አንዳንዴ የምናውቀውና የተደጋገመ ነገር ቢሆንም ነገሩ ሲነገር እንደ ማንቂያም ሊሆን ይችላል..
ለማንኛውም ምን ልል ነው.. በኃጢአት እንዳንወድቅ መርሳት የሌለብን በቃ ገና አሳቡ ሲመጣ ቅዱስ መስቀል ይዞ ልሰማህ አልችልም ማለት ነው..
አንዴ አሳቡን ከተቀበላችሁት በሃጢአት የመውደቅ እድሉ ስለሚሰፋ.. እዛው ገና አሳቡ ሲመጣ ነው አልሰማህም ማለት..
አንድ ፕሮቴስታንት ወንድሜ እንዲህ ብሎ ፌስቡክ ላይ መለጠፉን አሳዩኝ እና እንዴት ነው ነገሩ..?? "እንግዛው" እያሉ ነው.. በዋጋ ከተገዛሁ ቆየው ልበላቸው እንዴ ሎል..
በተለይ ደግሞ ጳውሎስ ፈቃዱ የተባሉ አገልጋይም አሉ ያው ታውቋቸው ይሆናል የሳቸውንም ኮመንት ሳይ መልካም ነው አስባለኝ.. የሆነ positive ነገር ስላላቸው ማለት ነው..
Paulos Fekadu Tessema ፡
አለማወቃቸውን በማሳወቅ እያገዘን ይመስለኛል። ተራ ያልደረሳቸውን በዙር ብንልካቸው እንዴት መልካም መሰለህ?
😁😁 ተጫዋች ናቸው ይመቻቸው
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ እና ለእኔም በግሌ የሚመጣልኝ ቃል..??
ብዙዎች አሁን ላይ በነቢይ ስም "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደሚሰሙ ይነግሩናል..
መልካም ይህን የእግዚአብሔርን ድምጽ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው ነው የሚቀበሉት..
ስለዛ ለእርሱ የእግዚአብሔር ቃል ሲል መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሊሆን አይችልም ይልቁንም ለእርሱም የሚመጣለት ቃልም ጭምር እንጂ..
ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ነው የሚለው አያስኬድም ቢያንስ ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ:
1ኛ ቆሮንቶስ 10
5፤ እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።
ጳውሎስ ከላይ ጀምሮ እስራኤላውያን ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ እንደተጠመቁ እናም መንፈሳዊ መብልና መጠጥንም እንደተመገቡ ይናገርና ግን ደግሞ ከፍጻሜው ሳይደርሱ ብዙዎች በኃጢአት በምድረ በዳ እንደ ወደቁ.. እግዚአብሔርም በሚበዙት ደስ እንዳልተሰኘ ይናገራል..
ይህ ሁሉ ደግሞ ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን ልጆች ምሳሌ ይሆን ዘንድ እንደተፃፈ ይናገራል:
1ኛ ቆሮንቶስ 10
6፤ እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ 👉ምሳሌ ሆነልን።
11፤ ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ 👉እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን 👉ሊገሥጸን ተጻፈ።
እንግዲህ እኛም እውነተኛውን ሙሴን ኢየሱስን እንተባበር ዘንድ ከተጠመቅን.. መንፈሳዊን መብል ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከተቀበልን.. ሁሌም የሚከተለንን ኢየሱስን ከያዝን በሁዋላ ጥሪያችንን ሳናጸና በኃጢአት ተሰነከክለን አንውደቅ
2ኛ ጴጥሮስ 1
10፤ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት ውስጥ
"በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።"
[ኤፌ 6:10]
ከላይ ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ወታደራዊ በሆነ መልኩ ይናገራቸውና : "በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።" ይላል.. ምክንያቱም ክርስቲያኖች የምርም ወታደሮች(ተዋጊዎች) ናቸውና.. ይህም ደግሞ መጋደላቸው ከደምና ሥጋ ጋር ሳይሆን ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር እንደ ሆነ ቀጠል አድርጎ እዛው ክፍል ላይ ይነግራቸዋል..
ክርስቲያን ከሆንክ በቃ ውግያ ውስጥ ነህ.. ምናልባት ምንም ውግያ እያየህ ካልሆነ እጅ ሰጥተህ ተማርከህ ይሆናል..
