የብልህ ክርስቲያን ተማሪ አንዱ መገለጫ..
ቴዮሎጂን እንደ አዲስ አለመስራት.. በጣም በቀላሉ ሊስት እንደሚችል በማሰብ የጥንት አባቶቹ ያስተላለፉለትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ብቻ መናገር.. ስለዚህም ለጭንቅላቱ የሚከብድ ነገር ሲገጥመው ራሱ ተምሮ ከፍ ማለትን የሚመርጥ እንጂ ከአባቶቹ የተቀበለውን የጌታን ትምህርት ወደራሱ ዝቅታ ለማውረድ የማይታገል..
እርሱ ብልህ ተማሪ ነው
@Apostolic_Answers
ጠያቂ: ጥምቀት ያድናል..??
መላሽ: ኢየሱስ ያድናል ነው
አከብራቸዋለሁ ግን ምን ዓይነት መልስ ነው ይሄ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMrPr9AvQ/
እስቲ ልጠይቃችሁ:
በወንጌል ላይ “ኢየሱስ” የሚሉ ስሞች ሲኖሩ የ2000ው እትም “ኢየሱስ” ከሚለው ስም ፊት ምን የሚል ቃል ይጨምራል..?? ያው ከግእዙ ስለተተረጎመ ወይ ከግእዙ አንጻር መልሱ..
የግእዙ “ኢየሱስ” ከሚለው ፊት የሚጨምረው ቃል አስተምህሮ ላይ ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም ግን እስቲ የ2000ውን አልያም የግእዙን እዩና ጻፉልኝ.. ከወንጌል ዝምብላችሁ የፈለጋችሁት ቦታ ቼክ አድርጉ ሂዱና.. ያው አብዛኛው እንደዛ ስለሆነ..
ኮመንት ላይ ኢየሱስ የሚለውንና ከሱ ፊት አብሮ ያለውን ቃል ብቻ ጻፉ.. ከዛ ውጪ መጻፍ አይቻልም
አንድ ወዳጅ አለኝ ሁሌም ሊበደረኝ ሲል ሚልክልኝ ጥቅስ
“ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም”
[መዝ 112: 5]
ስንት ጊዜ ሙሉ ሳይመልስ ይቆይና ሲጨንቀው ደግሞ ሚልክልኝ ጥቅስ..
“ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።”
[ሉቃ 6: 30]
ጥቅሶችን በቦታቸው እንጠቀም ለማለት ነው😁😁
ኮመንት ላይ ምትመልሱት በጣም ደስ የሚል ጥያቄ
“እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?”
[1ቆሮ 15: 30]
ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ክቡር ቅዱስ ጳውሎስ ነው.. እና በሚያስፈራ ኑሮ ለምን እንኖራለን..?? ይላል.. ከታች ዝቅ ብሎ “በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ታገልሁ” በማለት የአውሬ ጭካኔ ካላቸው ሰዎች ጋር ሳይቀር እንደታገለ ይናገራል.. ከኃጢአትስ ርቀን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እየፈጸምን ለምን እንኖራለን..??
“ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ” ፈታ እንበል ላይፍ አጭር ናት ለምን አንልም..??
“ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?”
እስቲ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ምን እንደሆነ እዛው ክፍሉ ላይ ያለውን አንብባችሁ ኮምንት ላይ መልሱ..
1ቆሮ 15:30-34 አንብቡና መልሱ..
መልካም እግዚአብሔርን የመውደድና የመፍራት ቀን ይሁንላችሁ ደግሞ..
@Apostolic_Answers
ኧረ በቅዱስ ሚካኤል አንዷ ወዳጄ አሜሪካ ስላለ ገዳም ምን ብትለኝ..?? በ እውነት ምንም ነገር አልጨማመርኩም እና የተባልኩትን ሳስቀምጥ:
- አንድ ሰፋ ያለ አዳራሽ አለ(ኖርማል ነው ይሄ)
- እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ሩም ይኖረዋል ሚተኛበት ምናምን(እ…..ሺ)
- ቲቪ አለ ማንም አያይበትም እንጂ(ኧረ አታስቁን😆😆)
- የጋራ ኪችን አለ ሻይ ምናምን አለ(😭😭 እዚ ጋር አልቻልኩም)
- ፍሪጅም አለ.. ስከፍተው ጭራሽ ሙሉ ምግብ ነው አላለችም(🤣🤣)
አሞላቀቃችኋቸው የምር.. ከብዷቸው እንዳይርቁ እኮ ነው😁😁 ደስ ይላል ቀስ በቀስ እንዲያድጉ..
