apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

እንዴት ልጸልይ..??

- አባታችን ሆይን ጸልይ መድኃኒታችን ኢየሱስ ያስተማረን ነው..

- ጸሎተ ሃይማኖትን መጸለይ.. በመንፈስ ሆነህ ጸልየው ምክንያቱም እግዚአብሔርን አንተ እንዲህ ነህ እናም በአንተ እናምናለን የሚል የሃይማኖት ምስክርነት አለው

- ከጸሎት መጽሐፍት ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ የቅዱሳንን ጸሎት ማየት ለምሳሌ የዳዊትን መዝሙር.. ብዙ ነገሮችን ስለሚነካ አባ ጊዮርጊስም እንደሚለው “የምስጋና ጎርፍ ከአፉ ፈሰሰ” ስለዚህ በእርሱ ምስጋና ማመስገን.. እንዲሁ የማንበብ ጉዳይ ሳይሆን ከልብ መጸለይ.. እንደ አቅም የቻላችሁትን ብቻ.. እንዲሁ ውዳሴ ማርያምንም..

- የልባችሁን ደግሞ ለአባታችሁ ለእግዚአብሔር ማውራት.. በእናንተው አነጋገር ለቃሉ ማማር ሳትጨነቁ ዝም ብላችሁ ከልባችሁ ማውራት..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዲት ነገር ግልጽ ላድርግ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ስላለው የግድላት ድርሳናት ተዓምራት ጉዳይ..

ያው እኛ ሃገር አንዳንድ ሰው ባለማወቅ “ቤተ ክርስቲያን ስህተት ነው እስካላለች ድረስ ያለውን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለብህ” የሚል ትምህርትን የሚሰጡ አሉ.. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እኔ እስከማውቀው እንዲህ ያለ ነገር የለም.. ለመንፈሳዊ ሕይወትህ እንዲጠቅምህ አድርገህ ተጠቀምበት ከዛ ውጪ የተጻፈውን ሁሉ ተቀበል የሚባል ነገር የለም..

በግብጽ ያለው እንግዲህ እኔ እስከ ደረስኩበት ድረስ ቢያንስ ከታች ያሉትን ይመለከታል

1. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌም እንደተናገሩት በግብጽ ገድላት ተዓምራትን እንደ ታሪክ ለይተው አስቀመጧቸው እንጂ በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ ምናምን አያካትቷቸውም.. ስንክሳር ይነበባል

2. እንደዚህም ሆኖ በነዚህ መጽሐፍት ውስጥ እንደ እኛ ሃገር ብዙም ግራ ሚያጋቡ ነገሮች የሉም..

3. የዚህን ያህል ትውልድ ይማርልሃል የሚል ዓይነት እና የቦታ ቃል ኪዳኖች ከመዳን አንጻር የሉም(እስከ ጠየኩት ድረስ)

4. ድርሳነ መላእክት እንዲሁ ያሉ አልመሰለኝም እስከተመለሰልኝ ድረስ

አንድ ፕሮቴስታንት ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ቢፈልግ የነዚህን መጽሐፍት ነገር ሁሉ መቀበል አይጠበቅበትም.. ሲመጣ ብቻ ሳይሆን ሲኖርም.. ምናልባት ግን አይ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ አትልም ካላችሁ አንድ ቀን ኦፊሻሊ እስኪነገር ድረስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ ነው..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

“አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረካቸው ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛርሙርቱ ሰጠ።”
[ሉቃስ 9: 16]

ጌታችን በተዓምሩ ምግብን አበርክቶ መገባቸው.. ጌታችን በሥጋዊ ነገሮችም ይባርካል.. ከ እኛ የሚጠበቀው ግን አስቀድመን ጽድቁን መንግስቱን መሻት ነው..

