apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ደጋግማችሁ አትጻፉ በአንድ አድርጋችሁ ላኩ አልኩ እኮ.. አይሰማም እንዴ..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኢየሱስ እስከ 30 ዓመቱ ድረስ ጡት ጠብቷል..??🤦‍♂️🤦‍♂️

ባይሆን የእናንተን እንየው😎

https://vm.tiktok.com/ZMr6Wayuy/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ ወዳጆቼ አንዱ ስለ ደኀነት ጠየቀኝና (ሮሜ እና ያዕቆብ ላይ ያለውን በማነጻጸር) እና ስመልስለት የተወሰነች ሰፋ አለች ሳላስበው.. በጠዋቱ ይሄንን ሁሉ ቀድቼማ ለአንድ ሰው ብቻ አይሆንም ብዬ ላጋራችሁ አሰብኩ.. እና በጣም ይጠቅማል ስሙት ተረጋግታችሁ.. ከታች አስቀምጥላችኋለሁ
👇👇👇👇

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ሴትን ተጸየፈ..??

https://vm.tiktok.com/ZMrjvLUDB/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይሄ “ፍጡር ወኢፍጡር” የሚለው ርእስ ሲያከራክር በመሃል አንዱ አጥብቆ የሚተችኝ ወዳጄ ምን ያህል በክርክሩ ውስጥ እንደተማረ ሳይ ደስ ብሎኛል.. ክርስቶስን በጣም ነው የተማረው እና የክርክሩን ትርፍ አገኘሁት.. ለምሳሌ ያህል:

1. Double consubstantiality የኦርቶዶክስ ትምህርት አይደለም ብሎ ጀምሮ አሁን የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ነው አለ

2. ተዋሕዶ ላይ Prosopic union የለም hypostatic union እንጂ የሚል ሰው ካለ ጠርጥሩት በማለት ንስጥሮሳዊውን አገላለጽ ያምን የነበረው ወዳጃችን the union is not prosopic rather it is hypostatic ማለት ጀምሯል.. ስለዚህም ፍጡር ፕሮሶፖንን እንዳልነሳ አስተዋለ ማለት ነው..

3. በሥጋ ፍጡር አይባልም ብሎ በብዙ ሲከራከረን የነበረው ወንድም አሁን ላይ ግን ይሄ መከራከሪያ አይደለም አለን ቢያንስ..

ጌታ ይመስገን ዋናው ነገር ትምህርቱን መያዛቸው ነው.. ስለዛ በዚህ ውስጥ የክርስትና ትምህርት በደንብ እንዲያዝ ማድረግ ከተቻለ መልካም ነው..

አሁንም ቢሆን በአንድ ምክንያት እዚህ ርእስ ላይ ሰፋ ያለ ቪዲዮ በዩቲዩብ ስለማጋራችሁ ከዛ በኋላ አከራካሪ ራሱ አይሆንባችሁም የትኛውንም አስተሳሰብ ለያዛችሁ ወንድሞች..

እባካችሁን ያው ማንንም ለማስደበር ሳይሆን ሳስተውለው በጣም ደስ ስላለኝ ብቻ ነው.. ያው ክርክሩም ከንቱ ስላልሆነ ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የሆነ ማያውቁትን ነገር አጋጣሚ አንስቼ.. እነ በጋሻውም እንዲህ ነበሩ ሲሉኝ..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

😆😆ይሄ ጊዜ.. አጋጣሚ ቴሌግራም ከመደለቴ በፊት saved message ላይ ያሉ ነገሮችን ቼክ ሳደርግ አሁን አግኝቼው ነው😁😁 ትንሽ ቆየት ያለ ቪዲዮ..

ሁለት ግምብ ፊቶች

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጌታችን ኢየሱስ ለእመቤታችን ሞቷል አልሞተም ሲባል ለሷ አልሞተም የሚል ሰውም እየሰማን ነው.. ኧረ እንደው ፍቱን እንደው ቢያንስ በሆዳችሁ ያዙት..

