ደግሞ ጾም ነገ ሊገባ ነው ይኸው በውስጥ መስመር "በማወቅም ባለማወቅም ያስከፋሁዋችሁ ይቅር በሉኝ" የምትል ጽሑፍ እኔ ጋርም እየደረሰች ነው.. ፍቱ ፍቱ ዘንድሮ እንኳን እንለፋት እቺን ሳክስ😁😁
ያው ከልብ ይቅርታ መጠየቅ ያለብንን እንጠይቅ.. አይመስላችሁም..??🤪🤪
ይኸው አንዱ የተመታ ጴንጤ ደግሞ ፌስቡክ ላይ የጅብ አእምሮን መሪጌታ በጥበብ አቅምሰውሃል እያለኝ ነው😝😝
እኔ ደግሞ ምንድን ነው ብዬ ሰዓት ወስጄ ለማንበብ መታገሌ ይሄንን ግራ የገባው ጽሑፍ😁😁
ወገን ውጭ ግን መጽሐፍት ምናምን እንዴት ነው እንደዚ ውድ የሚሆኑት😭😭 በዶላር ስለሆኑ መሰለኝ..
ስንት ብር ብከፍል ለአንዲቷ..?? 8 ሺ ምናምን ብር🙄🙄 እኔ ለእናንተ የማልሆነው የለ ይኸው የሆነች ነገር ላካፍላችሁ ደፋ ቀና እላለሁ ትላለህ ሎል.. አይ ግን ጸዴ ነው.. ለጀመርኩት ነገር በጣም አጋዥ ነው.. ስለዛ ጠብቁ በተስፋ "ነገረ ቤተ ክርስቲያን እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" ላይ👍👍 እና ደግሞ የምትጠቅም ነገር እንዲያጋራችሁ እና ደግሞ ቶሎ እንዲጨርሳትም ፕሊስ በጸሎታችሁ አስቡት ይሄንን ሶዬ
Icon corner ይልሃል🤪🤪 የጸሎት ቦታዬ😁😁
እስቲ ከታች ያለው ማን እንደሆነ ያወቀ ሽልማት አለው😁😁
እና ደግሞ እስቲ የእናንተን icon corner አሳዩን😁😁 እኔ ዛሬ ነው እቺን ያስተካከልኳት..
ዮው ሰዎች ሰዎች..
ከፖላንድ የሚመጣ ሰው ካለ አሳውቁኝ ፕሊስ.. ከወንድሜ ላይ እቃ ትቀበሉልኛላችሁ.. እና ይዛችሁት ትመጣላችሁ.. ቀላል ነገር ነው..
በዚህ አግኙኝ 👉 @aklil11
ስለ ትብብራችሁ አመሰግናለሁ😁😁
ያዕቆብ ለራሔል ስለነበረው ፍቅር መጽሐፍ ሲናገር እንዲህ ይላል
ኦሪት ዘፍጥረት 29
20፤ ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።
ሰባት ዓመት ሙሉ ራሄልን ስለማግኘት ለላባ(ለራሔል አባት) ተገዛ.. እና በጣም የሚያስገርመው ግን ሰባት ዓመት መገዛቱ ሳይሆን "እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።" መባሉ ነው..
ሰው ጌታችን ኢየሱስን አብዝቶ ሲያፈቅር ከእርሱ ጋር መኖርን እያሰበ ብዙ የዝች ዓለምን ውጥንቅት ይታገሳል.. ከእርሱ ጋር ስለመኖር ራሱን ይገዛል
@Apostolic_Answers
እግዚአብሔር ፍቅር እና ምህረቱም የበዛ ቸር አምላክ እንደ ሆነ ሁሉ በእርሱ ላይ የሚያምጹትን ደግሞ የሚቀጣ አምላክ ነው..