በሐዲስ ኪዳን ጌታችን የሰጠን ትልቁ ምግብ ራሱን ነው.. ይህም ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ ነው.. ከዚህ ማእድ ለመካፈል ደግሞ የሚያስፈልገን ንስሐ ብቻ ነው.. መድኃኒታችን ከእኛ የሚፈልገው መመለሳችንን ብቻ እንጂ ስንመለስ እርሱ ራሱ በደስታ አቅፎ ያኖረናል

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይቅርታ የኔ ተወዳጆች ምንም ርእሱ ላይ ለመናገር አይደለም ክርስቶስ በሚያውቀው.. ግን በቃ ቀሲስ ዶር ዘበነ በድጋሜ ተጠይቀው የመለሱትን ስሰማ እንደው ደስ አለኝም እና ደግሞ በቀደመው መልሳቸው ተጨንቀው የነበሩ ካሉም ለነሱም ይሆን ዘንድ ነው..

ይህንን ርእስ ግን እንደ ርእስ የትም ቤት አታንሱት በጌታ በቂ ነገር ስለተባለበት

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ”[ሉቃስ 1:13]

መልአኩ የዘካርያስ ጸሎት እንደተሰማለት ነግሮ መጀመሩ ቀድሞውኑ ጸሎቱ ምን እንደሆነ ያውቃል ማለት ነው.. እና ያ ጸሎትም በእግዚአብሔር ዘንድ እንደተሰማ ይነግረዋል.. ጸሎትንም የማሳረግ ሥራን ሊሰሩ ይችላሉና ነው.. ልክ ራዕይ ላይ እንዳለው..

የዮሐንስ ራእይ 8
3፤ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
4፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።

እዚህ ጋር መልአክ የሚለውን ለኢየሱስ የሚሰጡ አሉ ግን እኔ እስካየሁት ኢየሱስ መሆኑን የሚያመለክት ግልጽ የሆነ ነገር የለውም.. ሲቀጥል “ሌላም መልአክ” የሚለው አገላለጽ እንደሌሎቹ መልአክ መሆኑን አመልካች ነው..

እና ደግሞ “መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ” ተብለዋል[ዕብ 1:14]

እንዴት ነው የሚያግዙን..?? የሚያግዙን እንደሆነ ከተነገረን ከመላእክት ጋር ግንኙነት አታድርጉ የሚሉን ከየት አምጥተው ነው..??

መዳንን ትወርሱ ዘንድ ያላችሁ እናንተ.. መልአኩ ያግዛችሁ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለሙስሊም ኡስታዞች✌️✌️

https://vm.tiktok.com/ZMrHgEQhe/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አይመስላችሁም..??

አንድ ያስተዋልኩት ከጉዋደኞቻችን ጋር ስንቃለድ ስናወራ ምናምን ቃላቶች እና ርእሶች የተወሰነ መገደብ አለባቸው..

ቀለል አድርገን ስናወራ ምናምን ለኛ ኖርማል የሆኑ ግን በጊዜ ሂደት እግዚአብሔርን መፍራትን የሚቀንሱና መዳፈርን የሚያለማምዱ ይመስለኛል.. በተለይ ደርቲ ሚመስል ነገርን መራቅ የተሻለ ይመስለኛል.. አይመስላችሁም..??

እዚው ሚዲያ ላይ ያለው ሳይሆን በአካል አልያም በውስጥ ስናወራ ማለቴ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

🤣🤣 ላዛሩ ይመችሽ ብሮስኪ.. እስቲ ሁላችሁም ፎሎው እያደረጋችሁ አበረታቱት ጸዴ ሰው ነው በጣም.. የኔንም ቪዲዮዎች ኤዲት የሚያደርግልኝ እሱው ነው..

ፎሎው ምናምን አይረሳ ፕሊስ

https://vm.tiktok.com/ZMruC3SBt/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ማር ማሪ ኢማኑኤል የሚባሉት አባት ስለ ዶናልድ ትራምፕ ሲናገሩ እንደው እሱ ካልተመረጠ ክርስትና ከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃል ያውም በዓለም ላይ ስለዚህ ይህ ሰው እንዲመረጥ እጸልያለሁ ነገር አሉ..

የቤተ ክርስቲያን ራስ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ይህንን ሲያይ ምን ይል ይሆን እንደው.. ሥጋ ስለሆንን አንዳንዴ መንፈሳዊውን ነገር በሥጋ ብቻ እናስበዋለን.. ከዛም በጣም በሰው ላይ እንታመናለን.. የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ በአንድ አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ያውም ፕሮቴስታንት ላይ አይመሠረትም..

