀደምም ለማሳየት እንደ ሞከርነውም ኢየሱስ በእስልምና በዘር ደረጃ ጭራሽ የአዳም ዘርም አይደለም ያስብለዋል የሚለውን ሌላ ማሳያ ይሆናል (ስለዚህም ፍጹም ሰውነቱንም ይክዳል አምላክነቱን ብቻ ሳይሆን ማለት ነው)

ምናልባት ግን ኢየሱስ ተመልሶ መጥቶ ሞትን ይቀምሳል የሚል ሰው ካለ.. ከቁርአን በግልጽ ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣና እንደ ሚሞት የተነገረበትን ክፍል ቢሰጡን..

ቁርአን ላይ አጥተው ምናልባት ወደ ሃዲሳቱ ጎራ ለማለት ከሞከሩ ደግሞ ቁርአኑ ለእስልምና ትምህርት በቂ አይደለም ለማለት ያስደፍረናል ማለት ነው።

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሰባኪ ነኝ ዘማሪ ነኝ ምናምን በሚለው ውጭ ያሉ እህቶችን ገንዘብ የምትፈልጥ ከሆነ የምር በቃ ፍልጥ ሰገጥ ነህ🤝

በቃ የምታገለግል ከሆነ አርፈህ አገልግል.. አንቺም ደግሞ አገልጋይ ነኝ ላለ ሁሉ ሳንቲም አትላኪ.. በተለይ አረብ ሃገራት ምናምን ያላችሁ.. ሠራ ሠራ ጠርቀም ጠርቀም አድርጋችሁ ተመለሱ እንጂ አታባክኑ.. ምክንያት እየፈጠሩ ሳያስነቁ ለመንጠቅ ምናምን የሚሞክሩ ስለሚኖሩ..

ያው ምንም ነገር ያለ አግባብ አይሁን ለማለት እንጂ ንፉግነትንም እያስተማርኩ አይደለም..

ቆይ ጽሑፍ እንዳይረዝምብኝ ቀጣይ ደግሞ ከእህቶች ጋር ስላለን ቅርበት እናወራለን🤭🤭 ወይስ ይብራ..?? "ይቅር አይነገር" የሚል ካለ ተበላ😬😬

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወሳኝ ነጥብ ትላለህ..

የሆነ ነገር ለማድረግ ስንነሳ በዛ ነገር ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት እንደፍራለን..??

ለምሳሌ ሚስት ኖራህ እርሷን ወደ ጎን አድርገህ ሌላ ሴት ጋር ለመሄድ(በሌላ አማርኛ cheat ለማድረግ) ብታስብ.. በዚህ ጉዳይ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??

እሺ አንድ ሰው ላይ ክፋት ለመስራት ለመነሳት ብትሞክር እዚህ ሥራህ ውስጥ ኢየሱስን ለማስገባት ትደፍራለህ..??

ለምሳሌ እነርዚህ ነገሮች ላይ ጌታችንን ለማሳተፍ ጭራሽ አትደፍርም.. መቼስ እንደው አንደኛውን ካልናቅኸው በስተቀር..

👉ስለዛስ ምን..?? የሆነ ነገርን ስናደርግ የምናደርገውን ነገር በዚህ እንመዝነው.. እዚህ ላይ ኢየሱስን ለማስገባት ያስደፍረኛል..?? እንበል.. የማያስደፍር ከሆነ ከዛ ነገር እንራቅ ምንም ይሁን ምን

ኢየሱስ የሕይወታችን መልኅቅ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አይ ያረጋል.. በጣም ነው የምወደው የምር.. ጌታ አብዝቶ ይርዳው.. እውቀት ማስተዋል ጥበብን አሁንም ያብዛለት..

ይህንን ስል ያው ምንም ሊሳሳት የማይችል የክርስትና ልኬት ነው እያልኩም አይደለም.. ያው እርሱም በተደጋጋሚ እንደሚናገረው እንኳን አንድ ግለሰብ ሲኖዶስም ይሳሳታል(እዚህ ላይ ግን እኔ የማውቀው ሎካል ሲኖድ እንጂ አለም አቀፋዊ ሲሆን አይሳሳትም.. እርሱም አለም አቀፋዊውን አላለም)

እንደው ስም መጥራት ዝገት ሊሆን ይችላል ግን መምህር ያረጋል : ብርሃኑ አድማስ እና የኔታ ገብረ መድኅን ያው በተመለከትኩት ልክ በጣም ነው የምወዳቸው..

