apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ነገረ ክርስቶስ እና ነገረ ማርያም ላይ 2 ጥያቄዎች በአጭር ደቂቃ

https://vm.tiktok.com/ZMrSGwk3A/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበቡ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ክፍል ውስጥ

ባለፈው ሳምንት ተሳንፌ አልያም ሳልችል ቀርቼ ስላልጻፍኩላችሁ ዛሬ ከሁሉም ከተነበቡት መጽሐፍት ውስጥ የሆነች የሆነች ጥቅስ ነው ማጋራችሁ

1️⃣ከወንጌል:- [የዘሪው ምሳሌ]

“ሌላውም(ዘር) በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው።”
[ሉቃስ 8:7]

ጌታችን በምሳሌ ሲናገር ዘሪ ዘሩን ሊዘራ እንደወጣና ዘሩም በተለያየ ቦታ ላይ እንደወደቀ ይናገራል.. ከነዚህ ውስጥ አንዱ በእሾህ መካከል ነው የወደቀው.. በእሾህ መካከል በመውደቁም ፍሬ እንዳይኖረው እሾሁ አነቀው ይለናል..

ምሳሌውንም ጌታ ኢየሱስ ሲያብራራ ዘር የተባለው “የእግዚአብሔር ቃል” እንደሆነ ከተናገረ በኋላ እንዲህ ይላል:

“በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ (ቃሉን)የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።”

2️⃣ ከሐዋርያት ሥራ:

“የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከብ መሪውንና የመርከቡን ባለቤት ያምን ነበር።”
[ሐዋ 27:11]

ክቡር ቅዱስ ጳውሎስ በእስር ሆኖ ለይግባኝ ወደ ሮም በሚሄድበት ጊዜ በመርከብ ላይ ያዩት መከራ በስመአብ.. አንተርፍም ብለው ተስፋ ቆርጠው ነበር.. ጳውሎስ ግን በኋላ ያጽናናቸዋል መልአክ እንደተገለጠለትና በሰላም እንደሚደርሱ እንደነገረውም ይነግራቸዋል.. “እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።” ይላቸዋል.. ሙሉውን አንብቡት

3️⃣ከጳውሎስ መልእክታት:-

“አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።”
[1ቆሮ 15: 33]

ሰውን አንጸየፍም.. ግን ደግሞ በቅድስና እና በሃይማኖት እንኖር ዘንድ የታዘዝን እኛ አዋዋላችን በኃጢአት እና በኑፋቄ መንደሮች ቢሆን እኛም ቀስ በቀስ ወደ እነርሱ አስታሳሰብ ልንሳብ እንችላለን.. አስቀድሞም በምሳሌ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ነበር:

“ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤
የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።”
[ምሳሌ 13:20]

4️⃣ከቀሩት መጽሐፍት:- (እንዴት እንደሆነ ባላውቅም እዚህ ክፍል ላይም እኛ ጋር ዕብራውያን ነው የተነበበው.. ያው ይህ መጽሐፍ የጳውሎስ እንደሆነ እኛ ሃገር አከራካሪም አይደለም ብዬ ነው)

“እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፡ ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፡ ያለው እርሱ ነው”
[ዕብ 5:5]

ለክህነት አገልግሎት ማንም ቢሆን ራሱን አያከብርም.. ለምሳሌ እነ አሮን.. ኋላ ክርስቶስም ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም አለ.. ሥጋ እንደመሆኑ ራሱን የሚያከብር ሳይሆን በተዋሕዶ የቃል ገንዘብን ገንዘቡ አድርጎ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” የሚለው ቃል ለእርሱም ተነገረ እንጂ.. ንስጥሮስ ስለ ኢየሱስ ሊቀ ክህነት ሲናገር ሰውነቱ ብቻ ነው ሊቀ ካህናት ይላል.. ቄርሎስ እንደመለሰው.. ኋላም በ11ኛው ቃለ ግዘቱ(በኤፌሶን ግባዔ) ላይም እንደ ገለጸው ሊቀ ካህናት እርሱ ሥግው ቃል ነው…”

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጋዲ ተመረቀ ይልሃል ማስተርሱን😁😁

እንኳን ደስ አለህ ብሮስኪ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለዝች ዓለም እንግዶች የማንመስለውስ ነገር..?? እንግዳ ለጥቂት ጊዜ ይቀመጣል ከዛም ወደ መኖሪያው ይሄዳል..

