እስቲ ልጠይቃችሁ..
ጸሎት ስትጸልዩ ከጸሎት መጽሐፍ ውጪ የራሳችሁን ጸሎት መጸለይ አይቻልም..??
አንድ ሰው "የእኛ ጸሎት ያው ሥጋዊ ስለሆነ" በሚለው ከቻልን ዳዊቱን መጸለይ ነው እንጂ የራሳችንን ጸሎት መጸለይ አይቻልም ቢል እንዴት ታስባላችሁ..??
አንድ ፕሮቴስታንት ወዳጄ ወደ ክርስትና(ቤተ ክርስቲያን) ሊመለስ ሊጠመቅ እንደሚፈልግ አሳወቀኝ..
ግን አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ.. ይህም የኦርቶዶስ ወጣቶች community አለ ወይ..?? የሚል ነው..
ብዙውን ጊዜ ከፕሮቴስታንት ሲመለሱ የሚገጥመው ችግር ይህ ነው ሰው ራሱ ማጣት.. ቢያንስ በ 15 ቀን ምናምን እየተገናኙ ጸልየው የእግዚአብሔርን ቃል ተማምረው የሚለያዩ አይነት ግሩፖች ሊኖሩ ያስፈልጋል..
ከዚህ ቀደም አቡም @AbuNak ይህንን ነገር ሲለኝ ነበር እና ገና ያልተጠመቁ ሰዎች ካሉ እንዲሁም ሌሎችም ብዙም ሳንበዛ በቃ የሆነ ኅብረት ይኑረን..
እስቲ ምን አይነት ግሩፕ ሊኖረን እንደሚችል አስቡና ላይቭ ገብተን እናወራበታለን አሳባችህን እንሰማለን
ቆይ የቅዱሳንን ገድል(ታሪክ) በፊልም ሳይ ለምንድን ነው መንኩስ መንኩስ የሚለኝ😭😭
አይ ግን የሆነ ባንመነኩስም ክርስቶስን በደንብ ያስናፍቁናል እና እዩ ለማለት ያህል ነው
መልካም አዳር..
ነገ ከቅዳሴ መልስ እንገናኝ
“አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን"
እቺን ስትጸልዩ ጭራሽ ፈተና ወደኔ አይምጣ በሚል ሳይሆን እዛ ፈተና ውስጥ ደግሞ አልውደቅ አቅምን ስጠኝ እያላችሁ እያሰባችሁ..
ለምሳሌ ፈተናው ዝሙት አይነት ከሆነ ወደ ዝሙት አታግባን ነገር ማለት ነው..
ስለዛ ቀጣይም የምንለው "ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ" አይደል.. እውነተኛ ክርስቲያን በራሱ የሚተማመን ሳይሆን መታመኑን በአምላኩ በእግዚአብሔር ያደረገ ነው.. ስለዚህ እግዚአብሔርም አቅም ይሆነዋል
ለመኝታም ወደ አልጋህ ስትወጣ የምታስበውን ምረጥ😉
በመኝታዬም አስብሃለሁ፥
በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
[መዝ 63:6]
መልካም አዳር
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ = hermeneutical anarchy
ማዕከላዊ ተርጓሚ አካል በሌለበት(state of hermeneutical anarchy) በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የምትመራ አንድ ቤተክርስትያን መመስረት ሀሳባዊ እንጂ ተግባራዊ አይደለም። ይህ ማለት ልክ ሕገ መንግስትን ይዞ ሶስቱ የመንግስት አካላት አያስፈገልኝም በራሴ ተረድቼ እመራለው እንደማለት ነው(ሕግ የለም ከማለት ምንም አይለይልም) ። በተግባር ደረጃ የክርስትያኖችን ህብረት ያወድማል እንጂ አያለማም ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ስፍር ቁጥር የሌለው እርስ በእርሳቸው የማይስማሙት የፕሮቴስታንት ቡድኖች ናቸው ። Doctrine ንም ቢሆን ተለዋወጭ ና ብዙ በሆነው በሰው የግል አስተያየት ላይ የተመሰረተ ስላደረገው ምንም ዶክትሪን ሃይማኖት ስለመሆኑ ያለን ፍጹም እርግጠኝነት(certitude) አጥፍቶታል ።
