🙄🙄 “ሰው” ሁሉ ሲመልሰው..
እኔ የምታውቁት አልመሰለኝም እኮ.. እኔን ሲጀመር ማን ነው የደን ጠባቂ አድርጎ የሾመኝ🙄🙄
በሉ ሌላ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ልጠይቃችሁና መጀመሪያ ለሚመልስ እሸልማለሁ.. አሁን ከ10 ደቂቃ በሁዋላ እለጥፍላችኋለሁ
ያለ እኔ ፍላጎት መቆጣጠር የማልችለው አስጸያፊ አሳብ ይመጣብኛል ምን ተሻለኝ..??
https://vm.tiktok.com/ZMMy2vEBC/
በጣም ደስ ስላለኝ ዛሬ የገጠመኝን ልንገራችሁ..
ወንድማችሁ አክሊል ኢሚግሬሽን አካባቢ እየዛገ ነበርና እዛው በቆምኩበት አንድ በእድሜ ምናልባት 20 አካባቢ የሚመስል ልጅ መጣና ሰላም አለኝ ምናምን አድናቂህ ነኝ እወድሃለሁ ምናምን አለ እና ጭራሽ ዛሬ አገኝሃለው ብዬ እያሰብኩ ነበር አለኝ.. እናም አገኘኝ🤭🤭
በጣም ደስ ያለኝ ግን ፕሮቴስታንት መሆኑን ሲነግረኝ ነው.. “ፕሮቴስታንት ነኝ ግን ጥምቀት እና የጌታ ሥጋና ደም ላይ በጣም ረድተኸኛል” አለኝ.. በሰዓቱ እዛ ኢሚግሬሽን ግቢ ውስጥ የነበረውን ድካሜን ረስቼው ጌታን አመሰገንኩት.. ፕሮቴስታንት ሆኖ ጆሮ ለእኔ መስጠቱ በራሱ ደስ ይላል.. ጭራሽ ወዶ ይከታተለኛል ተመስገን..
ጥምቀት ላይ ጌታ በጣም አብዝቶ ረድቶኝ ሚዲያው ላይ ሃሪፍ ነገር ያስቀመጥኩ ይመስለኛል.. ቅዱስ ቁርባን ላይም ብዙ ሰርተናል ግን በቅርቡ ደግሞ በጣም በቀላል እያደረግን ብዙ እሰራበታለሁ..
ሁሉን ግን የሚሠራው ተስፋዬ ኢየሱስ ነውና እርሱን አመሰግነዋለሁ..
ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ፕሮቴስታንቶች መጸለይን አትርሱ
እና ደግሞ የሄድኩበትም ጉዳይ ዛሬ እንደማይሳካ 100% እርግጠኛ ነበርሁ ግን ደግሞ እሱንም ጌታ ረድቶኝ ተሳካልኝ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከጳውሎስ እና ከሌሎችም የመልእክት ክፍል:
ከጳውሎስ:
ወደ ቆላስይስ 2
16፤ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።
17፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
-አይሁዳውያን ካለተገረዙት ወገን የሚመጡትን ክርስቲያኖች እንደ እነርሱ በዓላትና የሙብልና የመጠጥ ሥረዓት ስለሌላቸው ይተቿቸዋል.. ታድያ ግን ጳውሎስ በእንደነርዚህ ነገሮች ሊተቹ እንዳይገባ ይናገራል ምክንያቱም እነዛ ሁሉ በብሉይ ኪዳን ለሚመወጣው ነገር እንደ ጥላ የሆኑ ነበሩና ነው.. ስለዚህም አሁን ወደ አዲሱ ሥረዓት መጥተናልና አስቀድሞ የነበሩትን በዓላት ሁሉ ከአሕዛብ የመጡትመ እንዲያከብሯቸው አይገደዱም.. ይልቁንም በሐዲስ ኪዳን እንደ አዲስ መንፈሳዊ የሆኑ በዓላት ይኖረናል ነው።
ከያዕቆብ መልእክት
የያዕቆብ መልእክት 2
14፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
የተለመደ ጥቅስ ነው.. ግን ለድኀነት(ድኀነታችንን ለመፈፀም) ምን ያህል ሥራ ነው የሚጠበቅብን..?? እንግዲህ ጌታችንም በወንጌል እንዳለ 30: 60 እና 100 ፍሬ የሚያፈራ ይኖራል.. ስለዚህም አንዳንዱ አነስ ያለ ፍሬ ሌላውም በዛ ያለ ፍሬን ሊያፈራ ይችላል..