እናንተም ልክ እንዲሁ የምትወዷቸው መምህራን ይኖራሉ.. ማንንም ስትሰሙ ግን ከጥንት በመጣው በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሚዛንነት ሊሆን ይገባዋል..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የአንዲት የጸነሰች ሴት ምራቅ ወደ ሌላኛዋ ሴት ገብቶ ያችኛዋ እንድትጸንስ ምክንያት ሆነ..??

አንዲት በጣም ጎበዝ እህቴ ድርሳነ ዑራኤልን ጠቅሳ ይህ ታሪክ እጅግ ከባድ እንደሆነ አነሳች እና ትንሽ አወራን እና ያወራነው ትንሽዬ ናት ግን ከጠቀማችሁ ጠቅለል ያለውን ነገር ልስጣችሁ..

በቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት ውስጥ ለአእምሮ የሚከብዱ ተአምራትን ብናገኝ እንዲሁ ትክክል ነው አይደለም እያሉ ሲከራከሩ ከመዋል ትክክል ከመሰለህ በእምነት "በእውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን..??" ብለህ ተቀብለህ እለፍ

አይ አልቀበልም ካልክ ደግሞ ያው በመቀበል ባለመቀበል ላይ ድኅነትህ ስለማይመሰረት እንዲሁ ሳትነቅፍ እለፈው.. ነቅፈኸው ምናምን ድንገት ግን የምርም የእግዚአብሔር ተአምር ቢሆንስ..?? ተበላህ ማለት አይደል..

ሰው ለጸሎት እና ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ጊዜ ቢሰጥ መልካም ነው.. ያው እንዲሁ ይሄኛው ተአምር ትክክል ነው ይሄኛው አይደለም ምናምን እያለ ፈራጅ ሆኖ ቁጭ ብሎ ሲከራከር ከሚውል ማለት ነው።

ያው ትምህርት ነክ ነገር ቢሆን ቀላል ነው በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መዝነኸው ታልፋለህ.. ተአምር ሲሆን ግን ይለያል.. ለአእምሮዬ ከባድ ነው ብለህ ብትነቅፍ ያ ተአምር ግን የምርም የእግዚአብሔር ሊሆን ስለሚችል ካልተቀበልክ አልተቀበልክም ነው ቢያንስ ግን አትንቀፍ ነው።

ያው ከእኛ በዘለለ የአንድ መምህርንም ትምህርት ሰማሁና ከሰማሁትም አንጻር አካፈልኳችሁ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለዩኒቨርሲቲ እና high school ተማሪዎች የሰጠሁዋችሁን የቤት ሥራ አሁን አስገቡልኝ🤪🤪

@aba_abi ላይ ላኩልኝ እስከ ነገ ድረስ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የቤት ሥራ ለዩኒቨርሲቲ እና Highschool ተማሪዎች

ትምህርት ቤቶች ላይ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ሥራ ይጠበቅባታል..

Highschool ላይ እንዲሁም በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትልቅ ሥራ እንደሚጠበቅብን ግልፅ ማሳያዎች አሉ.. በሌላ ቤተ እምነቶች እና በዓለማዊነት የሚወሰዱ ክርስቲያን ወንድም እህቶቻችን ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም..

እናም የቤት ሥራው ምንድን ነው..
1. በሌላ ቤተ እምነቶች የሚሠሩ ሥራዎች ባስተዋላችሁት ልክ ምን ይመስላል

2. ትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የክርስቲያኖች(ኦርቶዶክስ) እንቅስቃሴ ምን ይመስላል

3. ክርስቲያኖች በእምነት እንዲጸኑ እኛ ጋር ቢኖር ወይም ቢደረግ ብላችሁ የምትመኙት..

