apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ድክም ሲላችሁ.. ሲሰለቻችሁና መጸለይ እንኳ ሲከብዳችሁ.. የጌታችንን ትንሳዔ አስቡ.. የእርሱ ትንሳዔ የእኛን ትንሳዔ አረጋግጧልና ሞተን እንደማንቀር እንደምንነሳ ከእርሱም ጋር ለዘላለም እንደምንኖር አስቡ..

ያንን ሕይወት ስናስብ በዝች አላፊ ጠፉ በሆነችው ኑሮዋችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ቀላል ይሆኑብንና በዚህም ሰዓት ከጌታችን ጋር መኖር ከእርሱም ጋር መዋል ለእኛ መልካም እንደሆነ ያስተምረናል.. ለሁሉም ነገር ግን ጸጋው ያግዘን ያበርታን.. ምን ያህል አቅመ ቢሶች እንደሆንን ስለሚያውቅ በድካማችን የሚራራልን ሊቀ ካህናት ነው ያለን.. ስለዛ በምንም ሁኔታ ውስጥ ስንሆን እርሱን ተስፋ እናድርግ.. ተስፋችን እርሱ ነው..

መልካም ውሎ እናንተ በጌታ መንግስት(በቤተ ክርስቲያን) ውስጥ ያላችሁ የንጉሥ ልጆች.. እንደ ንጉሥ ልጅ የምንውልበት ቀን ይሁንልን.. ንጉሡ ትህትናውን አሳይቶናል እኛም እንደሱ በትህትና ሰዎችን በመውደድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም እንውል ዘንድ ይርዳን..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ተፋልሶ” ብለህ ከራሱ ከ2000ው ኅትመት ሕዳግ ላይ ኮርጀህ መጽሐፍ የጻፍከው.. አንተ ትለያለህ የምር😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrut2rFU/

👆👆👆

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጌታቸው(ተፋልሶ) ምንድን ነው ሚሉን😁😁

የዚ ዘመን “ነቢይ” የመሆን መስፈርትስ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMruBQsV3/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የ….. መልእክት

☹️☹️ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ዝናብ እየዘነበ ስለነበር ነው መሰለኝ አርፍጄ ተነሳሁ.. አላርም አልጠቀምም ነበር ብዙ ጊዜ.. እና ቅዳሴ ወንጌል ተነቦ እንዳለቀ ደረስኩ😭😭 ስለዛ ሌሎቹ ላይም አልደረስኩም..

እስቲ ኮመንት ላይ አሳውቁኝ.. አንዳችሁ ከወንጌል አንዳችሁ ከጳውሎስ አንዳችሁ ከሐዋርያት ሥራ አንዳችሁ ከቀሩት እያደረጋችሁ..

መልካም የጌታ ቀን

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መልስ..??😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrmrtWKN/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እኔ ምላችሁ የቲክቶክ ጀማዎች.. ምንድነው ፕሮፋይላችሁን ብዙዎቻችሁ የኔን ፎቶ አድርጋችኋል😁😁 አውቃለሁ ፍቅራችሁን የምትገልጹበት እንደሆነ

ግን የኔ ተወዳጆች ከይቅርታ ጋር ሌላ ብታደርጉ.. እንዲ ሲሆን ሌላ ነገር ሊያስመስል ስለሚችል.. ፍቅራችሁን እረዳዋለሁ እንድች ብላችሁ እንዳታስቡ😁😁 በቃ ቀይሯት እወዳችኋለሁ አመሰግናለሁ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የብልህ ክርስቲያን ተማሪ አንዱ መገለጫ..

ቴዮሎጂን እንደ አዲስ አለመስራት.. በጣም በቀላሉ ሊስት እንደሚችል በማሰብ የጥንት አባቶቹ ያስተላለፉለትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ብቻ መናገር.. ስለዚህም ለጭንቅላቱ የሚከብድ ነገር ሲገጥመው ራሱ ተምሮ ከፍ ማለትን የሚመርጥ እንጂ ከአባቶቹ የተቀበለውን የጌታን ትምህርት ወደራሱ ዝቅታ ለማውረድ የማይታገል..