Immaculate conception የተባለን ትምህርት ዶግማዋ ያደረገች የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ራሱ አልሞተላትም ስትል አይሰማም.. እንደውም ለሷም ሞቶላታል ግን የቀራንዮውን ሥራ አስቀድማ እንድታገኘው አደረጋት ይላሉ..

እኛ ሃገርም ከእነርሱ ተወስዳ በአንዳንዶች የምትሰጥ አባባል አለች አ.. አንድ ሰውን ጉድጓድ ውስጥ ሳይገባ በፊት ብታድነውም ከገባ በኋላ ብታድነውም ሁለቱም ማዳን ነው እንደውም የመጀመሪያው ማዳን የተሻለ ነው.. እመቤታችንንም በዛ መልኩ አድኗታል የምትል የካቶሊክ ወንድሞቻችን ማብራሪያ አለች..

እኛ ደግሞ ጭራሽ ለጥጠን የጌታ ሰው መሆንና መሞት ከእመቤታችን ጋር አይገናኝም እያልን እንዲሁ በድፍረት ባንናገር መልካም ነው.. ወይ አታንሱ እንዲህ ዓይነት ርእስ ጭራሹኑ.. በቃ ዝም ማለት

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በውስጥ የምጻጻፍበትን ቴሌግራም አካውንቴን ላጠፋው ስለሆነ በውስጥ አውርታችሁኝ ምናልባት ከኔ ጋር ያልጨረሳችሁት ነገር ካለ😁😁 ምናልባት በሆነ ጉዳይ ጠብቁኝ ምናምን ያልኳችሁ ካላችሁ አንዴ አስታውሱኝ በውስጥ ሳልደልተው በፊት.. እንዲሁ ላለማጥፋት ነው..

ያው ቻናል ላይ ምናምን እኖራለሁ እንቀጥላለን

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንድ ስመ ጥር የሆኑ ታላላቅ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን የሆነ ጉዳይ ላይ የተናገሩትን በአንድ ወቅት ላይ አይቼ እኔ በዛ ሰዓት ከማስበው በጣም ርቆብኝ በጣም አስጨንቆኝ ነበር..

የልጅ ነገር ሆኖ ከርስትናን ራሱ ጥያቄ ውስጥ እስክከተውም አደረገኝ.. ግን በጣም ጌታ ረዳኝና ያየኋቸው የአባቶቼ አገላለጾች ለጥቅም ሆነልኝና ነገረ ማርያም ላይ የተለጠጠና ከልክ ያለፈ ነገር እንዳይኖረኝ አደረገኝ.. ከዛ በፊት በኔው ስህተት ባለማወቅ አንዳንድ ነገሮች ላይ የተለጠጠ ነገር ይዤ ነበር.. እና ቢያንስ ከዚ ጠበቀኝና ለጥቅም ሆነልኝ..

ግን ያኔ የተሰማኝ ስሜት በጣም ከባድ ነበር.. እና አንዳንዴ በግልጽ የሆነ ነገርን ስናገር ክርስቲያኖች ያንን ስሜት እንዳያዩትም በማሰብ ነው..

የኦርቶዶክስ ውበት የሚታየው ነገሮች ያልተለጠጡና ትውፊታዊ እስከሆኑ ብቻ ነው..

ቀባጠርኩባችሁ😁😁 መልካም ምሽት

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት:

“ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?”
[ሮሜ 6: 2]

ክርስትና በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት እንጂ እንዲሁ ድርጅት አይደለም.. ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ በ5ኛው ምእራፍ የእግዚአብሔር ጸጋ ከኃጢአት ይልቅ እንደበዛና ኃጢአትንም እንዲያሸንፍ ይናገራል.. ስለዚህም ከኃጢአት ሁሉ ነጻ የሚያወጣን ሆነ..

