ኧኸ ምርጦች.. ይህንን ዓመት በቅዳሴ እንደ ጀመራችሁት ተስፋ በማድረግ (ያው ያልሰቀደሳችሁም ኖርማል ነው የዓመቱን የመጀመሪያ እሁድ አትቀሩም😉)
እና ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
"ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል"
[ማቴ 11:5]
ምናልባት ካወቃችሁ.. በመምህራን ወይም በሌሎችም ወንድሞች የሆነ አዳራሽ ተከራይተው ምናምን ለአንድ ቀን መንፈሳዊ ፕሮግራም ያዘጋጃሉ.. ያው ታዳሚዎቹም የተወሰነ ብር ከፍለው ነው የሚገቡት..
እና ምን አሰብኩ..?? እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢረዳን በዚህ ዓመት ቢያንስ አንድ ቀን ጎዳና ላይ የሚኖሩ ወንድም እህቶቻችንን ሰብስበን ጸዴ መንፈሳዊ ፕሮግራም እናዘጋጅላቸዋለን.. እና ወንጌል ለእነርሱም ይሰበካል.. በዚህ ምድር ቤት ባይኖራቸው እንኳን በሰማይ ግን አባታቸው ያዘጋጀላቸው በገንዘብ የማይታመን መኖሪያ እንዳላቸው ይነገራቸዋል.. ወደዚህ ዘላለማዊ መኖሪያቸውም ይገቡ ዘንድ ወደ ንስሐ እና ቅዱስ ምስጢር እንዲቀርቡ ይሰበክላቸዋል.. ስለዚህም የኢየሱስ ፍቅር በልባቸው በዝቶ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል" ወደ ማለት ያድጉ ዘንድ.. ያው ይሄ እየጠነከሩ ሲሄዱ ነው የዛንው ቀን ያልቃል ማለቴ አይደለም😁😁
አዲስ ዓመት ሲመጣ እቅድ የማውጣት አባዜ ሲኖርብህ😁😁 ብቻ ግን እኛ ባንችለው ራሱ ሌሎች የምትችሉ አድርጉት እስቲ😊🤗
@Apostolic_Answers
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥
መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
መዝሙር 27:4
መልካም ቀን😊🤗
ሃሪፍ ክርስቲያን ዐቃቤ እምነት(የእምነት ጠባቂ) ለመሆን የሚያስፈልግህ ምንድን ነው..??
1. ቅዱስ ቁርባን
2. ቅዳሴ አለመቅጣት (መጸለይም)
3. ከምታወራበት ጊዜ በላይ ማንበብ
4. ቋንቋ ኢንግሊዘኛ አንብበህ መረዳት ብትችል.. ያው ግእዝም ብታውቅ ይጠቅማል..
ምን ላንብብ..?? እንዴትስ ላጥና..?? የሚለውን ዝርዝር አሳብ ቀጣይ ትላለህ😁😁
አስቀያሚ አጋጣሚ😭😭
አርፍጄ ነበር የተኛሁት.. ያው ለቅዳሴ ደግሞ በጊዜ መነሳት አለብኝ.. 11:30 ምናምን ተነስቼ መሄድ አለብኝ(አጠገቤ ነው)
አርፍጄ ወደ 7 ሰዓት ላይ ተኝቼ ጭራሽ 9 ሰዓት ስልክ ቢደወልብኝስ🤦♂️🤦♂️
ይኸው ተመልሼ መተኛት አቅቶኝ ከአንድ ሰዓት በላይ ታገልኩ ለመተኛት ግን ወፍ😭😭
ቅዳሴ ሲያልቅ ደግሞ ጭራሽ ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ጋርም የተወሰነ ጊዜ እንደማሳልፍ ትዝ አለኝ🥹🥹
ይበለኝ አርፍጄ ተኝቼ እና ስልኬን ከፍቼ ነው ጉድ የሆንኩት😆😆
ሐዋርያዊ መልሶች - መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት
ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀመርን.. ስለዛ ከዚህ ቀደም ተመዝግባችሁ አጋጣሚ ትምህርቱ ያለፋችሁ እንዲሁም ጭራሹኑ ያልተመዘገባችሁም አሁን መመዝገብ ይቻላል..