hermeneutical anarchyን ተክትሎ በጎራ መከፋፈል የማይቀር ነው ፤ የየሰዉ የግል አረዳድ ከሌላው ስለሚለይ ተቀራራቢ አረዳድ ያላቸው አንድ ቡድን ይሆናሉ ። ይህም በተራው የመጋቢነትን ድርሻ ያቀለዋል(undermines Pastoral authority) ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ለመምህራን እንድንታዘዝ ቢያዘንም ከሀሰተኛ ነብያት እንድንጠነቀቅ እና መንፈስን ሁሉ እንድንመረምር ይነግረናል ስለዚህ ለመምህራን ምንታዘዘው እውነተኞች እስክሆኑ ድረስ ነው ። እውነተኛ መምህር መሆኑ ታድያ በምን ይታወቃል? ለመጽሐፍ ቅዱስ ባለን የግል አረዳድ የምንመራ ከሆነ እውነተኛ መምህር የምንለው ከግል አረዳዳችን ጋር ተስማምቶ ያገኘነውን ሊሆን ነው ። አሁንም ደግሞ የእያንዳንዱ የግል አረዳድ ከሌላው ስለሚለይ ሁሉም በየራሱ የፈለገውን ወደ ሚያደርግበት ቤተክርስትያናዊ ቀውስ ይከተናል ።
ይህ እሳቤ በቤተክርስትያን አንድነትን የሚያጠፋ ፣ መከፋፈልን የሚያመጣ ፣ መምህርነትን የሚያቀል ፣ ዶግማ ቢስ የሚያደርግ የቤተክርስትያናዊ ቀውስ ሁሉ ምንጭ (mother of all ecclesiastical chaos) ነው ። ክርስቶስ አንድ እንሆን ዘንድ ያቀረበውን ጥሪ እና ጸሎት[ዮሐ 17፡21] ከንቱ ያደረገ ሰይጣናዊ ሀሳብ ነው!
"ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም " 2 ጴጥ 1:20
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከመልእክታት ከተነበበው
"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።"
[1ጴጥ 4:3]
በአሕዛብ ፈቃድ ለምንመላለስ ጌታ ብርታቱን ይስጠን.. እስካሁን ስንበድል የኖርንበት ዘመን ይበቃናል ብለን ቀሪውን ዘመናችንን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር እንኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ያስጨክነን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ዛሬም ልጠይቃችሁ እስቲ.. ያው እኔ የምሰጠውን ተከታታይ የክርስትና ትምህርት የምትማሩ ልጆች ከትንሽ ማብራሪያ ጋር አድርጋችሁ መልሱ እስቲ
2. የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በቅብብሎሽ እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥል ሲሆን፤ የቅብብሎሹ አስጀማሪ ማን ነው?
ሀ. ነቢያት ለ. ሐዋርያት
ሐ. ሊቃውንት መ. መልስ የለም
አንድ እስላም ልጅ የኔ ቪዲዮ ላይ ሪያክት ለማድረግ እንደ ሞከረ ተመለከትኩ.. እና "መካከለኛ" የሚለውን ቃል ያብራራሁበት ቪዲዮ ላይ ነው ሪያክት ያደረገው.. ክፍሉ "አምላክም ሰውም" የሚል አሳብ አይገኝበትም ነው ያለው.. እውነቱን ለመናገር ለእንደነዚህ አይነት ልጆች መልስ መስጠት ብዙም አልወድም.. ግን አንድ ክርስቲያን መልስ ስጥበት ስላለኝ ምናልባት ደግሞ ክፍሉን በደንብ ለማብራራትም ምክንያት ላድርገው ብዬ ነው😁😁
እና እዝችው ጋር በአጭሩ መልሷን ጽፌ ላስቀምጥላችሁ ወይስ አጭር ቪዲዮ ቲክቶክ ላይ ይሰራላችሁ..??