ይህንን መልሱና ከዛም ነገ እንድትልኩልኝ አድራሻዬን አስቀምጥላችሁዋለሁ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"

"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"

"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"

ዲ/ን ያረጋል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

+ ቅዱሳት ሥዕላት+

በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ትውፊት መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት ማለት(precising definition)፡ በአብያተ ክርስትያናት ግድግዳ ፣ በሸራ ፣ በብራና ፣ በወረቀት እና በመስቀል ላይ በቀለም አልያም በጭረት 2 ጎን(2D) ተደርገው የሚሳሉ የእግዚአብሔርን እና የቅዱሳኑን ማንነት የሚገልፁ መንፈሳዊ ጥበብ ናቸው ።  በአምልኳችን(ቅዳሴ) ጊዜ የማይታዩትን ቅዱሳንን መገኘት እና በምድር ያለው ቅዳሴ በሰማይ ካለው ጋር አንድ መሆኑን ለማዘከር ያገለግላሉ ፤ በዚህ መልኩ ሕሊናችንን ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ስለሚያደርጉት በመንፈሳዊ ትርጓሜ "የሰማይ መስኮቶች"¹ ይባላሉ ።

ሥዕላት የሚመስሉትን ራሱኑ ባይሆኑም ያንን የሚወክሉ እና በውስጣቸው የሚይዙ ናቸው ፤ የመጽሀፍ ቅዱስ ምንባባት ያማሩና የተወደዱ፡ ልደትን፣ ደብረታቦርን፣ ሕማማትን፣ ስቅለትን፣ ትንሣኤን እና የመሳሰሉትን የሚወክሉ እና በሕሊናችን የሚስሉ ሥዕላት እንደሆኑ ሁሉ ቅዱሳት ሥዕላትም በቅዱስ ጎርጎርዩስ ታላቁ አባባል "ላልተማሩ የተዘጋጁ ወንጌላት ናቸው"² ። ከመጽሀፍ ቅዱስ የሚለዩት pictorial ስለሆኑ እንጂ ሁለቱም የሚመስሉትን የሚወክሉ Icon(ምስል) ናቸው   ።  ቅዱስ ባስልዩስ እንደሚለው³ " ለሥዕል የሚደረግ ክብር ለተመሰለው ዋና አካል ያልፋል " ቅዱሳት ሥዕላትን ስናከብር ወረቀቱን፣ ቀለሙን ፣ እንጨቱን ሳይሆን በነዚህ ነገሮች የተመሰለውን አካል ነው ። ለመስቀል ስንሰግድ ለእንጨቱ ቢሆን ምንሰግደው ዛፍ ባየን ቁጥር ለእርሱም ልንሰግድ ነዋ! ።

ማንኛውም ሰው ምስልን ከመጠቀም ነጻ አይደለም ። በቀለም የተሳሉ ሥዕላትን ባንጠቀም እንኳን በሕሊና የተሳሉትን ሥዕላት መጠቀማችን አይቀርም ። ቅዱስ ጳውሎስ "ክርስቶስ እንደተሰቀለ ኾኖ ተስሎላችሁ ነበር "⁴ በማለት inevitable የሆነውን በሕሊና መሳልን እንደመልካም ነገር ያነሳል ፤ ለምስል የሚደረግ ክብር ለተመሰለው አካል እንደሆን የማታምን ሆይ ክርስቶስ በሕሊናህ ተስሎ ስትጸልይ ፣ ስትሰግድ እና ስታመሰግን የሰገድከው ለcognitive image ነው ወይስ ለክርስቶስ?

አንዳንዶች "የተቀረጸውን ምስል ለራስህ አታድርግ ፣ አትስገድላቸው ፣ አታምልካቸውም " የሚለውን የኦሪት ቃል⁵ ሥዕላትን የሚከለክል ነው ይላሉ ። ይህንን የሚሉ ግን መጽሐፍ ሌላ ምን ተናገረ የሚለውን ስለማይሰሙ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ያጋጩታል (ወይም suppressed evidence Fallacy  ) ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ አትስገዱላቸው ብቻ ሳይሆን አታምልኳቸውም ስለሚል ምስል የተባለው የሥዕል ዓይነት የሆነው ጣዖት እንጂ ሁሉም አይነት ሥዕላት እንዳልሆኑ ያሳያል ፤ በሌላ ቦታ ደግም እግዚአብሔር ሙሴን "2 ኪሩቤሎችን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ በስርየቱ መክደኛ ላይም ታደርጋቸዋለህ "⁶ ይለዋል ፤ እንደገናም የክርስቶስ indirect representation የሆነውን የነሐስ እባቡን ምስል ሰርቶ እንዲሰቅለውና ህዝቡ አይቶት እንዲድን ይነገረዋል⁷ ።