@aklilabi ላይ ጆይን በሉና እዛው ላይ አሳውቃችሁዋለሁ
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የፕሮቴስታንት መዝሙር የዘመረችው እህታችን በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ገዳም ውስጥ ነው የተደበቀችው አሉ😬😬
እመቤቴን በጣም ነው ያነደደችሽ ግን በቃ አፉ እንበላታ😬😬
በመንፈሳዊ ሕይወትህ ስትደክም
በደከምክባቸው በእነዚህ ወቅቶች ላይ ራስህን መግዛትና ከኃጢአት መራቅ ሲያቅትህ አስተውለህ ይሆናል.. ይህም ከጌታ ተለይተህ ብቻህን ማሸነፍ እንደማትችል ያስተምርሃል..
ስለዚህም ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ሕይወት ስትመለስና የመንፈስ ፍሬዎች ሊታዩብህ ሲጀምሩ እንዳትኮፈስና ሌሎች ደካሞች ላይም እንዳትፈርድ ያደርግሃል..
ምክንያቱም አንተም ያሸንፈከው ኃይልን በሚሰጥህ በክርስቶስ እንጂ በራስህ እንዳልሆነ ታውቀዋለህና.. ስለዛ ለእነርሱም እንድታዝንላቸውና እንድትጸልይላቸው ያደርግሃል..
ጌታ ሁላችንን ያበርታን..
ደግሞ እንኳን አደረሳችሁ.. መልካም ቀን😊🤗
እስቲ ልጠይቃችሁ.. ኮመንት ላይ አሳውቁኝ..
በክርስቲያኖች እና በፕሮቴስታንቶች መካከል ያለ የትምህርት ልዩነት.. ለእናንተ ትልቁ ልዩነት የምትሉትን አንድ ወይም ሁለቱን ብቻ ጻፉልኝ😊😊
በአማራ ክልል አካባቢ ያሉ ወንድም እህቶቻችን አባት እናቶቻችን እንደምታውቁት በብዙ መከራ ውስጥ እያለፉ ነው እና እስቲ እንደው እንጸልይላቸው በጌታ.. ምስኪን ሕዝብ.. ከጦርነት ወደ ጦርነት.. እግዚአብሔር በቃ ይበላቸው.. እንደው ስንጸልይ አንርሳቸው ለማለት ያህል ነው..
አይዟችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን..
ጌታችን ይመጣል ለዘላለምም ከእርሱ ጋር እንኖራለን
ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩት ግን አሁን ላይ እርሱን የወደዱት ናቸው.. "ወንድም ጌታ ይወድሃል" ማለት ብቻ ሳይሆን አንተስ ጌታን ትወደዋለህ ወይ ነው..
እወደዋለሁ ካልክ እንግዲያውስ ቃሉን ጠብቅ.. ለመዳን ተጠመቅ ካለህ አሜን በል.. ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የራሱ ሥጋና ደም እንደሆነ ከነገረህ አሜን በል.. አይ ካልክ በቃ ገና አልወደድኸውም..
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለንም ወደ ቅዱስ ምስጢር እየቀረብን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ካላጠነከርን ትእዛዙን ካልጠበቅን እርሱን መውደዳችን በምን ይታወቃል..??
"ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።"
[1ቆሮ 16: 22]
@Apostolic_Answers
ከአንዱ ጉዋደኛዬ የተላከልኝ መልእክት 😁😁
ስማ!!አንተ ዕለታዊ የነዳጅ ዋጋ የሆንክ ሰው🤪🤪አይ እንኳን ሰላም አደረሰህ ይሄ አመት የቅዳሴ(ያው እንደምታስቀድስ አውቃለሁ አለበዚያ እንደዚህ ልትሆን አትችልም)እና የማህሌት አመት (ማህሌት ምናምን ሚቆም ሰው ቅናት ዝሙት ትዕቢት ይጠፋለታል ሲል ሰምቻለሁ ዲ/ን ብርሀን አድማስ)ይሁንልህ በየደብሩ እየዞርን ምናድር ያድርገን!