ያው ኮመንት ስለዘጋሁባችሁ በሪያክሽን አሳውቁኝ
እዚሁ በጽሑፍ ይመለስ የምትሉ፡ 👍 ተጫኑ
በቲክቶክ የምትሉ፡ 👏 ተጫኑ
ኦው ደግሞ እሁድ መጣልን.. እስቲ ነገ ደግሞ ቅዳሴ ላይ የሚነበበውን የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል በደንብ ስሙና ከዚያም ግሩፕ ላይ ደግሞ አውሩበት..
መልካም አዳር እናንተ የተመታችሁ ሰዎች.. ምንም በቃ ልወዳችሁ አልቻልኩም.. ስለዛ ለእናንተ ጻፍ ጻፍ ይለኛል😭😭
የምር ግን እግዚአብሔር ይመስገን
አዳም ሁሉ ነገር ተሰጠውና አንዲት ነገር ተከለከለ.. እና ሰይጣን ደግሞ አዳም ትኩረቱን እሷ ላይ እንዲያደርግ አደረገው.. እና አዳም በተሰጡት ነገሮች ከማመስገን ይልቅ በተከለከለው ምንም ጥቅም በማይሰጠው ነገር አማራሪ ሆነ..
የኔ ተወዳጆች የምር እግዚአብሔር እኮ የሰጠን ብዙ ነው.. ጭራሽ ልጁንም ሰጠ እንጂ.. እና በትንሹም በትልቁም አናማርር.. ይልቁንም እናመስግነው እንጂ..
ሆስፒታል ነበርኩ ዛሬ የሆነ ሰው ታሞ.. በቃ ማርያምን በጣም ነው የሚከብደው ህመማቸው.. በህመም ለሚሰቃዩት ሁሉ እግዚአብሔር ፈውስን ይስጥ..
በቃ "እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን"
ወንጌል አንድምታ ላይ:
ማቴ 12፡32 ትርጓሜ
እውን "መካነ ንስሐ"(purgatory) ኦርቶዶክሳዊ ነው..?? አይደለም ይህ የካቶሊክ ትምህርት ነው.. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም እንዲህ ያለ አስተምህሮ..
አንድምታ በእጅጉ ሕይወትን በሚሰጥ እውቀት የተሞላ ድንቅ ትርጉዋሜ ነው ግን ያው አንዳንዴ እንዲህ በስህተት ሊገባ የሚችል ነገር ደግሞ ሊገኝ ይችላልና የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስለምናውቅ በስህተት እንደ ገባ(ወይም እንደተባለ) አስበን እናልፈዋለን.. ኖርማል ነው..
የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ(ሃይማኖታችን) ውስጥ ግን ምንም እንከን ሊገኝ አይችልም.. እሱን መቼም እንዳትረሱ..
@Apostolic_Answers
ሌላ ጥብስ ጥያቄ😃😃
መላእክት እና ቅዱሳን በሲዖል ያሉ ነፍሳትን[በዛ ያለ ቁጥር ያላቸውን] ያወጣሉ የሚል በአንዳንድ ገድላት ድርሳናት ውስጥ የምናያቸው ነገሮች በትምህርት ደረጃ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ..??
በትምህርት ደረጃ ካለ ከሊቃውንት አባቶች (ከጥንት እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት) ትምህርት ውስጥ ጠቅሳቹ አስረዱ
እዚህ ላይ ምንም አላልኩም ደግሞ እኔ.. ያው መረዳታችሁን ለማወቅ በዛውም እኔም እጠቀም ይሆናል በማለት ነው😊🤗
ምንኩስና
ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
[ዮሐንስ 17:15]
https://vm.tiktok.com/ZMj9dx23X/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
[ዮሐንስ 3: 36]
በልጁ በኢየሱስ ማመን ምንድር ነው..?? ይህንን ለማወቅ ከፍ ብለን የወንጌል ክፍሉን እናንብብ.. መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ይናገራል:-
የዮሐንስ ወንጌል 3
32፤ [ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው] ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
33፤ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
በኢየሱስ ማመን እንዲሁ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ብቻ ማመን ሳይሆን የእርሱን ምስክርነት ወይም የክርስቶስን ትምህርት አሜን ብሎ መቀበልም ነው..