የሚያስገርመው ደግሞ ፍሬን ማፍራት ቀላል ሊሆንም ይችላል.. ለምሳሌ ጌታ በፍርድ ቀን የሚጠይቀውን ይወስድና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡
ክርስቶስ ከአንተ የሚጠይቀው ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተመለከትክን..?? ታስሬ አስፈትተኸኛልን..?? ታምሜስ አድነኸኛልን..?? አይደለም ያለው ግን ደግሞ "መጥታችሁ ጠይቃችሁኛልን..??" ነው።
በአጠቃላይ ሥራ ሲባል በቅድሰና ሕይወት እየኖሩ ጌታን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶን በመምሰል ሕይወት ማደግ ነው..
ሥራ ድኀነትን ለመፈጸም ያስፈልጋል ብለን ከመከራከርና ከማሳመን ዘለን ደግሞ ቃሉን እንድንፈጽምና የምንሠራ እንድንሆን ጌታ ይርዳን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የትኛውንም ሪያክት እንዳደርግበት የምትፈልጉትን የጴንጤ ነቢያት ቪዲዮ እና ልምምድ(የድሮም ያሁንም: የሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያሉትን) በቴሌግራም @aklil11 ላይ ላኩልኝ
https://vm.tiktok.com/ZMMAsL9Qu/
አንድ አባት ምን ብለው ሲያስተምሩ ሰማሁ..
እውነተኛ ጉዋደኛ ማለት አንተን ከፍ የሚያደርግህ እንጂ ወደ ታች የሚጥልህ አይደለም.. ከፍታ ደግሞ ኢየሱስ ነው እናም ለአንተ እውነተኛ ጉዋደኛ ወደ ኢየሱስ የሚያቀርብህ ነው.. ወደ ሰይጣን የሚያቀርብህ እርሱ ጉዋደኛህ አይደለም..
ትልቁ ቁም ነገር:- አንተም እውነተኛ ጉዋደኛ ከሆንህ እንግዲያውስ ጉዋደኛህን ወደ ኢየሱስ ከፍ አድርገው.. ሃረቄ ቤት ምናምን ሳይሆን ቅዳሴ ውሰደው.. ይሄ እህቶችንም ይመለከታል ያው..
@Apostolic_Answers
እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ..
ኢየሱስ ራሱን ዘላለማዊ መስዋዕት አድርጎ አቀረበ.. ስለዚህም በዘላለም ሁሉ ውስጥ ይህ መስዋዕቱ እየሰራ ይኖራል.. ይህ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነው..
ጥያቄው የሚሆነው እንዲህ ነው👇👇
አንድ ሰው ከላይ ያለውን ተቀብሎ አንዴ በኢየሱስ የተሠራው ሥራ ሁሌም ተግባራዊ ስለሚሆን ይህንን እውነታ ብቻ ለመግለጽ “ኢየሱስ ይማልዳል” የሚለውን ቃል ቢጠቀም.. ይህንን ቃል መጠቀሙ በራሱ ምንፍቅና(የሃይማኖት ተፋልሶ) ያስብለዋል..??
መልሳችሁን ኮመንት ላይ
ቅዳሴ ላይ “ስግዱ” ሲባል ባለንበት የምንቀመጥ ሰዎች እዚህ ጋር አንዴ እንሰብሰብ እስቲ😁😁
እኔ ራሴም እንደዛ አደርግ ነበር ግን ኢየሱስ ራሱ ሲንበረከክና በፊቱም ሲደፋ እንደነበር ሳስበው የምር ሼም ያዘኝ.. አንዳንዴማ አፈር መሆኑን ስናይ እኮ ነው የማንንበረከከው.. ኧረ ኢየሱስ መሬት ላይ ነው የተንበረከከው😬😬
እንደው አካብጄ ከሆነ እንጃ ግን ሳስበው ዝገት.. ስለዛ ከታች ኮመንት ላይ ደግሞ ወንድምና እህቶች ሥርዓቱን ያስተምሩናል..
ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ
እንደዚህ ዓይነት ቪዲዮ ላይ ስሜ ሲነሳ እንደው ማርያምን በራሴ እንዳዝን ነው የሚያደርገኝ.. ስንፍናዬን ሳስበው.. ብቻ ይሁነው.. ስላበረታታኝ ወንድሜን አመሰገንሁ
https://vm.tiktok.com/ZMMhu1UyH/
ባል እና ሚስቶች መካከል በጣም ከሚያጉዋጉን ነገሮች ውስጥ🤪🤪
-አብሮ ቤት ውስጥ መጸለይ
-አብሮ ማስቀደስ እና ቶሎ ቶሎ መቁረብ
-አብሮ ገዳም ለ3 ቀን ምናምን መሄድ
-ዩ ኖው መቃለዱ አብሮ ማዛጉ መሳሳቁ ምናምን ወጣ እያሉም ፈታ ማለቱ(እሷ ልጅ እስክትወልድ ነው ይሄ.. ከዛ በሁዋላ ብቻህን መፍታታት ነው ማን😆😆 ስቀልድ ነው ደግሞ እንዳትሰግጥ)
-በልጆች እግዚአብሔር ሲባርክ ደግሞ ልጆችን ቅዱሳን አድርጎ ማሳደግ.. መቼስ ቶሎ ቶሎ የሚቆርቡ እናት እና አባት ያለው ልጅ አስቡት የሚሆነውን😁😁
-ከዛ ደግሞ ማርጀት ይመጣል ግን አርጅተውም አብረው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ..