ከዚህ በላይ በቤቱ ላሉት መልስን ለወጡት ነፍስ ደግሞ መመለስ ምክንያትን አብዝቶ ይስጥህ!!በየቤቱ እየዞርን ልጆቻቸው ጴንጤ የሆኑባቸው ቤተሰቦች ቤት ሄደን ተከራክረን ወደ በረት ምንመልስ ያድርገን! ከዛ ወላጆች ደስ ብሏቸው ምን እናድርግላችሁ?ሲሉን አይይ ምንም ቸኮሌት ብቻ ስጡን የምንልበት አመት ይሁንልህ![🤭]
ብቻ ደስተኛ ነኝ አንተ በመኖርህ ብዙ ጠቅመከኛል ብቻ ጌታ ከእናቱ ጋር እና ከቅዱሳኑ ጋር ሁሌም ካንተ ጋር ይኑር መልካም በአል አሜን የማይነበብ ፊርማ!እንዱ ለአክሊለ ሰማዕት(አኬ) ከላከው የተወሰደ ይመቾት❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ለማንኛውም ሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ😊🤗
ሰንበት ት/ቤት ዛሬ የዶግማ ኮርስ ፈተና ፈትኛቸው🤦♂️🤦♂️
ሙሉውን ደረቅ ጥያቄ ነበር እና በጣም ከብዷቸው ይኸው መልስ መስጫውን በነጠብጣብ አድርገው መስቀል ሰርተውበት ሰጡኝ😭😭
እኔም ጥያቄውን ረስቼው የሰሩትን የመስቀል ምልክት ውበት እያየሁ ማርክ እየሰጠሁ ነው😭😭 (ደግሞ ስቀልድ ነው😁😁)
ግን ክርስቲያኖች አስተምህሮዋችንን በደንብ ልንማር ልናውቅ ይገባል
"ለእናትህ ሁለተኛ ልደትን ከውኃዎች የሰጠሃት ልጅ ሆይ"
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ : በእንተ ልደተ ክርስቶስ : hymn 11
ለእናቱ ሁለተኛ ልደት የሰጠ ልጅ😊😊
@Apostolic_Answers
አንዱ ወዳጄ "ሃሪፍ ዐቃቤ እምነት ነኝ ብለህ ታስባለህ ብሮ" ብሎ ጠየቀኝ..
አዲስ ነው እዚህ መሰለኝ.. ያው ከዚህ ቀደምም ስለተናገርኩ.. እኔ መምህርም ዐቃቤ እምነትም የምባል አይደለሁም.. ወደፊት ሃሪፍ ዐቃቤ እምነት የመሆን ፍላጎቱ አለኝ ጌታ ይርዳኝ..
ለጊዜው ግን በስሱ የምናውቃትን ከክርስቲያን ወንድም እህቶች ጋር ማውራት እንጂ ሌላ ምንም የለም😁😁
አንድ በጣም የሚያስፈራና የሚያሳፍርም ነገር😳😳
እግዚአብሔርን እንደ ጠላት ማየት
የሆነ ነገርን በጣም ከወደድን እና ያ ነገር ደግሞ በእግዚአብሔር ያልተወደደ ከሆነ.. እግዚአብሔር ከዛ እንድንርቅ ከሆነ ፍላጎቱ እና እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ከምንወደው በላይ ያንን ነገር ከወደድን እግዚአብሔርን የምናይበት መንገድ "ከምንፈልገው ነገር የሚነጥለን ጠላታችን" አድርገን ነው..
ከዛም ያ ሰው ከሁለት አንዱን መምረጥ ግድ እየሆነበት ሲመጣ.. ከእግዚአብሔር ይልቅ ያንን በእግዚአብሔር የተጠላውን ነገር ይመርጥና እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ እየተወ ይሄዳል..