የጴጥሮስ ሥዕለ አካሉና የአካሉ መገለጫ የሆነው ጥላው ሲያርፍባቸው ሰዎች ተፈውሰዋል⁸ ፤ ጴጥሮስ በጥላው(ሥዕለ አካል) ፈወሰ የሚልን መጽሀፍ ቅዱስ የሚያነብ ሰው በሥዕሉ ደግሞ ፈወሰ ቢባል ለምን ይደንቀዋል? "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ" የሚል ኅብረተ ሰብእ ከአጥሩ የሚበልጠውን የባለቤቱን ምስል መናቅ ባለቤቱን መናቅ መሆኑን ማመን እንዴት ከበደው? ። ወዳጄ "የቤተመንግሥቱን  ልብስ ብታቃል ንጉሱን  ማቃለልህ አይደል? ታድያ የንጉሱን ሥዕል መናቅ ንጉሱን መናቅ መኾኑን አትመለከትም ?" ለእግዚአብሔርና ለቅዱሳኑ ሥዕል የሚደረግ ንቀት እነርሱን መናቅ የሚሰጥ ክብረ ደግሞ እነርሱን ማክበር መሆኑን ልብ ይሏል ።

***
¹ Windows into heaven
² Gregory the great, letters, letter 105
³ Basil the great, on the holy Spirit, 18
⁴ ገላ 3
⁵ ዘጸ 20:14
⁶ ዘጸ 25:18
⁷ ዘኅ 21:8
⁸ ሐዋ 5:15

ዋቢ
ዲ/ን ዮሀንስ ጌታቸው፣ ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኅቡእ ስሞች..??

አንዳንድ የጸሎት መጽሐፍት ላይ የአምላክ ኅቡእ ስሞች ተብለው የሚዘረዘሩ አሉ ኃይልንም ያደርጋሉ ይባላል..

እና እኔስ ጸሎቴ ውስጥ ልጠቀማቸው..??

ተጠቀም አትጠቀም አልልህም.. ግን እኔ አልጠቀምባቸውም.. በተለያዩ መጽሐፍት ላይ በርካታ ናቸው እና የምርም የአምላክ ስም መሆናቸውን አላውቅም.. በዛ ላይ ትልቅ ሃይልን የሚያደርግ ኢየሱስ የሚል ስም አለን..

ከምንም በላይ ደግሞ ታላቁ ጸሎት ቅዳሴያችን ላይም አንጠቀምም..

እና ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንዲህ ያለ ነገር አይታይም እኔ እስከማውቀው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"ፕሮቴስታንቲዝም" ከክርስትና ጋር ያለው ትልቁ ልዩነት ያው ዋናዎቹን ለማስቀመጥ ያህል:

- "ጸጋ ብቻ" ሲሉ የእኛን ነፃ ፈቃድ መካዳቸው(በተለይ ካልቪኒስቶች)
- ጥምቀት ለድኅነት አያስፈልግም ማለታቸው
- ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም ማለታቸው
- ምስጢረ ክህነትን አለማመናቸው
- የምትታይ ቤተ ክርስቲያን የለችም ማለታቸው
- የእውነተኛነት ልኬት የሆነውን ቅዱስ ትውፊት አለመቀበላቸው

ሌሎችም በርካታ ሊነሱ ይችላሉ.. የተሻሉ የሚባሉ ፕሮቴስታንቶችን ያማከለ ነው ይሄ

ኢየሱስ ይማልዳል አይማልድም የሚለውን ዝርዝር ውስጥ አላካተትኩትም ምክንያቱም አሁን አሁን ብዙዎቹ "ይማልዳል" የሚለውን ቃሉን ይጠቀሙታል እንጂ አሳቡ ከእኛው ጋር ተመሳሳይ እየሆነ ነው.. የአሳብ ልዩነት ከሌለ ወሳኞቹ ላይ ትኩረት ማድረጉ መልካም ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“መልአክን ከሰማይ ወደ ምድር የጣለው ትእቢት ነበረ.. ሰውንም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርገው ትህትና ነው"

ትህትና ትእቢተኛውን ጠላት የምንረታበት ትሁቱን ጌታ የምንመስልበት ትልቅ መሣሪያ ነው.. ትህትና ስላችሁ ሰው ፊት ለመታየት ያህል ብቻ እንዲሁ መተወን ሳይሆን እውነተኛ ትህትናን ማለቴ ነው.. እውነተኛ ትህትና አንደበት ላይ ሳይሆን ልብ ላይ ነው..