ታድያ ግን እዚህ ላይ አያቆምም.. በጥምቀት ከጌታ ጋር አንድ በመሆን የኢየሱስ ስንሆን በሞቱም ደግሞ በመምሰል ነው.. ይህም ከሞቱ ጋር ደግሞ አንድ በመሆን ለኃጢአት እንድንሞትና ለጽድቅ እንድንኖር ነው.. ይህ አዲሱ ሕይወት ነው.. ይህም ለእግዚአብሔር ልጆች እንደሚገባ ዓይነት ኑሮን የመኖር ሕይወት ነው..

አዲሱ ሰው እንዳይደክምና እንዳይወድቅ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ከእናቱ ከቤተክርስቲያን እየተመገበ ሊያድግና ሊጠነክር ይገባዋል..

ወገን ከቅዱስ ምስጢር ርቀን(ተርበን) በመንፈሳዊ ሕይወታችን ቀነጨርን እኮ😁😁 እያሰብንበት.. ጌታ በምህረቱ ያስበን..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ

ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

@eotcLibrary

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ማኅበረ ቅዱሳን” የተወደደው ማኀበር ሆይ.. አንድ መጽሐፍ በማኀበሩ በኩል ሲታተም.. በማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ “ታርሞ ተፈቅዶ” የወጣ የሚል ነገር መጽሐፉ ላይ ስናይ.. የምር ግን በምን ደረጃ ነው ምትመረምሩት..?? በዛ መጽሐፍ ውስጥ የሚተላለፈው ትምህርት ሁሉስ ማኅበሩን ይወክላል..?? እንደው ይህንን ነገር ላውቅ ወደድሁ..

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስለምትሰሩ ከእናንተ በተቻለ አቅም ጥርት እና ጽድት ያለ ነገር ነው ምንጠብቀው እወቁልን.. እግዚአብሔር ይህንን ማኅበር ይጠብቅ.. ሁሌም እርሱው ይስራበትም

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሰው ከወኃ እንዴት ይወለዳል..?? ውኃን ከዚህ ነገር ጋር ማገናኘት አይከብድም..??

Well ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጣም የምወድለት መልሱ ለዚህ..

https://vm.tiktok.com/ZMrdDsC5p/

_______

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“መላጣ ቢሆንም እንኳን ይሁን ብዬ ላገባው የምችለው ሰው አክሊል ነው” የሚል ኮመንት ስታይ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የምታስገቡት @aklil11 ላይ ሲሆን አንዴ ከላካችሁ በኋላ edit ማድረግ አይቻልም.. ሲቀጥል መልእክት ደራርባችሁ እንዳትልኩ.. አንድ ጊዜ ብቻ ላኩ

1. ሰው ሲድን አስቀድሞ ሕግጋትን በመፈጸም ነው..?? ካልሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማስረጃ..??

2. አይሑዳውያንም አሕዛብም ወደ ጌታ የሚቀርቡበትና የክርስቶስን ሥራ የሚያገኙት በሕግ ወይስ በእምነት..?? ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

3. መልካም ሥራን የምንሰራው ስለዳንን ብቻ ወይስ መዳናችንንም ለመፈጸም..?? ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

4. መልካም ሥራን መስራት የዘላለም ሕይወትን ከማጨድ ጋር ይገናኛል..?? ከተገናኘ ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

5. ድናችኋል..?? ተብላችሁ ብትጠየቁ መልሳችሁ ምንድን ነው..?? ለምትናገሯቸው ሁሉ አንድ አንድ ጥቅስ ከቅዱስ ጳውሎስ..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

👆👆👆👆

ሦስቱንም በደንብ ስሙና ካወራሁት ውስጥ ጥያቄ እጠይቅና ለ5 ሰው የ50 ብር ካርድ እሞላለሁ.. ማታ 3:00 ላይ..

የጠቀስኳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በደንብ እዩዋቸው

ለማስታወስ ያህል ያኛውን የመጽሐፉን ባለፈው የሰጠኋችሁን ደግሞ ነገ ማታ ጥያቄውን እሰጣችኋለሁ.. ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧኸ.. የክርስቶስ ወገኖች እንዴት ናችሁልኝ..