በታሪክ ውስጥ ከጥንትም ከነ ቁስጥንጥኖስም ጀምሮ ኦርቶዶክስ ነገሥታት የራሳቸውን መልካም ነገርም ሆነ አሳዛኝ ነገርም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥለው አልፈዋል.. መልካም ሲያደርጉ እሰየው.. ከዛ ውጪ ግን ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅ የማያንቀላፈው የእስራኤል ጠባቂ አምላካችን ነው.. እርሱን ብቻ ተስፋ እናደርጋለን.. ደገኛ ንጉሥን ከሰጠንም እሰየው..

ከዛ ውጪ ግን ቴዎድሮስንም ተስፋ አናደርግም ሎል ስቀልድ ነው😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በቅዱስ መስቀል ምልክት ማማተብ..??

ፕሮቴስታንቲዝም ሰዎችን በማያውቁት ነገር ምን ያህል ወደ ትችትና ጥፋት ብቻ እንደሚመራ ማሳያ..

https://vm.tiktok.com/ZMrmfJYU3/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤
ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር”
[ምሳሌ 23: 17]

ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና ማለት የሚያደርጉትን ነውር አይተህ ምናልባትም እየተደሰቱበት እንደሆነም አስተውለህ እንደው እኔም እንዲህ ደስታን ባገኝ ብሎ ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና.. ምክንያቱም ኃጢአተኞች በቶሎ ይጠፋሉና.. ልክ መዝሙረኛው እንደሚለው ነው..

“ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ፡
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፤
ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።”

ስለዚህም በሚያጠፋው ኃጢአት ልብህ አይማረክ.. ይልቁንስ “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” መጠጊያህም እግዚአብሔር ይሆናል.. ለዘላለምም ደስታ ከእርሱ ይሆንልሃል..

“ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር”

እግዚአብሔርን የመፍራትና የማፍቀር ቀን ይሁንልን የዛሬውም የሁሉ ቀን ውሎዋችንም

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ክርስቲያኖች ይሄንን ቪዲዮ ብቻ በማየት ሙስሊም ትሆናላችሁ እውነትን ከፈለጋችሁ”
ተብላችኋል😭😭

https://vm.tiktok.com/ZMrayWEJs/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ነገረ ክርስቶስ” የተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተሰጠውን የማኅበረ ቅዱሳንን ገለጻ ቪዲዮ አየሁ..

መጽሐፉ ውስጥ ጥቂት እንከን ሊገኝ ይችላል.. ያው እንግዲህ ያቺ እንከን ግን ከባድ ጉዳይ ከሆነች ማጥራቱ መልካም ነው.. ማኅበሩም ከዚህ ቀደም እንዳልሁት ጌታ የሚሰራበት የሚጠቀምበት እንደሆነ አስባለሁ አምናለሁም.. የተወደደ ማኅበር.. እዛ ያሉ ወጣቶች ትሕትናቸውም ያስቀናኛል በነገራችን ላይ..

ግን ትንሽ እንደው ግራ ያጋባችኝ ነገር..

የለቀቁት ቪዲዮ ላይ መጽሐፉ ሰሞኑን ሚዲያ ላይ ላለው ክርክርም መልስ ሆነ ብለዋል.. በየት በኩል ነው መልስ ሚሆነው..?? “በሥጋው ፍጡር አይባልም ከተዋሕዶ በኋላ” በማለት በቪዲዮው ላይ የተናገሩት ለምሳሌ መምህር ብርሃኑ አድማስ እንኳን ለዚህ ክርክር እንደማመሳከሪያ አይሆንም አውዱ የተለየ ነው ብለዋል እኮ.. ምናልባት አንዱ የክርስቶስ ውሕድ(composed) ባሕርይ “ፍጡር ወኢፍጡር” ነው የሚለውን በማኅበር ደረጃ የማይቀበሉት ሆነው ከሆነ በጣም አደገኛ ይመስለኛል..

