ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
“በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።”
[2 ጢሞ 2: 2]
ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ነገር..
1. የክርስትና ትምህርት ሐዋርያት ጋር ብቻ አይቀርምና ለተማሪዎቻቸው ያስተላልፉታል.. ስለዚህም “በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን” ይለዋል
2. ይኸው ትምህርት ደግሞ ከሐዋርያት ተማሪዎችም ወደ ቀጣዮቹ እየተላለፈ ይሄዳልና ጢሞቴዮስን “ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ” ይለዋል
3. አደራ የሚሰጣቸው ሰዎች ደግሞ የታመኑ እና ሌሎችን ሊያስተምሩ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው ይናገራል.. ይህ ደግሞ ትምህርቱ በታማኝነት ወደቀጣይም ሲተላለፍ እንደሚኖር አመልካች ነው.. ጌታችን ኢየሱስ “እስከ ዓለም ፍፃሜ ሁል ጊዜ ከ እናንተ ጋር ነኝ” በማለቱ እስከ ዓለም ፍጻሜ መቀጠሉ የማይቀር ነው.. ጠባቂውም መንፈስ ቅዱስ ነው
4. ይህ የሚተላለፍ የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን በብዙ ምስክሮች ፊት የተሰማ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ነው.. እርግጥ በኋላ በጽሑፍ ያለውም ይተላለፋል(2ተሰ 2:15)
ማጠቃለያ:
የክርስትና ትምህርት በዚህ መልኩ እየተላለፈ የሚሄድ ከሆነ ማንም ሰው እንደ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስን እያነበበ በራሱ መረዳት አዳዲስ ትምህርቶችን ማምጣት አይችልም ማለት ነው..
@Apostolic_Answers
ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት ለድኀነት እንደሚያስፈልግ አያስተምርም ካለ አንድ ሰው በቃ “መጽሐፍ ቅዱስ” እያለ የሚጠራው የራሱን መረዳት ነው..
ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የእግዚአብሔር ቃል ብለው የሚጠሩት መጽሐፉን አንብበው ከዛም ራሳቸው የተረዱትን መረዳት ነው.. የሰው መረዳት እንዴት መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ ይጠራል..??
ኧረ እቺ አገላለጽ ራሱ ተገልጣልኝ ነው መሰል ወገን😁😁
ንጉሥ ዳዊት በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ:
“ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው?”
[2ሳሙ 7:18]
ብቸኛው ልጅህን ኢየሱስን እስክትሰጠን ድረስ እንዲሁ የወደድከን ኸረ እኛ ማን ነን..?? እንደ ስንፍናችን ሳይሆን በምህረትህ የጎበኘኸን ሁሌም የምትታገሰን እኛ ማን ነን..??
ይህንን ስናስረዳና ሰዎችን ለማገዝ ስንሞክር ከሥር ከሥር የምታበላሹ ወንድሞች ተዉ ፍቱን😭😁
1. የሃይማኖት መከራከሪያ የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እና ትምህርቶች የተብራሩበት የሊቃውንት መጽሐፍት ናቸው.. (ማስረጃ ለምሳሌ አድማሱ ጀንበሬ መድሎተ አሚን እና የቦሩ ሜዳው ነገር)
2. ገድላት ተዓምራት ኦሪጅናሎቹም ቢገኙ ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል.. infallible የሚባለው መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው..
ቅዳሴ tip 1 ይልሃል😁😁
የቅዳሴ ቀን ሌሊት ስትነሱ ትንሽ ደቂቃ ቀደም ብላችሁ ተነሱና የተረጋጋ መዝሙር ስሙ.. እና መዝሙሩ ሥጋችንን ብቻ ሳይሆን መንፈሳችንንም ያነቃቃዋል..
በሉ ነገ ቅዳሴ ላይ እና ከዛም በኋላም እንገናኝ.. መልካም አዳር
“ገድላት” ምናምን የሚሉ ተሃድሶዎች የሚጠሩን ወደ ሃሰተኛ ነቢያት እግር ሥር እንደሆነ ይመልከቱ..