ፆም ወቅት ላይ እንዲሁ የሥጋ መራብ ብቻ እንዳይሆን በረሃብ ውስጥ ትህትናን ይዘን ጌታችንንም ልንራበው ይገባል.. አጫጭር ጸሎቶችን እንጸልይ.. አባታችን ሆይ ጸሎትን ሊሆን ይችላል.. ጸሎተ እግዚእትነ ማርያምን..

አልያም “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ” እያልን ደጋግመን መጸለይ.. የትም ቦታ ብንሆን አይከብድም አጭር ስለሆነች..

በርቱልኝ በትንሹ እየጀመርን እያደግን እንሂድ.. በዳዊት የምትጸልዩ ሰዎች በርቱልን እግዚአብሔር አብዝቶ ይርዳችሁ አሁንም ተሰነካክላችሁ በስንፍና እንዳትወርዱ..

ስግደት በነገራችን ላይ በአምላካችን ፊት ሲሆን ትልቅ አምልኮን መግለጫ ነውና እንደ አቅሚቲ 12ም ብትሆን 3ትም ብትሆን በመንፈስ ሆነን እንስገድ.. የበረታችሁ እንደብርታታችሁ..

ይህ የጾም ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወታችን አንድ እርምጃ ምናድግበት ይሁንልን.. ከጌታችን ጋር ያለንን ሕይወት የምናድስበት ወይም የምናጠነክርበት ይሁንልን

መልካም የፆም ጸሎት ጊዜ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

የዮሐንስ ወንጌል 20
17፤ ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ፡ ብለሽ ንገሪአቸው፡ አላት።

ጌታ ኢየሱስ “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” አለ.. “አባቴ” ብሎ ለይቶ ተናገረ አመላክ እንደመሆኑ እርሱ ብቻውን የባህሪ ልጁ ነውና.. “አምላኬ” አለ የእኛን ሥጋ ይዟልና ነው.. ይህም የሱ የሚየው በፈቃዱ ያደረገው መሆኑ ነው.. ሰውን ወድዶ ራሱን ዝቅ አድርጎ በፈቃዱ የባርያን መልክ ይዟልና ሰው እንደመሆኑ አንዱ ጌታ ኢየሱስ “አምላኬ” ይለዋል አብን..

“አላረግሁም” አለ.. አንድ የገባላቸው ቃል አለ ይህም ወደ አብ ቢሄድ ቅዱሱን መንፈስ እንደሚልክላቸው ነው.. እና አላረገምና ያ አልተፈጸመም ነው..

ካረገ በኋላ ግን ቃል እንደገባው መንፈሱን ላከ.. በመንፈሱም አሰራር ቤተ ክርስቲያንን ወለደ.. ዛሬ ይህ ቅዱስ መንፈስ የወረደበትን ቀንን እና የቤተ ክርስቲያናችንን ልደት የምናስብበት ቀን ነው.. ጌታ መንፈሱን ባፈሰሰባት በአካሉ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ያጽናን.. መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ይርዳን..

መንፈስ ቅዱስ አዳኝ ሕይወትን የሚሰጥ ጌታ ነው.. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ እንድናድግ የሚረዳን በዓለም እና ሥጋ ላይ የሚያስጨክነን ነው..

መልከም በዓለ መንፈስ ቅዱስ
መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ አንድ ወዳጄ ምን ቢል..

በዚህ ሁኔታ ፕሮቴስታንት ላይ የምንሰራ ልጆች እስልምና ላይ እንደሚሰሩት ልጆች ራሳችንን መሸፈናችን አይቀርም😆😆

ካሁን በኋላ ፍቅርሲዝም ላይ ነው ምንሰራው እያለ ነው🤣🤣

You get it..?? If you don’t get it forget about it

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንዴ ግን ሰው አደገኛ ነው የምር..

