ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:
“በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።”
[ሮሜ 10: 2]
ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እስራኤላውያን እጅጉን ተጨንቋል.. አሕዛብ እንኳን ክርስቶስን በማመን ወደ እግዚአብሔር ሕዝብነት ሲጨመሩ የእግዚአብሔር የተመረጠ የኪዳን ሕዝብ የተባለው ያ ታላቅ ሕዝብ እስራኤል ግን የነቢያት ሁሉ ተስፋ የሆነውን መሲሕ ባለመቀበል ከኪዳኑ ሊወጡና ሊጠፉ ነው.. ስለዚህም ጳውሎስ ስለ እነርሱ ተጨንቆ: “ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው።” ይላል ከላይ..
ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ይቀናሉ.. ጳውሎስም(የጠርሴሱ ሳውል) ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆኖ ለአባቶች አምላክ ተቀንቶ ክርስቶስን ሲያሳድድ ነበር ያው ጌታ ሳያገኘው በፊት.. እስራኤል ለእግዚአብሔር ያላቸው ቅንአት ጥሩ ቢሆንም ግን ደግሞ ይህ ቅንአት ያለ እውቀት ነበር.. ስለዚህም ጳውሎስ ምን አለ..?? “በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።”
እና የኔ ተወዳጆች ክርስቲያኖችም ለጌታችን ወይም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለተሰጠን ሃይማኖት በጣም ቅንአት አለብን.. በጣም መልካምም ነው.. ግን ደግሞ በእውቀት መሆን አለበት..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
አንድ ወዳጄ እንዲህ አለ:
የክርስትና ትምህርትን(ስነ መለኮት) መማር ማለት የሆኑ ትምህርቶችን ሰምቶ ሰምቶ እንደው ጭንቅላት ውስጥ የማስቀመጥ ነገር አይደለም.. ሳይንስና ፍልስፍናን ስትማርም ይህንን ነው ምታደርገው..
ስነ መለኮት ስትማር ውስጥህን ሊዋሐደው ይገባል ቃሉ.. ይህ የሚሆነው ደግሞ እግዚአብሔርን ስትቀርበው ነው.. ይህንን ያለ ቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ማግኘት አይቻልም.. ስትጸልይ ስትቆርብ ጌታ(የአብ ቃል) በአንተ አንተም በጌታ ስለምትሆን እግዚአብሔር በደንብ ይገለጥልሃል.. ኦርቶዶክሳዊ መረዳትም እየኖረህ ይሄዳል..
አልያ ግን አይተሃል አንዳንዱ ብዙ ዓመት ተምሪያለሁ ብሎ ኋላ ግን ጌታን ይክደዋል.. ይሄ የተነገረውን ወይም ያነበበውን እንደ ፍልስፍና እና ሳይንስ ጭንቅላት ውስጥ ብቻ አከማችቶ የያዘና የሆነ የተሻለ የሚመስል ነገር ሲመጣበት የሚወድቅ ነው.. ወይም ሲናገርም ከዚህ በፊት ካስቀመጠው ብቻ እንጂ ቃሉ ተዋሕዶት አይደለም..
ዌል ገዢ አሳብ ይመስለኛል..
"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"
"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"
"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"
ዲ/ን ያረጋል
እውነት ነው እንዴ ጋይስ..??
ስፖርት መስራት ፈልጌ አንዱ ጀለስ “ክብደት ማንሳት አእምሮን ይደፍናል ይባላል.. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶቹ እንዳይጠፉብህ” አለኝ🙄🙄
“ወደ ቅድስት ጠረጴዛ(መሠዊያ) ቅረብ: እሳት እንደሚያጋሳ አንበሳ ለሰይጣን አስፈሪ ሆነህም ተመለስ”
ይሄንን ጸዴ አንበሳ ሳየው ትዝ አለኝ ከላይ ያለው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አባባል
የሚያስሸልመው ጥያቄ ነገ ማታ 2:00 ነው የሚሆነው.. በሉ ተዘጋጁ..
“የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በአቡነ ጎርጎርዮስ.. ገጽ 1-90
ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች.. ወንድማችን “መሸ” research እየሰራ አንድ ጉዳይ ላይ እስቲ የምትችሉ ሰዎች ከታች ያለውን ፎርም ሊንክ ውስጥ ገብታችሁ ሙሉለት.. ጥያቄዎቹን እያነበባችሁ ታዲያ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScgni-IwfQIaA_-e0rO0Gbd2buMEHJIl0DKmqKQTAVXqIzTpQ/viewform?usp=pp_url
አበበ:- እመቤታችን አምላክን ስትወልድ በክብር ላይ ክብር ሆኖላት ታላቅ ክብርን አገኘች.. ትልቁ ክብሯ ወላዲተ አምላክ መሆኗ ነው
ገረመው፣ ደጀኔ እና ቶላ:-ኢየሱስን ስትወልድ አስቀድሞ ያልነበረ ክብርን አገኘች..?? እግዚኦ ምንፍቅና
ምንፍቅና..??
ነቃ ደንገጥ ቆፍጠን ብለን እናንብብ እንማር እንጂ ወገን 😁😁 ከሥር ከሥር ክርስቲያኑን የሚያውኩት ላይ እንዝመትባቸው እንዴ ፕሮቴስታንቱን ትተን😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..
የሉቃስ ወንጌል 24
43፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ።
ጌታችን ከሙታን ከተነሣ በኋላ በደቀመዛሙርቱ ፊት ምግብን በላ.. የትንሣኤ ሥጋን ይዞ ምግብን የበላው ግን እኛም ሞተን ስንነሣ እየበላን ስለምንኖር ነው..?? ወይም የትንሣኤ ሥጋ ምግብ ያስፈልገው ይሆን..?? ጌታም በሌላ ክፍል እንደነገረን በትንሣኤስ ሁላችን እንደ መላእክት እንኖራለን እግዚአብሔርን እያመሰገንን ብቻ..
👉 ይህ ነገር አሁን በደካማው ሥጋችን ስናስበው የማያስደስት ሊመስለን ይችላል.. ያኔ ግን በትእሣኤ ሥጋ ስንሆን ጭራሽ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ በጌታ የሆነ ደስታ ይሞላናል.. ፍጹም የሆነ የማይጎድል.. አሁንም በጭላንጭል ከቅዱስ ቁርባን እየተሳተፍን experience እናደርገዋለን.. በጭላንጭል ያልሁት አሁን ላይ በድካም ውስጥ ስለምንሆንም ከሚመጣው አንጻር ነው.. እንጂ አሁንም በጌታ የሆነ ደስታ ከእኛ ጋር ነው
ጌታችንም እዚህ ጋር የተመገበው ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ማመን ከብዷቸው ስለነበር ምትሃት መስሏቸው ነበርና በሥጋ እንደተነሣ ለማስረገጥ ነው.. ለዛ ነው ከፍ ብሎ እዛው ላይ እንዲህ የሚለው..
“እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና 👉ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፦ በዚህ አንዳች 👉የሚበላ አላችሁን? አላቸው።”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
አንዳንድ ክርስቲያኖች ላይ የማየው ድክመት..
በጭፍን እንዲሁ መምህር የተባለውን ሁሉ መከተል ስህተት ውስጥ እንድንወድቅ ያደርጋል.. የሆነ ርእስ ላይ ጥያቄ ከፈጠረባችሁና መላሹ ሲመልስ “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” ብሎ የሚመልስ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከአባቶች ሰፋ ያለ ማስረጃ እንዲያቀርብ 👉ጠይቁት..
ሰፋ ያለ ማስረጃ ከሁለቱ ማቅረብ ካልቻለ ቢያንስ ለጊዜው የራሱ የሰውዬው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ብላችሁ አትያዙ.. ቅዱስ ትውፊት የሁሉም መመዘኛ ነው..
@Apostolic_Answers
በቃ የምታነቡትንና ከዛም የምትፈተኑበትን መጽሐፍ ልጠቁማችሁ..
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ..
እስከ ገጽ 90 ድረስ ያለውን.. በጣም ትናንሽ ናት ገጿ.. ስለዛ በርትታችሁ በጣም ተረጋግታችሁ በማስተዋል አንብቧት.. በጣም ትጠቀማላችሁ ማርያምን..