“የአገላለጽ ልዩነት በቻ ነው ያለው” የሚለው አገላለጽ ራሱ እንጃ.. ከተዋሕዶ በኋላ በክርስቶስ ውስጥ “ያልተፈጠረ” ብቻ እንጂ “የተፈጠረ” የሚባል ነገር የለም ከተባለ በቃ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ያለው አንድነት አፍ ላይ ያለ ምስክርነት ብቻ ይሆናል.. በነሣው ሥጋ ከፍጡራን እንደ አንዱ ሚሆነው ሥጋ ፍጡርነቱን ያልተወ እንደሆነ ብቻ ነው.. ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንዴት ያከራክራል ይሄ..?? ይሄ የ double consubstantiality ትምህርትን ሚጋፋ ይመስለኛል..

በነገራችን ላይ መጽሐፉ የጌታችን አስታራቂነት ላይም የተዛባ የሚመስል ነገር ተቀምጧል.. “በምድር ሳለም አስታረቋል አይባልም ይቅር አለን ነው ሚባለው” የሚል ዓይነት ነገር.. እሁድ እሁድ በውዳሴ ማርያም “ለሐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆነ” እያልን ነው ምንጸልየው እንግዲህ.. የእርሱ ማስታረቅ እንደ ቅዱሳን እንዳልሆነ ማሳየት እንጂ ይሄ ዓይነቱ አገላለጽ ጭራሹኑ በቤዛነቱ በኩል ያለውን አስታራቂነቱን መዘንጋትን ሊያመጣ ይችላል ብዬ ነው..

ምንም እኮ ከባድ ነገር የለውም.. አንድ መጽሐፍ ነው አለቀ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ስህተት ካለው ቀላል ነው ቀጣይ ኅትመት ላይ ማሻሻል..

ለማንኛውም ይህንን ድንቅ ማኅበር አሁንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን አብዝቶም ይስራበት

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ”
[መዝ 17: 8]

በሉት እረኛውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን..

መልካም ውሎ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዲየግ.. እስካሁን ከመለሳችሁ በቂ ነው..

ብዙ ጊዜ “ጌታ/ጌታችን” የሚል ቃል መጠቀም በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ አልተለመደም(which is sad) ግን ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግእዝ መጽሐፍ ቅዱሷ ላይ “ኢየሱስ” የሚሉትን ንባባት እንኳን “እግዚእ ኢየሱስ/ጌታ ኢየሱስ” ነው ብላ ምታነባቸው.. በቅዳሴዋም ላይ ለምሳሌ ወንጌል ሲነበብ ከዚሁ ስለሚነበብ ካስተዋላችሁ ቄሱ የሚሉት “ጌታችን ኢየሱስ” ነው።

የሆነ ጊዜ ላይ ያጋራኋችሁ ዘጠኝ ቃላት ብቻ የያዘችው አጭር ጸሎት አለች አ..?? ያው ብዙዎቻችሁ ትጸልዩባት ይሆናል.. በዓለማችን ላይ አብዛኛው ኦርቶዶክስ ይጸልይባታል

“Lord Jesus Christ Son of God have mercy on me a sinner”
[ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እኔን ኃጢአተኛውን/ዋን ማረኝ]

ጸሎቷ ይህች ናት እና ደጋግሞ ከልብ መጸለይ ነው መድኃኒታችንን እያሰብን.. እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይም በተደጋጋሚ ያለ ቃል ነው “ጌታ ኢየሱስ” የሚለው.. የመጽሐፉ መጨረሻ ላይም “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” ይላል..

እና ይህ ድምጽ(ቃል) የቤተ ክርስቲያን ነው.. ግን ደግሞ መልሶ ለብዙ ክርስቲያኖች እንግዳ አጠራር እየሆነ ነው.. ያሳዝናል.. ቢያንስ ሚዲያው ላይ ማንም እንግዳ አይሆንበትም😁👍

“ክርስቲያን” የሚለውንም ቃል ሁሌ በኦርቶዶክስ ቦታ የምጠቀመው ለዚህ ነው.. ክርስቲያን የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን ብቻ ነን.. ይሄንን ለማስረገጥ ነው..