እኛም እንዲ ይደረግልን እንዳንል ብቻ😁😁
20,000 ገባን እንዴ ለካ እዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ.. ምንም ሳናስተዋውቀው በቻናል ደረጃ ቴሌግራም ላይ 20k መግባት ቀላል አይደለም..
ከምንም በላይ ግን እዚህ ያለን ቤተሰቦች ክርስትና ላይ ያላችሁ መረዳት ምናምን እና ምንግባባውም ነገር ያበደ ነው.. ቴሌግራም ሁሌም ቢሆን cool ነው የምር.. የቲክቶክ ጀማ እንዳይቀየም እንጂ😁😁
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበቡ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ክፍል ውስጥ
ባለፈው ሳምንት ተሳንፌ አልያም ሳልችል ቀርቼ ስላልጻፍኩላችሁ ዛሬ ከሁሉም ከተነበቡት መጽሐፍት ውስጥ የሆነች የሆነች ጥቅስ ነው ማጋራችሁ
1️⃣ከወንጌል:- [የዘሪው ምሳሌ]
“ሌላውም(ዘር) በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው።”
[ሉቃስ 8:7]
ጌታችን በምሳሌ ሲናገር ዘሪ ዘሩን ሊዘራ እንደወጣና ዘሩም በተለያየ ቦታ ላይ እንደወደቀ ይናገራል.. ከነዚህ ውስጥ አንዱ በእሾህ መካከል ነው የወደቀው.. በእሾህ መካከል በመውደቁም ፍሬ እንዳይኖረው እሾሁ አነቀው ይለናል..
ምሳሌውንም ጌታ ኢየሱስ ሲያብራራ ዘር የተባለው “የእግዚአብሔር ቃል” እንደሆነ ከተናገረ በኋላ እንዲህ ይላል:
“በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ (ቃሉን)የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።”
2️⃣ ከሐዋርያት ሥራ:
“የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከብ መሪውንና የመርከቡን ባለቤት ያምን ነበር።”
[ሐዋ 27:11]
ክቡር ቅዱስ ጳውሎስ በእስር ሆኖ ለይግባኝ ወደ ሮም በሚሄድበት ጊዜ በመርከብ ላይ ያዩት መከራ በስመአብ.. አንተርፍም ብለው ተስፋ ቆርጠው ነበር.. ጳውሎስ ግን በኋላ ያጽናናቸዋል መልአክ እንደተገለጠለትና በሰላም እንደሚደርሱ እንደነገረውም ይነግራቸዋል.. “እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።” ይላቸዋል.. ሙሉውን አንብቡት
3️⃣ከጳውሎስ መልእክታት:-
“አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።”
[1ቆሮ 15: 33]
ሰውን አንጸየፍም.. ግን ደግሞ በቅድስና እና በሃይማኖት እንኖር ዘንድ የታዘዝን እኛ አዋዋላችን በኃጢአት እና በኑፋቄ መንደሮች ቢሆን እኛም ቀስ በቀስ ወደ እነርሱ አስታሳሰብ ልንሳብ እንችላለን.. አስቀድሞም በምሳሌ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ነበር:
“ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤
የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።”
[ምሳሌ 13:20]
4️⃣ከቀሩት መጽሐፍት:- (እንዴት እንደሆነ ባላውቅም እዚህ ክፍል ላይም እኛ ጋር ዕብራውያን ነው የተነበበው.. ያው ይህ መጽሐፍ የጳውሎስ እንደሆነ እኛ ሃገር አከራካሪም አይደለም ብዬ ነው)
“እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፡ ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፡ ያለው እርሱ ነው”
[ዕብ 5:5]
ለክህነት አገልግሎት ማንም ቢሆን ራሱን አያከብርም.. ለምሳሌ እነ አሮን.. ኋላ ክርስቶስም ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም አለ.. ሥጋ እንደመሆኑ ራሱን የሚያከብር ሳይሆን በተዋሕዶ የቃል ገንዘብን ገንዘቡ አድርጎ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” የሚለው ቃል ለእርሱም ተነገረ እንጂ.. ንስጥሮስ ስለ ኢየሱስ ሊቀ ክህነት ሲናገር ሰውነቱ ብቻ ነው ሊቀ ካህናት ይላል.. ቄርሎስ እንደመለሰው.. ኋላም በ11ኛው ቃለ ግዘቱ(በኤፌሶን ግባዔ) ላይም እንደ ገለጸው ሊቀ ካህናት እርሱ ሥግው ቃል ነው…”
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ለዝች ዓለም እንግዶች የማንመስለውስ ነገር..?? እንግዳ ለጥቂት ጊዜ ይቀመጣል ከዛም ወደ መኖሪያው ይሄዳል..
