ሰሞኑን ለተነሳው የ “ፍጡር ወፈጣሪ” የልዩነት ጥያቄዎች ምናልባትም የማያዳግም ምላሽ..
እና ለፕሮቴስታንቲዝም ደግሞ ቻሌንጅ
https://vm.tiktok.com/ZMMVEc93w/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ የተነበበው የጳውሎስ መልእክት
ወደ ሮሜ 7
5፤ በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤
6፤ አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።
“በሥጋ ሳለን” ሲል በቀድሞው በአሮጌው ማንነታችን ወይም ለኃጢአት በሚገዛው ሥጋ ማለት ነው.. ብልቶቻችን ለሞት የሆነ ፍሬን ያፈሩ ነበር ነው.. ይህም የኃጢአት መሻት ነው..
“በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት” ይላል.. ይህ ማለት ሕግ ኃጢአት ነው ወይም ሕግ ሰዎችን ኃጢአት እንዲሠሩ ያደርጋል ሳይሆን ኃጢአቱ የሚታወቀው ግን በሕጉ ነው ነው.. እንዴት..?? ያው ሕግ “ይህንን አታድርግ” የሚል ስለሆነ አታድርግ የተባልከውን ስታደርግ እሱ ኃጢአት መሆኑ ከተፃፈው ሕግ አንፃር ይታወቃል ማለት ነው..
እዚህ ጋር አስተውሉ ሕግ ሲመጣ ለ እኛ ከኃጢአት የምንርቅበትን አቅም ይዞልን የመጣ አይደለም.. በቃ እንደውም ኃጢአታችንን የሚቆጥር ነው.. ይህ በጽሑፍ የሆነው ሕግ ግን ጸጋ እስኪመጣ እንደ ሞግዚት ሆኖ ያቆየ ብቻ ነበር.. አሁን ጸጋ በኢየሱስ ሆነልን.. “ይህም ጸጋ” ይላል ጳውሎስ “ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊ ምኞትን የሚያስክደን ነው” ይላል(ቲቶ 2:11)
በእርዚህ በተሰጠን አቅም በሆነልን ጸጋ አዲስ ኑሮን እንኖራለን.. ይህም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ መኖር ነው.. ሕጉ ይህንን አያስችልም ጸጋው ግን ያስችላል.. ስለዚህም ጳውሎስ እዚሁ ጋር እንዲህ ይላል: “በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም”
ያው የኒቆዲሞስን ነገር ብዙ ቦታ ስለምናገኝ ነው ከጳውሎስ መልእክት ያካፈልኳችሁ..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
እስቲ አንድ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጨመር ቢፈልግ እንደ አዲስ መጪ ሊቀበልና ሊመሰክር የሚገባው ሃይማኖት የቱ የቱን ነው..??
እስቲ ደግሞ ወንድም እህቶቼ ያላቸውን ምልከታ ልስማ.. ኮመንት ላይ አሳውቁኝ
ለፕሮቴስታንቶች አንድ ጥያቄ
በኢየሱስ ታምናላችሁ..?? (ከምን አንጻር እንደሆነ ይመልከቱ)
https://vm.tiktok.com/ZMMXfgkGU/
“መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” በሚል ርእስ የሁለቱን ዲቤት ዛሬ ገና ሳየው.. እና ያየሁትም ጥያቄና መልሳቸውን ነው.. እኔም የጋበዝኳችሁ እሱን ፓርት ነው..
ጋቪን(ፕሮቴስታንት) : በጣም ደስ የሚል የተረጋጋና የሚሰማ ሰው ነው
ትሬንት ሆርን(ካቶሊክ) : ጎበዝ መላሽ ብቻ ሳይሆን በጣም ጎበዝ ጠያቂም ነው.. የካቶሊኮችን አፕሮች ሙሉ በሙሉ የምቀበል ባይሆንም እኔ.. እሱን አሳያችኋለሁ አንድ ቀን.. ትሬንት ሆርን ግን ያው አቀራረቡም ደስ የሚል ሰው ነው
https://www.youtube.com/live/kn7qdPSHSJk?t=3880&si=7WYodYiUmX3P6xKl
ሰው ዳግም የሚወለደው ስላመነ ነው..?? ወይስ ዳግም ሰወለተወለደ ያምናል ነው..??
