በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ወዳጆቼ እባካችሁን እባካችሁን.. ስልኬ ላይ ካርድ የምትልኩ.. አመሰግናለሁ ግን እባክህን ከዚህ ድርጊትህ ተቆጠብ😁😁
የድምጽም የኢንተርኔትም የዓመት ያልተገደበ(unlimited) ጥቅል ስላለኝ ምንም አይጠቅምም መላካችሁ..
ስልኬ ላይ ማታ የገባ ካርድ አለ ለዛ ነው የምጽፈው.. ያው ላኪው ማን እንደሆነ ስላላወቅሁ እዚሁ ተናገርሁ
አሁን ላይ እውነተኛ እስራኤላውያን ማን ናቸው..??
https://vm.tiktok.com/ZMjcvWq24/
ተከታታይ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ
ምዝገባ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነው.. ትምህርቱ ነገ ወይም ቅዳሜ ይጀመራል..
ያልተመዘገባችሁ ከሥር ባለው ሊንክ ተመዝገቡና.. ሞልታችሁ ስትጨርሱ እዛው ላይ በሚያመጣላችሁ የቴሌግራም ሊንክ ግቡ
https://forms.gle/5dC2px1dD7LJxwsv7
አንዳንዴ የምናውቀውና የተደጋገመ ነገር ቢሆንም ነገሩ ሲነገር እንደ ማንቂያም ሊሆን ይችላል..
ለማንኛውም ምን ልል ነው.. በኃጢአት እንዳንወድቅ መርሳት የሌለብን በቃ ገና አሳቡ ሲመጣ ቅዱስ መስቀል ይዞ ልሰማህ አልችልም ማለት ነው..
አንዴ አሳቡን ከተቀበላችሁት በሃጢአት የመውደቅ እድሉ ስለሚሰፋ.. እዛው ገና አሳቡ ሲመጣ ነው አልሰማህም ማለት..
አንድ ፕሮቴስታንት ወንድሜ እንዲህ ብሎ ፌስቡክ ላይ መለጠፉን አሳዩኝ እና እንዴት ነው ነገሩ..?? "እንግዛው" እያሉ ነው.. በዋጋ ከተገዛሁ ቆየው ልበላቸው እንዴ ሎል..
በተለይ ደግሞ ጳውሎስ ፈቃዱ የተባሉ አገልጋይም አሉ ያው ታውቋቸው ይሆናል የሳቸውንም ኮመንት ሳይ መልካም ነው አስባለኝ.. የሆነ positive ነገር ስላላቸው ማለት ነው..
Paulos Fekadu Tessema ፡
አለማወቃቸውን በማሳወቅ እያገዘን ይመስለኛል። ተራ ያልደረሳቸውን በዙር ብንልካቸው እንዴት መልካም መሰለህ?
😁😁 ተጫዋች ናቸው ይመቻቸው
"መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ እና ለእኔም በግሌ የሚመጣልኝ ቃል..??
ብዙዎች አሁን ላይ በነቢይ ስም "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደሚሰሙ ይነግሩናል..
መልካም ይህን የእግዚአብሔርን ድምጽ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው ነው የሚቀበሉት..
ስለዛ ለእርሱ የእግዚአብሔር ቃል ሲል መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሊሆን አይችልም ይልቁንም ለእርሱም የሚመጣለት ቃልም ጭምር እንጂ..
ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ነው የሚለው አያስኬድም ቢያንስ ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች
"የሞቱ ሰዎች ይማልዳሉ የሚለውን ከየት አመጣችሁት..??"
https://vm.tiktok.com/ZMjsRPjWL/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ:
1ኛ ቆሮንቶስ 10
5፤ እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።
ጳውሎስ ከላይ ጀምሮ እስራኤላውያን ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ እንደተጠመቁ እናም መንፈሳዊ መብልና መጠጥንም እንደተመገቡ ይናገርና ግን ደግሞ ከፍጻሜው ሳይደርሱ ብዙዎች በኃጢአት በምድረ በዳ እንደ ወደቁ.. እግዚአብሔርም በሚበዙት ደስ እንዳልተሰኘ ይናገራል..