እውነተኛ ትህትና የሚመጣው ትሁቱ ጌታ በእኛ ሲኖር ብቻ ነው.. እርሱ በእኛ የሚኖረው ደግሞ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ስንካፈል ነው..

ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:

"ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ"
[ማቴ 11:29]

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሰይጣንን ፍራቻ..??

ጠንቋይ ትፈራለህ..?? ወይም በሌላ ቤተ እምነት በክርስትና ስም የሚሰራውን መንፈስ ትፈራለህ..??

ፍራቻ የሚመጣው ከእምነት ጉድለት ነው.. የምን እምነት ..?? ከክፉ ሁሉ በሚጠብቀን በእረኛችን ላይ ያለን እምነት.. እግዚአብሔር የምርም እረኛችን እንደሆነ በሙሉ ልባችን ካመንን ምን ያስፈራናል..?? ምክንያቱም ከእርሱ የሚያልፍ የለም..

ስለዛ እረኛችንን ስናውቀው ስናምነው ፍራቻ ይርቃል.. ከመዝሙረኛውም ጋር ሆነን እንዲህ እንላለን:

"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው"

ግን.. ከእረኛችን አንራቅ.. ሁሌም እርሱን ጠባቂያችን እናድርግ..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦

"ጌታ ይገሥጽህ" አለው እንጂ #የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
[ይሁዳ 1:3]


አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
[141:3]

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጌታችን የእኛን ባህሪ የነሳውና የተዋሃደው ሊፈውሰው ነው..

ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዲህ ይላል..

“ያልነሳውን አላዳነውም: ከመለኮቱ ጋር የተዋሐደው እርሱ ግን ድኗል:: ግማሽ አዳም ብቻ ወድቆስ ቢሆን(ነፍሱ ቀርታ ሥጋው ብቻ ቢሆን ውድቀት የገጠመው) እንግዲያውስ ክርስቶስም የሚነሳውና የሚያድነውም ግማሹን ሊሆን ይችላል.. ነገር ግን ሙሉ ሰውነቱ(ባህሪው) ከወደቀ ግን እንግዲያውስ ከሙሉ የወልድ ባህሪ ጋር ሊዋሐድ እና ሙሉ በሙሉ ሊድን ይገባዋል::”

[ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ : መልእክት ወደ ክሊዶንዩስ (To Cledonius the Priest Against Apollinarius)]


@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ትእቢት ላስቸገረው ትሕትናን ለሚፈልግ ሰው ፍቱን መድኃኒት የሆነ ጸሎት.. ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም.. ሉቃስ 1 ላይ ያለው ወላዲተ አምላክ የጸለየችው ማለት ነው..

የሉቃስ ወንጌል 1
47፤ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤

በዚህ የሚጀምረው ጸሎት..

ይህ ጸሎት ቅድስት ድንግል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወክላ የጸለየችው ጸሎት ይመስላል.. ያው ጸሎቱ ከእመቤታችን ውጪ በግለሰብ ደረጃ ለአንተ አይመጥን ይሆናል ለቤተ ክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያን ግን ኖርማል ነው.. አንተ ደግሞ የዛች ቤተ ክርስቲያን አባል ነህ እንኳን ደስ አለህ😁😁

ስለዚህም እንዲሁ እመቤታችን እንዲህ አለች ብሎ የመድገም ነገር ብቻ ሳይሆን አንተ ራስህ ደግሞ የቅድስት ቤተክርስቲያን አባል መሆንህን እያሰብክ በጣም ተረጋግተህ ከወላዲተ አምላክ ጋር ጸልየው..

በዚህ ውስጥ ወይ ትእቢት እየተሸነፈ ትሕትና እያየለ ይሄዳል ወይ አንተ ተሸንፈህ ጸሎቱን ከልብ ለመጸለይ ይደብርህና ትተወዋለህ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መንፈስ ቅዱስ

ጌታ ኢየሱስ ሲያርግ "ሌላ አጽናኝ" ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች ተጥለን ነበር..