ሲቀጥል የተአምራት መጽሐፍት ለሃይማኖት መከራከሪያ እንደማይሆኑ ከቦሩ ሜዳው ጉባኤ እነሆ
https://vm.tiktok.com/ZMMukMHvm/
—————————————
የተለያዩ ርእሶች ላይ አባቶች ምን አሉ የሚለውን እንዴት በቀላሉ ማወቅ እንችላለን..??
Website recommendation
https://vm.tiktok.com/ZMMmsrNJr/
2ኛ ቆሮንቶስ 11
2፤ በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
ይህን ጥቅስ ጠቅሶ አንድ “ሊቀ ጠበብት ዶር” ሲናገር ከሰማሁትና እንዴት እንዴት ነው የሚያመሰጥረው ያስባለኝ ድንቅ ትርጓሜ:
1. እዚህ ላይ “እንደ ንጽሕት ድንግል” የተባለችው እመቤታችን ናት (ዋው ሎል)
2. ለዮሴፍ ታጨች የተባለውም ልክ እጩ ዶክተር እንደሚባለው ነው.. ለጋብቻ እንደሚነገረው ዓይነት እጮኝነት አይደለም..
🤭🤭 ካመሰጠሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ ኤታባቱ
ቀጠሮ ላይ የሚያረፍድ ሰው በጣም ነው ማልወደው.. ለምሳሌ ዛሬ 2:30 ላይ ለመገናኘት ከሰዎች ጋር ተቀጣጠርን..
እና ይኸው 4:30 ሆኗል ላገኛቸው እየሄድኩ ነው.. እየደረስኩ እኮ ነው.. ትንሽ ደቂቃ ብቻ☹️☹️
ሰው ዳግም የሚወለደው ስላመነ ነው..?? ወይስ ዳግም ሰወለተወለደ ያምናል ነው..??
ለዳግም ልደት ጥመቀት ብቻ ሳይሆን እምነትም ተክዷል
https://vm.tiktok.com/ZMM9AmuhL/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”
[ማቴዎስ 24: 24]
ዛሬ እንግዲህ የጌታችንን ዳግም መምጣት የምናስብበት በዓል ነው.. እና በዝች ቀን በተነበበው ወንጌል ላይ ደግሞ ጌታ ዳግም ሊመጣ አቅራቢያ ላይ የሚከሰቱ ክስተቶችን ይናገራል.. ከእነርዚህ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ደግሞ ከላይ የተጠቀሰው ነው..
ኢየሱስ “እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ” ብሎ ከነገረን ውስጥ አንዱ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ነቢያቶች እንደሚነሱ ነው.. እና እነዚህ ሐሰተኞች ደግሞ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” ተባለላቸው..
የምርም ምልክቱ አሁን ላይ መታየት የጀመረ ይመስላል.. በተለይ ከመቶ አመት ወዲህ የተነሰው የጴንጤቆስታል እንቅስቃሴ ትልቅ ማሳያ ነው.. በኢየሱስ ስም የሚመጣው Antichrist(የክርስቶስ ተቃዋሚው) የሚሠራበት እንቅስቃሴ ይመስላል.. ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ይላል:
2ኛ ተሰሎንቄ 2
9-10፤ ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
ኢየሱስ በዚህ መንፈስ የተታለሉትን ሁሉ በምህረቱ ነፃ ያውጣ.. እኛንም ይጠብቀን..
መልካም የጌታ ቀን
ጌታችን ይመጣል
@Apostolic_Answers
ጌታ በአሁኑ እሁድ ይመጣ ይሆን..??
እለቱ : እሑድ
ቀኑ : 29
ወሩ : መጋቢት
ዘመኑ : ዮሐንስ
እንዲ ሲሆን ነው ኢየሱስ የሚመጣው.. ግን ደግሞ በየትኛው ዓመተ ምህረት ላይ እንደሆነ አይታወቅም.. እንዲህ የሚል ነገር በአንዳንድ መጽሐፍት ላይ ተጽፎ ይገኛል..