ይህ ሁሉ ደግሞ ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን ልጆች ምሳሌ ይሆን ዘንድ እንደተፃፈ ይናገራል:
1ኛ ቆሮንቶስ 10
6፤ እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ 👉ምሳሌ ሆነልን።
11፤ ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ 👉እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን 👉ሊገሥጸን ተጻፈ።
እንግዲህ እኛም እውነተኛውን ሙሴን ኢየሱስን እንተባበር ዘንድ ከተጠመቅን.. መንፈሳዊን መብል ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከተቀበልን.. ሁሌም የሚከተለንን ኢየሱስን ከያዝን በሁዋላ ጥሪያችንን ሳናጸና በኃጢአት ተሰነከክለን አንውደቅ
2ኛ ጴጥሮስ 1
10፤ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት ውስጥ
"በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።"
[ኤፌ 6:10]
ከላይ ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ወታደራዊ በሆነ መልኩ ይናገራቸውና : "በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።" ይላል.. ምክንያቱም ክርስቲያኖች የምርም ወታደሮች(ተዋጊዎች) ናቸውና.. ይህም ደግሞ መጋደላቸው ከደምና ሥጋ ጋር ሳይሆን ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር እንደ ሆነ ቀጠል አድርጎ እዛው ክፍል ላይ ይነግራቸዋል..
ክርስቲያን ከሆንክ በቃ ውግያ ውስጥ ነህ.. ምናልባት ምንም ውግያ እያየህ ካልሆነ እጅ ሰጥተህ ተማርከህ ይሆናል..
አንድ ወታደር ሊዋጋ ሲወጣ ለመርታት በሚገባ ሊታጠቅ እንዲሁም ንቃት ሊኖረው ይገባዋል.. ውግያው ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር ሲሆን ደግሞ እኚህ ሰራዊት የብዙ አመት ልምድ ስላላቸው(ቢያንስ የ7000 አመት) የእነርሱን ጦር የሚከላከል እንዲሁም ደግሞ የሚያጠቃ ሁነኛ የሆነ ትጥቅ ያስፈልግሃል..
ኢየሱስ: ጌታችን ኢየሱስ የዲያቢሎስን ሽንገላ የምንቃወምበት.. መልሰንም ደግሞ የምናጠቃበት ተዋጊያችን ነው.. ከእኛ የሚጠበቀው ይህንን ኢየሱስን መያዝ ነው.. እንዲዋጋልንም መፍቀድ ነው..
ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል ወይም መልእክት መያዝ.. የእርሱን መንገድ እንድንከተል ያግዘናል.. እንዲሁም በእምነት ሆኖ መጸለይ..
ሁሌም ግን የነቃን እንሁን.. ለምንም አይነት ዲያቢሎሳዊ ወይም ሥጋዊ ሽንገላ(የሃጢአት አሳብ) እድል አንስጥ
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
መልካም ሥራ የምንሠራው ስለ ዳንን ነው ወይስ ለመዳን..??
ስለ ሁለቱም ነው.. እንዴት እንደሆነ ይመልከቱ😊😊
https://vm.tiktok.com/ZMj3x47vw/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የመልእክት ክፍል
“ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።”
[ያዕቆብ 1:14-15]
ጥፋት በሃጢአት ምኞት ይጀምራል.. ያው በሃሳብህ ወይም በልብህ ምኞትህን እየፈጸመኸው ነው.. ከዛ ምኞት በድርጊት ይፈጸማል.. ከዚያም ሞት ይከተላል.. ለዛም ነው በነገራችን ላይ ጌታ ኢየሱስ ሥሩን ሲነካው "ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል" ያለን..
ስለዛ ቆንጂትን አይተህ ሰግጠህ ለሌላ ነገር አትመኛት.. ያቺ ምኞትህ ኃጢአትን ጸንሳ ትወልዳለችና.. እንደዚህ ዓይነት አሳብ ከመጣብህና የራስህ ሴት ካልሆነች በቃ ሩጥ ከአካባቢዋ😁😁 እና ጸልይ..