እኛም ለትንሽ ጊዜ እናርፍባትና ጌታ ወዳዘጋጀልን የዘላለም መኖሪያ እንሄዳለን.. ድክም ሲላቹ ኢየሱስን አስቡት መኖሪያ አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ እንደሆነ..

ስለዚህስ..??

“ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ #በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።”

[1ኛ ጴጥሮስ 1: 17]

መልካም አዳር
@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ግልጽ ማስረጃ😳😳

https://vm.tiktok.com/ZMrkjLDR1/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በተክሊል ሚያገባ ሰው እኮ አይጀንጅን ያበደ አ እንዴ..

ለ20 ደቂቃ ምትቀመጥ ፖስት😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መምህር በትረማርያም ስለ መምህር ገ/መደኅን ይህንን እንዳጋሩ ደረሰኝ..

እውነት ከሆነ በጣም ደስ ይላል ክርስቶስን.. መምኀር ገብረ መድኅን እግዚአብሔር ይስጥልን..

መምህር አባ ገ/ኪዳንና መምህር ብርሃኑ አድማስም ቢያጠሩት መልካም ነው.. በተዓምር መምህር ብርሃኑ አድማስ “ፍጡር ወኢፍጡር” ወይም “በሥጋው ፍጡር” የሚለውን ትምህርት አያጡትም.. ምክንያቱም ይህ double consubstantialityን የሚክድ እንደሆነ ይረዱታል.. council of Chalcedon reexamined የተሰኘውን መጽሐፍ እየጋበዙን ይህ ለሳቸው እንጃ.. ስለዛ የቀሩት መምህራንም(ብርሃኑ አድማስ እና አባ ገብረ ኪዳንም) አንዴ ግልጽ ቢያደርጉት መልካም ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ ፍቅራችሁ ጸናብኝ መሰለኝ ይኸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት እንኳን ሰፋ ያለ ትምህርት ቪዲዮ እቀርጽላችሁ ጀመር🙄🙄

ወደ 1 ሰዓት ያህል የሚረዝም ትምህርት ቀረጽኩላችሁ.. ጌታ ቢፈቅድ ነገ YT ላይ አስቀምጥላችኋለሁ😁😁

ተኙ ምን አለባችሁ እኔ አሁን ቪዲዮውን የተወሰነ ላስተካክል ደግሞ🥱🥱 ሎል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዱ ጉዋደኛዬ ትላንት ምን አለኝ..

ኃጢአት ያደረግሁ ሰዓት ወይም ውድቀት ውስጥ ስገባ እፈራለሁ.. እጅጉን ምፈራው ግን አምላኬን መናፈቅ ያቆምኩ የመሰለኝ ጊዜ ነው.. ከዳዊት ጋር አብሬ እንዲህ የማልል ከመሰለኝ

“ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥
አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።”
[መዝ 42:1]

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በቃ 5 ሰው ሸልሚያለሁ ፍቱ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የምታስገቡት @aklil11 ላይ ሲሆን አንዴ ከላካችሁ በኋላ edit ማድረግ አይቻልም.. ሲቀጥል መልእክት ደራርባችሁ እንዳትልኩ.. አንድ ጊዜ ብቻ ላኩ

1. ሰው ሲድን አስቀድሞ ሕግጋትን በመፈጸም ነው..?? ካልሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማስረጃ..??

2. አይሑዳውያንም አሕዛብም ወደ ጌታ የሚቀርቡበትና የክርስቶስን ሥራ የሚያገኙት በሕግ ወይስ በእምነት..?? ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

3. መልካም ሥራን የምንሰራው ስለዳንን ብቻ ወይስ መዳናችንንም ለመፈጸም..?? ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

4. መልካም ሥራን መስራት የዘላለም ሕይወትን ከማጨድ ጋር ይገናኛል..?? ከተገናኘ ማስረጃ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ..??