ተደጋግፈው ጉዞ ወደ ኢየሱስ
ምንድን ነው የምንቀባጥረው ወገን😁😁
ናሆም እና አንድ ሌላ ሰው ተሸልሟል..
አንድ ሌላ ሰው ያልሁት ድንገት ስሙ መጠቀሱ ላያስፈልግ ስለሚችል ነው.. ምክንያቱም ፕሮቴስታንት ነው..
የሥራችሁን ይሰጣችሁ ለፕሮቴስታንት ታስሸልሙኛላችሁ😆😆
አይ ግን ልጁ የጻፈውን እዩ.. በተለይ የዚ ጥምቀት እና ቅዱስ ቁርባን ነገር👍👍 ጌታ ይመስገን.. ወንድማችንንም አብዝቶ ይርዳው
መልሱ ግን ምናልባት ለማታውቁት..
ልታዩት ስትቀርቡ ያለው መስታወት ነው እና የራሳችሁን ፊት ነው የሚያሳያችሁ.. አደገኛ አውሬ የተባልኸው አንተው ነህ ማን😭😭
የመጀመሪያው ካርድ የሚያስሸልመው ጥያቄ..
ይህ ጽሑፉ ላይ የተጠቀሰው ታስሮ ያለው አደገኛ አውሬ ምን እንደሆነ ገምቱ.. ጉዋደኛዬ አይታዋለች😊😊
50 ብር ካርድ ነው ምሸልመው😁😁 ግን ቶሎ ቶሎ በየጊዜው እሸልማለሁ
ከሃገረ ካናዳ ሁለት ጉዋደኛማቾች የተወሰነ ሰግጠው ተከራክረው አሳምነው ገንዘብ አስገቡልኝ.. 25,200 ብር.. በጣም ይቅርታ አሳመኑኝ😁😁
እና በቃ ለኔ የዘነበ ለናንተ ያካፋ ብዬ የሆነ ጥያቄ እየጠየኳችሁ ለሚመልስ ሰው ለምን ካርድ መሸለም አልጀምርም😁😁
መጀመሪያ ግን አስቤ የነበረው give away ነገር ነበር.. ሐዋርያዊ መልሶች ቲሸርት ወይ ሁዲ ምናምን.. ያው እሱን በቀላሉ አንሰጥም ቆይ ላስብበት እንዴት እንደምሰጥ..
በቃ ጥያቄውን ማታ እንጀምረዋለን🤪👍
ገሃነም መግባት እንድትፈሩ የሚያደርጋችሁ ምንድር ነው..??
የሚፋጅ እሳት..??
የማያንቀላፋ ትል..?? ሎል
በጣም የሚያስፈራው ጋይስ.. ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ ማጣታችን ነው.. ወይኔ አስባችሁታል ኢየሱስን ዳግም ላናገኘው ስናጣው..?? ማለት አሁን እኮ እበድለዋለሁ ምናምን እኮ ግን የፈለገ ቢሆን ኢየሱስን በቃ አጥተኸዋል ካሁን በኋላ ምንም እድልም የለህ ስባል.. በስምአብ የምር በጣም ያስፈራል.. የኔ ኢየሱስ የኔ ጌታ የኔ አባት የኔ ተስፋ..
ጌታ እዚህ የሰጠንን እድል ተጠቅመን በንስሐ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይርዳን.. የሚታገሰንም ለዚሁ ነው በነገራችን ላይ.. ጴጥሮስ እንዲህ እንዳለ:
2ኛ ጴጥሮስ 3
9፤ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
@Apostolic_Answers
Here we go.. አጋጣሚ ልተኛ አልቻልሁም ዛሬ.. ይኸው ቅዳሴ ሰዓት ሊደርስ ነው😆😆 በሉ ከቅዳሴ መልስ መጻፍ መቻሌንም እንጃ ሎል..
