apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ = hermeneutical anarchy

ማዕከላዊ ተርጓሚ አካል በሌለበት(state of hermeneutical anarchy) በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የምትመራ አንድ ቤተክርስትያን መመስረት ሀሳባዊ እንጂ ተግባራዊ አይደለም። ይህ ማለት ልክ ሕገ መንግስትን ይዞ ሶስቱ የመንግስት አካላት አያስፈገልኝም በራሴ ተረድቼ እመራለው እንደማለት ነው(ሕግ የለም ከማለት ምንም አይለይልም) ። በተግባር ደረጃ የክርስትያኖችን ህብረት ያወድማል እንጂ አያለማም ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ስፍር ቁጥር የሌለው እርስ በእርሳቸው የማይስማሙት የፕሮቴስታንት ቡድኖች ናቸው ። Doctrine ንም ቢሆን ተለዋወጭ ና ብዙ በሆነው በሰው የግል አስተያየት ላይ የተመሰረተ ስላደረገው ምንም ዶክትሪን ሃይማኖት ስለመሆኑ ያለን ፍጹም እርግጠኝነት(certitude) አጥፍቶታል ።
 
hermeneutical anarchyን ተክትሎ በጎራ መከፋፈል የማይቀር ነው ፤ የየሰዉ የግል አረዳድ ከሌላው ስለሚለይ ተቀራራቢ አረዳድ ያላቸው አንድ ቡድን ይሆናሉ ። ይህም በተራው የመጋቢነትን ድርሻ ያቀለዋል(undermines Pastoral authority) ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ለመምህራን እንድንታዘዝ ቢያዘንም ከሀሰተኛ ነብያት እንድንጠነቀቅ እና መንፈስን ሁሉ እንድንመረምር ይነግረናል ስለዚህ ለመምህራን ምንታዘዘው እውነተኞች እስክሆኑ ድረስ ነው ። እውነተኛ መምህር መሆኑ ታድያ በምን ይታወቃል? ለመጽሐፍ ቅዱስ ባለን የግል አረዳድ የምንመራ ከሆነ እውነተኛ መምህር የምንለው ከግል አረዳዳችን ጋር ተስማምቶ ያገኘነውን ሊሆን ነው ።  አሁንም ደግሞ የእያንዳንዱ የግል አረዳድ ከሌላው ስለሚለይ ሁሉም በየራሱ የፈለገውን ወደ ሚያደርግበት ቤተክርስትያናዊ ቀውስ ይከተናል ።

ይህ እሳቤ በቤተክርስትያን አንድነትን የሚያጠፋ ፣ መከፋፈልን የሚያመጣ ፣ መምህርነትን የሚያቀል ፣ ዶግማ ቢስ የሚያደርግ  የቤተክርስትያናዊ ቀውስ ሁሉ ምንጭ (mother of all ecclesiastical chaos) ነው ። ክርስቶስ አንድ እንሆን ዘንድ ያቀረበውን ጥሪ እና ጸሎት[ዮሐ 17፡21] ከንቱ ያደረገ ሰይጣናዊ ሀሳብ ነው!

"ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም " 2 ጴጥ 1:20

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ላይቭ ነን🤪🤪

https://vm.tiktok.com/ZMjaVvEcs/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከመልእክታት ከተነበበው


"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።"
[1ጴጥ 4:3]

በአሕዛብ ፈቃድ ለምንመላለስ ጌታ ብርታቱን ይስጠን.. እስካሁን ስንበድል የኖርንበት ዘመን ይበቃናል ብለን ቀሪውን ዘመናችንን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር እንኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ያስጨክነን..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ላይቭ ነን

https://vm.tiktok.com/ZMjPvMYbq/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬም ልጠይቃችሁ እስቲ.. ያው እኔ የምሰጠውን ተከታታይ የክርስትና ትምህርት የምትማሩ ልጆች ከትንሽ ማብራሪያ ጋር አድርጋችሁ መልሱ እስቲ


2. የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቅብብሎሽ እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥል ሲሆን፤ የቅብብሎሹ አስጀማሪ ማን ነው?