ይህንን ስናስተውል ደግሞ ምን እንረዳለን..?? ለምሳሌ ኢየሱስ ጥምቀት ለድኅነት እንደሆነ እና ቅዱስ ቁርባንም የራሱ ሥጋና ደም እንደ ሆነ አስተምሯል.. እና ይህንን የማይቀበሉ #ሁሉ ገና የኢየሱስን ምስክር ያልተቀበሉ ወይም በኢየሱስ ያላመኑ ናቸው ማለት ነው..
አምኛለሁ ስላልክ አምነሃል ማለት አይደለም.. እምነትህ በቃሉ ሲመዘን ሃሰተኛ የማያድን እምነት ነው..
ስለዚህም በኢየሱስ ያምኑ ዘንድ እንዲህ እንላለን:
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እናላችሁ በሆነ አጋጣሚ "ጥናታዊ ጽሑፍ" እንዳዘጋጅ ተነገረኝ.. እና ርዕሱን ራሴ እንድመርጥ እድሉን ሰጥተውኛል..
"እና ምን እናድርግህ አትጨቅጭቀን" አላችሁ..?? ዲየግ አሳቤማ ጽሑፉን ከሠራሁ አይቀር ለክርስቲያን ወንድም እህቶችም ልትጠቅም የምትችል የሆነች መጽሐፍ ነገርም ማድረግ ፈለግሁ..
እና ግን ርዕስ እስቲ አስቡ😁😁
እኔ "የሰው ውድቀት" (ጥንተ አብሶ እያሉ የሚጠሩት) ላይ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካለው ጥንታዊ ነገረ ክርስቶስ አንጻር ልሠራ ነበር ያሰብሁት ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ተውኹት..
አሁን ላይ እያሰብኩ ያለሁት ምናልባት ማርቲን ሉተር(ማ ኒግ ሎል) ላይ መሥራት አስቢያለሁ.. ቴዮሎጂውን.. ከዚያም እግረ መንገዴን ከእርሱ አንጻር አሁን ያሉትን እየተስፋፉ ያሉትን ጰንጤ ዲኖሚኔሽን ቴዮሎጂን በስሱ መዳሰስ
እስቲ እናንተ የተሻለ የምትሉት ካለ ተባበሩኝ በዚህ 1 ሳምንት ውስጥ😭😭
እቺን ነገር የምታውቋት😁😁 አንዱ ጉዋደኛዬ እኮ አሁን አስታውሶኝ😁😁 አመት ሆናት.. አንዱ ፕሮቴስታንት የጸለየልኝ(የጸለየብኝ)😭😭
አስቂኝ ቢሆንም.. ግን ደግሞ አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ስንፍናችን ስላልተወን ጠብቆቱን ከእኛ ስላላነሳ.. የሚያስደንቀውን ምህረቱን በእኛ ስለሚገልጥ እናመሰግነዋለን..
አንዳንድ ሰዎች ግን ወደ ወላዲተ አምላክ ስንጠጋ "ኢየሱስን ከለለችባችሁ" ሲሉን ያስገርማል..