አንዱ ፕሮቴስታንት ወንድም ሃሰተኛ ነቢያት ምናምን እያለ ልምምዱን ምናምን ይተቻል.. እና ያው ተቃውሞ እንደሚደርስበት የሚጠበቅ ነው.. ብዙ ፕሮቴስታንት ወንድሞች የሚቀበሉትን “አገልግሎት” ስለነካ ማለት ነው.. ለዚ ወንድም መልስ መመለስ ብሎም ደግሞ አገልግሎቱን ተገን አድርጎ መጥፎ ነገር ካደረገም ማሳየት ኖርማል ሊሆን ይችላል.. ያው እሱም ቢያገኝ ሊያሳይ ስለሚችል..

ግን ደግሞ ፐርሰናል የሆኑ ድክመቶቹን ማውጣት አይደብርም..?? ለምሳሌ ጫት ተገኘበት ብለው ፎቶ አሳዩበት.. እሺ ይሁን እሱ.. አብረው ደግሞ እርቃኑን(በግልገል ሱሪ) ያለበትን ፎቶ ለቀቁበት.. በጣም ያሳዝናል ክርስቶስን.. በዚ ደረጃ እንዴት አናስብም..?? ደግሞ ብዙ ሰው የሚጽፈው ኮመንት.. ነቢያቱ አምላኮቻቸው ነው ሚመስሉት የምር..

አስባችሁታል ፈሪሳውያኑ ኢየሱስን በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል፣ አጋንንት አለበት ምናምን እያሉ ያን ሁሉ ሲናገሩት ኢየሱስ የነሱን ነውር ቢገልጥባቸው ኖሮ..?? ነውርን ቢገልጥ እንደ ኢየሱስ ማን መግለጥ ይችልበት ነበር.. ጌታ ግን መልስ እየሰጠ ያልፍ ነበር..

እና ያው ይህንን ያገናኘሁት ራሳቸውን እንደ ክርስቲያን ስለሚቆጥሩ ይህንን አስበው እንኳን እንዴት አያርፉም ብዬ ነው.. ያው ሰው ሥጋዊ ሆኖ እንዲህ ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎችን ሊወስን ይችላል ግን እንደው ቢያንስ መለስ ቢባል..

አንተም እንግዲህ ብሮስኪ አይዞህ.. ቀላል ነገር ነው.. ዋና ልዋኝ ብትል እንኳን ሊታይ የሚችል ነገር ነው እና እልህ ውስጥ ባትጋባ ከቻልክ.. እና ሰው ሁሉ ደካማ ነውና ትነስም ትብዛም እንወድቃለን.. እንደ ወጣት ልታጠፋ ትችላለህ ግን ውስጥህን አብዝቶ እንዳይጎዳው ኮመንቶችን ምናምን አትይ ለትንሽ ጊዜ.. ከጉዋደኞችህ ጋር ጊዜን አሳልፍ..

አያገባን ይሆናል ስለ ወንድማማቾቹ ግን እንደ ሰው ስለደበረኝ ነው..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:

“በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።”
[ሮሜ 10: 2]

ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እስራኤላውያን እጅጉን ተጨንቋል.. አሕዛብ እንኳን ክርስቶስን በማመን ወደ እግዚአብሔር ሕዝብነት ሲጨመሩ የእግዚአብሔር የተመረጠ የኪዳን ሕዝብ የተባለው ያ ታላቅ ሕዝብ እስራኤል ግን የነቢያት ሁሉ ተስፋ የሆነውን መሲሕ ባለመቀበል ከኪዳኑ ሊወጡና ሊጠፉ ነው.. ስለዚህም ጳውሎስ ስለ እነርሱ ተጨንቆ: “ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው።” ይላል ከላይ..

ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ይቀናሉ.. ጳውሎስም(የጠርሴሱ ሳውል) ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆኖ ለአባቶች አምላክ ተቀንቶ ክርስቶስን ሲያሳድድ ነበር ያው ጌታ ሳያገኘው በፊት.. እስራኤል ለእግዚአብሔር ያላቸው ቅንአት ጥሩ ቢሆንም ግን ደግሞ ይህ ቅንአት ያለ እውቀት ነበር.. ስለዚህም ጳውሎስ ምን አለ..?? “በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።”

እና የኔ ተወዳጆች ክርስቲያኖችም ለጌታችን ወይም አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለተሰጠን ሃይማኖት በጣም ቅንአት አለብን.. በጣም መልካምም ነው.. ግን ደግሞ በእውቀት መሆን አለበት..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንድ ወዳጄ እንዲህ አለ:

የክርስትና ትምህርትን(ስነ መለኮት) መማር ማለት የሆኑ ትምህርቶችን ሰምቶ ሰምቶ እንደው ጭንቅላት ውስጥ የማስቀመጥ ነገር አይደለም.. ሳይንስና ፍልስፍናን ስትማርም ይህንን ነው ምታደርገው..

ስነ መለኮት ስትማር ውስጥህን ሊዋሐደው ይገባል ቃሉ.. ይህ የሚሆነው ደግሞ እግዚአብሔርን ስትቀርበው ነው.. ይህንን ያለ ቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ማግኘት አይቻልም.. ስትጸልይ ስትቆርብ ጌታ(የአብ ቃል) በአንተ አንተም በጌታ ስለምትሆን እግዚአብሔር በደንብ ይገለጥልሃል.. ኦርቶዶክሳዊ መረዳትም እየኖረህ ይሄዳል..

አልያ ግን አይተሃል አንዳንዱ ብዙ ዓመት ተምሪያለሁ ብሎ ኋላ ግን ጌታን ይክደዋል.. ይሄ የተነገረውን ወይም ያነበበውን እንደ ፍልስፍና እና ሳይንስ ጭንቅላት ውስጥ ብቻ አከማችቶ የያዘና የሆነ የተሻለ የሚመስል ነገር ሲመጣበት የሚወድቅ ነው.. ወይም ሲናገርም ከዚህ በፊት ካስቀመጠው ብቻ እንጂ ቃሉ ተዋሕዶት አይደለም..

ዌል ገዢ አሳብ ይመስለኛል..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

"የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ብዙ ችግር ያመጣባት ከልክ ማለፍ ነው"

"ኦርቶዶክሳዊነት መጠን ነው"

"ከመጠን ያለፈ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው"

ዲ/ን ያረጋል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እውነት ነው እንዴ ጋይስ..??

ስፖርት መስራት ፈልጌ አንዱ ጀለስ “ክብደት ማንሳት አእምሮን ይደፍናል ይባላል.. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶቹ እንዳይጠፉብህ” አለኝ🙄🙄

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ወደ ቅድስት ጠረጴዛ(መሠዊያ) ቅረብ: እሳት እንደሚያጋሳ አንበሳ ለሰይጣን አስፈሪ ሆነህም ተመለስ”

ይሄንን ጸዴ አንበሳ ሳየው ትዝ አለኝ ከላይ ያለው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አባባል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የሚያስሸልመው ጥያቄ ነገ ማታ 2:00 ነው የሚሆነው.. በሉ ተዘጋጁ..

“የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በአቡነ ጎርጎርዮስ.. ገጽ 1-90

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች.. ወንድማችን “መሸ” research እየሰራ አንድ ጉዳይ ላይ እስቲ የምትችሉ ሰዎች ከታች ያለውን ፎርም ሊንክ ውስጥ ገብታችሁ ሙሉለት.. ጥያቄዎቹን እያነበባችሁ ታዲያ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScgni-IwfQIaA_-e0rO0Gbd2buMEHJIl0DKmqKQTAVXqIzTpQ/viewform?usp=pp_url

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ኢየሱስ አምላኬና ተስፋዬ ነው
ቅዱስ መስቀሉም
የሃይማኖት በትሬ ነው”

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ: መጽሐፈ ምስጢር

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ምናልባት ከበድ ያለ ጥያቄ

https://vm.tiktok.com/ZMrefnV2d/

Читать полностью…
Subscribe to a channel