ለዳግም ልደት ጥመቀት ብቻ ሳይሆን እምነትም ተክዷል
https://vm.tiktok.com/ZMM9AmuhL/
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል
“ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”
[ማቴዎስ 24: 24]
ዛሬ እንግዲህ የጌታችንን ዳግም መምጣት የምናስብበት በዓል ነው.. እና በዝች ቀን በተነበበው ወንጌል ላይ ደግሞ ጌታ ዳግም ሊመጣ አቅራቢያ ላይ የሚከሰቱ ክስተቶችን ይናገራል.. ከእነርዚህ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ደግሞ ከላይ የተጠቀሰው ነው..
ኢየሱስ “እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ” ብሎ ከነገረን ውስጥ አንዱ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ነቢያቶች እንደሚነሱ ነው.. እና እነዚህ ሐሰተኞች ደግሞ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” ተባለላቸው..
የምርም ምልክቱ አሁን ላይ መታየት የጀመረ ይመስላል.. በተለይ ከመቶ አመት ወዲህ የተነሰው የጴንጤቆስታል እንቅስቃሴ ትልቅ ማሳያ ነው.. በኢየሱስ ስም የሚመጣው Antichrist(የክርስቶስ ተቃዋሚው) የሚሠራበት እንቅስቃሴ ይመስላል.. ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ይላል:
2ኛ ተሰሎንቄ 2
9-10፤ ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
ኢየሱስ በዚህ መንፈስ የተታለሉትን ሁሉ በምህረቱ ነፃ ያውጣ.. እኛንም ይጠብቀን..
መልካም የጌታ ቀን
ጌታችን ይመጣል
@Apostolic_Answers
ጌታ በአሁኑ እሁድ ይመጣ ይሆን..??
እለቱ : እሑድ
ቀኑ : 29
ወሩ : መጋቢት
ዘመኑ : ዮሐንስ
እንዲ ሲሆን ነው ኢየሱስ የሚመጣው.. ግን ደግሞ በየትኛው ዓመተ ምህረት ላይ እንደሆነ አይታወቅም.. እንዲህ የሚል ነገር በአንዳንድ መጽሐፍት ላይ ተጽፎ ይገኛል..
ግን ይሄ እይታ ብቻ እንጂ የጌታ ቤተ ክርስቲያን እምነት አይደለም.. እንደ ሌባ እንደሚመጣ ብቻ ነው ምናውቀው.. ዛሬም ይሁን ነገ ወይ ሌላ ቀን አናውቅም
@Apostolic_Answers
ባለፈው የጠየኳችሁን ጥያቄ የመለሱትን ሁለት ልጆች አሁን ገና ሸለምኳቸው አጋጣሚ በሰዓቱ ሳልችል ቀርቼ😁😁
ክርስቲያኖች ብዙዎች ስንሆን እንዴት አንድ ሥጋ ሆንን..?? የሚል ነበር ጥያቄው.. እና ሥጋ የምትለዋ አሳብ ላይ ትኩረት ስላደረግሁ የጌታ ሥጋና ደም ያሉትን ሸለምኩ.. theotokos እና LMHVN ለሚል ስማቸው..
[1ኛ ቆሮንቶስ 10: 16-17]
የምንቆርሰው ኀብስት ከጌታ ሥጋ ጋር ኀብረት ያለው አይደለምን..?? አንድ ኀብስት ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን ኀብስት እንካፈላለንና።
ዛሬም ትጠየቃላችሁ በቃ😁😁
የኢየሱስ ባህሪ አዎ አንድ ነው ግን ነጠላ አይደለም.. ነጠላ ካልሆነና ከሁለት የሆነ አንድ ከሆነ የሁለቱም ባህርያት መገለጫዎች ጸንተው ይሮናሉ..