መጽሐፉ የልላችሁ PDF ከታች አስቀምጣለሁ.. አልያም ግሩፕ ላይ
ሽልማቱ እንደተጠበቀ ነው👍👍
በጣም ሃሪፍ.. አሁን ደግሞ ስለ ኢየሱስ ማውራቱ(ማስተማሩ) እንዳለ ሆኖ ግን ደግሞ ወደ ኢየሱስም እንይ.. ስለ እሱ ስናወራ ሳይሆን እሱን ስናየው ነው እሱ ውድ ሌላው የሚያጓጓን ሁሉ ደግሞ ርካሽ የሚሆንብን..
ኢየሱስ እኮ ምን ያህል ባለጠግነታችን እንደሆነ ይህ እምነት ከውስጣችን ጋር በደንብ ስላልተዋሐደ ነው ስለ ሃብት አብዝተን ምንጨነቀው..
ኢየሱስን ማየት ስናቆም ሙሉ በሙሉ አስተሳሰባችን ምድራዊ ብቻ ይሆናል.. ስለ ኢየሱስ አውርተን እውቅናን ማግኘት እንጂ በኢየሱስ መታወቃችን ትዝ አይለንም..
ነፍሳችን ኢየሱስን መናፈቅ መጀመር አለባት.. ከመዝሙረኛው ጋር ሆነን እነዲህ ልንል ይገባል:
“ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥
አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። “
ከጌታ ሥጋና ደም መራቃችን በጣም እየጎዳን ነው ወዳጆቼ..
ቆራጥ እንሁን.. ወደ ቅዱስ ምስጢር ስለ መቅረብ አሁን ማሰብ እንጀምር.. በምህረቱም እንቅረብ.. አለዚያ ግን እግዚአብሔርን የመምሰል ሕይወት ከየትም አይመጣም..
እንግዲህ ተስፋችን እርሱው ጌታችን ነውና በምህረቱ ያቅርበን ያስበን
@Apostolic_Answers
ጌታችን ኢየሱስ ለእመቤታችን ሞቷል አልሞተም ሲባል ለሷ አልሞተም የሚል ሰውም እየሰማን ነው.. ኧረ እንደው ፍቱን እንደው ቢያንስ በሆዳችሁ ያዙት..
Immaculate conception የተባለን ትምህርት ዶግማዋ ያደረገች የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ራሱ አልሞተላትም ስትል አይሰማም.. እንደውም ለሷም ሞቶላታል ግን የቀራንዮውን ሥራ አስቀድማ እንድታገኘው አደረጋት ይላሉ..
እኛ ሃገርም ከእነርሱ ተወስዳ በአንዳንዶች የምትሰጥ አባባል አለች አ.. አንድ ሰውን ጉድጓድ ውስጥ ሳይገባ በፊት ብታድነውም ከገባ በኋላ ብታድነውም ሁለቱም ማዳን ነው እንደውም የመጀመሪያው ማዳን የተሻለ ነው.. እመቤታችንንም በዛ መልኩ አድኗታል የምትል የካቶሊክ ወንድሞቻችን ማብራሪያ አለች..
እኛ ደግሞ ጭራሽ ለጥጠን የጌታ ሰው መሆንና መሞት ከእመቤታችን ጋር አይገናኝም እያልን እንዲሁ በድፍረት ባንናገር መልካም ነው.. ወይ አታንሱ እንዲህ ዓይነት ርእስ ጭራሹኑ.. በቃ ዝም ማለት
@Apostolic_Answers
በውስጥ የምጻጻፍበትን ቴሌግራም አካውንቴን ላጠፋው ስለሆነ በውስጥ አውርታችሁኝ ምናልባት ከኔ ጋር ያልጨረሳችሁት ነገር ካለ😁😁 ምናልባት በሆነ ጉዳይ ጠብቁኝ ምናምን ያልኳችሁ ካላችሁ አንዴ አስታውሱኝ በውስጥ ሳልደልተው በፊት.. እንዲሁ ላለማጥፋት ነው..
ያው ቻናል ላይ ምናምን እኖራለሁ እንቀጥላለን
አንዳንድ ስመ ጥር የሆኑ ታላላቅ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን የሆነ ጉዳይ ላይ የተናገሩትን በአንድ ወቅት ላይ አይቼ እኔ በዛ ሰዓት ከማስበው በጣም ርቆብኝ በጣም አስጨንቆኝ ነበር..
