ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“እርሱም፦ ‘መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ’ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።”
[ዮሐንስ 21: 6]
ጌታችን ጀሞት ከተነሳ በኋላ ደጋግሞ ተገለጠ.. አሁን የተገለጠው በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ነው.. እና እነዚህ አሥ አጥማጅ ሐዋርያትም በዛን ለሊት ብዙ ቢታገሉም ምንም ሊያጠምዱ አልቻሉም ነበር..
እና ጌታችን መጥቶ “መረቡን በስተቀኝ ጣሉት” አላቸው.. እነሱም እንዲሁ አደረጉና ለማውጣት እስኪከብዳቸው መረቡ በዓሣ ተመላ.. ዮሐንስም ይሄኔ “ጌታ እኮ ነው” አለ.. ጴጥሮስም ራሱን ወዳ ባህር ጥሎ ወደ ጌታ ሮጠ..
ድኀነትን የተጠሙ በዓለም ያሉትን ዓሣዎች ወደ መረብ(ቤተ ክርስቲያን) ለማጥመድ የአገልጋይ ድካም ብቻውን ዋጋ የለውም.. የጌታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የፕሮቴስታንት መዝሙርን መስማት የማይገባን ምክንያት ሁለተኛ ማጠናከሪያ አሳብ..
https://vm.tiktok.com/ZMMo6j8yF/
ጌታችን ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ሞተ በእርሱ በኩል የተሠራው የማዳን ሥራ ለየትኛውም ሰው ነው.. ግን ደግሞ ይህንን የእርሱን የማዳን ሥራ ለማግኘት ሰዎች አሜን ብለው መቀበል አለባቸው.. ካላመኑ ድኀነቱን አያገኙም.. ይልቁንም በብሉይ ኪዳን እንደነበሩ ሰዎች አዳማዊያን ብቻ ሆነው ይኖራሉ.. ይህ ከባድ ቁስል የሚፈወሰው በኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም አይደለም..
ቅዱስ ሄራንዮስ እንዲህ ይላል:
“በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ ሆኖ ወደ ሰማእትነት እንጨት ላይ ከምድር ከፍ ባለው(ኢየሱስ) በእርሱ በማመን ሰው ከቀደመው የእባብ ቁስል እንዲድን እንጂ በሌላ መንገድ አይሆን ዘንድ..”
[Against heresies bk. 4: chap 2: sec 8]
አንድ እዚሁ ግሩፕ ላይ ያለ ወዳጃችን “እስቲ ጥያቄ ጠየቅህ ያሸነፈ የዓመት ቴሌግራም ፕሪምየም ልሸልም” አለኝ..
ዌል ይሄ የ50 ወይም የ100 ብር ካርድ አይደለም ስለዛ ቀለል አድርገን ጠይቀን አናልፈውም.. ይልቁንም እኔ አንድ አሳብ አሰብሁ..
አንድ ትንሽዬ መጽሐፍ አለች ከሷ የተወሰነ ክፍሏን በደንብ እንድታነቡና ከዛ ይወጣል ጥያቄው.. ከዛ ያሸነፈ ይሸለማል.. ምናልባት 2 እና 3 የሚወጡትንም ማበረታቻ ወይ እኔ እሸልማቸው ይሆናል.. ያው ምናልባት😁😁
በዛውም ያንን ጽሑፍ እንድታጠኑ ያደርጋችኋል ማለት ነው..
ወይስ ሌላ የተሻለ አሳብ አላችሁ
ለወዳጆቻችሁ ሥጦታ መስጠት ፈልጋችሁ ግን ደግሞ ምን መስጠት እነዳለባችሁ ግራ ሊገባችሁ ይችላል.. እና ለሥጦታ ምናምን ክራፍቶች ደስ ይላሉ.. መኖሪያ ቤትንም ሆነ ቢሮን ስለሚያስውቡ ለራሳችንም ልንጠቀምባቸው እንችላለን..