በተዋሕዶ ጊዜ ሁለትነት የጠፋው የሥጋ የሆነውን እያጠፋ ሳይሆን አንዱ የአንዱን ሳያጠፋ በተአቅቦ ነው.. ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋው ፍጡረነቱን እንዳጣው የሚያስመስሉ መምህራንን አየሁ.. በእርግጥ የተቆራረጡ ቪዲዮዎችን ነው ያየሁት.. ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ አባታዊ ማስረጃ የቀረበባቸው ቪዲዮዎች አይደሉም.. ማስረጃ የሚገኝለትም አይመስለኝም..
ግን ደግሞ ይሄ እንዲህ ከቀጠለ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ስም የሚያጠለሽ መስሎ ስለታየኝ ከመጽሐፍ ቅዱስም ከአባቶችም አድርጌ በሰፊው ልስራበት ብዬ አሰብኩ..
ምን ታስባላችሁ ሰፊ ነገር ልስጣችሁ ወይስ ይብራ..??
መልሶቻችሁን አየሁት.. በጣም ነው ደስ የምትሉት ማርያምን.. ብዙ ታውቃላችሁ.. ጌታ እውቀታችሁን ሕይወትም ደግሞ ያድርግላችሁ.. በርቱልኝ
ስለዛ በአጭሩ አምስቱ አእማደ ምስጢራትን አምኖ.. “ጸሎተ ሃይማኖት” የምንለውን የኒቂያውንና የቁስጥንጥንያውን ጉባኤ የሃይማኖት መግለጫ በእምነት የሚመሰክር.. እርሱ ይጠመቃል ቅዱስ ቁርባንም ይቀበላል..
ከዚያም ሌሎችን ደግሞ ቀስ እያለ እያመነ ይሄዳል.. ታድያ ግን ልቡን ክፍት ማድረግም አለበት..
@Apostolic_Answers
አንድ ሰው ወደ ክርስትና መምጣት ቢፈልግና ሁሉን አምኖ ግን የእመቤታችንን ሥጋ ፍልሰት መቀበል ቢከብደውስ..??
ዌል ሥጋዋ ላለመፈለሱ ምንም ማረጋገጫ ስለሌለው ቢያንስ በሁሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትም ስለሚታመን ነገሩን ሳይቃወም እንዲሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይቀላቀላል ከዚያም በጌታ እርዳታ በጸሎትም ወደ ማመን ይምጣ..
ይህንን ማመን ስለከበደው ብቻ አናስቀረውም ማለት ነው ከጌታ ቤተ ክርስቲያን.. ግን እንዲያምን ማስረዳት ያለብንን ሁሉ እናስረዳዋለን
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
“በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።”
[2 ጢሞ 2: 2]
ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ነገር..
1. የክርስትና ትምህርት ሐዋርያት ጋር ብቻ አይቀርምና ለተማሪዎቻቸው ያስተላልፉታል.. ስለዚህም “በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን” ይለዋል
2. ይኸው ትምህርት ደግሞ ከሐዋርያት ተማሪዎችም ወደ ቀጣዮቹ እየተላለፈ ይሄዳልና ጢሞቴዮስን “ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ” ይለዋል
3. አደራ የሚሰጣቸው ሰዎች ደግሞ የታመኑ እና ሌሎችን ሊያስተምሩ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው ይናገራል.. ይህ ደግሞ ትምህርቱ በታማኝነት ወደቀጣይም ሲተላለፍ እንደሚኖር አመልካች ነው.. ጌታችን ኢየሱስ “እስከ ዓለም ፍፃሜ ሁል ጊዜ ከ እናንተ ጋር ነኝ” በማለቱ እስከ ዓለም ፍጻሜ መቀጠሉ የማይቀር ነው.. ጠባቂውም መንፈስ ቅዱስ ነው
4. ይህ የሚተላለፍ የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን በብዙ ምስክሮች ፊት የተሰማ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ነው.. እርግጥ በኋላ በጽሑፍ ያለውም ይተላለፋል(2ተሰ 2:15)
ማጠቃለያ:
የክርስትና ትምህርት በዚህ መልኩ እየተላለፈ የሚሄድ ከሆነ ማንም ሰው እንደ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስን እያነበበ በራሱ መረዳት አዳዲስ ትምህርቶችን ማምጣት አይችልም ማለት ነው..