ዘላለማዊ ቅጣቱ ደግሞ እርሱን የማይፈልጉትን ሙሉ በሙሉ መተው ነው.. የኔ ተወዳጆች አስቡት የእግዚአብሔር ምሕረት በበዛበት በእርዚህ ምድር ላይ ስንኖር እንኳን አንዳንዴ ሰው ከእግዚአብሔር ሲርቅ ሁሉ ነገር ጨላልሞበት በጭንቀት ተውጦ ራስን እስከ ማጥፋት ይደርሳል.. ራስን ለማጥፋት ያደረሰው ምንም ዓይነት ጭንቀት ሊኖር ይችላል ግን እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ሲተው ከዛ በብዙ እጥፍ ስቃይ እና ጭንቀት ውስጥ ሰው ይገባል.. አሁን በዚህ ዓለም በአንጻሩ ቀለል ካለው መከራ ለማምለጥ ራሳችንን እናጠፋ ይሆናል ያንን ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር የተራቆተ ሰላም ማጣትን እና ጭንቀትን እንዲሁም መከራን ግን በምንም አናመልጠውም.. ራስን ማጥፋት ያኔ የለም.. ምክንያቱም የሰው አፈጣጠሩ ሞቶ እንዲቀር አይደለምና.. በኢንተርኔት ልደበርም አትል ነገር ሎል.. ያው የዚህ ዓለም የሆነው ጣዕም ጊዜያዊ እንጂ እስከ ዘላለም እንዲቀጥል ሆኖ የተፈጠረ አይደለምና..
እና እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ ማጣት እርሱ ነው ትልቁ ሲዖል.. ከዚህ ይልቅ የሚጎዳ እሳትም ምንም የለም.. ገነትን ገነት የሚያስብለው የእግዚአብሔር መኖሩ ነው፤ ሲዖልንም ሲዖል የሚያስብለው የእግዚአብሔር አለመኖር ነው..
እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር እንኖር ዘንድ አንድያ ልጁን ኢየሱስን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን ወደደው.. ዓለሙ ግን ጀርባውን ሰጠ.. ከዚህ ጠማማ ዓለም ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ያፈለሰን እግዚአብሔር ይመስገንና ይህንን ክብር እንዳናጣ የቆምን የመሰለን እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ.. ኢየሱስን የመምሰል ሕይወት ይኑረን.. ሌሎችም ደግሞ ወደ እርዚሁ መንግስት(ቤተ ክርስቲያን) ይጨመሩ ዘንድ ምክንያት እንሁን..
ቀባጠርኩባችሁ አበዛሁባችሁ መሰል ጽሑፉን.. ከተገቢው ነገር ውጪ እንዳይቀባጥር.. ጌታ ኢየሱስም ደግሞ በነገር ሁሉ እንዲረዳውና እንዲሰማው ስለ ወንድማችሁ አክሊልም መጸለይን አትርሱበት.. እሺ ማዳላት እንዳይሆን ስለ ሐዋርያዊ መልሶች አባላት ሁሉ እርስ በእርስ እንረዳዳ በጸሎት😁😁 እና ስለሌሎችም ሁሉ..
መልካም የጾምና ጸሎት ቀን..
@Apostolic_Answers
እዚህ ምድር ላይ ሆነን ስናይ ጸሐይ በምስራቅ ትወጣለች በምዕራብ ትገባለች.. ይህም የሆነበት ምክንያት ምድር በራሷ ዛቢያ(imaginary axis) ላይ በየ 24 ሰዓቱ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ስለምትዞር ነው
ይሄንን አሁን ሁሉም ያምናል.. ሁሉም ለምን አመነ..?? ሳይንስ ነግሮት.. ስለዚህም ራሴው በግል ካልደረስኩ እዚህ ላይ አልቀበልም አይልም.. እንዲያ የሚባል ከሆነ ውጥንቅጡ የበዛ መግባባት የሌለውም ዓለምን እንፈጥራለን..