ግን ይሄ እይታ ብቻ እንጂ የጌታ ቤተ ክርስቲያን እምነት አይደለም.. እንደ ሌባ እንደሚመጣ ብቻ ነው ምናውቀው.. ዛሬም ይሁን ነገ ወይ ሌላ ቀን አናውቅም
@Apostolic_Answers
ባለፈው የጠየኳችሁን ጥያቄ የመለሱትን ሁለት ልጆች አሁን ገና ሸለምኳቸው አጋጣሚ በሰዓቱ ሳልችል ቀርቼ😁😁
ክርስቲያኖች ብዙዎች ስንሆን እንዴት አንድ ሥጋ ሆንን..?? የሚል ነበር ጥያቄው.. እና ሥጋ የምትለዋ አሳብ ላይ ትኩረት ስላደረግሁ የጌታ ሥጋና ደም ያሉትን ሸለምኩ.. theotokos እና LMHVN ለሚል ስማቸው..
[1ኛ ቆሮንቶስ 10: 16-17]
የምንቆርሰው ኀብስት ከጌታ ሥጋ ጋር ኀብረት ያለው አይደለምን..?? አንድ ኀብስት ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን ኀብስት እንካፈላለንና።
ዛሬም ትጠየቃላችሁ በቃ😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
ወደ ገላትያ 5
14፤ ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡ የሚል ነው።
ተወዳጅ መልእክታትን የጻፈ ይህ ሐዋርያ “ሕግ ሁሉ በፍቅር ይፈጸማል” ይለናል.. በሌላ ክፍልም እንዲህ ይላል:
ወደ ሮሜ 13
9፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ፡ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፥ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።
ለምን ነው እነዚህ ሁሉ ትእዛዛት ሌላውን ውደድ በሚለው ውስጥ የሚጠቃለለው..?? ምክንያቱም በምትወደው ሰው ላይ እነዚህን ሁሉ ትእዛዛት አትተላለፍምና ነው.. ለምሳሌ በምትወደው ሰው ላይ በውሸት አትመሰክርበትም፣ የምትወደውን ሰው አትገድልም.. ሌሎችንም እንዲሁ አትፈጽምም..
ስለዚህም ቀጣይ እንዲህ ይላል..
“ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።”
ወንድሙ ሐዋርያው ዮሐንስ ደግሞ እንዴት መዋደድ እንዳለብን ሲናገር: “ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።” ይለናል [1ኛ ዮሐንስ 3:18]
ስለዚህ እናንተን መውደዴ በሥራ ሊገለጥ ሊታይ ይገባዋል.. ጌታ እርስ በእርስ በእውነት እንድንዋደድ ይርዳን..
መልካም የጌታ ቀን😊🤗
@Apostolic_Answers
ኧረ እኔ መልሳችሁን ሳየው ተሸማቀኩ አጠርኩ😁😁 እንደው ሌላ ሰው እንዳያይብን አጠፋሁት ሎል.. ከባቢሎን ምርኮ ተብሎ ሙሴ..?? ያውም የአሕዛብ ንጉሥ..??😭😭 አሮን..?? ፈርዖን..??😭😭
ለማንኛውም የፋርስ(Persia) ንጉሥ ቂሮስ(Cyrus) ነው..
እዝራ ምእራፍ 1 ብቻ አንብቡ..
እስቲ አሳብ ስጧት..
አንዲት እህታችን ከንስሐ አባቷ ጋር ያው በጣም ትቀራረባለች እና ካላገባሽ እያሏት ነው.. ያው እሷ ደግሞ ገና ተማሪም ስለሆነች አትፈልግም.. በዛ ላይ ባሉንም ያመጡላት/የመረጡላት ራሳቸው ናቸው (የንስሐ ልጃቸውን)
እና የግድ አሏት.. ሌላ የንስሐ አባትም እንድትይዝ አልለቀቋትም.. በእርዚህ መሃል ቆንጂት ተጨነቀች😁😁 ምን ታድርግ..??
ያው ኮመንታችሁን ታየዋለች.. ደግሞ እንደለመዳችሁት ቀልድ እንዳታበዙ🙄🙄