እና በጣም ሚያማምሩ ክራፍቶችን ልታገኙ የምትችሉበትን ቦታ ልጠቁማችሁ መጣሁ.. ተቀላቀሏቸውና አሁን ባትፈልጉ ራሱ ሲያስፈልጋችሁ ትጠቀሙታላችሁ.. ያው አዲስ ቴሌግራም ከፍተው ነው..
👇👇👇👇
@hanicraft00
@hanicraft00
ተቀላቀሏቸው.. ስልካቸው ባዮዋቸው ላይ አለላችሁ ስትፈልጓቸው😎
የሃይማኖት ችግር ተገኝቶብኝ አይደለም ተሃድሶ የተባልኩት ነበር ያለው..??😁😁
ሌዲስ ኤንድ ጀንታላ ሜን.. ዊ ጋት ሂም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMMv23HVM/
አንዱ ብሮ ቴሌግራም ላይ ጽፎልኝ ያው ብዙ ስለሚላክ አጋጣሚ አላየሁትም እና እንዳየው ምን ቢያደርግ..?? ቴሌግራም የዓመት premium 🎁 ላከልኝ.. ምን ጉድ ነው ብዬ ሳየው ይኸው እያወራኝ ነው.. ጉበኛ ሰው ነው😁😁
አሁን በቃ የምጠቀማቸው ኢሞጂዎች ራሱ እናንተ መጠቀም የማትችሏቸውን ነው😁😁
ከጉባኤ ኬልቄዶን በኋላ ከተነሱ ድንቅ የተዋሕዶ ነገረ ክርስቶስ(miaphysite christology) ተንታኞች ውስጥ ግምባር ቀደሙ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ነው.. ግባዔ ኬልቄዶን ከተደረገ ከ15 ዓመት በኋላ የተወለደ ነው.. እና ከቄርሎስ በኋላ በሚገባ ነገረ ክርስቶስን ያብራራ ሰው ነው.. ለኬልቄዶናውያንም ብዙ መልስን መልሷል..
እና ኬልቄዶንን እንደ ንስጥሮሳዊ ጉባዔ ስለሚያየው “የኬልቄዶን ደጋፉዎችን(አባቶችን) የሚያያቸው የአውጣኪያዊነትን ሰይጣን በንስጥሮሳዊ ብዔልዜቡል ለማውጣት እንደሚሹ ሰዎች ነበር” 🤭🤭 ይመቸው..
በረከቱ ይደርብን የዚህ ሊቅ ቅዱስ አባት
@Apostolic_Answers
ዌል አሁን ደግሞ ጺማችንን እንቆረጣለን.. ምክንያቱም የራሳችን ወንድሞች እውነተኛው ፍየል(the real GOAT) ይሉን ጀመር
https://vm.tiktok.com/ZMMnwcKkj/
ክርስቶስ ተንሥአ እምውታን በአብይ ኃይል ወሥልጣን
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:
“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት(የመጀመሪያ) ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።”
[1ኛ ቆሮንቶስ 15: 20]
ሞት ኢየሱስን ሊይዘው አልቻልም.. ጌታችን ሞትን ያለበት ድረስ ሄዶ ኃይል አሳጣው.. እርሱ ራሱ በባህሪው መሞት መነሳት ያልነበረበት ሲሆን በፈቃዱ ስለ እኛ ሲል ሞተ ተነሣም.. ኢየሱስ የትንሳኤያችን በኩር ነው.. እርሱ ተነስቷልና እኛም እንነሣለን..
ስለርዚህም የእርሱ ትንሳኤ ትንሳኤያችን ነው
እኛስ የተሰቀለውን ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንሰብካለን
እንኳን አደረሳችሁ እናንት የእግዚአብሔር ምርጦች
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..
የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፡ እያሉ ጮኹ።
[ዮሐንስ 12: 13]
የጌታችንን ንግሥና እየመሰከረች ኢየሩሳሌም ተቀበለችው.. እርሱም ወደ እርሷ ትሁት ሆኖ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ገባ..
ዛሬም እኛም ኢየሩሳሌምን መስለን የክብርን ጌታ እንደ ንጉሥ ወደ ልባችን ይገባ ዘንድ እንቀበለው.. እርሱም እንደ ትህትናው ወደ እኛ ልብ ይግባ በልባችንም ይንገስ..