ይህንን ለምን አነሳሁ..?? ኤቲስቶች መለኮታዊ የሆኑ ነገሮች ላይ በግሌ experience ካላደረግሁኝ አላምንም ሲሉ ይሰማል.. ለምሳሌ ተዓምራት.. ሌላ ሰው ቢናገራቸውም አይቀበሉም.. ሳይንሳዊ ነገሮችን አንተ ራስህ ምንም ዓይነት ኤክስፒሪያንሱ ሳይኖርህ ካመንክ መለኮታዊ ነገሮች ላይም እምነትን ቀላቅለህ ከዛ ለመረዳት የማትሞክር..??
@Apostolic_Answers
እስቲ ዛሬ ደግሞ ቅዳሴ ላይ ከሚነበቡት ቅዱሳት መጽሐፍት ወጣ ብለን ቅዳሴው ላይ ከምንላቸው ውስጥ አንዱን:
"ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ንኡ ንሰግድ ሎቱ ወንዕቀብ ትእዛዛቲሁ ከመ ይስረይ ለነ ኃጣውኢነ"
ትርጉም:
መዓዛ ያለው ሽቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው.. ኑ እንስገድለት ትእዛዛቱንም እንጠብቅ ኃጢአታችንንም ይቅር ይለን ዘንድ
ኢየሱስ ለሚለብሱት ሁሉ መዓዛ ነው.. የክርስቲያኖች መዓዛቸው.. ለእርሱ በፍርሃትና በፍቅር ለሚሰግዱለት ከልባቸው ለሚወዱት ትእዛዛቱንም ለሚጠብቁ ሁሉ ሞገሳቸው አለኝታቸው ሕይወታቸው ነው..
ትእዛዛቱን እንጠብቅ ዘንድ ጌታ ይርዳን.. "የሚወደኝ ቢኖር ትእዛዜን ይጠብቃል"
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
አጋንንት የሚወጣው በማን ስም ነው..?? በእግዚአብሔር ኃይል በኢየሱስ ስም ብቻ ነው የሚወጣው..
የመላእክትና የቅዱሳን ስም ለምን ይጠራል አጋንንትን በማውጣት ሰዓት..?? የእነርሱ ስም የሚጠራበት ምክንያት አጋንንቱን ለማባረር ሲጸለይ በዛ ጸሎት ውስጥ ቅዱሳኑም ደግሞ አብረውን እንዲጸልዩ ነው.. ጸሎታቸው ኃይል ያደርጋል ስለተባለ ጸሎታቸው ታግዘን ዘንድ ነው.. እኛ በብዙ የእምነትም የቅድስናም ጉድለት አለብንና
@Apostolic_Answers
ኧኸ እናንተ የማታ ሰዎች እንዴት አመሻችሁ..
አንዷ ጉዋደኛዬ ምን ብላ ጠየቀችኝ.. ሐዋርያቱ በነበሩበት ዘመን አሁን ላይ ባለው መልኩ Netflix ምናምን እና ብቻ አሉ አ የውጭ ወጣ ያሉ ፊልሞች ያኔም ቢኖሩ ኖሮ.. አትዩ ይባል ነበር..?? ብላ ጠየቀችኝና "ጳውሎስ ግን አይጠቅማችሁም ብሎ የሚከለክል ይመስለኛል" አለችኝ😁😁 ቅዱስ ጳውሎስ የተወደደ ሐዋርያ.. እኔም እንደዛ ይመስለኛል..
እናንተስ..??
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው
የያዕቆብ መልእክት 4
7፤ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
8፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
9፤ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
10፤ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።
በእርዚህ በጾሙ መግቢያ እንዴት ያለ ታላቅ ምክር ነው እግዚአብሔር በቃሉ በኩል የሰጠን..?? ቅዳሴ ላይ የተነበበው ክፍል መሆኑ ደግሞ በጣም ደስ ይላል..
-"ዲያቢሎስን ተቃወሙት ከእናንተ ይሸሻል" የእርሱን አሳብ አለመቀበል.. ይልቁንም "አንተ ሰይጣን ከእኔ ራቅ" ማለት..