እግዚአብሔር ይጠብቀን ከዚህ.. ብዙ በእግዚአብሔር የተጠሉ ነገሮችን እናደርግ ይሆናል.. ክርስቲያን ግን ከነዛ ነገሮች ለመውጣት ይታገላል እንጂ ጭራሹኑ በእግዚአብሔር ላይ የበላይ አያደርግም..
ኃጢአት ብቻ አይደለም.. ከጌታ የሚያርቅህ ጉዋደኛ እና ቤተሰብም ቢሆን ከኢየሱስ ሊበልጡብን አይገባም..
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:
"ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም.."
[ማቴ 10:37]
@Apostolic_Answers
እስቲ አንድ ጊዜ ቸኮላት በሉ..
"በሉ" እንጂ "ብሉ" አላልኩም..
ማን እንደላከልኝ አልናገርም.. ያው ሄዳቹ ለእኛም ላኪልን እንዳትሏት ሎል.. እህታችን ግን ለአገልግሎቱ መፋጠን ያደረግሽው ቀላል አይደለም ሎል😝😝 አይ ግን አመሰግናለሁ የምር አንቺ **😊🤗 ደግሞ ዘጭ ነው😁😁
+ ቅዱሳት ሥዕላት+
በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ትውፊት መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት ማለት(precising definition)፡ በአብያተ ክርስትያናት ግድግዳ ፣ በሸራ ፣ በብራና ፣ በወረቀት እና በመስቀል ላይ በቀለም አልያም በጭረት 2 ጎን(2D) ተደርገው የሚሳሉ የእግዚአብሔርን እና የቅዱሳኑን ማንነት የሚገልፁ መንፈሳዊ ጥበብ ናቸው ። በአምልኳችን(ቅዳሴ) ጊዜ የማይታዩትን ቅዱሳንን መገኘት እና በምድር ያለው ቅዳሴ በሰማይ ካለው ጋር አንድ መሆኑን ለማዘከር ያገለግላሉ ፤ በዚህ መልኩ ሕሊናችንን ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ስለሚያደርጉት በመንፈሳዊ ትርጓሜ "የሰማይ መስኮቶች"¹ ይባላሉ ።
ሥዕላት የሚመስሉትን ራሱኑ ባይሆኑም ያንን የሚወክሉ እና በውስጣቸው የሚይዙ ናቸው ፤ የመጽሀፍ ቅዱስ ምንባባት ያማሩና የተወደዱ፡ ልደትን፣ ደብረታቦርን፣ ሕማማትን፣ ስቅለትን፣ ትንሣኤን እና የመሳሰሉትን የሚወክሉ እና በሕሊናችን የሚስሉ ሥዕላት እንደሆኑ ሁሉ ቅዱሳት ሥዕላትም በቅዱስ ጎርጎርዩስ ታላቁ አባባል "ላልተማሩ የተዘጋጁ ወንጌላት ናቸው"² ። ከመጽሀፍ ቅዱስ የሚለዩት pictorial ስለሆኑ እንጂ ሁለቱም የሚመስሉትን የሚወክሉ Icon(ምስል) ናቸው ። ቅዱስ ባስልዩስ እንደሚለው³ " ለሥዕል የሚደረግ ክብር ለተመሰለው ዋና አካል ያልፋል " ቅዱሳት ሥዕላትን ስናከብር ወረቀቱን፣ ቀለሙን ፣ እንጨቱን ሳይሆን በነዚህ ነገሮች የተመሰለውን አካል ነው ። ለመስቀል ስንሰግድ ለእንጨቱ ቢሆን ምንሰግደው ዛፍ ባየን ቁጥር ለእርሱም ልንሰግድ ነዋ! ።
ማንኛውም ሰው ምስልን ከመጠቀም ነጻ አይደለም ። በቀለም የተሳሉ ሥዕላትን ባንጠቀም እንኳን በሕሊና የተሳሉትን ሥዕላት መጠቀማችን አይቀርም ። ቅዱስ ጳውሎስ "ክርስቶስ እንደተሰቀለ ኾኖ ተስሎላችሁ ነበር "⁴ በማለት inevitable የሆነውን በሕሊና መሳልን እንደመልካም ነገር ያነሳል ፤ ለምስል የሚደረግ ክብር ለተመሰለው አካል እንደሆን የማታምን ሆይ ክርስቶስ በሕሊናህ ተስሎ ስትጸልይ ፣ ስትሰግድ እና ስታመሰግን የሰገድከው ለcognitive image ነው ወይስ ለክርስቶስ?