እኛም ለትንሽ ጊዜ እናርፍባትና ጌታ ወዳዘጋጀልን የዘላለም መኖሪያ እንሄዳለን.. ድክም ሲላቹ ኢየሱስን አስቡት መኖሪያ አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ እንደሆነ..
ስለዚህስ..??
“ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ #በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።”
[1ኛ ጴጥሮስ 1: 17]
መልካም አዳር
@Apostolic_Answers
“ነገረ ክርስቶስ” የተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተሰጠውን የማኅበረ ቅዱሳንን ገለጻ ቪዲዮ አየሁ..
መጽሐፉ ውስጥ ጥቂት እንከን ሊገኝ ይችላል.. ያው እንግዲህ ያቺ እንከን ግን ከባድ ጉዳይ ከሆነች ማጥራቱ መልካም ነው.. ማኅበሩም ከዚህ ቀደም እንዳልሁት ጌታ የሚሰራበት የሚጠቀምበት እንደሆነ አስባለሁ አምናለሁም.. የተወደደ ማኅበር.. እዛ ያሉ ወጣቶች ትሕትናቸውም ያስቀናኛል በነገራችን ላይ..
ግን ትንሽ እንደው ግራ ያጋባችኝ ነገር..
የለቀቁት ቪዲዮ ላይ መጽሐፉ ሰሞኑን ሚዲያ ላይ ላለው ክርክርም መልስ ሆነ ብለዋል.. በየት በኩል ነው መልስ ሚሆነው..?? “በሥጋው ፍጡር አይባልም ከተዋሕዶ በኋላ” በማለት በቪዲዮው ላይ የተናገሩት ለምሳሌ መምህር ብርሃኑ አድማስ እንኳን ለዚህ ክርክር እንደማመሳከሪያ አይሆንም አውዱ የተለየ ነው ብለዋል እኮ.. ምናልባት አንዱ የክርስቶስ ውሕድ(composed) ባሕርይ “ፍጡር ወኢፍጡር” ነው የሚለውን በማኅበር ደረጃ የማይቀበሉት ሆነው ከሆነ በጣም አደገኛ ይመስለኛል..
“የአገላለጽ ልዩነት በቻ ነው ያለው” የሚለው አገላለጽ ራሱ እንጃ.. ከተዋሕዶ በኋላ በክርስቶስ ውስጥ “ያልተፈጠረ” ብቻ እንጂ “የተፈጠረ” የሚባል ነገር የለም ከተባለ በቃ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ያለው አንድነት አፍ ላይ ያለ ምስክርነት ብቻ ይሆናል.. በነሣው ሥጋ ከፍጡራን እንደ አንዱ ሚሆነው ሥጋ ፍጡርነቱን ያልተወ እንደሆነ ብቻ ነው.. ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንዴት ያከራክራል ይሄ..?? ይሄ የ double consubstantiality ትምህርትን ሚጋፋ ይመስለኛል..