- "እግዚአብሔርን ግን ቅረቡት እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል" በንስሐ ወደ እርሱ መቅረብ መመለስ.. ቸር አባት እርሱም ደግሞ እጆቹን ዘርግቶ በናፍቆት ይቀበለናል.. በቤቱም ሥጋና ደሙን እየተቀበልን ጠንካራ ልጆች ወደ መሆን ያሳድገናል..
- ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ..
- ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ..
- በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል..
በቃሉ ስለሚመክረን ድንቅ መካር የሆነው እርሱ የተመሰገነ ይሁን..
መልካም የጌታ ቀን.. መልካም ጾም ጸሎት
@Apostolic_Answers
ወንድማችን ሰለሞን አቡበከርን ምን ልጠይቅላችሁ..??
@aklil11 ላይ ላኩልኝ እንድጠይቅላችሁ የምትፈልጉትን..
https://vm.tiktok.com/ZMMjErngs/
ብዙዎቻችሁ እንደመለሳችሁት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው.. ግሩሜ ነበር ከሮማኒያ ያመጣልኝ.. ወዳጀ ብዙ😁😁
እና ደግሞ የጸሎት ቦታ ለማዘጋጀት ትንሽ ቦታ ነው የሚያስፈልገው.. ያደለው ለብቻው የጸሎት ክፍል ቢኖረውም ፒስ ነው.. አሁን ለምሳሌ እኔ ግን ከአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ በጣም ትንሽዬ ክፍት ቦታ ፈልጌ ነው ያዘጋጀሁት.. ያው ስለዛ ትንሽ ቦታ ፈልጋችሁ ማድረግ ትችላላችሁ ነው.. ያው የሌላችሁን ነው😊😊
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
የዮሐንስ ወንጌል 4
10፤ ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ውኃ አጠጪኝ፥ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፡ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር፡ አላት።
ጌታችን ኢየሱስ መንገድ ከመሄድ ደክሞ ሲካር በምትባል በሰማርያ ከተማ ያርፋል.. በቦታውም የያዕቆብ የውኃ ጉድጉዋድ ነበር.. እና ከዛም የውኃ ጉድጉዋድ አንዲት ሳምራዊት ሴት ውኃ ልትቀዳ ትመጣለች.. ከጌታ ኢየሱስ ጋርም በዛ ትገናኛለች
ከዚያም ኢየሱስ "ውኃ አጠጭኝ" የሚላት.. እና አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩምና ሴቲቱ "አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን እንዴት ከኔ ከሳምራዊቷ ትለምናለህ..??" አለችው.. እርሱ ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ እንደነበር ገና አላወቀችም ነበርና
በዚህ ሰዓት ነበር ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ያለው: "ውኃ አጠጪኝ፥ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፡ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር"
እግዚአብሔርን ለመለመን እርሱን ማወቅ ይቀድማል.. አውቀነው በእምነት ስንለምነው እርሱ ደግሞ ሁሌ የሚፈልቅን የሕይወትንም ውኃ ይሰጠናል.. ዳግምም አንጠማም
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እያጠናህ መዝሙር ማዳመጥ ጭራሽ ነው የማያስኬደው😁😁
ቲክቶክ ላይ ለቅቄው ነበር.. ግን ደግሞ የሊፕ ሲንክ(lip sync) ጸጋው አለህ እንዳይሉኝ ፈርቼ ወዲያው አጠፋሁት😆😆
Ofc እዚም ለ10 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት ነው😁😁
ያኔ Logic የተማርክ ሰሞን ሁሉን ነገርህን በ deductive reasoning ማስቀመጥ ሲለምድብህ🤪🤪
P1 : There’s no place like home
P2 : home(sweet home) is really the church
C : so there’s no place like the church
@Apostolic_Answers
"[የኢየሱስ እናት] በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል" [ሉቃ 2:35]
ትላንት ቅዳሴ ካለቀ በሁዋላ የተነበበው የተዓምረ ማርያም ክፍል አምስቱን የማርያምን ሃዘኖቿን የሚያነሳ ነበር.. እና እንደ አዲስ እያሰብሁት በጣም እየገረመኝ ነበር.. እኛ ሃገር 5ቱ ሃዘናት የሚባሉት የትኞቹ ሃዘኖቿ እንደሆኑ ልዘርዝርላችሁ እስቲ..