መልካም የንጉሣችን ቀን
@Apostolic_Answers
ፕሮቴስታንት መምህራን ቲክቶክ ላይ የመጨረሻ አማራጫቸውን እየተጠቀሙ ይመስላል😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMMgaXLL7/
አበበ:- እመቤታችን አምላክን ስትወልድ በክብር ላይ ክብር ሆኖላት ታላቅ ክብርን አገኘች.. ትልቁ ክብሯ ወላዲተ አምላክ መሆኗ ነው
ገረመው፣ ደጀኔ እና ቶላ:-ኢየሱስን ስትወልድ አስቀድሞ ያልነበረ ክብርን አገኘች..?? እግዚኦ ምንፍቅና
ምንፍቅና..??
ነቃ ደንገጥ ቆፍጠን ብለን እናንብብ እንማር እንጂ ወገን 😁😁 ከሥር ከሥር ክርስቲያኑን የሚያውኩት ላይ እንዝመትባቸው እንዴ ፕሮቴስታንቱን ትተን😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..
የሉቃስ ወንጌል 24
43፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ።
ጌታችን ከሙታን ከተነሣ በኋላ በደቀመዛሙርቱ ፊት ምግብን በላ.. የትንሣኤ ሥጋን ይዞ ምግብን የበላው ግን እኛም ሞተን ስንነሣ እየበላን ስለምንኖር ነው..?? ወይም የትንሣኤ ሥጋ ምግብ ያስፈልገው ይሆን..?? ጌታም በሌላ ክፍል እንደነገረን በትንሣኤስ ሁላችን እንደ መላእክት እንኖራለን እግዚአብሔርን እያመሰገንን ብቻ..
👉 ይህ ነገር አሁን በደካማው ሥጋችን ስናስበው የማያስደስት ሊመስለን ይችላል.. ያኔ ግን በትእሣኤ ሥጋ ስንሆን ጭራሽ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ በጌታ የሆነ ደስታ ይሞላናል.. ፍጹም የሆነ የማይጎድል.. አሁንም በጭላንጭል ከቅዱስ ቁርባን እየተሳተፍን experience እናደርገዋለን.. በጭላንጭል ያልሁት አሁን ላይ በድካም ውስጥ ስለምንሆንም ከሚመጣው አንጻር ነው.. እንጂ አሁንም በጌታ የሆነ ደስታ ከእኛ ጋር ነው
ጌታችንም እዚህ ጋር የተመገበው ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ማመን ከብዷቸው ስለነበር ምትሃት መስሏቸው ነበርና በሥጋ እንደተነሣ ለማስረገጥ ነው.. ለዛ ነው ከፍ ብሎ እዛው ላይ እንዲህ የሚለው..
“እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና 👉ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፦ በዚህ አንዳች 👉የሚበላ አላችሁን? አላቸው።”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
አንዳንድ ክርስቲያኖች ላይ የማየው ድክመት..
በጭፍን እንዲሁ መምህር የተባለውን ሁሉ መከተል ስህተት ውስጥ እንድንወድቅ ያደርጋል.. የሆነ ርእስ ላይ ጥያቄ ከፈጠረባችሁና መላሹ ሲመልስ “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” ብሎ የሚመልስ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከአባቶች ሰፋ ያለ ማስረጃ እንዲያቀርብ 👉ጠይቁት..
ሰፋ ያለ ማስረጃ ከሁለቱ ማቅረብ ካልቻለ ቢያንስ ለጊዜው የራሱ የሰውዬው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ብላችሁ አትያዙ.. ቅዱስ ትውፊት የሁሉም መመዘኛ ነው..
@Apostolic_Answers
በቃ የምታነቡትንና ከዛም የምትፈተኑበትን መጽሐፍ ልጠቁማችሁ..
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ..
እስከ ገጽ 90 ድረስ ያለውን.. በጣም ትናንሽ ናት ገጿ.. ስለዛ በርትታችሁ በጣም ተረጋግታችሁ በማስተዋል አንብቧት.. በጣም ትጠቀማላችሁ ማርያምን..