አንዳንዶች "የተቀረጸውን ምስል ለራስህ አታድርግ ፣ አትስገድላቸው ፣ አታምልካቸውም " የሚለውን የኦሪት ቃል⁵ ሥዕላትን የሚከለክል ነው ይላሉ ። ይህንን የሚሉ ግን መጽሐፍ ሌላ ምን ተናገረ የሚለውን ስለማይሰሙ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር ያጋጩታል (ወይም suppressed evidence Fallacy ) ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ አትስገዱላቸው ብቻ ሳይሆን አታምልኳቸውም ስለሚል ምስል የተባለው የሥዕል ዓይነት የሆነው ጣዖት እንጂ ሁሉም አይነት ሥዕላት እንዳልሆኑ ያሳያል ፤ በሌላ ቦታ ደግም እግዚአብሔር ሙሴን "2 ኪሩቤሎችን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ በስርየቱ መክደኛ ላይም ታደርጋቸዋለህ "⁶ ይለዋል ፤ እንደገናም የክርስቶስ indirect representation የሆነውን የነሐስ እባቡን ምስል ሰርቶ እንዲሰቅለውና ህዝቡ አይቶት እንዲድን ይነገረዋል⁷ ።
የጴጥሮስ ሥዕለ አካሉና የአካሉ መገለጫ የሆነው ጥላው ሲያርፍባቸው ሰዎች ተፈውሰዋል⁸ ፤ ጴጥሮስ በጥላው(ሥዕለ አካል) ፈወሰ የሚልን መጽሀፍ ቅዱስ የሚያነብ ሰው በሥዕሉ ደግሞ ፈወሰ ቢባል ለምን ይደንቀዋል? "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ" የሚል ኅብረተ ሰብእ ከአጥሩ የሚበልጠውን የባለቤቱን ምስል መናቅ ባለቤቱን መናቅ መሆኑን ማመን እንዴት ከበደው? ። ወዳጄ "የቤተመንግሥቱን ልብስ ብታቃል ንጉሱን ማቃለልህ አይደል? ታድያ የንጉሱን ሥዕል መናቅ ንጉሱን መናቅ መኾኑን አትመለከትም ?" ለእግዚአብሔርና ለቅዱሳኑ ሥዕል የሚደረግ ንቀት እነርሱን መናቅ የሚሰጥ ክብረ ደግሞ እነርሱን ማክበር መሆኑን ልብ ይሏል ።
***
¹ Windows into heaven
² Gregory the great, letters, letter 105
³ Basil the great, on the holy Spirit, 18
⁴ ገላ 3
⁵ ዘጸ 20:14
⁶ ዘጸ 25:18
⁷ ዘኅ 21:8
⁸ ሐዋ 5:15
ዋቢ
ዲ/ን ዮሀንስ ጌታቸው፣ ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
ኅቡእ ስሞች..??
አንዳንድ የጸሎት መጽሐፍት ላይ የአምላክ ኅቡእ ስሞች ተብለው የሚዘረዘሩ አሉ ኃይልንም ያደርጋሉ ይባላል..
እና እኔስ ጸሎቴ ውስጥ ልጠቀማቸው..??