የልጅ ነገር ሆኖ ከርስትናን ራሱ ጥያቄ ውስጥ እስክከተውም አደረገኝ.. ግን በጣም ጌታ ረዳኝና ያየኋቸው የአባቶቼ አገላለጾች ለጥቅም ሆነልኝና ነገረ ማርያም ላይ የተለጠጠና ከልክ ያለፈ ነገር እንዳይኖረኝ አደረገኝ.. ከዛ በፊት በኔው ስህተት ባለማወቅ አንዳንድ ነገሮች ላይ የተለጠጠ ነገር ይዤ ነበር.. እና ቢያንስ ከዚ ጠበቀኝና ለጥቅም ሆነልኝ..
ግን ያኔ የተሰማኝ ስሜት በጣም ከባድ ነበር.. እና አንዳንዴ በግልጽ የሆነ ነገርን ስናገር ክርስቲያኖች ያንን ስሜት እንዳያዩትም በማሰብ ነው..
የኦርቶዶክስ ውበት የሚታየው ነገሮች ያልተለጠጡና ትውፊታዊ እስከሆኑ ብቻ ነው..
ቀባጠርኩባችሁ😁😁 መልካም ምሽት
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት:
“ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?”
[ሮሜ 6: 2]
ክርስትና በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት እንጂ እንዲሁ ድርጅት አይደለም.. ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ በ5ኛው ምእራፍ የእግዚአብሔር ጸጋ ከኃጢአት ይልቅ እንደበዛና ኃጢአትንም እንዲያሸንፍ ይናገራል.. ስለዚህም ከኃጢአት ሁሉ ነጻ የሚያወጣን ሆነ..
ታድያ ግን እዚህ ላይ አያቆምም.. በጥምቀት ከጌታ ጋር አንድ በመሆን የኢየሱስ ስንሆን በሞቱም ደግሞ በመምሰል ነው.. ይህም ከሞቱ ጋር ደግሞ አንድ በመሆን ለኃጢአት እንድንሞትና ለጽድቅ እንድንኖር ነው.. ይህ አዲሱ ሕይወት ነው.. ይህም ለእግዚአብሔር ልጆች እንደሚገባ ዓይነት ኑሮን የመኖር ሕይወት ነው..
አዲሱ ሰው እንዳይደክምና እንዳይወድቅ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ከእናቱ ከቤተክርስቲያን እየተመገበ ሊያድግና ሊጠነክር ይገባዋል..
ወገን ከቅዱስ ምስጢር ርቀን(ተርበን) በመንፈሳዊ ሕይወታችን ቀነጨርን እኮ😁😁 እያሰብንበት.. ጌታ በምህረቱ ያስበን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
“ማኅበረ ቅዱሳን” የተወደደው ማኀበር ሆይ.. አንድ መጽሐፍ በማኀበሩ በኩል ሲታተም.. በማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ “ታርሞ ተፈቅዶ” የወጣ የሚል ነገር መጽሐፉ ላይ ስናይ.. የምር ግን በምን ደረጃ ነው ምትመረምሩት..?? በዛ መጽሐፍ ውስጥ የሚተላለፈው ትምህርት ሁሉስ ማኅበሩን ይወክላል..?? እንደው ይህንን ነገር ላውቅ ወደድሁ..
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስለምትሰሩ ከእናንተ በተቻለ አቅም ጥርት እና ጽድት ያለ ነገር ነው ምንጠብቀው እወቁልን.. እግዚአብሔር ይህንን ማኅበር ይጠብቅ.. ሁሌም እርሱው ይስራበትም
@Apostolic_Answers
ሰው ከወኃ እንዴት ይወለዳል..?? ውኃን ከዚህ ነገር ጋር ማገናኘት አይከብድም..??
Well ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጣም የምወድለት መልሱ ለዚህ..
https://vm.tiktok.com/ZMrdDsC5p/
_______
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“እርሱም፦ ‘መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ’ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።”
[ዮሐንስ 21: 6]
ጌታችን ጀሞት ከተነሳ በኋላ ደጋግሞ ተገለጠ.. አሁን የተገለጠው በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ነው.. እና እነዚህ አሥ አጥማጅ ሐዋርያትም በዛን ለሊት ብዙ ቢታገሉም ምንም ሊያጠምዱ አልቻሉም ነበር..