መጽሐፉ የልላችሁ PDF ከታች አስቀምጣለሁ.. አልያም ግሩፕ ላይ
ሽልማቱ እንደተጠበቀ ነው👍👍
በጣም ሃሪፍ.. አሁን ደግሞ ስለ ኢየሱስ ማውራቱ(ማስተማሩ) እንዳለ ሆኖ ግን ደግሞ ወደ ኢየሱስም እንይ.. ስለ እሱ ስናወራ ሳይሆን እሱን ስናየው ነው እሱ ውድ ሌላው የሚያጓጓን ሁሉ ደግሞ ርካሽ የሚሆንብን..
ኢየሱስ እኮ ምን ያህል ባለጠግነታችን እንደሆነ ይህ እምነት ከውስጣችን ጋር በደንብ ስላልተዋሐደ ነው ስለ ሃብት አብዝተን ምንጨነቀው..
ኢየሱስን ማየት ስናቆም ሙሉ በሙሉ አስተሳሰባችን ምድራዊ ብቻ ይሆናል.. ስለ ኢየሱስ አውርተን እውቅናን ማግኘት እንጂ በኢየሱስ መታወቃችን ትዝ አይለንም..
ነፍሳችን ኢየሱስን መናፈቅ መጀመር አለባት.. ከመዝሙረኛው ጋር ሆነን እነዲህ ልንል ይገባል:
“ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥
አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። “
ከጌታ ሥጋና ደም መራቃችን በጣም እየጎዳን ነው ወዳጆቼ..
ቆራጥ እንሁን.. ወደ ቅዱስ ምስጢር ስለ መቅረብ አሁን ማሰብ እንጀምር.. በምህረቱም እንቅረብ.. አለዚያ ግን እግዚአብሔርን የመምሰል ሕይወት ከየትም አይመጣም..
እንግዲህ ተስፋችን እርሱው ጌታችን ነውና በምህረቱ ያቅርበን ያስበን
@Apostolic_Answers
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖቷን ዘርዝራ እንደ ካቶሊክ አላስቀመጠችም ስለዛ ሃይማኖቷ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ያስቸግራል ለሚሉ..
እኛ በ እርግጥ እያንዳንዱን ነገር define እናድርግ አንልም.. ግን ደግሞ ሃይማኖታችን በተገለጠልን ልክ በግልጽ ተነግሯል.. ለምሳሌ የኒቂያው እና የቁስጥንጥንያው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የተደነገገው ሁሌም የምንጸልየው “የሃይማኖት ጸሎት) እሱ ነው ሃይማኖታችን..
እዛ ላይ የተነገሩት ደግሞ በስፋት በጥንታውያን አባቶች ለምሳሌ በቅዱስ አትናቴዎስ በኩልም ተብራርተዋል.. ከዛ በተረፈ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ 5ቱ ዓዕማድ ምስጢራት ተብሎ የሚሰጥ ትምህርት አለ እሱንም መመልከት..