@Apostolic_Answers
ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት ለድኀነት እንደሚያስፈልግ አያስተምርም ካለ አንድ ሰው በቃ “መጽሐፍ ቅዱስ” እያለ የሚጠራው የራሱን መረዳት ነው..
ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የእግዚአብሔር ቃል ብለው የሚጠሩት መጽሐፉን አንብበው ከዛም ራሳቸው የተረዱትን መረዳት ነው.. የሰው መረዳት እንዴት መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ ይጠራል..??
ኧረ እቺ አገላለጽ ራሱ ተገልጣልኝ ነው መሰል ወገን😁😁
ንጉሥ ዳዊት በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ:
“ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው?”
[2ሳሙ 7:18]
ብቸኛው ልጅህን ኢየሱስን እስክትሰጠን ድረስ እንዲሁ የወደድከን ኸረ እኛ ማን ነን..?? እንደ ስንፍናችን ሳይሆን በምህረትህ የጎበኘኸን ሁሌም የምትታገሰን እኛ ማን ነን..??
ይህንን ስናስረዳና ሰዎችን ለማገዝ ስንሞክር ከሥር ከሥር የምታበላሹ ወንድሞች ተዉ ፍቱን😭😁
1. የሃይማኖት መከራከሪያ የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እና ትምህርቶች የተብራሩበት የሊቃውንት መጽሐፍት ናቸው.. (ማስረጃ ለምሳሌ አድማሱ ጀንበሬ መድሎተ አሚን እና የቦሩ ሜዳው ነገር)
2. ገድላት ተዓምራት ኦሪጅናሎቹም ቢገኙ ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል.. infallible የሚባለው መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው..
ቅዳሴ tip 1 ይልሃል😁😁
የቅዳሴ ቀን ሌሊት ስትነሱ ትንሽ ደቂቃ ቀደም ብላችሁ ተነሱና የተረጋጋ መዝሙር ስሙ.. እና መዝሙሩ ሥጋችንን ብቻ ሳይሆን መንፈሳችንንም ያነቃቃዋል..
በሉ ነገ ቅዳሴ ላይ እና ከዛም በኋላም እንገናኝ.. መልካም አዳር
“ገድላት” ምናምን የሚሉ ተሃድሶዎች የሚጠሩን ወደ ሃሰተኛ ነቢያት እግር ሥር እንደሆነ ይመልከቱ..
ሲቀጥል የተአምራት መጽሐፍት ለሃይማኖት መከራከሪያ እንደማይሆኑ ከቦሩ ሜዳው ጉባኤ እነሆ
https://vm.tiktok.com/ZMMukMHvm/
—————————————
የተለያዩ ርእሶች ላይ አባቶች ምን አሉ የሚለውን እንዴት በቀላሉ ማወቅ እንችላለን..??
Website recommendation
https://vm.tiktok.com/ZMMmsrNJr/
2ኛ ቆሮንቶስ 11
2፤ በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
ይህን ጥቅስ ጠቅሶ አንድ “ሊቀ ጠበብት ዶር” ሲናገር ከሰማሁትና እንዴት እንዴት ነው የሚያመሰጥረው ያስባለኝ ድንቅ ትርጓሜ:
1. እዚህ ላይ “እንደ ንጽሕት ድንግል” የተባለችው እመቤታችን ናት (ዋው ሎል)
2. ለዮሴፍ ታጨች የተባለውም ልክ እጩ ዶክተር እንደሚባለው ነው.. ለጋብቻ እንደሚነገረው ዓይነት እጮኝነት አይደለም..
🤭🤭 ካመሰጠሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ ኤታባቱ