5. ድናችኋል..?? ተብላችሁ ብትጠየቁ መልሳችሁ ምንድን ነው..?? ለምትናገሯቸው ሁሉ አንድ አንድ ጥቅስ ከቅዱስ ጳውሎስ..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

👆👆👆👆

ሦስቱንም በደንብ ስሙና ካወራሁት ውስጥ ጥያቄ እጠይቅና ለ5 ሰው የ50 ብር ካርድ እሞላለሁ.. ማታ 3:00 ላይ..

የጠቀስኳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በደንብ እዩዋቸው

ለማስታወስ ያህል ያኛውን የመጽሐፉን ባለፈው የሰጠኋችሁን ደግሞ ነገ ማታ ጥያቄውን እሰጣችኋለሁ.. ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧኸ.. የክርስቶስ ወገኖች እንዴት ናችሁልኝ..

ፆም ወቅት ላይ እንዲሁ የሥጋ መራብ ብቻ እንዳይሆን በረሃብ ውስጥ ትህትናን ይዘን ጌታችንንም ልንራበው ይገባል.. አጫጭር ጸሎቶችን እንጸልይ.. አባታችን ሆይ ጸሎትን ሊሆን ይችላል.. ጸሎተ እግዚእትነ ማርያምን..

አልያም “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ” እያልን ደጋግመን መጸለይ.. የትም ቦታ ብንሆን አይከብድም አጭር ስለሆነች..

በርቱልኝ በትንሹ እየጀመርን እያደግን እንሂድ.. በዳዊት የምትጸልዩ ሰዎች በርቱልን እግዚአብሔር አብዝቶ ይርዳችሁ አሁንም ተሰነካክላችሁ በስንፍና እንዳትወርዱ..

ስግደት በነገራችን ላይ በአምላካችን ፊት ሲሆን ትልቅ አምልኮን መግለጫ ነውና እንደ አቅሚቲ 12ም ብትሆን 3ትም ብትሆን በመንፈስ ሆነን እንስገድ.. የበረታችሁ እንደብርታታችሁ..

ይህ የጾም ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወታችን አንድ እርምጃ ምናድግበት ይሁንልን.. ከጌታችን ጋር ያለንን ሕይወት የምናድስበት ወይም የምናጠነክርበት ይሁንልን

መልካም የፆም ጸሎት ጊዜ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

የዮሐንስ ወንጌል 20
17፤ ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ፡ ብለሽ ንገሪአቸው፡ አላት።

ጌታ ኢየሱስ “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” አለ.. “አባቴ” ብሎ ለይቶ ተናገረ አመላክ እንደመሆኑ እርሱ ብቻውን የባህሪ ልጁ ነውና.. “አምላኬ” አለ የእኛን ሥጋ ይዟልና ነው.. ይህም የሱ የሚየው በፈቃዱ ያደረገው መሆኑ ነው.. ሰውን ወድዶ ራሱን ዝቅ አድርጎ በፈቃዱ የባርያን መልክ ይዟልና ሰው እንደመሆኑ አንዱ ጌታ ኢየሱስ “አምላኬ” ይለዋል አብን..

“አላረግሁም” አለ.. አንድ የገባላቸው ቃል አለ ይህም ወደ አብ ቢሄድ ቅዱሱን መንፈስ እንደሚልክላቸው ነው.. እና አላረገምና ያ አልተፈጸመም ነው..

ካረገ በኋላ ግን ቃል እንደገባው መንፈሱን ላከ.. በመንፈሱም አሰራር ቤተ ክርስቲያንን ወለደ.. ዛሬ ይህ ቅዱስ መንፈስ የወረደበትን ቀንን እና የቤተ ክርስቲያናችንን ልደት የምናስብበት ቀን ነው.. ጌታ መንፈሱን ባፈሰሰባት በአካሉ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ያጽናን.. መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ይርዳን..

መንፈስ ቅዱስ አዳኝ ሕይወትን የሚሰጥ ጌታ ነው.. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ እንድናድግ የሚረዳን በዓለም እና ሥጋ ላይ የሚያስጨክነን ነው..