እርሱ ብልህ ተማሪ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በፕሮቴስታንት ውስጥ ካሉ ሰው ሰራሽ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ

https://vm.tiktok.com/ZMr58rPH6/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጠያቂ: ጥምቀት ያድናል..??
መላሽ: ኢየሱስ ያድናል ነው

አከብራቸዋለሁ ግን ምን ዓይነት መልስ ነው ይሄ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrPr9AvQ/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እስቲ ልጠይቃችሁ:

በወንጌል ላይ “ኢየሱስ” የሚሉ ስሞች ሲኖሩ የ2000ው እትም “ኢየሱስ” ከሚለው ስም ፊት ምን የሚል ቃል ይጨምራል..?? ያው ከግእዙ ስለተተረጎመ ወይ ከግእዙ አንጻር መልሱ..

የግእዙ “ኢየሱስ” ከሚለው ፊት የሚጨምረው ቃል አስተምህሮ ላይ ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም ግን እስቲ የ2000ውን አልያም የግእዙን እዩና ጻፉልኝ.. ከወንጌል ዝምብላችሁ የፈለጋችሁት ቦታ ቼክ አድርጉ ሂዱና.. ያው አብዛኛው እንደዛ ስለሆነ..

ኮመንት ላይ ኢየሱስ የሚለውንና ከሱ ፊት አብሮ ያለውን ቃል ብቻ ጻፉ.. ከዛ ውጪ መጻፍ አይቻልም

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንድ ወዳጅ አለኝ ሁሌም ሊበደረኝ ሲል ሚልክልኝ ጥቅስ

“ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም”
[መዝ 112: 5]


ስንት ጊዜ ሙሉ ሳይመልስ ይቆይና ሲጨንቀው ደግሞ ሚልክልኝ ጥቅስ..

“ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።”
[ሉቃ 6: 30]

ጥቅሶችን በቦታቸው እንጠቀም ለማለት ነው😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኮመንት ላይ ምትመልሱት በጣም ደስ የሚል ጥያቄ

“እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?”
[1ቆሮ 15: 30]

ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ክቡር ቅዱስ ጳውሎስ ነው.. እና በሚያስፈራ ኑሮ ለምን እንኖራለን..?? ይላል.. ከታች ዝቅ ብሎ “በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ታገልሁ” በማለት የአውሬ ጭካኔ ካላቸው ሰዎች ጋር ሳይቀር እንደታገለ ይናገራል.. ከኃጢአትስ ርቀን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እየፈጸምን ለምን እንኖራለን..??

“ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ” ፈታ እንበል ላይፍ አጭር ናት ለምን አንልም..??

“ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?”

እስቲ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ምን እንደሆነ እዛው ክፍሉ ላይ ያለውን አንብባችሁ ኮምንት ላይ መልሱ..

1ቆሮ 15:30-34 አንብቡና መልሱ..

መልካም እግዚአብሔርን የመውደድና የመፍራት ቀን ይሁንላችሁ ደግሞ..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ በቅዱስ ሚካኤል አንዷ ወዳጄ አሜሪካ ስላለ ገዳም ምን ብትለኝ..?? በ እውነት ምንም ነገር አልጨማመርኩም እና የተባልኩትን ሳስቀምጥ:

- አንድ ሰፋ ያለ አዳራሽ አለ(ኖርማል ነው ይሄ)
- እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ሩም ይኖረዋል ሚተኛበት ምናምን(እ…..ሺ)
- ቲቪ አለ ማንም አያይበትም እንጂ(ኧረ አታስቁን😆😆)
- የጋራ ኪችን አለ ሻይ ምናምን አለ(😭😭 እዚ ጋር አልቻልኩም)
- ፍሪጅም አለ.. ስከፍተው ጭራሽ ሙሉ ምግብ ነው አላለችም(🤣🤣)

አሞላቀቃችኋቸው የምር.. ከብዷቸው እንዳይርቁ እኮ ነው😁😁 ደስ ይላል ቀስ በቀስ እንዲያድጉ..

እኛም እንዲ ይደረግልን እንዳንል ብቻ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ”
[መዝ 97: 10]

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

20,000 ገባን እንዴ ለካ እዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ.. ምንም ሳናስተዋውቀው በቻናል ደረጃ ቴሌግራም ላይ 20k መግባት ቀላል አይደለም..

ከምንም በላይ ግን እዚህ ያለን ቤተሰቦች ክርስትና ላይ ያላችሁ መረዳት ምናምን እና ምንግባባውም ነገር ያበደ ነው.. ቴሌግራም ሁሌም ቢሆን cool ነው የምር.. የቲክቶክ ጀማ እንዳይቀየም እንጂ😁😁

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አይመስላችሁም..??

አንድ ያስተዋልኩት ከጉዋደኞቻችን ጋር ስንቃለድ ስናወራ ምናምን ቃላቶች እና ርእሶች የተወሰነ መገደብ አለባቸው..