እና ለማንኛውም ኢየሱስን ባማረ በተወደደ ቤተ ክርስቲያናዊ በሆነ ነገር ሁሉ መጥራት ፍቅርን ይጨምር ይሆናል እንጂ ምንም ጣጣ የለውም ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የከተማዎቹም “ዲያቆኔ” እያሉ “ሲዘምሩ” እኮ የተወሰነ አስግተውን ነበር

ዲ.ያ.ማ በቃ ተረጋጉ ይኸው ነው

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ያስቀደስኩት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነበር እና በጣም ነው ደስ የሚለው.. ያው ቅዳሴው በብዛት ይመሳሰላል.. ያው ግን ቅዱስ ምስጢር ላይ የተገለጠ ነገር ስለሆነ ያለው ኅብስቱን አውጥተው ምናምን ሰው እያየው ይጻልያሉ.. ልክ ጌታችን እንዳደረገው ቆርሰውም ይሰጣሉ ለሚቆርቡ ሁሉ..

ዌል 80% የሚሆነው ሰው ቆርቧል.. በጣም ደስ ይላሉ.. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም እዚህ ላይ በደንብ መስራት አለባት..

እና ደግሞ ገድላት ተዓምራት መጽሐፍት ስለከበዱኝ ወደ ኦርቶዶክስ አልመጣም የምትሉ ፕሮቴስታንቶች ምንም እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጨመር የግድ እነዚህን መጽሐፍት ተቀበሉ ባትባሉም ግን ደግሞ እንዲሁ በቃ የያዛችሁ ነገር ካለ እዚው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን መጠመቅ ትችላላችሁ.. አውሩኝና እኔም ላግዛችሁ እችላለሁ.. እኔ ግን ምመክራችሁ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ብትረዱ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በአንድ ቪዲዮ 3 ቪዲዮ ሎል

- ክፉ ሥራቸው
- እስልምና ላይ
- አይ ጌታቸው😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrx2yyfR/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የእርስ በእርስ ጦርነትና በተፈጥሮ አደጋ የሚመጣ ሞት በጣም አደገኛ ነው.. በእምነት ያልጠነከረን ሰው የ እግዚአብሔርን መኖር እንኳ ያጠራጥሩታል.. የውስጥ ስብራቱ ከባድ ነው..

በጎፋ የምንሰማው ነገር እንዴት ያማል በጌታ.. ኧረ አምላካችን ሆይ የምታስፈልጋቸው አንተ ነህና በዚህ ሰዓት አብዝተህ ቅረባቸው.. በጸሎት እናስብ የሞቱትን ነፍስ እንዲምር ያሉትንም እንዲያጽናና

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቅዱስ ቁርባን ሲወሰድ ሊፈራ አይገባም..??😭😭

የመለኮት ሥጋና ደም አይባልም..??


https://vm.tiktok.com/ZMr9jTJJg/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ድክም ሲላችሁ.. ሲሰለቻችሁና መጸለይ እንኳ ሲከብዳችሁ.. የጌታችንን ትንሳዔ አስቡ.. የእርሱ ትንሳዔ የእኛን ትንሳዔ አረጋግጧልና ሞተን እንደማንቀር እንደምንነሳ ከእርሱም ጋር ለዘላለም እንደምንኖር አስቡ..

ያንን ሕይወት ስናስብ በዝች አላፊ ጠፉ በሆነችው ኑሮዋችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ቀላል ይሆኑብንና በዚህም ሰዓት ከጌታችን ጋር መኖር ከእርሱም ጋር መዋል ለእኛ መልካም እንደሆነ ያስተምረናል.. ለሁሉም ነገር ግን ጸጋው ያግዘን ያበርታን.. ምን ያህል አቅመ ቢሶች እንደሆንን ስለሚያውቅ በድካማችን የሚራራልን ሊቀ ካህናት ነው ያለን.. ስለዛ በምንም ሁኔታ ውስጥ ስንሆን እርሱን ተስፋ እናድርግ.. ተስፋችን እርሱ ነው..