አንድ ወታደር ሊዋጋ ሲወጣ ለመርታት በሚገባ ሊታጠቅ እንዲሁም ንቃት ሊኖረው ይገባዋል.. ውግያው ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር ሲሆን ደግሞ እኚህ ሰራዊት የብዙ አመት ልምድ ስላላቸው(ቢያንስ የ7000 አመት) የእነርሱን ጦር የሚከላከል እንዲሁም ደግሞ የሚያጠቃ ሁነኛ የሆነ ትጥቅ ያስፈልግሃል..
ኢየሱስ: ጌታችን ኢየሱስ የዲያቢሎስን ሽንገላ የምንቃወምበት.. መልሰንም ደግሞ የምናጠቃበት ተዋጊያችን ነው.. ከእኛ የሚጠበቀው ይህንን ኢየሱስን መያዝ ነው.. እንዲዋጋልንም መፍቀድ ነው..
ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል ወይም መልእክት መያዝ.. የእርሱን መንገድ እንድንከተል ያግዘናል.. እንዲሁም በእምነት ሆኖ መጸለይ..
ሁሌም ግን የነቃን እንሁን.. ለምንም አይነት ዲያቢሎሳዊ ወይም ሥጋዊ ሽንገላ(የሃጢአት አሳብ) እድል አንስጥ
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እኔኮ የሚገርመኝ ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁ..?? ያው ዛሬ ብዙ ተገረምክብን እንዳትሉኝ እንጂ ሎል
ጌታ ኢየሱስ "መንፈስ ቅዱስ ይመጣል" ብሎ ተናገረ.. እና መጥቷልም..
ግን ደግሞ ሞንታነስ የሚባል ሰው ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ የተባለው እሱ እንደሆነ አድርጎ ራሱን አቀረበ😁😁 ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ማኒ የተባለም ሰው እንዲሁ ይመጣል የተባለው መንፈስ ቅዱስ እሱን እንደ ሆነ አስመስሎ ብቅ አለ 😁😁
በኋላ ደግሞ ሙሃመድ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተነገሩትን ለሱ የተነገሩ አስመስሎ መጣ🤭🤭
ሁሉም ግን የመቻቸው እውነተኛው መንፈስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለዘላለም ይኖር ዘንድ ወርዷል ይህች በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ ቤተ ክርስቲያንም ከላይ ያሉትን አንዳቸውንም አልተቀበለቻቸውም.. የመንፈስ ቅዱስ ጠላቶችም ናቸው።
@Apostolic_Answers
እስቲ ልጠይቃችሁ..
ጸሎት ስትጸልዩ ከጸሎት መጽሐፍ ውጪ የራሳችሁን ጸሎት መጸለይ አይቻልም..??
አንድ ሰው "የእኛ ጸሎት ያው ሥጋዊ ስለሆነ" በሚለው ከቻልን ዳዊቱን መጸለይ ነው እንጂ የራሳችንን ጸሎት መጸለይ አይቻልም ቢል እንዴት ታስባላችሁ..??
አንድ ፕሮቴስታንት ወዳጄ ወደ ክርስትና(ቤተ ክርስቲያን) ሊመለስ ሊጠመቅ እንደሚፈልግ አሳወቀኝ..
ግን አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ.. ይህም የኦርቶዶስ ወጣቶች community አለ ወይ..?? የሚል ነው..
ብዙውን ጊዜ ከፕሮቴስታንት ሲመለሱ የሚገጥመው ችግር ይህ ነው ሰው ራሱ ማጣት.. ቢያንስ በ 15 ቀን ምናምን እየተገናኙ ጸልየው የእግዚአብሔርን ቃል ተማምረው የሚለያዩ አይነት ግሩፖች ሊኖሩ ያስፈልጋል..
ከዚህ ቀደም አቡም @AbuNak ይህንን ነገር ሲለኝ ነበር እና ገና ያልተጠመቁ ሰዎች ካሉ እንዲሁም ሌሎችም ብዙም ሳንበዛ በቃ የሆነ ኅብረት ይኑረን..
እስቲ ምን አይነት ግሩፕ ሊኖረን እንደሚችል አስቡና ላይቭ ገብተን እናወራበታለን አሳባችህን እንሰማለን
ቆይ የቅዱሳንን ገድል(ታሪክ) በፊልም ሳይ ለምንድን ነው መንኩስ መንኩስ የሚለኝ😭😭
አይ ግን የሆነ ባንመነኩስም ክርስቶስን በደንብ ያስናፍቁናል እና እዩ ለማለት ያህል ነው
መልካም አዳር..