ቤተ ክርስቲያንን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሁላችን ተበትነን ነበር

በክርስቶስ የተሰራውን የማዳን ሥራ በእኛ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ያድሰን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ኖሮ በኢየሱስ የተሠራውንም የማዳን ሥራ ባላገኘንና በሞት ውስጥ በቀረን ነበር

በደከመን ጊዜ ያበረታን ዘንድ በበደልንም ጊዜ ወደ ንስሐ ይመራን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ለኃጢአት ባርያ ሆነን በቀረን ነበር

ቅዱሳንን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ራሱን ክርስቶስን እንዲመስሉ ለፈተናዎች ሁሉ ያስጨክናቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ባይወርድ ክርስቶስንስ መምሰል ከየት መጥቶ

ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ያስጨክነን.. ለእርሱ ምስጋና ይሁን.. አሜን😊

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

10,000 ገባን ለካ😝😝 በስንት ጊዜው😁😁

ቴሌግራም በጣም ቀርፋፋ ነው ግን ደግሞ በጣም cool ነው.. ልክ እንደኔ ማለት ነው😎😉 ሎል🤭🤭 የምር ግን ቴሌግራም በጣም ደስ ይላል..

ቲክቶክ በጣም በጥንቃቄ ካልተያዘ ራስን ማጥፊያ ቦታ.. ተመልካቾቹን ብቻ ሳይሆን የሚያገለግሉ ልጆችም የጸሎት እና የማንበቢያ ጊዜያቸውን ይሻማል በጣም..

ቴሌግራምም ጥንቃቄን ይፈልጋል በእርግጥ..

ብቻ ጸልዩ አንብቡ እደጉ ምናምን🤪🤪

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የሴት ጓደኛ(ፍቅረኛ ትላለህ😁) ያለችህ ወንድሜ ስለ ኢየሱስ ታወራታለህ..??

ትዝ ይለኛል ከትንሽ ጊዜ በፊት አንድ ጓደኛዬ እንዲህ ብዬ ስጠይቀው ሳቅ እያለ "ምን እንድትጠላኝ ነው..??" ብሎኝ ነበር.. እና ልክ በጊዜው የማይጠበቅ መልስ ስለሆነ አስቆኝ ነበር.. በእርግጥ እሱም እንደ ቀልድ ነው ያለኝ.. አሁን እንደውም እሷ ናት ስለ ኢየሱስ የምትነግረው ሎል

ግን ደግሞ የምርም እንዲህ ያሉ ነገሮች የሚፈጠሩ ከሆነ ከባድ ነው.. አንዳንዶቻችን ጭራሽ ስለ ኢየሱስ መወራት ሲጀመር የምንደነግጥም አለን.. ይህንን ስም ሲሰማ ሊደነግጥና ምቾት ሊነሳው የሚገባው ጠላታችን ዲያቢሎስ ብቻ ነው.. ስለ ኢየሱስ በየቦታው ልናወራ ይገባል.. ልናወራ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን ልንኖረውም ይገባል

ቆንጂት ከጓደኞችሽ ጋር ሆነሽ ስለሆነ ወንድ ለማውራት ካላፈርሽ ስለ ኢየሱስ ማውራት ጭራሽ ሊያሳፍርሽ አይገባም

ብሮዬ አንተም እንዲሁ.. በተለይ ጓደኛ ካለችህ አውራት ስለ ኢየሱስ ለሌሎች ጓደኞችህም አውራቸው.. ከራቁህ ይራቁህ.. የኔ ኢየሱስ የምደራደርበት አይደለም እንበል..

አለም እኮ ቀስ በቀስ በጌታችን ኢየሱስ እንድናፍር እያደረገችንም መሰለኝ..

ሕይወታችን ኢየሱስ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መስቀል መድኃኒታችን ነው..??😬😬

"መስቀል" ስንል ምን እያልን ነው የሚለውን እኛን ጠይቁን ፕሊስ ፕሮቴስታንት ወንድም እህቶቻችን..