ቀለል አድርገን ስናወራ ምናምን ለኛ ኖርማል የሆኑ ግን በጊዜ ሂደት እግዚአብሔርን መፍራትን የሚቀንሱና መዳፈርን የሚያለማምዱ ይመስለኛል.. በተለይ ደርቲ ሚመስል ነገርን መራቅ የተሻለ ይመስለኛል.. አይመስላችሁም..??

እዚው ሚዲያ ላይ ያለው ሳይሆን በአካል አልያም በውስጥ ስናወራ ማለቴ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

🤣🤣 ላዛሩ ይመችሽ ብሮስኪ.. እስቲ ሁላችሁም ፎሎው እያደረጋችሁ አበረታቱት ጸዴ ሰው ነው በጣም.. የኔንም ቪዲዮዎች ኤዲት የሚያደርግልኝ እሱው ነው..

ፎሎው ምናምን አይረሳ ፕሊስ

https://vm.tiktok.com/ZMruC3SBt/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ማር ማሪ ኢማኑኤል የሚባሉት አባት ስለ ዶናልድ ትራምፕ ሲናገሩ እንደው እሱ ካልተመረጠ ክርስትና ከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃል ያውም በዓለም ላይ ስለዚህ ይህ ሰው እንዲመረጥ እጸልያለሁ ነገር አሉ..

የቤተ ክርስቲያን ራስ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ይህንን ሲያይ ምን ይል ይሆን እንደው.. ሥጋ ስለሆንን አንዳንዴ መንፈሳዊውን ነገር በሥጋ ብቻ እናስበዋለን.. ከዛም በጣም በሰው ላይ እንታመናለን.. የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ በአንድ አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ያውም ፕሮቴስታንት ላይ አይመሠረትም..

በታሪክ ውስጥ ከጥንትም ከነ ቁስጥንጥኖስም ጀምሮ ኦርቶዶክስ ነገሥታት የራሳቸውን መልካም ነገርም ሆነ አሳዛኝ ነገርም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥለው አልፈዋል.. መልካም ሲያደርጉ እሰየው.. ከዛ ውጪ ግን ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅ የማያንቀላፈው የእስራኤል ጠባቂ አምላካችን ነው.. እርሱን ብቻ ተስፋ እናደርጋለን.. ደገኛ ንጉሥን ከሰጠንም እሰየው..

ከዛ ውጪ ግን ቴዎድሮስንም ተስፋ አናደርግም ሎል ስቀልድ ነው😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በቅዱስ መስቀል ምልክት ማማተብ..??

ፕሮቴስታንቲዝም ሰዎችን በማያውቁት ነገር ምን ያህል ወደ ትችትና ጥፋት ብቻ እንደሚመራ ማሳያ..

https://vm.tiktok.com/ZMrmfJYU3/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤
ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር”
[ምሳሌ 23: 17]

ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና ማለት የሚያደርጉትን ነውር አይተህ ምናልባትም እየተደሰቱበት እንደሆነም አስተውለህ እንደው እኔም እንዲህ ደስታን ባገኝ ብሎ ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና.. ምክንያቱም ኃጢአተኞች በቶሎ ይጠፋሉና.. ልክ መዝሙረኛው እንደሚለው ነው..

“ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ፡
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፤
ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።”

ስለዚህም በሚያጠፋው ኃጢአት ልብህ አይማረክ.. ይልቁንስ “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” መጠጊያህም እግዚአብሔር ይሆናል.. ለዘላለምም ደስታ ከእርሱ ይሆንልሃል..

“ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር”

እግዚአብሔርን የመፍራትና የማፍቀር ቀን ይሁንልን የዛሬውም የሁሉ ቀን ውሎዋችንም

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ክርስቲያኖች ይሄንን ቪዲዮ ብቻ በማየት ሙስሊም ትሆናላችሁ እውነትን ከፈለጋችሁ”
ተብላችኋል😭😭

https://vm.tiktok.com/ZMrayWEJs/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ነገረ ክርስቶስ” የተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተሰጠውን የማኅበረ ቅዱሳንን ገለጻ ቪዲዮ አየሁ..

መጽሐፉ ውስጥ ጥቂት እንከን ሊገኝ ይችላል.. ያው እንግዲህ ያቺ እንከን ግን ከባድ ጉዳይ ከሆነች ማጥራቱ መልካም ነው.. ማኅበሩም ከዚህ ቀደም እንዳልሁት ጌታ የሚሰራበት የሚጠቀምበት እንደሆነ አስባለሁ አምናለሁም.. የተወደደ ማኅበር.. እዛ ያሉ ወጣቶች ትሕትናቸውም ያስቀናኛል በነገራችን ላይ..