ነገ ከቅዳሴ መልስ እንገናኝ
“አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን"
እቺን ስትጸልዩ ጭራሽ ፈተና ወደኔ አይምጣ በሚል ሳይሆን እዛ ፈተና ውስጥ ደግሞ አልውደቅ አቅምን ስጠኝ እያላችሁ እያሰባችሁ..
ለምሳሌ ፈተናው ዝሙት አይነት ከሆነ ወደ ዝሙት አታግባን ነገር ማለት ነው..
ስለዛ ቀጣይም የምንለው "ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ" አይደል.. እውነተኛ ክርስቲያን በራሱ የሚተማመን ሳይሆን መታመኑን በአምላኩ በእግዚአብሔር ያደረገ ነው.. ስለዚህ እግዚአብሔርም አቅም ይሆነዋል
ለመኝታም ወደ አልጋህ ስትወጣ የምታስበውን ምረጥ😉
በመኝታዬም አስብሃለሁ፥
በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
[መዝ 63:6]
መልካም አዳር
ሰላም ለእናንተ ይሁን
ሐዋርያዊ መልሶች ተከታታይ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ዙር 3 ሊጀምር ነው
መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ፎርሙን ሞልታችሁ submit ስትሉት የሚመጣላችሁን የቴሌግራም ሊንክ በመጫን ግቡ
👇👇👇
https://forms.gle/5dC2px1dD7LJxwsv7
👉🏿የውርስ ኃጢአት(original sin)
👉🏿እመቤታችን ከውርስ ኃጢአት ከማሕጸን ጀምሮ ተጠብቃለች የሚለው (immaculate conception)
ዲን ያረጋል
ይህ የአሣ ቅርጽ ጥንት ላይ አባቶቻችን እንደ አርማ ይጠቀሙበት ነበር..
ቅዱስ ቁርባንን የሚያሳይ እንደሆነም ይነገርለታል.. በዋናነት ግን አሣ በግሪክ ἰχθύς (ኢክቱስ) ይባላል.. ከላይ የአሣ ቅርጽ ውስጥ ያሉት ፊደላት በ capital letters ተጽፈው ነው ἰχθύς የሚለው።
እና ἰχθύς የሚለውን ደግሞ ፊደላቱን እንዲህ ይተነትኗቸዋል፡
Ἰ - Ἰησοῦς - ኢየሱስ
Χ - Χρῑστός - ክርስቶስ
Θ - Θεοῦ - የእግዚአብሔር
Y - Yἱός - ልጅ
Σ - Σωτήρ - አዳኝ
የሻወር tip
ሻወር ስትወስዱ መዝሙር ከፍታችሁ ይሁን.. በተለይ የንስሐ መዝሙር..
በቃ ደስ ይላል ግድ ነው😉
የሚጠቅመውም ሰው ይኖር ይሆናል ይሄ ቲፕ🤪🤪
በትግራይ ያሉ ወንድም እህቶቻችን እናት አባቶቻችን ሃዘን ላይ ናቸው አ..
ጌታ እንደው ያረፉ የወንድም እህቶቻችንን ነፍስ ሁሉ ይማር.. ለእናቶችና ለሌሎችም መጽናናቱን ይስጥልን.. ስንጸልይ እናስባቸው..
ስልኬን ስጠቀም ብዙ ጊዜ የሚገርመኝ ነገርን ልንገራችሁ..
እያየሁት ቻርጁ ይቀንሳል እና ቻርጅ ማድረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ እና ቻርጀር መሰኪያውም ሩቄ አይደለም ግን "አደርገዋለሁ ቆይ" እያልኩ እዘናጋና ብዙ ጊዜ እጄ ላይ ሆኖ መጨረሻዋን አጋጣሚ ሳላይ ይዘጋል..
ኃጢአት እናደርጋለን እና ደግሞ ንስሐ መግባት እንዳለብን እናውቃለን.. እና ንስሐ መግባት የሚያስቸግርም ነገር አይደለም.. ግን ደግሞ "ቆይ እገባለሁ" እያልን እንዘናጋለን.. ከዚያም ሳናስበው ምናልባት ያልቅልናል(እንሞታለን)..