 ሀ. ነቢያት      ለ. ሐዋርያት      
ሐ.  ሊቃውንት      መ. መልስ የለም

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቅዱስ መስቀል

https://vm.tiktok.com/ZMjPYR4yD/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንድ እስላም ልጅ የኔ ቪዲዮ ላይ ሪያክት ለማድረግ እንደ ሞከረ ተመለከትኩ.. እና "መካከለኛ" የሚለውን ቃል ያብራራሁበት ቪዲዮ ላይ ነው ሪያክት ያደረገው.. ክፍሉ "አምላክም ሰውም" የሚል አሳብ አይገኝበትም ነው ያለው.. እውነቱን ለመናገር ለእንደነዚህ አይነት ልጆች መልስ መስጠት ብዙም አልወድም.. ግን አንድ ክርስቲያን መልስ ስጥበት ስላለኝ ምናልባት ደግሞ ክፍሉን በደንብ ለማብራራትም ምክንያት ላድርገው ብዬ ነው😁😁

እና እዝችው ጋር በአጭሩ መልሷን ጽፌ ላስቀምጥላችሁ ወይስ አጭር ቪዲዮ ቲክቶክ ላይ ይሰራላችሁ..??

ያው ኮመንት ስለዘጋሁባችሁ በሪያክሽን አሳውቁኝ

እዚሁ በጽሑፍ ይመለስ የምትሉ፡ 👍 ተጫኑ

በቲክቶክ የምትሉ፡ 👏 ተጫኑ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኦው ደግሞ እሁድ መጣልን.. እስቲ ነገ ደግሞ ቅዳሴ ላይ የሚነበበውን የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል በደንብ ስሙና ከዚያም ግሩፕ ላይ ደግሞ አውሩበት..

መልካም አዳር እናንተ የተመታችሁ ሰዎች.. ምንም በቃ ልወዳችሁ አልቻልኩም.. ስለዛ ለእናንተ ጻፍ ጻፍ ይለኛል😭😭

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የምር ግን እግዚአብሔር ይመስገን

አዳም ሁሉ ነገር ተሰጠውና አንዲት ነገር ተከለከለ.. እና ሰይጣን ደግሞ አዳም ትኩረቱን እሷ ላይ እንዲያደርግ አደረገው.. እና አዳም በተሰጡት ነገሮች ከማመስገን ይልቅ በተከለከለው ምንም ጥቅም በማይሰጠው ነገር አማራሪ ሆነ..

የኔ ተወዳጆች የምር እግዚአብሔር እኮ የሰጠን ብዙ ነው.. ጭራሽ ልጁንም ሰጠ እንጂ.. እና በትንሹም በትልቁም አናማርር.. ይልቁንም እናመስግነው እንጂ..

ሆስፒታል ነበርኩ ዛሬ የሆነ ሰው ታሞ.. በቃ ማርያምን በጣም ነው የሚከብደው ህመማቸው.. በህመም ለሚሰቃዩት ሁሉ እግዚአብሔር ፈውስን ይስጥ..

በቃ "እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን"

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወንጌል አንድምታ ላይ:
ማቴ 12፡32 ትርጓሜ

እውን "መካነ ንስሐ"(purgatory) ኦርቶዶክሳዊ ነው..?? አይደለም ይህ የካቶሊክ ትምህርት ነው.. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም እንዲህ ያለ አስተምህሮ..

አንድምታ በእጅጉ ሕይወትን በሚሰጥ እውቀት የተሞላ ድንቅ ትርጉዋሜ ነው ግን ያው አንዳንዴ እንዲህ በስህተት ሊገባ የሚችል ነገር ደግሞ ሊገኝ ይችላልና የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስለምናውቅ በስህተት እንደ ገባ(ወይም እንደተባለ) አስበን እናልፈዋለን.. ኖርማል ነው..


የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ(ሃይማኖታችን) ውስጥ ግን ምንም እንከን ሊገኝ አይችልም.. እሱን መቼም እንዳትረሱ..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንዴ ክርስቲያኖች አስተሳሰባቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል እያልኩ የማካፍላቸው አሳቦች አንዳንዶችን የሚያስቆጣ አንዳንዶችንም የሚያስደነግጥ ሆኖ አገኘዋለው.. አንዳንዴ የክርስትና አስተምህሮ ምንድን ነው የሚለውን ለይቶ ያለማወቅ ችግር ኖርማል ክርስቲያኖች ላይ ብቻ ሳይሆን "አገልጋዮች" ላይም ይታያል..