ወላዲተ አምላክ እኮ ወደ ልጇ ትጸልይልህና አንተን ደግሞ እንዲህ ትልሃለች : "እርሱ የሚልህን አድርግ" [ልክ እንደ ዮሐ 2ቱ]
ወደ ድንግል በቀረብክ ቁጥር እሷ ደግሞ እየጸለየችልህ "እርሱ የሚልህን አድርግ" ካለችህ እርሷን መቅረብ አብዝቶ ኢየሱስን መቅረብ ነው ማለት ነው.. ኢየሱስን እንድትሰማ ከሆነ የምታደርግህ ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋለህ
እማ በልጅሽ በኢየሱስ መንገድ እንድንሄድ እርጂን
መልካም የወላዲተ አምላክ ቀን
ፈተና ዝም ብዬ ትምህርት እንዲሆን ብቻ ብዬ ሳወጣ
13. ለመዳናችን ምክንያት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. አብ ዓለምን እንዲሁ ከመውደዱ የተነሳ አንድያ ልጁ ኢየሱስን መላኩ
ለ. ወልድ ስለ ዓለም ሁሉ መዳን ባህሪያችንን መንሳቱ እናም የማዳንን ሥራ መስራቱ
ሐ. መንፈስ ቅዱስ በወልድ የተሠራውን የማዳን ሥራ በእኛ ላይ ማድረጉ
መ. ሁሉም መሠረታዊ የመዳናችን ምክንያቶች ናቸው።
አንድ ጉዋደኛዬ ከፍቅረኛው ጋር ተጣልቶ ነገር.. ሁለቱንም አወራሁዋቸው ምናምን.. እና ይኸው ታርቀው ፊት ለፊቴ እንዴት እንደ ሚጃጃሉብኝ😏😭
ጭራሽ እኮ እኔን ላሽ ብለው ብቻቸውን ሆኑ🤭🤭 ከተለየሁዋቸው በሁዋላ ለሆነ ጉዳይ ስደውል ራሱ አያነሳም😭😭
እና የእኔንና የእነሱን ሁኔታ አሁን ላይ አስቡት😭😭 ምነው ባልስታረቅሁዋቸውም አልኩ.. ሎል
በኔ የደረሳ በእናንተ ይድረስ😏😏
የድሮውቹ ክርስቲያኖች እና የእኛ ልዩነት የእውቀት ብቻ ሳይሆን የመከራከሪያ ርእስም ጭምር ነው ልዩነቱ..
አይተኸዋል የክርክሩን ርእስ..?? "ባርቶስ ላይ ያሉት ኅቡእ ስሞች" ይልሃል😁😁 የምርህን ነው ብሮ..?? የሆነ ገድል ወይም ድርሳን ላይ እንዲህ ይላል ይልሃል😁😁 ይመቸው..
ከዛ ማይ ክርስቲያን ብራዘርስ እንደ ርእስ ይይዙታል.. ሎል.. ያው መቃወም አልችልም በእርግጥ😁😁
እነዚህን ርእሶች እያነሳህ እድሜህን የምትጨርሰው ፕሮቴስታንት ወንድሜ.. በስህተት "ጥምቀት ለድኅነት አያስፈልግም" በሚል ቪዲዮ እንዳትሰራ.. "ቅዱስ ቁርባን የጌታ ሥጋና ደም አይደለም" ለማለት እንዳትደፍር.. "ድንግል ማርያም የአምላክ እናት አይደለችም" ለማለት እንዳታስበው..
ይህንን እና የመሳሰሉትን ለማንሳት ስትሞክር ያኔ ጭራሽ አስበው ምን ያህል ዋጋህን እንደሚሰጡህ🤪🤪 የምር ግን ያው እነዚህ የማንደራደርባቸው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ናቸው.. እና የመከራከሪያ ርእሶቻችን እነዚህ ቢሆኑ ፒስ ነበር
@Apostolic_Answers
ዮው.. ገና ላስመርጣችሁ pol ሳላደርግ ብዙ ኮመንት ሰጣችሁና ያው የአብዛኛዎቻችሁን አመለካከት አይቼበታለሁ.. እና ያው ከኔ አሳብ ጋር የተመሳሰለ ነው ምናልባት እዚ ብዙ ጊዜም አብረን ስለቆየን ለመግባባት አንቸገርም መሰለኝ.. ስለዛ ፖሉን ተውኩት
ብቻ ግን እስቲ የጠራውን የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለሁሉም ክርስቲያኖች ማዳረስ ላይ ብቻ ትኩረት እናደርጋለን.. በዚህ መካከል አስተምህሮዋችን ያልሆኑትንም የምናይ ይሆናል..
ጌታ ሁላችንን የእርሱን ትምህርት እናውቅና በእምነትም ከፍ እንል ዘንድ ይርዳን።
ሰላም እደሩልኝ