በማንኛውም የሃጢአት ዓይነቶች ላይ ይህንን ተግባራዊ እናድርግ..
መልካም የጌታ ቀን😊🤗
@Apostolic_Answers
ዛሬ በጠዋት ተከሰትሁ
"በሥላሴ እያመንሁና እየተማጸንሁ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለሁ" ብለን ቀናችንን በጸሎት ከጀመርን አይቀር ሙሉ ቀኑን ሰይጣንን ስንክደው እግዚአብሔርን ደግሞ ስናከብረው እንዋል..
መልካም ውሎ በእጅጉ የተወደዳችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች..
የመጽሐፍ ግብዣ ለፕሮቴስታንቶች..
በመካነ የሱስ ጸሐፊ የተፃፈ
https://vm.tiktok.com/ZMj7c3d4D/
"ፍኖተ ጽድቅ" ላይ የቀረበው ግጥም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMjWbjfxB/
ሰላም ለእናንተ ይሁን
ሐዋርያዊ መልሶች ተከታታይ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ዙር 3 ሊጀምር ነው
መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ፎርሙን ሞልታችሁ submit ስትሉት የሚመጣላችሁን የቴሌግራም ሊንክ በመጫን ግቡ
👇👇👇
https://forms.gle/5dC2px1dD7LJxwsv7
👉🏿የውርስ ኃጢአት(original sin)
👉🏿እመቤታችን ከውርስ ኃጢአት ከማሕጸን ጀምሮ ተጠብቃለች የሚለው (immaculate conception)
ዲን ያረጋል
Cartoonist
ካርቱኒስት ካላችሁ እስቲ ለመንፈሳዊው ነገር እገዛችሁ ስለተፈለገ በውስጥ አግኙኝ
@aklil_abi ላይ ፃፉልኝ😉
ያሳዝናል: ያስቃል: ያስተምርማል😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMjGLFG13/
ይህ የአሣ ቅርጽ ጥንት ላይ አባቶቻችን እንደ አርማ ይጠቀሙበት ነበር..
ቅዱስ ቁርባንን የሚያሳይ እንደሆነም ይነገርለታል.. በዋናነት ግን አሣ በግሪክ ἰχθύς (ኢክቱስ) ይባላል.. ከላይ የአሣ ቅርጽ ውስጥ ያሉት ፊደላት በ capital letters ተጽፈው ነው ἰχθύς የሚለው።
እና ἰχθύς የሚለውን ደግሞ ፊደላቱን እንዲህ ይተነትኗቸዋል፡
Ἰ - Ἰησοῦς - ኢየሱስ
Χ - Χρῑστός - ክርስቶስ
Θ - Θεοῦ - የእግዚአብሔር
Y - Yἱός - ልጅ
Σ - Σωτήρ - አዳኝ
የሻወር tip
ሻወር ስትወስዱ መዝሙር ከፍታችሁ ይሁን.. በተለይ የንስሐ መዝሙር..
በቃ ደስ ይላል ግድ ነው😉
የሚጠቅመውም ሰው ይኖር ይሆናል ይሄ ቲፕ🤪🤪
ልክ የኃጢአት አሳቦች ሲመጡብህ😁😁
ትንሽ ካሳፈጥካቸው ችግር ስለሆነ ገና ሲመጡ ነው በቃ😁😁
@Apostolic_Answers
በትግራይ ያሉ ወንድም እህቶቻችን እናት አባቶቻችን ሃዘን ላይ ናቸው አ..
ጌታ እንደው ያረፉ የወንድም እህቶቻችንን ነፍስ ሁሉ ይማር.. ለእናቶችና ለሌሎችም መጽናናቱን ይስጥልን.. ስንጸልይ እናስባቸው..
መንፈሳዊ በሚመስል ነገር የተከለለ አለማዊነት
https://vm.tiktok.com/ZMjQkJJ4M/