ለምሳሌ ተአምሩ ላይ እንዳነሳሁት

እና ለመተቸት የሚሯሯጡ ወንድሞች ምናምን አያስጨንቁም.. የሚያስጨንቀኝ ከኔ አንዳንድ ነገሮችን የሚሰሙ ወንድም እህቶች ጉዳይ ብቻ ናቸው..

ስለዛ የእናንተን አሳብ ማወቅ ፈለኩ.. እንደዚህ ዓይነት ትምህርቶችን ስትሰሙ የተወሰነ ይረብሻችሁዋል ስለዚህም ይቅር ወይስ ለእናንተ ኖርማል ነው.. ያስፈልጋሉ ብዬ የማስባቸውን ላካፍላችሁ..??


ያው ለዚህ pol አዘጋጅላችሁዋለሁ ከታች አንዱን ትመርጣላችሁ ወደ ማታ ላይ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ..

የዮሐንስ ወንጌል 1
19፤ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
20፤ መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
21፤ እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም፡ አለ። #ነቢዩ_ነህን? አይደለሁም፡ ብሎ መለሰ።


ዮሐንስ እርሱ ክርስቶስ እንዳልሆነ መሰከረላቸው በኋላም ዮሐንስ ኤሊያስ እንዳልሆነም መሰከረላቸው ግን ቀጣይ ደግሞ "ነቢዩ ነህን?" ብለው ጠይቀውታል.. ልብ በሉ "ነቢይ ነህን?" አላሉትም ይልቁንም "ነቢዩ ነህን" ነው ያሉት እርሱም "አይደለሁም" አለ..

ጥያቄው፡
"ነቢዩ ነህን?" ሲሉ ማንን እያሰቡ ነው..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ ጋይስ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁና መልሱ ከዛም ይህንን ጥያቄ ከየት እንዳመጣሁት እስቲ ገምቱ..


1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንት የብሉይ እና ስንት የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍትን ይዟል..??


2. አብዛኛውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት የጻፈው ማን ነው..??

ይህ ከምን ፈተና ላይ የተገኘ እንደሆነ እስቲ ገምቱ በዛውም😝😝

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዲያቆን ሄኖኬ ለገና ያሰበውን መንፈሳዊ መርሃ ግብር አየሁ እና የምር ይመቸው.. ሄኖኬ ምርጥ ሰው ነው.. ጌታ ይርዳው.. መዝሙር እና ጸሎቱንም እናለማመዳችሁዋለን ቀኑ እስኪደርስ ብለዋል እና ልንቀውጠው ነው..

የምር እቺ ቀን የማትረሳ የምስጋና ቀን ነው የምትሆነው.. እግዚአብሔር ይርዳቸው ይርዳን

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዮኒ በሚም ተመልሷል.. እሱ ነው የሰራው😁😁

ስንቱን ዘለን ዕቅበተ እምነት ላይ እንዳረፍን😁😁ይሄ ዕቅበተ እምነት አይደለም የምር😁😁


@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ክርስትና ትክክለኛ ሃይማኖት መሆኑን በምን እናውቃለን..??


https://vm.tiktok.com/ZMjm633Bx/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንድ ሰዎች ግን ወደ ወላዲተ አምላክ ስንጠጋ "ኢየሱስን ከለለችባችሁ" ሲሉን ያስገርማል..


ወላዲተ አምላክ እኮ ወደ ልጇ ትጸልይልህና አንተን ደግሞ እንዲህ ትልሃለች : "እርሱ የሚልህን አድርግ" [ልክ እንደ ዮሐ 2ቱ]

ወደ ድንግል በቀረብክ ቁጥር እሷ ደግሞ እየጸለየችልህ "እርሱ የሚልህን አድርግ" ካለችህ እርሷን መቅረብ አብዝቶ ኢየሱስን መቅረብ ነው ማለት ነው.. ኢየሱስን እንድትሰማ ከሆነ የምታደርግህ ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋለህ

እማ በልጅሽ በኢየሱስ መንገድ እንድንሄድ እርጂን

መልካም የወላዲተ አምላክ ቀን

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወደ ኢትዮጵያ መጣ ከተባለው የፕሮቴስታንት "ነቢይ" ጋር ተያይዞ የኔ እይታ

https://vm.tiktok.com/ZMj5yqjNQ/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በነገራችን ላይ መልስ ከመለሳችሁ በሁዋላ.. ከላይ በቀኝ በኩል የአምፖል ምልክቱን እየተጫናቹ አንብቡ ትንሽዬ ማብራሪያ አለችው

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ፈተና ዝም ብዬ ትምህርት እንዲሆን ብቻ ብዬ ሳወጣ


13. ለመዳናችን ምክንያት የሆነው የቱ ነው?