ተጠቀም አትጠቀም አልልህም.. ግን እኔ አልጠቀምባቸውም.. በተለያዩ መጽሐፍት ላይ በርካታ ናቸው እና የምርም የአምላክ ስም መሆናቸውን አላውቅም.. በዛ ላይ ትልቅ ሃይልን የሚያደርግ ኢየሱስ የሚል ስም አለን..
ከምንም በላይ ደግሞ ታላቁ ጸሎት ቅዳሴያችን ላይም አንጠቀምም..
እና ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እንዲህ ያለ ነገር አይታይም እኔ እስከማውቀው
@Apostolic_Answers
"ፕሮቴስታንቲዝም" ከክርስትና ጋር ያለው ትልቁ ልዩነት ያው ዋናዎቹን ለማስቀመጥ ያህል:
- "ጸጋ ብቻ" ሲሉ የእኛን ነፃ ፈቃድ መካዳቸው(በተለይ ካልቪኒስቶች)
- ጥምቀት ለድኅነት አያስፈልግም ማለታቸው
- ቅዱስ ቁርባን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም አይደለም ማለታቸው
- ምስጢረ ክህነትን አለማመናቸው
- የምትታይ ቤተ ክርስቲያን የለችም ማለታቸው
- የእውነተኛነት ልኬት የሆነውን ቅዱስ ትውፊት አለመቀበላቸው
ሌሎችም በርካታ ሊነሱ ይችላሉ.. የተሻሉ የሚባሉ ፕሮቴስታንቶችን ያማከለ ነው ይሄ
ኢየሱስ ይማልዳል አይማልድም የሚለውን ዝርዝር ውስጥ አላካተትኩትም ምክንያቱም አሁን አሁን ብዙዎቹ "ይማልዳል" የሚለውን ቃሉን ይጠቀሙታል እንጂ አሳቡ ከእኛው ጋር ተመሳሳይ እየሆነ ነው.. የአሳብ ልዩነት ከሌለ ወሳኞቹ ላይ ትኩረት ማድረጉ መልካም ነው
@Apostolic_Answers
“መልአክን ከሰማይ ወደ ምድር የጣለው ትእቢት ነበረ.. ሰውንም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርገው ትህትና ነው"
ትህትና ትእቢተኛውን ጠላት የምንረታበት ትሁቱን ጌታ የምንመስልበት ትልቅ መሣሪያ ነው.. ትህትና ስላችሁ ሰው ፊት ለመታየት ያህል ብቻ እንዲሁ መተወን ሳይሆን እውነተኛ ትህትናን ማለቴ ነው.. እውነተኛ ትህትና አንደበት ላይ ሳይሆን ልብ ላይ ነው..
እውነተኛ ትህትና የሚመጣው ትሁቱ ጌታ በእኛ ሲኖር ብቻ ነው.. እርሱ በእኛ የሚኖረው ደግሞ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ስንካፈል ነው..
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ:
"ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ"
[ማቴ 11:29]
@Apostolic_Answers
ሰይጣንን ፍራቻ..??
ጠንቋይ ትፈራለህ..?? ወይም በሌላ ቤተ እምነት በክርስትና ስም የሚሰራውን መንፈስ ትፈራለህ..??
ፍራቻ የሚመጣው ከእምነት ጉድለት ነው.. የምን እምነት ..?? ከክፉ ሁሉ በሚጠብቀን በእረኛችን ላይ ያለን እምነት.. እግዚአብሔር የምርም እረኛችን እንደሆነ በሙሉ ልባችን ካመንን ምን ያስፈራናል..?? ምክንያቱም ከእርሱ የሚያልፍ የለም..
ስለዛ እረኛችንን ስናውቀው ስናምነው ፍራቻ ይርቃል.. ከመዝሙረኛውም ጋር ሆነን እንዲህ እንላለን:
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው"
ግን.. ከእረኛችን አንራቅ.. ሁሌም እርሱን ጠባቂያችን እናድርግ..
@Apostolic_Answers
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦
"ጌታ ይገሥጽህ" አለው እንጂ #የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
[ይሁዳ 1:3]
አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
[141:3]
@Apostolic_Answers