Читать полностью…ወደ ሮሜ 16
17፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት 👉የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች 👉እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ 👉ፈቀቅ በሉ፤
የኛን ትመህርት የሚቃወሙትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሁሉ እንድንመለከትና ከእነርሱም ዘንድ ፈቀቅ እንድንል ተወዳጁ ሐዋርያ ይነግረናል.. ስለ እርዚህም በፍቅርና በየዋሕነት በጴንጤው ያለውን እናያለን ሰዎችንም ከመሰናክል ለመታደግ እንሞክራልን ማለት ነው.. ይሄ ሐዋርያዊ ነው
———————————
በአረብ ሃገራት ያላችሁ እህቶቻችን ከየትኛውም መምህርም ሆነ ዘማሪ ገንዘብ(መዋጮ) ስትጠየቁ ልትልኩላቸው የሚገባ ቪዲዮ ሎል
ከላይ ላለው ጥያቄ አብዛኛው ሰው የመለሰውና የኔም መረዳት የሆነው እነሆ
👇👇👇👇
“ቃሉን ስለተጠቀሙ ብቻ ምንፍቅና አያስብለውም.. ቃሉንማ ሐዋርያውም ተጠቅሞታል.. እና ዋናው መረዳታቸው ምን ይመስላል የሚለው ነው.. እና ደግሞ በኒቂያው ጉባኤ ለምሳሌ ወልድ በባህሪው ከአብ ጋር አንድ እንደሆነ ለመግለፅ የተጠቀሙት “ሆሞኡሲዮስ” የሚለው ቃል ከኒቂያው ጉባኤ በፊት በመናፍቃን ለምንፍቅናቸው ቃሉን ተጠቅመውት ነበር ሁዋላ ግን ያንንው ቃል እኛ ለቀና ነገር ተጠቀምነው.. እና ቃላት በራሳቸው ሳይሆን ይልቁንም የሚያዝሉት አሳብ ምንድር ነው የሚለው መታወቅ አለበት”
የምን ሃከር ምናመን ነው.. ነቢያቱ ቀጥታ ከባንክ ያልታወቀ ገንዘብ ምእመኑ እንዲያወጣ እያደረጉት ነው አሉ.. ይምቻቸው😁😁
ሃከር❌
ነቢይ😎✅
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት:
1ኛ ተሰሎንቄ 4
3፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ መቀደሳችሁ ነውና፤ እርሱም ከዝሙት እንድትርቁ
ቅድስና የክርስቲያን ሕይወት ሲሆን ይህም አንድ ሰው ዳግም ከወኃና መንፈስ ከተወለደ በሁዋላ በጸጋው ድጋፍ የሚኖረው ክርስቶስን የመምሰል ሕይወት ነው.. ይህ ለክርስቲያን ድኅነቱኑን የሚፈጽምበትም ነው.. “የጠራችሁ ቅዱስ ነውና እናንተም በኑሮዋችሁ ቅዱሳን ሁኑ” እንደሚለው ማለት ነው..
ኃጢአት ከቅድስና ያጉዋድላል.. በተለይም ብዙ ጊዜ ወጣቶችን የሚጥለው ዝሙት ነው.. ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ደጋግሞ ከዝሙት እንድንርቅ ይመክረናል.. ባንርቅ ግን ስለ እርዚህ ነገር ጌታ እንደሚበቀልም ይናገራል እዚሁ ክፍል ላይ ዝቅ ብሎ..
ክርስቲያን እንደ ንቁ ወታደር ነው.. እርሱን ማርኮ ሊጥለው የሚችለውን ነገር ሁሉ ቸል ባለማለት አስቀድሞ ያስወግዳል.. ዝሙት ከሃሳብ ጀምሮ ከዚያም ያድጋልና ገና ወደ አሳብ ሲመጣ መቃወምና ቆርጦ መጣል.. እንዲህ ያለ አሳብ ሊያመጡብን ከሚችሉ ምስሎች ጽሑፎች እንዲሁም ሌሎችም ዓይንን መጠበቅ.. የዓይንህን ቅድስና በዛው ጠበቅህ ማለት ነው..
የቅድስና ትልቁ መሠረት ደግሞ በራስ አለመደገፍ ይልቁንም በክርስቶስ መደገፍ ነው.. የእመቤታችን ጸሎት ያግዘን
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እነዚህ ሥራዎች.. ያምራሉ የምር.. አንዲት አርሱ የሚሏት ግምብ ፊት ጉዋደኛዬ ነበር የሰጠችኝ.. ቆይ እያንዳንዱን ሥእላት አሳያችሁዋለሁ
Читать полностью…በእንተ ተሠግዎተ ቃል(on the incarnation of the logos”
ይህንን የቅዱስ አትናቴዎስን ሥራ ብዙዎቻችሁ ታውቁታላችሁ እንደው ቢያንስ በስም ማለት ነው..
ይህንን የመጨረሻ አስገራሚ የሆነ ሥራ ስንት ዓመቱ እያለ ቢጽፈው ሃሪፍ ነው..?? ገና የ19 ዓመት ልጅ እያለ🙄🙄
ወገን አመቱ እንደ አሁኑ አልነበረም እንዴ የሚቆጥረው ያኔ..?? ግራ አጋባን እኮ😁😁
አርዮስንም "የጨመቃት"(ሎል) ገና በ26 እና 27 ዓመቱ.. ዲያቆን እያለ ነው..