  ሀ. አብ ዓለምን እንዲሁ ከመውደዱ የተነሳ አንድያ ልጁ ኢየሱስን መላኩ

  ለ. ወልድ ስለ ዓለም ሁሉ መዳን ባህሪያችንን መንሳቱ እናም የማዳንን ሥራ መስራቱ

  ሐ. መንፈስ ቅዱስ በወልድ የተሠራውን የማዳን ሥራ በእኛ ላይ ማድረጉ

  መ. ሁሉም መሠረታዊ የመዳናችን ምክንያቶች ናቸው።

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መልስ(ክፍል 1) 1ጢሞ 2:15 ላይ ለተሰጠው ትችት


https://vm.tiktok.com/ZMjfJbJdB/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንድ ጉዋደኛዬ ከፍቅረኛው ጋር ተጣልቶ ነገር.. ሁለቱንም አወራሁዋቸው ምናምን.. እና ይኸው ታርቀው ፊት ለፊቴ እንዴት እንደ ሚጃጃሉብኝ😏😭

ጭራሽ እኮ እኔን ላሽ ብለው ብቻቸውን ሆኑ🤭🤭 ከተለየሁዋቸው በሁዋላ ለሆነ ጉዳይ ስደውል ራሱ አያነሳም😭😭

እና የእኔንና የእነሱን ሁኔታ አሁን ላይ አስቡት😭😭 ምነው ባልስታረቅሁዋቸውም አልኩ.. ሎል

በኔ የደረሳ በእናንተ ይድረስ😏😏

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የድሮውቹ ክርስቲያኖች እና የእኛ ልዩነት የእውቀት ብቻ ሳይሆን የመከራከሪያ ርእስም ጭምር ነው ልዩነቱ..

አይተኸዋል የክርክሩን ርእስ..?? "ባርቶስ ላይ ያሉት ኅቡእ ስሞች" ይልሃል😁😁 የምርህን ነው ብሮ..?? የሆነ ገድል ወይም ድርሳን ላይ እንዲህ ይላል ይልሃል😁😁 ይመቸው..

ከዛ ማይ ክርስቲያን ብራዘርስ እንደ ርእስ ይይዙታል.. ሎል.. ያው መቃወም አልችልም በእርግጥ😁😁

እነዚህን ርእሶች እያነሳህ እድሜህን የምትጨርሰው ፕሮቴስታንት ወንድሜ.. በስህተት "ጥምቀት ለድኅነት አያስፈልግም" በሚል ቪዲዮ እንዳትሰራ.. "ቅዱስ ቁርባን የጌታ ሥጋና ደም አይደለም" ለማለት እንዳትደፍር.. "ድንግል ማርያም የአምላክ እናት አይደለችም" ለማለት እንዳታስበው..

ይህንን እና የመሳሰሉትን ለማንሳት ስትሞክር ያኔ ጭራሽ አስበው ምን ያህል ዋጋህን እንደሚሰጡህ🤪🤪 የምር ግን ያው እነዚህ የማንደራደርባቸው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ናቸው.. እና የመከራከሪያ ርእሶቻችን እነዚህ ቢሆኑ ፒስ ነበር

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"መላእክት ከምን እንደተፈጠሩ እኛ አናውቅም"

ዲያቆን ያረጋል


ግላዊ ምልከታስ ምንድር ነው..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዮው.. ገና ላስመርጣችሁ pol ሳላደርግ ብዙ ኮመንት ሰጣችሁና ያው የአብዛኛዎቻችሁን አመለካከት አይቼበታለሁ.. እና ያው ከኔ አሳብ ጋር የተመሳሰለ ነው ምናልባት እዚ ብዙ ጊዜም አብረን ስለቆየን ለመግባባት አንቸገርም መሰለኝ.. ስለዛ ፖሉን ተውኩት

ብቻ ግን እስቲ የጠራውን የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለሁሉም ክርስቲያኖች ማዳረስ ላይ ብቻ ትኩረት እናደርጋለን.. በዚህ መካከል አስተምህሮዋችን ያልሆኑትንም የምናይ ይሆናል..