በነገራችን ላይ መጽሐፉ የጌታችን አስታራቂነት ላይም የተዛባ የሚመስል ነገር ተቀምጧል.. “በምድር ሳለም አስታረቋል አይባልም ይቅር አለን ነው ሚባለው” የሚል ዓይነት ነገር.. እሁድ እሁድ በውዳሴ ማርያም “ለሐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆነ” እያልን ነው ምንጸልየው እንግዲህ.. የእርሱ ማስታረቅ እንደ ቅዱሳን እንዳልሆነ ማሳየት እንጂ ይሄ ዓይነቱ አገላለጽ ጭራሹኑ በቤዛነቱ በኩል ያለውን አስታራቂነቱን መዘንጋትን ሊያመጣ ይችላል ብዬ ነው..
ምንም እኮ ከባድ ነገር የለውም.. አንድ መጽሐፍ ነው አለቀ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ስህተት ካለው ቀላል ነው ቀጣይ ኅትመት ላይ ማሻሻል..
ለማንኛውም ይህንን ድንቅ ማኅበር አሁንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን አብዝቶም ይስራበት
@Apostolic_Answers
“እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ”
[መዝ 17: 8]
በሉት እረኛውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን..
መልካም ውሎ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች
ዲየግ.. እስካሁን ከመለሳችሁ በቂ ነው..
ብዙ ጊዜ “ጌታ/ጌታችን” የሚል ቃል መጠቀም በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ አልተለመደም(which is sad) ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግእዝ መጽሐፍ ቅዱሷ ላይ “ኢየሱስ” የሚሉትን ንባባት እንኳን “እግዚእ ኢየሱስ/ጌታ ኢየሱስ” ነው ብላ ምታነባቸው.. በቅዳሴዋም ላይ ለምሳሌ ወንጌል ሲነበብ ከዚሁ ስለሚነበብ ካስተዋላችሁ ቄሱ የሚሉት “ጌታችን ኢየሱስ” ነው።
የሆነ ጊዜ ላይ ያጋራኋችሁ ዘጠኝ ቃላት ብቻ የያዘችው አጭር ጸሎት አለች አ..?? ያው ብዙዎቻችሁ ትጸልዩባት ይሆናል.. በዓለማችን ላይ አብዛኛው ኦርቶዶክስ ይጸልይባታል
“Lord Jesus Christ Son of God have mercy on me a sinner”
[ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ]
ጸሎቷ ይህች ናት እና ደጋግሞ ከልብ መጸለይ ነው መድኃኒታችንን እያሰብን.. እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይም በተደጋጋሚ ያለ ቃል ነው “ጌታ ኢየሱስ” የሚለው.. የመጽሐፉ መጨረሻ ላይም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” ይላል..
እና ይህ ድምጽ(ቃል) የቤተ ክርስቲያን ነው.. ግን ደግሞ መልሶ ለብዙ ክርስቲያኖች እንግዳ አጠራር እየሆነ ነው.. ያሳዝናል.. ቢያንስ ሚዲያው ላይ ማንም እንግዳ አይሆንበትም😁👍
“ክርስቲያን” የሚለውንም ቃል ሁሌ በኦርቶዶክስ ቦታ የምጠቀመው ለዚህ ነው.. ክርስቲያን የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን ብቻ ነን.. ይሄንን ለማስረገጥ ነው..
እና ለማንኛውም ኢየሱስን ባማረ በተወደደ ቤተ ክርስቲያናዊ በሆነ ነገር ሁሉ መጥራት ፍቅርን ይጨምር ይሆናል እንጂ ምንም ጣጣ የለውም ነው..
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከቅዱስ ወንጌል ክፍል:
“በምሳሌም ብዙ ነገራቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።”
[ማቴዎስ 13: 3-4]
ጌታችን የዘሪውን ምሳሌ ይናገራል.. ባለፈው ሳምንትም ከሉቃስ ወንጌል ይኸው ምሳሌ ተነቦ አካፍያችሁ ነበር.. ያኔ በእሾህ መካከል የወደቀውን ዘር ምሳሌ ነበር ያየነው.. ዛሬ ደግሞ በመንገድ ዳር ስለወደቀው ዘር ምሳሌ እንይ..