መልከም በዓለ መንፈስ ቅዱስ
መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ አንድ ወዳጄ ምን ቢል..

በዚህ ሁኔታ ፕሮቴስታንት ላይ የምንሰራ ልጆች እስልምና ላይ እንደሚሰሩት ልጆች ራሳችንን መሸፈናችን አይቀርም😆😆

ካሁን በኋላ ፍቅርሲዝም ላይ ነው ምንሰራው እያለ ነው🤣🤣

You get it..?? If you don’t get it forget about it

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እስቲ በኮመንት አሳውቁኝ😁😁

በባለፈው አንድ የራይድ ሹፌር ወደ አንድ ቦታ እያደረሰኝ የምለቃቸውን ነገሮች እንደሚከታተልና ያው እንደምመቸው ምናምን ነገረኝ በአጭሩ..

ግን መጀመሪያ ያየውህ ጊዜ ፕሮቴስታንት ትመስለኝ ስለነበረ ምንም ሳልሰማ ቶሎ ነበር ማሳልፍህ አለኝ🙈😁 ከዛ በኋላ ግን የሆነ ነገር ሲያስፈልገኝ ወደ አንተ ቻናል ነው ምመጣው አለ.. ይመቸው ሎል

❓❓እስቲ እንዲሁ ከኔ ከምታዩት ወይም ከምትሰሙት እንደው ገና ያላወቁኝ ሰዎች ፕሮቴስታንት ብለው እንዲገምቱ የሚያደርጋቸው ምን ይመስላችኋል..??

ያው መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን በደንብ ያወቀ ሰው በቀላሉ እንደሚለይ ይገባኛል ግን ያው ገና በማጥናት ላይ ላለ ሰው..

እስቲ ደብድቡኝ ደግሞ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቅዱስ ቁርባን

ቅዱስ ቁርባን(የጌታ ሥጋና ደም) የምን ሥጋ ነው..?? የፈጣሪ ወይስ የፍጡር ሥጋ..??

ሥጋ ምንም እንኳን ፍጡር ቢሆንም ይህንን ፍጡር ሥጋ ግን ፈጣሪ አምላክ የሆነ እርሱ ቃል የራሱ ሥጋ አድርጎታልና ይህ ሥጋ የአምላክ ሥጋ ነው.. ስለዚህ ሕይወትን የሚሰጥ ነው..

የአምላክን ሥጋ በፍርሃትና በታላቅ አክብሮት ለመሳተፍ ያብቃን.. መልካም አዳር.. ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይሄንን የግብጾችን እና የሲሪያዎችን አላስቀመጥኩላችሁም ለካ እዚህ ላይ.. እነሱ ጋር መወዛገብም የለ ቀለል አድርገው ነው የሚመልሱት..

ጠያቂ:- አንዱ የከርስቶስ ባህሪ(ከተዋሕዶ በኋላ) ፍጡር ነው ወይስ ኢፍጡር..??

ዲያቆን:- ሁለቱንም ነው(ፍጡር ወኢፍጡር) ምክንያቱም አስቀድሞ ከመጡበት ባህሪ አንዱ ወደ አንዱ አለተቀየረምና..

አንዳንድ ብዙም በማያነቡ ምእመናን ላይ የሚለማመዱ ሰዎች “creature” ለ prosopon “created” ደግሞ ለ Hypostasis ሲሉ ሰማሁ.. ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ክብሩን ወድዶ ተሳሳትኩ ላለማለት እንዲ እንደሚሟሟት አይገባኝም.. እኔ እንደው ክርስቶስን ክርስቲያኖች ላይ እንዲ የሚቀልድና የሚለማመድባቸው ሳይ ውስጤ ነው ሚቃጠለው..

ለማንኛውም Creature is something created.. በመጽሐፍ ቅዱስም ምንም ፕሮሶፖን ለሌላቸው irrational ነገሮች creatures የሚለውን ይጠቀማል.. እና መዝገበ ቃላቶችም “ፍጡር” የሚለውን ሲፈቱ “የተፈጠረ” ብለው ነው..