@Apostolic_Answers
“ሉተርን ተቹ” ብለው የሚከሱ ሰዎች ካልቪንን ሲከሱ😁😁
ትንሽ ሲበሳጩ የሚሰድቧቸው አባቶች ነው ያሏቸው አንዳንዶቹ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMM7FANgW/
የፕሮቴስታንት እምነትን እንድንጠየፈው ከሚያደርጉን ምክንያቶች(ሰዎች) መካከል🤦♂️🤦♂️
https://vm.tiktok.com/ZMMWQotrs/
የየኔታ በትረማርያም ማብራሪያ
ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክም ሰውም እንዳልነው ሁሉ ፈጣሪም ፍጡርም እንለዋለን። ይህንንም ግልጽ በሆነ አነጋገር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጽፎልናል። "ፍጡር ወኢፍጡር" እንዲል (ሃይ. አበ. ፴፭)። ፍጡር ሥጋ ፍጡርነቱን ሳይለቅ ፈጣሪ ሆነ። ፈጣሪ መለኮትም ፈጣሪነቱን ሳይለቅ ፍጡር ሆነ። በሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፴፮ እንደተገለጸው ኢያፍለሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ ወኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር ተብሏል። ፍጡር ሥጋ ፍጡርነትን ሳይለቅ ፈጣሪነትን ገንዘብ አድርጓል። መለኮትም ፈጣሪነትን ሳይለቅ ፍጡር ሥጋን ገንዘብ አድርጓል።
ይህ የየቀድሞ ማንነትን ሳይለውጡ ሌላውን ገንዘብ ማድረግ ተዋሕዶ በተዐቅቦ ይባላል።
ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ይባላል። ይህም ማለት ሥጋው ቅድመ ዓለም የነበረ ሳይሆን የተፈጠረ ነው ማለት ነው።
አርዮስ ክርስቶስ በመለኮቱ ፍጡር በማለቱ ታላቅ ክሕደትን ካደ። ለዚህም ሠለስቱ ምእት በመለኮቱ ፈጣሪ መሆኑን ለመግለጽ ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ብለው መልሰውለታል። በሥጋው ፍጡር እንደሆነ ግን እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስና ሌሎችም ቅዱሳን ሊቃውንት የጻፉት ነው። አንዳንዱ ክርስቶስን አምላክም ሰውም፣ ፈጣሪም ፍጡርም ስንለው እንደ ካቶሊክ የምንታዌ ትምህርት አድርገው ያስቡታል። ግን ስሕተት ነው። አንድን ሰው በነፍሱ ረቂቅ በሥጋው ግዙፍ ስንለው ሁለት እያደረግነው አይደለም። ያው አንዱ አካል ረቂቅም ግዙፍም መሆኑን መግለጽ ነው እንጂ።
አንዳንዶች ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋ ፍጡርነቱን ለቋል የሚሉ አሉ። ነገር ግን ሃይ. አበ. ፴፮ ላይ በግልጽ ተጽፏል። ሲዋሐድ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረውን እንቲኣሁነት (የራሱን ገንዘብነት) ሳይለቅ ነው። በተዋሕዶ ጊዜ ፈጣሪ ቃል ወደፍጡር ሰውነት አልተለወጠም። ፍጡር ሥጋም ወደ ፈጣሪ መለኮት አልተለወጠም። አይ ከተዋሕዶ በኋላ ፈጣሪ ብቻ እንለዋለን ከተባለ ግን ይህ የአውጣኪ ክሕደት ነው። መለኮት ሥጋን ውጦታል ያሰኛል። ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሰው ካልነው ፍጡርም እንለዋለን ማለት ነው። ሰው ስንለው ግን እንደሌላው ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻ) አንለውም። አምላክም ሰውም ፈጣሪም ፍጡርም እንለዋለን እንጂ።
© በትረማርያም አበባው
(የመጻሕፍተ ሊቃውንት የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ መምህር)
@betremariyamabebaw
@betremariyamabebaw
☝️☝️☝️☝️
የሳቸው ቴሌግራም ቻናል ነው ተቀላቀሏቸውና ሌሎችንም ትምህርቶች አግኙ
ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ.. በጌታ ስም የሚምጣ የተባረከ ነው
መሲሕ ኢየሱስ አድነን(ሆሣዕና).. በአህያ ላይ ተቀምጠህ በጌታ ስም የመጣህ የተባረክ የዳዊት ልጅ ሆይ ሆሣዕና አንተ መድኃኒት ነህና
ከቅዳሴ ምናምን በኋላ እንገናኝ እንዳትቀሩ ከቅዳሴ😊🤗
በመዝሙር ዜማ ዘፈን ዘፍነው ነው መሰለኝ ያው ይቅርታ እያሉ ነው..
ግን ምን አሳቀኝ መሰላችሁ.. “መዝሙር አልመሰለንም ነበር የአራዳ ሙዚቃ መስሎን ነበር”🤣🤣 ጭራሽ..
ግን ይሄ ነገር ኖርማል መዝሙር ነው ወይስ በዓላዊ ዘፈን..?? እኔ ራሴም አላውቀውም😁😁