የዚህን ምሳሌ ትርጉም ጌታችን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል:
“የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።”
[ማቴዎስ 13: 19]
ቃሉን ሰምቶ በማያስተውል አለ.. እነዚህ ቃሉን ይሰማሉ ግን ከልበ ደንዳናነት ወጥተው በደንብ ተረድተውት ፍሬን ሊያፈሩበት ሲገባ ሰሚ ብቻ የሆኑና ወደ ሕይወት ለመቀየር ፍላጎት የሌላቸው እግዚአብሔርንም የማይናፍቁ ናቸው.. እንዲህ ያሉት በመንገድ ተመሰሉ ጠባቂም የላቸውምና ስለዚህ ክፉ መንፈስ ያንንም የሰሙትን ቃል ከልቡ ይነጥቃል..
ቃሉን የምንሰማ ብቻ ሳይሆን የምናስተውለውና የምናደርገውም ያድርገን አምላካችን..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
“አንዱ ውሕድ የሆነው የክርስቶስ ባሕርይ የተፈጠረ ነው ወይስ ያልተፈጠረ..??” ለሚል ጥያቄ
“አንዱ ፍጡር ሌላኛው ፈጣሪ የሚል አርዮሳዊ/ንስጥሮሳዊ/ካቶሊካዊ ነው” እያሉ ያልተጠየቁትን ሚመልሱ ሰዎችን ባየሁ ቁጥር ሚሰማኝ ስሜት😁😁
ያው እዚህ ርእስ ላይ ምንም አልልም.. ዝም ብሎ ማለፍ ነው😁😁
“[በዚህ ዓለም] ዘውድን የሚቀዳጀው(ባለ ጠጎች የሆኑቱ) እንኳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይራዱት ዘንድ ድንኳን ሰፊውን(ጳውሎስን) እና አሣ አጥማጁን(ጴጥሮስን) ይለምናል.. ቢሞቱ እንኳን”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ : homilies on 2 Corinthians: Hom. 26
እንኳን ለጵጥሮስ ወጳውሎስ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ.. የእነርዚህን እጅግ የተወደዱ ሐዋርያት በረከት በመምህራኖቻችን እና በሁላችን ላይ ያሳድር.. አሜን
@Apostolic_Answers
እስቲ በኮመንት አሳውቁኝ😁😁
በባለፈው አንድ የራይድ ሹፌር ወደ አንድ ቦታ እያደረሰኝ የምለቃቸውን ነገሮች እንደሚከታተልና ያው እንደምመቸው ምናምን ነገረኝ በአጭሩ..
ግን መጀመሪያ ያየውህ ጊዜ ፕሮቴስታንት ትመስለኝ ስለነበረ ምንም ሳልሰማ ቶሎ ነበር ማሳልፍህ አለኝ🙈😁 ከዛ በኋላ ግን የሆነ ነገር ሲያስፈልገኝ ወደ አንተ ቻናል ነው ምመጣው አለ.. ይመቸው ሎል
❓❓እስቲ እንዲሁ ከኔ ከምታዩት ወይም ከምትሰሙት እንደው ገና ያላወቁኝ ሰዎች ፕሮቴስታንት ብለው እንዲገምቱ የሚያደርጋቸው ምን ይመስላችኋል..??
ያው መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን በደንብ ያወቀ ሰው በቀላሉ እንደሚለይ ይገባኛል ግን ያው ገና በማጥናት ላይ ላለ ሰው..
እስቲ ደብድቡኝ ደግሞ😁😁
ቅዱስ ቁርባን
ቅዱስ ቁርባን(የጌታ ሥጋና ደም) የምን ሥጋ ነው..?? የፈጣሪ ወይስ የፍጡር ሥጋ..??
ሥጋ ምንም እንኳን ፍጡር ቢሆንም ይህንን ፍጡር ሥጋ ግን ፈጣሪ አምላክ የሆነ እርሱ ቃል የራሱ ሥጋ አድርጎታልና ይህ ሥጋ የአምላክ ሥጋ ነው.. ስለዚህ ሕይወትን የሚሰጥ ነው..
የአምላክን ሥጋ በፍርሃትና በታላቅ አክብሮት ለመሳተፍ ያብቃን.. መልካም አዳር.. ነገ ቅዳሴ ላይ እንገናኝ..
ይሄንን የግብጾችን እና የሲሪያዎችን አላስቀመጥኩላችሁም ለካ እዚህ ላይ.. እነሱ ጋር መወዛገብም የለ ቀለል አድርገው ነው የሚመልሱት..