መስቀል ስንል እንደው የሆነ የተመሳቀለ እንጨትን ብቻ የማሰብ ጉዳይ አይደለም.. ይልቁንም እዛ መስቀሉ ላይ የኛ ኢየሱስ እጆቹን ዘርግቶ ምን ያህል እንደሚወደን፤ የአጋንንትንም ራስ ሲቀጠቅጥ፤ በነገሮች ሁሉ ኃይል ሲሆነን ሲያሳየን ይታየናል

ስለዚህም መስቀል ስንል እጹ ብቻውን ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ነው የምናየው.. "መድኃኒት" ካልነው እንግዲያውስ መስቀል ማለታችን እጹ ብቻውን ሳይሆን ኢየሱስንም አብረን ስለምንለው ነው።

ቅዱስ መስቀል ኃይላችን ነው.. የክርስቶስ መስቀል ምርኩዛችን ነው። የክርስቲያኖች ትልቁ አርማችን ምልክታችንም ነው..

አንዳንድ ሰው ጊዜ ሰጥቶ "የኢሉሚናቲ የሰይጣን ምልክት" እያለ ያወራል.. ያውም ምንም በማያውቀው ነገር.. ስለ ክርስቲያኖች ምልክት ስለ ኢየሱስ መስቀልስ ጊዜ ሰጥተህ ታወራለህ ወይ..??

የኢየሱስ መስቀል ስንል ስለ እንጨቱ ብቻ እያልን አይደለም.. ይልቁንም እዛ እንጨት ላይ የኔና የእናንተ ጌታ ኢየሱስ ክንዶቹን ዘርግቶ እለተ ዐርብ ላይ ያለውን ያንን ነው የምንናገረው።

በመስቀሉ አናፍርም.. በእርሱም የምንሰብከው የተሰቀለውን ክርስቶስን ነውና

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ስትጸልይ ምንድን ነው የሚያጣድፍህ..?? እስቲ ረጋ በል..

ባክህን እኔም እንደዛው ነኝ😭😭 አንዳንዴማ ለራሴውም የምጸልይ አይመስልም እኮ.. የሆነ በቃ ይህንን ማንበብ ወይም ማለት አለብህ ብቻ ተብዬ የተገደድኩ ይመስል እሷን ለመጨረስ ያህል ፈጠን ፈጠን ማለት.. በተለይ ለሆነ ጉዳይ ከቸኮልክማ ተው😁😁

ስትጸልይ ቅዱሳኑ ከአንተ ጋር እንዲሆኑ ትፈልጋለህ.. ግን ቅዱሳኑ እንዳንተ በሩጫ ሲጸልዩ አስበው.. ለምሳሌ በጸሎተ እግዝእትነ ማርያም(የማርያም ጸሎት) ልትጸልይ ቆመህ መቼስ እመቤታችንም አብራህ እንድትጸልይ ትጠብቃለህ.. እና የእርሷ እርጋታ አለ.. ያንተ ግን ጥድፊያ.. እመቤታችን ተረጋግታ እንደምትለው ብትለው ሃሪፍ ነው..

አባታችን ሆይን ስትጸልይ እያንዳንዱን ቃልና ሃረግ በጣም በእርጋታ በለው.. ያኔ ወደ እግዚአብሔር በጣም ያቀርብሃል

ስትጸልይ ከአባትህ ጋር እየተገናኘህ ነው.. አባትህ ደግሞ አምላክህም ነው.. ስለዛ ረጋ በል👊😊

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላድገዛለት ይገዛል" 1ቆሮ 15: 28

https://vm.tiktok.com/ZM2nqCGCe/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ፊራ ከባድ ሰው.. ጌታ ይመስገን

ታናሽ ወንድማችን ነው(በእድሜ).. እኔ እንኳን የማውቀው ከ2 አመት አካባቢ በፊት "ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ አገልግሎት" በሚል ስም ተከታታይ የክርስትና ትምህርት የምሰጥበት ቻናል ላይ ጀምሮ ይመስለኛል..

እናማ አምና 12ኛ ክፍል ተፈትኖ 609 ነበር ያመጣው.. እና ከዚያም ፈተና ተፈትኖ አልፎ መንግስት የሰጠውን ዱባይ ሄዶ የመማር እድል አገኘ..

ስለ ሁሉም ነገር እምላከ ተክለሃይማኖት ይመስገን.. ጻድቁ አሁንም በአማላጅነቱ አይለይህ.. እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳህ

እንኳን ደስ አለህ ብሮ..

Читать полностью…
Subscribe to a channel