በነገራችን ላይ በውጩ ዓለም ሰባቱ የእመቤታችን ሃዘናት ነው የሚባለው.. ሰባቱንም ይዘረዝራሉ.. አንድም ግን ሰባት በሚል የተገለጸው ሙሉ በሙሉ የሃዘን ሕይወት እንደነበራትና ሃዘኗም እጅግ ጥልቅ እንደ ነበር የሚያመለክትም ነው.. እና የእመቤታችን ደረት ላይ 7 ሰይፍ እየወጋት ተደርጎ የሚሳል ስእልም አላቸው.. አረጋዊው ስምኦን "በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል" የሚለውን ቃል በመያዝ
ስለዛ ከታች 5 ብዬ የምዘረዝርላችሁ እንደው ዋናዎቹ ለማለት እንጂ ይህ ብቻ ሃዘን ገጥሟት አይደለም..
1. አረጋዊው ስምዖን በነፍሷ ሰይፍ እንደሚያልፍ በመናገር የኢየሱስን ሞት በትንቢት ሲናገር የገጠማት ሃዘን.. አስባችሁታል ገና ከመውለዷ ስለ በኩር ልጇ እንዲህ ያለ ነገር ስትሰማ..
2. በ12 ዓመቱ ከሥሯ ለ3 ቀን ሲጠፋባት.. ገና በለጋ እድሜዋ ወልዳው.. እንደ ወለደችው ደግሞ ሥጋዋ ሳይጠነክር ልጇን እንዳይገድሉባት ይዛው ከሃገር ሃገር በበረሃ ስትሰደድ.. በስንት መከራ አሳድጋው.. 12 ዓመቱ ላይ ለ3 ቀን ሙሉ አጠገቧ ስታጣው በትልቅ ሃዘን ውስጥ ሆና ፈለገችው..
3. ልጇን ኢየሱስን አሥረው ሲገርፉት.. ለአንድ እናት በተለይ ለእመቤታችን ይሄ በጣም ከባድ ነው.. ቀደም ብሎ አይሁድ ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ታውቃለች ይህ ያሳቅቃታል.. ከሱ የከፋው ደግሞ አብሮት የነበረው ይሁዳ በ30 ብር እንደሸጠው ስትሰማ የሚገባት ሃዘን አለ.. ይኸው አሁን ደግሞ በአደባባይ ልጇ ይገረፋል.. ይህ ለእርሷትልቅ ሃዘን ነበር..
4. ልጇ ኢየሱስ ሲሰቀል ሲገደል.. ጲላጦስ ኢየሱስን ከነፍሰ ገዳይ ወንበዴው በርባን ጋር አቁሞ "ማንን ልፍታላችሁ?" ብሎ ጠየቀ.. እመቤታችን ዘወር ዘወር ብላ በተስፋ "ኢየሱስን ፍታው" የሚል መልስን ከሕዝቡ ጠብቃ ይሆናል.. ግን ሕዝቡ በሊቃነ ካህናቱ ተመክረው "በርባንን ፍታው ኢየሱስን ስቀለው" ብለው ጮሁ.. ያንን የሰውን ምግብ የሚዘርፈውን.. ዓይን ያጠፋውን.. ሰው የገደለውን ፍታልን አሉት.. ሙታንን ያስነሳውን.. ቢርባቸው ምግብን አበርክቶ ያበላቸውን.. ቢታወሩ አይናቸውን ያበራላቸውን.. ዲዳ ቢሆኑ መስማትም ቢሳናቸው የፈወሳቸውን ልጇ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉት.. እመቤታችን ይህንን ስትሰማ ውስጧ ምን ያህል ተጎድቶ ይሆን.. ከዚያም ዓይኗ እያየ ሰቀሉት.. አንዱ ሐዋርያ ሲቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ሁሉ ጥለውት ተበተኑ.. እመቤታችን ከመስቀሉ ሥር ነበረች.. ሃዘኗ ምን ድረስ ይሆን እንደው በጌታ..