ጠያቂ:- አንዱ የከርስቶስ ባህሪ(ከተዋሕዶ በኋላ) ፍጡር ነው ወይስ ኢፍጡር..??
ዲያቆን:- ሁለቱንም ነው(ፍጡር ወኢፍጡር) ምክንያቱም አስቀድሞ ከመጡበት ባህሪ አንዱ ወደ አንዱ አለተቀየረምና..
አንዳንድ ብዙም በማያነቡ ምእመናን ላይ የሚለማመዱ ሰዎች “creature” ለ prosopon “created” ደግሞ ለ Hypostasis ሲሉ ሰማሁ.. ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ክብሩን ወድዶ ተሳሳትኩ ላለማለት እንዲ እንደሚሟሟት አይገባኝም.. እኔ እንደው ክርስቶስን ክርስቲያኖች ላይ እንዲ የሚቀልድና የሚለማመድባቸው ሳይ ውስጤ ነው ሚቃጠለው..
ለማንኛውም Creature is something created.. በመጽሐፍ ቅዱስም ምንም ፕሮሶፖን ለሌላቸው irrational ነገሮች creatures የሚለውን ይጠቀማል.. እና መዝገበ ቃላቶችም “ፍጡር” የሚለውን ሲፈቱ “የተፈጠረ” ብለው ነው..
ለማንኛውም በቃ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ልዩነት የላቸውም እዚህ ላይ..
ከመጽሐፉ እና ከክርክሩ ጋር ተያይዞ መምህር ብርሃኑ አድማስ የጻፉትን አየሁ.. እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው.. ያው የተቆራረጠ ቪዲዮ ብቻ ነው ያየሁት አሉ.. ሙሉ ነገር ቢደርሳቸው መልካም ነበር ግን ያም ሆኖ “በሥጋው ፍጡር አይባልም” ብለዋል እየተባሉ ያለ አግባብ ሲጠቀሱ የነበሩት አንደኛውም እሳቸው ስለ ነበሩ መጻፋቸው በጣም አስፈላጊ ነበር..
ከመጽሐፉ ጋር በተያያዘ ያው እሳቸው እንዳላዩትና ያወቁትም ከታተማ በኋላ እንደሆነና ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም እንደሆነ አስቀምጠዋል..
በእርግጥ ቴዮሎጂው ላይ ምንም አላሉበትም ግን ከሁለቱም አቅጣጫ ያለው አለመግባባት እንጂ ጤናማ ትምህርት እንደሆነ ጽፈዋል.. ይሄ ቢያንስ ያለ አግባብ በየቦታው እንዳይጠቀሱ ያደርጋቸዋል.. እና ደግሞ አለመግባባት እንደሆነ የተናገሩት ነገር እኔ ባይታየኝም ግን ደግሞ እሰየው ያድርግልን ነው ልል የምችለው.. ወንድሞች ተሳስተው ከሚሆን ሳንረዳቸው ቀርተን ቢሆን የተሻለ ነውና.. በእርግጥ ብዙ ነገር በውይይት ውስጥ ሲሻሻሉ ስላየን አሁን ላይ በጣም የተሻለ ነው.. እና ደግሞ እንዲህ ያሉ ክርክሮችን ተችተዋል.. I wish ሙሉ ቪዲዮውን ቢያዩት ቢያንስ የዩትዩቡን.. ለማንኛውም በቃ አሁን ሊቃውንት መምህራንም አሳቦቻቸውን በግልጽ እያሰፈሩ ስለሆነ አሁን ቀለል ባለ መልኩ ግንዛቤው ይኖረናል ብዬ አስባለሁ..
ስለዛ ከአሁን በኋላ አስፈላጊነቱን አይተው ተገቢ ከመሰላቸው ራሳቸው ሊቃውንቱ ትምህርቱን በጥሩ ሁኔታ ያስተላልፉልናል.. ለመምህራኖቻችን ሁሉ እግዚአብሔር ጥበብ ማስተዋል እውቀትን ይጨምርልን..
ቀጣይ የተወሰነ ሰፋ አድርጌ አንድ ርእስ ላይ በዩትዩብ እሰራላችኋለሁ ሰሞኑን.. መልካም ጊዜ