ለማንኛውም በቃ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ልዩነት የላቸውም እዚህ ላይ..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ከመጽሐፉ እና ከክርክሩ ጋር ተያይዞ መምህር ብርሃኑ አድማስ የጻፉትን አየሁ.. እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው.. ያው የተቆራረጠ ቪዲዮ ብቻ ነው ያየሁት አሉ.. ሙሉ ነገር ቢደርሳቸው መልካም ነበር ግን ያም ሆኖ “በሥጋው ፍጡር አይባልም” ብለዋል እየተባሉ ያለ አግባብ ሲጠቀሱ የነበሩት አንደኛውም እሳቸው ስለ ነበሩ መጻፋቸው በጣም አስፈላጊ ነበር..

ከመጽሐፉ ጋር በተያያዘ ያው እሳቸው እንዳላዩትና ያወቁትም ከታተማ በኋላ እንደሆነና ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም እንደሆነ አስቀምጠዋል..

በእርግጥ ቴዮሎጂው ላይ ምንም አላሉበትም ግን ከሁለቱም አቅጣጫ ያለው አለመግባባት እንጂ ጤናማ ትምህርት እንደሆነ ጽፈዋል.. ይሄ ቢያንስ ያለ አግባብ በየቦታው እንዳይጠቀሱ ያደርጋቸዋል.. እና ደግሞ አለመግባባት እንደሆነ የተናገሩት ነገር እኔ ባይታየኝም ግን ደግሞ እሰየው ያድርግልን ነው ልል የምችለው.. ወንድሞች ተሳስተው ከሚሆን ሳንረዳቸው ቀርተን ቢሆን የተሻለ ነውና.. በእርግጥ ብዙ ነገር በውይይት ውስጥ ሲሻሻሉ ስላየን አሁን ላይ በጣም የተሻለ ነው.. እና ደግሞ እንዲህ ያሉ ክርክሮችን ተችተዋል.. I wish ሙሉ ቪዲዮውን ቢያዩት ቢያንስ የዩትዩቡን.. ለማንኛውም በቃ አሁን ሊቃውንት መምህራንም አሳቦቻቸውን በግልጽ እያሰፈሩ ስለሆነ አሁን ቀለል ባለ መልኩ ግንዛቤው ይኖረናል ብዬ አስባለሁ..

ስለዛ ከአሁን በኋላ አስፈላጊነቱን አይተው ተገቢ ከመሰላቸው ራሳቸው ሊቃውንቱ ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ ያስተላልፉልናል.. ለመምህራኖቻችን ሁሉ እግዚአብሔር ጥበብ ማስተዋል እውቀትን ይጨምርልን..

ቀጣይ የተወሰነ ሰፋ አድርጌ አንድ ርእስ ላይ በዩትዩብ እሰራላችኋለሁ ሰሞኑን.. መልካም ጊዜ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዱ የክርስቶስ ባሕሪ የተፈጠረ ወይስ ያልተፈጠረ..??

https://youtu.be/_Fv5bTrh2Us

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ክርስቶስ ሰው እንደሆነ
በእውነት ካመናችሁ..”

[ሃይማኖተ አበው 124:37]


https://vm.tiktok.com/ZMrrGyxrG/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።”
[1ኛ ጴጥሮስ 2: 25]

የሞተልን እውነተኛ እረኛችን..

አንተ ታድለሃል ኢየሱስ የነፍስህ ጠባቂ ነው.. ለኃጢአት ሞተህ ለጽድቅ እንድትኖር ከሞተልህ እንግዲያውስ ጠብቆቱ ከኃጢአትም ጭምር ነው.. አንተ ብቻ ከዚህ ጠባቂህ አትኮብልል.. እረኛህ በአንተ: አንተም በእረኛህ ወደ ምትኖርበት ቅዱስ ምስጢር እንቅረብ.. ጠብቆቱንም እናጣጥም..

ለአንቺም..
ኢየሱስ የነፍስሽ እረኛና ጠባቂ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እሺ አሁን መጥታችሁ መዝሙሩን ትዘጉልኝ ወይስ ጥናቴን ያስትወኝ..??😁😁

በምን ደስ ላሰኝህ..??