5. ልጇ.. ብቸኛ ተወዳጁ ልጅዋ.. ወደ መቃብር ሲወርድ..
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
የዮሐንስ ወንጌል 10
35፤ መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥
36፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ፡ ትሉታላችሁን?
ጌታችን ኢየሱስ "እኔና አብ አንድ ነን" በማለት ሲናገር አይሁድ "አንተ ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ አደረግህ" በማለት ሊወግሩት ዲንጋይ አነሱ.. እናም ጌታ ኢየሱስ ሲመልስላቸው ከመዝሙር ጠቅሶ እንዲህ ይላቸዋል፡ "[የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን] እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?"
ታድያ ግን ጌታችን የእግዚአብሔር ቃል መጥቶላቸው "አማልክት" እንደተባሉት ከእነርዛ እንደ አንዱ ነው..?? በፍጹም.. ይህንን ያነሳባት ምክንያት፡
እዚህ ጋር ጌታ ኢየሱስ የሚመልስበት መንገድ "አምላክ" መባልማ የእግዚአብሔር ቃል ለመጣላቸውስ ተሰጥቶ የለም እንዴ.. መጽሐፉ አይሻር ነገር ይህንን ልትቃወሙት አትችሉም ነው። ስለዚህም እኔንም አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከኝን ትቃወማላችሁን..?? በማለት ይሰሙት ይቀበሉትና መዳንም ይሆንላቸው ዘንድ ራሱን ዝቅ ባደረገ መልኩ ይነግራቸዋል።
እንደ አንዱ እንዳልሆነ ሲናገር ግን እንዲህ ይላል፡ "እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ.. ባደርገው ግ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ"
እዚህ ላይ የአብን ሥራ ወልድ መስራት እንደሚችል ይናገራል.. ልክ ቀደም ብሎ 5ኛው ምእራፍ ቁጥር 17 ጀምሮ እንደተነገረው.. "አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ" ካለ በኋላ ዝቅ ብሎ ደግሞ "አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያንን እንዲሁ ያደርጋል" እንዳለው ማለት ነው። እና የአብን ሥራ ወልድ ማድረግ እንደሚችል ብቻ ሳይሆን የተናገረው.. አብ በወልድ እንዳለ ወልድም ደግሞ በአብ እንዳለም ጭምር ነው..
ይህንን የተናገረው ራሱን ከሌሎቹ በለየ መልኩ ነውና አሁንም አይሁድ "ደግመው ሊይዙት ፈለጉ ከእጃቸውም ወጣ" ይላል።
መልካም የጌታ ቀን እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች
@Apostolic_Answers
ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ሊቀ ካህናት አይደለም..??
የኢየሱስ ሊቀ ክህነት ወንጌል አይደለም..??
https://vm.tiktok.com/ZMMeMhUQD/
ታናሽ ወንድሜ(ጉዋደኛዬ) ዮኒ ለልደቴ በጣም ደስ የሚሉ መጽሐፍትን ሰጣኝ ከመጽሐፍቱም ውስጥ በተለይ ገ/ወልድ ገ/ጻድቅ በተባለ ሰው "the doctrine of the union of the divinity and humanity in Christ through preservation” በሚል የተዘጋጀ doctoral researchን ለማንበብ ቸኩያለሁ..
ይሄ እንዳለ ሆኖ ግን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን "በእንተ ድንግልና" መጽሐፍም አመጣልኝ.. እና ግን ልቤን የሰበረው "አይዞህ እንዴት መመለስ እንደምንችልም ውስጡ አለው" ሲለኝ ነው😭😭 እኔ ምንም አልገባኝም☹️☹️