መልካም ውሎ እናንተ በጌታ መንግስት(በቤተ ክርስቲያን) ውስጥ ያላችሁ የንጉሥ ልጆች.. እንደ ንጉሥ ልጅ የምንውልበት ቀን ይሁንልን.. ንጉሡ ትህትናውን አሳይቶናል እኛም እንደሱ በትህትና ሰዎችን በመውደድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም እንውል ዘንድ ይርዳን..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ተፋልሶ” ብለህ ከራሱ ከ2000ው ኅትመት ሕዳግ ላይ ኮርጀህ መጽሐፍ የጻፍከው.. አንተ ትለያለህ የምር😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrut2rFU/

👆👆👆

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጌታቸው(ተፋልሶ) ምንድን ነው ሚሉን😁😁

የዚ ዘመን “ነቢይ” የመሆን መስፈርትስ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMruBQsV3/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የ….. መልእክት

☹️☹️ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ዝናብ እየዘነበ ስለነበር ነው መሰለኝ አርፍጄ ተነሳሁ.. አላርም አልጠቀምም ነበር ብዙ ጊዜ.. እና ቅዳሴ ወንጌል ተነቦ እንዳለቀ ደረስኩ😭😭 ስለዛ ሌሎቹ ላይም አልደረስኩም..

እስቲ ኮመንት ላይ አሳውቁኝ.. አንዳችሁ ከወንጌል አንዳችሁ ከጳውሎስ አንዳችሁ ከሐዋርያት ሥራ አንዳችሁ ከቀሩት እያደረጋችሁ..

መልካም የጌታ ቀን

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

መልስ..??😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrmrtWKN/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እኔ ምላችሁ የቲክቶክ ጀማዎች.. ምንድነው ፕሮፋይላችሁን ብዙዎቻችሁ የኔን ፎቶ አድርጋችኋል😁😁 አውቃለሁ ፍቅራችሁን የምትገልጹበት እንደሆነ

ግን የኔ ተወዳጆች ከይቅርታ ጋር ሌላ ብታደርጉ.. እንዲ ሲሆን ሌላ ነገር ሊያስመስል ስለሚችል.. ፍቅራችሁን እረዳዋለሁ እንድች ብላችሁ እንዳታስቡ😁😁 በቃ ቀይሯት እወዳችኋለሁ አመሰግናለሁ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የብልህ ክርስቲያን ተማሪ አንዱ መገለጫ..

ቴዮሎጂን እንደ አዲስ አለመስራት.. በጣም በቀላሉ ሊስት እንደሚችል በማሰብ የጥንት አባቶቹ ያስተላለፉለትን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን ብቻ መናገር.. ስለዚህም ለጭንቅላቱ የሚከብድ ነገር ሲገጥመው ራሱ ተምሮ ከፍ ማለትን የሚመርጥ እንጂ ከአባቶቹ የተቀበለውን የጌታን ትምህርት ወደራሱ ዝቅታ ለማውረድ የማይታገል..

እርሱ ብልህ ተማሪ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በፕሮቴስታንት ውስጥ ካሉ ሰው ሰራሽ ትምህርቶች ውስጥ አንዱ

https://vm.tiktok.com/ZMr58rPH6/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጠያቂ: ጥምቀት ያድናል..??
መላሽ: ኢየሱስ ያድናል ነው

አከብራቸዋለሁ ግን ምን ዓይነት መልስ ነው ይሄ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrPr9AvQ/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እስቲ ልጠይቃችሁ:

በወንጌል ላይ “ኢየሱስ” የሚሉ ስሞች ሲኖሩ የ2000ው እትም “ኢየሱስ” ከሚለው ስም ፊት ምን የሚል ቃል ይጨምራል..?? ያው ከግእዙ ስለተተረጎመ ወይ ከግእዙ አንጻር መልሱ..

የግእዙ “ኢየሱስ” ከሚለው ፊት የሚጨምረው ቃል አስተምህሮ ላይ ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም ግን እስቲ የ2000ውን አልያም የግእዙን እዩና ጻፉልኝ.. ከወንጌል ዝምብላችሁ የፈለጋችሁት ቦታ ቼክ አድርጉ ሂዱና.. ያው አብዛኛው እንደዛ ስለሆነ..

ኮመንት ላይ ኢየሱስ የሚለውንና ከሱ ፊት አብሮ ያለውን ቃል ብቻ ጻፉ.. ከዛ ውጪ መጻፍ አይቻልም

Читать полностью…
Subscribe to a channel