እና ጌታችን መጥቶ “መረቡን በስተቀኝ ጣሉት” አላቸው.. እነሱም እንዲሁ አደረጉና ለማውጣት እስኪከብዳቸው መረቡ በዓሣ ተመላ.. ዮሐንስም ይሄኔ “ጌታ እኮ ነው” አለ.. ጴጥሮስም ራሱን ወዳ ባህር ጥሎ ወደ ጌታ ሮጠ..
ድኀነትን የተጠሙ በዓለም ያሉትን ዓሣዎች ወደ መረብ(ቤተ ክርስቲያን) ለማጥመድ የአገልጋይ ድካም ብቻውን ዋጋ የለውም.. የጌታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
የፕሮቴስታንት መዝሙርን መስማት የማይገባን ምክንያት ሁለተኛ ማጠናከሪያ አሳብ..
https://vm.tiktok.com/ZMMo6j8yF/
ጌታችን ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ሞተ በእርሱ በኩል የተሠራው የማዳን ሥራ ለየትኛውም ሰው ነው.. ግን ደግሞ ይህንን የእርሱን የማዳን ሥራ ለማግኘት ሰዎች አሜን ብለው መቀበል አለባቸው.. ካላመኑ ድኀነቱን አያገኙም.. ይልቁንም በብሉይ ኪዳን እንደነበሩ ሰዎች አዳማዊያን ብቻ ሆነው ይኖራሉ.. ይህ ከባድ ቁስል የሚፈወሰው በኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም አይደለም..
ቅዱስ ሄራንዮስ እንዲህ ይላል:
“በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ ሆኖ ወደ ሰማእትነት እንጨት ላይ ከምድር ከፍ ባለው(ኢየሱስ) በእርሱ በማመን ሰው ከቀደመው የእባብ ቁስል እንዲድን እንጂ በሌላ መንገድ አይሆን ዘንድ..”
[Against heresies bk. 4: chap 2: sec 8]
አንድ እዚሁ ግሩፕ ላይ ያለ ወዳጃችን “እስቲ ጥያቄ ጠየቅህ ያሸነፈ የዓመት ቴሌግራም ፕሪምየም ልሸልም” አለኝ..
ዌል ይሄ የ50 ወይም የ100 ብር ካርድ አይደለም ስለዛ ቀለል አድርገን ጠይቀን አናልፈውም.. ይልቁንም እኔ አንድ አሳብ አሰብሁ..
አንድ ትንሽዬ መጽሐፍ አለች ከሷ የተወሰነ ክፍሏን በደንብ እንድታነቡና ከዛ ይወጣል ጥያቄው.. ከዛ ያሸነፈ ይሸለማል.. ምናልባት 2 እና 3 የሚወጡትንም ማበረታቻ ወይ እኔ እሸልማቸው ይሆናል.. ያው ምናልባት😁😁
በዛውም ያንን ጽሑፍ እንድታጠኑ ያደርጋችኋል ማለት ነው..
ወይስ ሌላ የተሻለ አሳብ አላችሁ
ለወዳጆቻችሁ ሥጦታ መስጠት ፈልጋችሁ ግን ደግሞ ምን መስጠት እነዳለባችሁ ግራ ሊገባችሁ ይችላል.. እና ለሥጦታ ምናምን ክራፍቶች ደስ ይላሉ.. መኖሪያ ቤትንም ሆነ ቢሮን ስለሚያስውቡ ለራሳችንም ልንጠቀምባቸው እንችላለን..
እና በጣም ሚያማምሩ ክራፍቶችን ልታገኙ የምትችሉበትን ቦታ ልጠቁማችሁ መጣሁ.. ተቀላቀሏቸውና አሁን ባትፈልጉ ራሱ ሲያስፈልጋችሁ ትጠቀሙታላችሁ.. ያው አዲስ ቴሌግራም ከፍተው ነው..
👇👇👇👇
@hanicraft00
@hanicraft00
ተቀላቀሏቸው.. ስልካቸው ባዮዋቸው ላይ አለላችሁ ስትፈልጓቸው😎
የሃይማኖት ችግር ተገኝቶብኝ አይደለም ተሃድሶ የተባልኩት ነበር ያለው..??😁😁
ሌዲስ ኤንድ ጀንታላ ሜን.. ዊ ጋት ሂም😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMMv23HVM/