ግን ትንሽ እንደው ግራ ያጋባችኝ ነገር..

የለቀቁት ቪዲዮ ላይ መጽሐፉ ሰሞኑን ሚዲያ ላይ ላለው ክርክርም መልስ ሆነ ብለዋል.. በየት በኩል ነው መልስ ሚሆነው..?? “በሥጋው ፍጡር አይባልም ከተዋሕዶ በኋላ” በማለት በቪዲዮው ላይ የተናገሩት ለምሳሌ መምህር ብርሃኑ አድማስ እንኳን ለዚህ ክርክር እንደማመሳከሪያ አይሆንም አውዱ የተለየ ነው ብለዋል እኮ.. ምናልባት አንዱ የክርስቶስ ውሕድ(composed) ባሕርይ “ፍጡር ወኢፍጡር” ነው የሚለውን በማኅበር ደረጃ የማይቀበሉት ሆነው ከሆነ በጣም አደገኛ ይመስለኛል..

“የአገላለጽ ልዩነት በቻ ነው ያለው” የሚለው አገላለጽ ራሱ እንጃ.. ከተዋሕዶ በኋላ በክርስቶስ ውስጥ “ያልተፈጠረ” ብቻ እንጂ “የተፈጠረ” የሚባል ነገር የለም ከተባለ በቃ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ያለው አንድነት አፍ ላይ ያለ ምስክርነት ብቻ ይሆናል.. በነሣው ሥጋ ከፍጡራን እንደ አንዱ ሚሆነው ሥጋ ፍጡርነቱን ያልተወ እንደሆነ ብቻ ነው.. ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንዴት ያከራክራል ይሄ..?? ይሄ የ double consubstantiality ትምህርትን ሚጋፋ ይመስለኛል..

በነገራችን ላይ መጽሐፉ የጌታችን አስታራቂነት ላይም የተዛባ የሚመስል ነገር ተቀምጧል.. “በምድር ሳለም አስታረቋል አይባልም ይቅር አለን ነው ሚባለው” የሚል ዓይነት ነገር.. እሁድ እሁድ በውዳሴ ማርያም “ለሐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆነ” እያልን ነው ምንጸልየው እንግዲህ.. የእርሱ ማስታረቅ እንደ ቅዱሳን እንዳልሆነ ማሳየት እንጂ ይሄ ዓይነቱ አገላለጽ ጭራሹኑ በቤዛነቱ በኩል ያለውን አስታራቂነቱን መዘንጋትን ሊያመጣ ይችላል ብዬ ነው..

ምንም እኮ ከባድ ነገር የለውም.. አንድ መጽሐፍ ነው አለቀ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ስህተት ካለው ቀላል ነው ቀጣይ ኅትመት ላይ ማሻሻል..

ለማንኛውም ይህንን ድንቅ ማኅበር አሁንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን አብዝቶም ይስራበት

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ”
[መዝ 17: 8]

በሉት እረኛውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን..

መልካም ውሎ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዲየግ.. እስካሁን ከመለሳችሁ በቂ ነው..

ብዙ ጊዜ “ጌታ/ጌታችን” የሚል ቃል መጠቀም በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ አልተለመደም(which is sad) ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግእዝ መጽሐፍ ቅዱሷ ላይ “ኢየሱስ” የሚሉትን ንባባት እንኳን “እግዚእ ኢየሱስ/ጌታ ኢየሱስ” ነው ብላ ምታነባቸው.. በቅዳሴዋም ላይ ለምሳሌ ወንጌል ሲነበብ ከዚሁ ስለሚነበብ ካስተዋላችሁ ቄሱ የሚሉት “ጌታችን ኢየሱስ” ነው።

የሆነ ጊዜ ላይ ያጋራኋችሁ ዘጠኝ ቃላት ብቻ የያዘችው አጭር ጸሎት አለች አ..?? ያው ብዙዎቻችሁ ትጸልዩባት ይሆናል.. በዓለማችን ላይ አብዛኛው ኦርቶዶክስ ይጸልይባታል

“Lord Jesus Christ Son of God have mercy on me a sinner”
[ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ]

ጸሎቷ ይህች ናት እና ደጋግሞ ከልብ መጸለይ ነው መድኃኒታችንን እያሰብን.. እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይም በተደጋጋሚ ያለ ቃል ነው “ጌታ ኢየሱስ” የሚለው.. የመጽሐፉ መጨረሻ ላይም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” ይላል..