በነገራችን ላይ እግዚአብሔርን ደስ ልናሰኘው የምንችለው በመልኩ እንደምሳሌው ፈጥሮናልና ያንን እርሱው የሰጠንን መልክና ምሳሌ ስንጠብቅ ብቻ ነው.. ሌላ ተጨማሪ ነገር እንኳ አይፈልግም.. የእግዚአብሔር ምሳሌ ቅድስና ነው..

መልካም ወሎ.. ክርስቶስን በልባችሁ ይዛችሁ የምትውሉበት ቀን ይሁንላችሁ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በስመአብ ቴሌግራም ጭር አለብኝ ከመደለቴ😆😆

በቃ እዚው እየመጣሁ እናወራለን ሎል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ደጋግማችሁ አትጻፉ በአንድ አድርጋችሁ ላኩ አልኩ እኮ.. አይሰማም እንዴ..??

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኢየሱስ እስከ 30 ዓመቱ ድረስ ጡት ጠብቷል..??🤦‍♂️🤦‍♂️

ባይሆን የእናንተን እንየው😎

https://vm.tiktok.com/ZMr6Wayuy/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ ወዳጆቼ አንዱ ስለ ደኀነት ጠየቀኝና (ሮሜ እና ያዕቆብ ላይ ያለውን በማነጻጸር) እና ስመልስለት የተወሰነች ሰፋ አለች ሳላስበው.. በጠዋቱ ይሄንን ሁሉ ቀድቼማ ለአንድ ሰው ብቻ አይሆንም ብዬ ላጋራችሁ አሰብኩ.. እና በጣም ይጠቅማል ስሙት ተረጋግታችሁ.. ከታች አስቀምጥላችኋለሁ
👇👇👇👇

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ሴትን ተጸየፈ..??

https://vm.tiktok.com/ZMrjvLUDB/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይሄ “ፍጡር ወኢፍጡር” የሚለው ርእስ ሲያከራክር በመሃል አንዱ አጥብቆ የሚተችኝ ወዳጄ ምን ያህል በክርክሩ ውስጥ እንደተማረ ሳይ ደስ ብሎኛል.. ክርስቶስን በጣም ነው የተማረው እና የክርክሩን ትርፍ አገኘሁት.. ለምሳሌ ያህል:

1. Double consubstantiality የኦርቶዶክስ ትምህርት አይደለም ብሎ ጀምሮ አሁን የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ነው አለ

2. ተዋሕዶ ላይ Prosopic union የለም hypostatic union እንጂ የሚል ሰው ካለ ጠርጥሩት በማለት ንስጥሮሳዊውን አገላለጽ ያምን የነበረው ወዳጃችን the union is not prosopic rather it is hypostatic ማለት ጀምሯል.. ስለዚህም ፍጡር ፕሮሶፖንን እንዳልነሳ አስተዋለ ማለት ነው..

3. በሥጋ ፍጡር አይባልም ብሎ በብዙ ሲከራከረን የነበረው ወንድም አሁን ላይ ግን ይሄ መከራከሪያ አይደለም አለን ቢያንስ..

ጌታ ይመስገን ዋናው ነገር ትምህርቱን መያዛቸው ነው.. ስለዛ በዚህ ውስጥ የክርስትና ትምህርት በደንብ እንዲያዝ ማድረግ ከተቻለ መልካም ነው..

አሁንም ቢሆን በአንድ ምክንያት እዚህ ርእስ ላይ ሰፋ ያለ ቪዲዮ በዩቲዩብ ስለማጋራችሁ ከዛ በኋላ አከራካሪ ራሱ አይሆንባችሁም የትኛውንም አስተሳሰብ ለያዛችሁ ወንድሞች..

እባካችሁን ያው ማንንም ለማስደበር ሳይሆን ሳስተውለው በጣም ደስ ስላለኝ ብቻ ነው.. ያው ክርክሩም ከንቱ ስላልሆነ ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የሆነ ማያውቁትን ነገር አጋጣሚ አንስቼ.. እነ በጋሻውም እንዲህ ነበሩ ሲሉኝ..

Читать полностью…
Subscribe to a channel