እያንዳንዳችን በጌታ ፍርድ ወንበር ፊት እንገለጣለንና አንዘናጋ.. መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ እንግባ ወደ ቅዱስ ምስጢርም(ቁርባን) እንቅረብ።
@Apostolic_Answers
ሌላ ጥብስ ጥያቄ😃😃
መላእክት እና ቅዱሳን በሲዖል ያሉ ነፍሳትን[በዛ ያለ ቁጥር ያላቸውን] ያወጣሉ የሚል በአንዳንድ ገድላት ድርሳናት ውስጥ የምናያቸው ነገሮች በትምህርት ደረጃ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ..??
በትምህርት ደረጃ ካለ ከሊቃውንት አባቶች (ከጥንት እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት) ትምህርት ውስጥ ጠቅሳቹ አስረዱ
እዚህ ላይ ምንም አላልኩም ደግሞ እኔ.. ያው መረዳታችሁን ለማወቅ በዛውም እኔም እጠቀም ይሆናል በማለት ነው😊🤗
ምንኩስና
ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
[ዮሐንስ 17:15]
https://vm.tiktok.com/ZMj9dx23X/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
[ዮሐንስ 3: 36]
በልጁ በኢየሱስ ማመን ምንድር ነው..?? ይህንን ለማወቅ ከፍ ብለን የወንጌል ክፍሉን እናንብብ.. መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ይናገራል:-
የዮሐንስ ወንጌል 3
32፤ [ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው] ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
33፤ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
በኢየሱስ ማመን እንዲሁ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ብቻ ማመን ሳይሆን የእርሱን ምስክርነት ወይም የክርስቶስን ትምህርት አሜን ብሎ መቀበልም ነው..
ይህንን ስናስተውል ደግሞ ምን እንረዳለን..?? ለምሳሌ ኢየሱስ ጥምቀት ለድኅነት እንደሆነ እና ቅዱስ ቁርባንም የራሱ ሥጋና ደም እንደ ሆነ አስተምሯል.. እና ይህንን የማይቀበሉ #ሁሉ ገና የኢየሱስን ምስክር ያልተቀበሉ ወይም በኢየሱስ ያላመኑ ናቸው ማለት ነው..
አምኛለሁ ስላልክ አምነሃል ማለት አይደለም.. እምነትህ በቃሉ ሲመዘን ሃሰተኛ የማያድን እምነት ነው..
ስለዚህም በኢየሱስ ያምኑ ዘንድ እንዲህ እንላለን:
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እናላችሁ በሆነ አጋጣሚ "ጥናታዊ ጽሑፍ" እንዳዘጋጅ ተነገረኝ.. እና ርዕሱን ራሴ እንድመርጥ እድሉን ሰጥተውኛል..
"እና ምን እናድርግህ አትጨቅጭቀን" አላችሁ..?? ዲየግ አሳቤማ ጽሑፉን ከሠራሁ አይቀር ለክርስቲያን ወንድም እህቶችም ልትጠቅም የምትችል የሆነች መጽሐፍ ነገርም ማድረግ ፈለግሁ..
እና ግን ርዕስ እስቲ አስቡ😁😁
እኔ "የሰው ውድቀት" (ጥንተ አብሶ እያሉ የሚጠሩት) ላይ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካለው ጥንታዊ ነገረ ክርስቶስ አንጻር ልሠራ ነበር ያሰብሁት ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ተውኹት..
አሁን ላይ እያሰብኩ ያለሁት ምናልባት ማርቲን ሉተር(ማ ኒግ ሎል) ላይ መሥራት አስቢያለሁ.. ቴዮሎጂውን.. ከዚያም እግረ መንገዴን ከእርሱ አንጻር አሁን ያሉትን እየተስፋፉ ያሉትን ጰንጤ ዲኖሚኔሽን ቴዮሎጂን በስሱ መዳሰስ
እስቲ እናንተ የተሻለ የምትሉት ካለ ተባበሩኝ በዚህ 1 ሳምንት ውስጥ😭😭
እቺን ነገር የምታውቋት😁😁 አንዱ ጉዋደኛዬ እኮ አሁን አስታውሶኝ😁😁 አመት ሆናት.. አንዱ ፕሮቴስታንት የጸለየልኝ(የጸለየብኝ)😭😭
አስቂኝ ቢሆንም.. ግን ደግሞ አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ስንፍናችን ስላልተወን ጠብቆቱን ከእኛ ስላላነሳ.. የሚያስደንቀውን ምህረቱን በእኛ ስለሚገልጥ እናመሰግነዋለን..