ጌታ ሁላችንን የእርሱን ትምህርት እናውቅና በእምነትም ከፍ እንል ዘንድ ይርዳን።

ሰላም እደሩልኝ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"ነቢዩ ነህን..??"

በአጭሩ ሙሴ የተናገረው ነገር አለ እንዲህ ሲል:

ኦሪት ዘዳግም 18
16፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ #ነቢይ_ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።


ይህንን ነቢይ ይጠብቃሉ አይሁዳውያን.. እናም ይህ "ነቢይ" የተባለው ደግሞ ይመጣ ዘንድ ያለው መሲሑ(ክርስቶስ) ራሱ ነው.. ጴጥሮስ በቤተ መቅደስ እንዲህ ሲል እንደ መሰከረ:

የሐዋርያት ሥራ 3
22፤ ሙሴም ለአባቶች፦ ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።
23፤ ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች፡ አለ።
24፤ ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ 👉ስለዚህ ወራት ተናገሩ

ኢየሱስ ነቢይ ነውን..?? ነቢይ ማለት ከእግዚአብሔር ሰምቶ የሚናገር እንዲሁም ሰውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምር መምህር እንደማለት ነው.. ጌታ ኢየሱስ ደግሞ በባህሪው ከአብ ጋር አንድ ሆኖ የአብ ልጁ እንደ መሆኑ በአብ ዘንድ ያለውን ገልጦታል ተናግሮታል.. ከዚህ አንጻር ነቢይ ሊባል ይችላል..ከነቢያት እንደ አንዱ ሳይሆን የባህሪ ነቢይ ነው እርሱ..


ታድያ ግን መጥምቁ ዮሐንስን የጠየቁት አይሁዳውያን ሙሴ የተናገረለት ነቢይ ከመሲሑ ሌላ ስለመሰላቸው "መሲሑ ነህን..??" ብለው ከጠየቁና ከተመለሰላቸውም በሁዋላ "ነቢዩ ነህን..??" ብለው ጠይቀውታል..

እና እንዲያ ነው እላችሁዋለሁ..

ጌታ ኢየሱስም ሲናገር እንዲህ አለ:

የዮሐንስ ወንጌል 5
46፤ ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ነገ እሁድ ነው.. በጠዋት ወደ ቅዳሴ ልንሄድ ነው😃😃

ነገ ቅዳሴ ላይ የሚነበበውን የጳውሎስን መልእክት እና የወንጌል ክፍል ይዛችሁ ጠዋት አካባቢ እሱ ላይ አውሩበት

ለአሁን ግን እስቲ ደስ ያላችሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ኮመንት አድርጉ እና ሁላችሁም ሌላው የለጠፈውን እያነበባችሁ እንቅልፋችሁንም አሳምሩ.. ከቻላችሁ የተረጋጋ መዝሙር እየሰማችሁ አንብቡ ምናምን

የኔን እዚው ላስቀምጥ፡
👇👇👇

"በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ፡
እግዚአብሔር ይመስገን። "
[መዝሙር 31: 21]

እግዚአብሔር አባታችን.. እንወድሃለን አባ.. ተመስገን..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ላይቭ ነን🤪🤪

https://vm.tiktok.com/ZMjhwNtHk/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወኬ ወኬ.. ዛሬ ደግሞ ሁለት ወንድሞቼ ማለትም ልደት እና ዲያቆን አማን(ቲክቶክ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚሰጡት) አዲስ የቴሌግራም ቻናል ስለከፈቱ እናስተዋውቅላቸዋለን🤪🤪

እስቲ ሂዱና ሰርፕራይዝ አድርጓቸው😁😁

ዲያቆን አማን 👉 @house_of_immanuel


ልደተ-ቃል 👉 @christian_answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኤዲቲንጉዋን ለጊዜው እርሷት😁😁 ቀጣይ እናሻሽለዋለን

https://vm.tiktok.com/ZMjrC43hq/

Читать полностью…
Subscribe to a channel