እና ይህ ድምጽ(ቃል) የቤተ ክርስቲያን ነው.. ግን ደግሞ መልሶ ለብዙ ክርስቲያኖች እንግዳ አጠራር እየሆነ ነው.. ያሳዝናል.. ቢያንስ ሚዲያው ላይ ማንም እንግዳ አይሆንበትም😁👍

“ክርስቲያን” የሚለውንም ቃል ሁሌ በኦርቶዶክስ ቦታ የምጠቀመው ለዚህ ነው.. ክርስቲያን የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን ብቻ ነን.. ይሄንን ለማስረገጥ ነው..

እና ለማንኛውም ኢየሱስን ባማረ በተወደደ ቤተ ክርስቲያናዊ በሆነ ነገር ሁሉ መጥራት ፍቅርን ይጨምር ይሆናል እንጂ ምንም ጣጣ የለውም ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው ከቅዱስ ወንጌል ክፍል:

“በምሳሌም ብዙ ነገራቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።”
[ማቴዎስ 13: 3-4]

ጌታችን የዘሪውን ምሳሌ ይናገራል.. ባለፈው ሳምንትም ከሉቃስ ወንጌል ይኸው ምሳሌ ተነቦ አካፍያችሁ ነበር.. ያኔ በእሾህ መካከል የወደቀውን ዘር ምሳሌ ነበር ያየነው.. ዛሬ ደግሞ በመንገድ ዳር ስለወደቀው ዘር ምሳሌ እንይ..

የዚህን ምሳሌ ትርጉም ጌታችን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል:

“የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።”
[ማቴዎስ 13: 19]

ቃሉን ሰምቶ በማያስተውል አለ.. እነዚህ ቃሉን ይሰማሉ ግን ከልበ ደንዳናነት ወጥተው በደንብ ተረድተውት ፍሬን ሊያፈሩበት ሲገባ ሰሚ ብቻ የሆኑና ወደ ሕይወት ለመቀየር ፍላጎት የሌላቸው እግዚአብሔርንም የማይናፍቁ ናቸው.. እንዲህ ያሉት በመንገድ ተመሰሉ ጠባቂም የላቸውምና ስለዚህ ክፉ መንፈስ ያንንም የሰሙትን ቃል ከልቡ ይነጥቃል..

ቃሉን የምንሰማ ብቻ ሳይሆን የምናስተውለውና የምናደርገውም ያድርገን አምላካችን..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“አንዱ ውሕድ የሆነው የክርስቶስ ባሕርይ የተፈጠረ ነው ወይስ ያልተፈጠረ..??” ለሚል ጥያቄ

“አንዱ ፍጡር ሌላኛው ፈጣሪ የሚል አርዮሳዊ/ንስጥሮሳዊ/ካቶሊካዊ ነው” እያሉ ያልተጠየቁትን ሚመልሱ ሰዎችን ባየሁ ቁጥር ሚሰማኝ ስሜት😁😁

ያው እዚህ ርእስ ላይ ምንም አልልም.. ዝም ብሎ ማለፍ ነው😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የራሳቸውን ሕግ አውጥተው “ፉት” ያለውንም እንደ ፈሪሳውያን ሲዋጉ😁😁

እኔም ግን ቢቀር ጨራሹኑ ከሚሉት ወገን ነኝ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“[በዚህ ዓለም] ዘውድን የሚቀዳጀው(ባለ ጠጎች የሆኑቱ) እንኳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይራዱት ዘንድ ድንኳን ሰፊውን(ጳውሎስን) እና አሣ አጥማጁን(ጴጥሮስን) ይለምናል.. ቢሞቱ እንኳን”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ : homilies on 2 Corinthians: Hom. 26

ንኳን ለጵጥሮስ ወጳውሎስ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ.. የእነርዚህን እጅግ የተወደዱ ሐዋርያት በረከት በመምህራኖቻችን እና በሁላችን ላይ ያሳድር.. አሜን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ትንሽ እንዳስቀናችሁ ፍቀዱልኝ..

የጻድቁ አባት ጸሎት ሁላችሁን ያግዝ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ድንግል ማርያም ከሌለች ኢየሱስ የለም”..??

https://vm.tiktok.com/ZMrAkuvxp/

Читать полностью…
Subscribe to a channel