apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ይቅርታ አድርግልኝ እንግዲህ አቡ..
በአደባባይ የተናገርከው ስለሆነ
በአደባባይ መለስኩልህ..

https://vm.tiktok.com/ZMrqNVHBW/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የቅዱሳንን ምልጃ ማን ይቀበላል ማን ደግሞ አይቀበልም..??

የሚቀበሉት:-
1. ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ(ኦርቶዶክሱም ካቶሊኩም አሲሪያኑም)

2. ፕሮቴስታንት(እንደ ሉተራን ያሉት.. ያው የሰዎችን invocation ግን ይቃወማሉ)

በአጠቃላይ ይህንን የማይቀበል በጥንት ቤተ ክርስቲያን አባቶች የተወገዘ ነው.. ለምሳሌ የጄሮም against vigilantius ሥራ ይነበብ


የማይቀበሉ:-
- እስላም እና ጴንጤ(ኦንሊ ጂሰሶችን ጨምሮ)

እስላም ወይም ጴንጤ ካልሆንክና የኢየሱስ ከሆንክ የቅዱሳንን እገዛ በተለይም የእመቤታችንን ተጠቀም በጣም ይረዳሃል

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዮሐ 15:2 ላይ በግሪኩ “ፍሬ ማያፈራውን ያስወግደዋል” የሚለው የለም..??😭😭

https://vm.tiktok.com/ZMrVeNP6M/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዳንዴ እንዲሁ በልምድ ከሚባሉ ነገር ውስጥ..

“ኢየሱስ በምድር ሳለ አልማለደም ምልጃን አላቀረበም”

እስከማውቀው ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ አትልም.. አሁን ላይ እየማለደ(እየጸለየ) ባይኖርም በሥጋው ወራት ግን ጸሎትና ምልጃን አቅርቧል.. በቲክቶኩ መንደር አንዲት እህት ባለማወቅ ከብዙ ጊዜያት በፊት “እመቤቴን ሰው ናት ልትሉ ነው እንዴ” እያለች ስትከራከር አስታውሳለሁ.. ካላት ፍቅር አንጻር ያው ባለማወቅ የሌለውንም መናገር ነው ይሄ..

መድኃኒታችን ኢየሱስንም በምድርም አልማለደም ማለትን ልክ እንደዛች እህታችን ነው ማየው.. ምክንያቱም ለጌታ ያለን ፍቅርና ክብር የሚታየው እንዲሁ በመሸፋፈን ሳይሆን እንዳለ ያለውን በመቀበል ነው.. ጸለየ ቢባል ምን ይከብዳል ሞቷል እንኳ እየተባለ..

ያው ግን የ እርሱ ጸሎት እንደ ማንኛውም ሰው ጸሎት አይደለም ምክንያቱም:

1. እርሱ ሲጸልይ ሰው እንደመሆኑ ቢጸልይም እንኳ እርሱ ግን ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክም ነው.. ስለዚህም የጸለየው ሥግው ቃል ነው..

2. ሲጸልይ ከታላቅ መስዋእት ጋርም ነው ይህም የራሱን ሥጋ አንዴ ለዘላለም በማቅረብ ነው.. ይህም ሥጋ የአምላክ(የቃል) ሥጋ ነው

ያው ለማስታወስ ያህል ብቻ እንጂ ይህ ይጠፋችኋል ብዬ አይደለም

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“ይህንም ብሎ፡ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና፡ ብሎ ጮኸ።”
[ዮሐንስ 11:43]

ከሞተ አራት ቀን ወደ ሆነው “ይሸታል” ወደተባለው ሙት ጌታችን መጥቶ አስነሳው.. መግነዙን ፍቱት አለ.. እና አባ ሲያስተምሩ ምን አሉን በኃጢአት ብትተሳሰሩ እንኳ ጌታን ተስፋ አድርጉት እርሱ ከታሠራችሁበት ማሰሪያ ፈትቶ ነጻ ያደርጋችኋል.. እርሱን ብቻ ተስፋ አድርጉ.. የሞተውን አበቃለት የተባለውን እንኳ አስነስቷልና..

እርሱ የትኛውንም ልብ ሳይጸየፍ በልዩ ፍቅሩ በዛ ሊኖር ይመጣልና እናንተ ደግሞ ጌታን የሚቀበል ልብ ይኑራችሁ.. ጌታችሁ የልባችሁን በር ዘወትር ያንኳኳልና ክፈቱለት እርሱ ይግባ..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እሺ ጋይስ ቪዲዮ የለቀቀውንም ወንድም አናግሬው ቪዲዮውን አንስቶታል.. ያው በስልክ ያለውም contact ውስጥ ስለመጣልኝ ነው እንደዛ ያልኩት ብሏል እና አጋጣሚ በስህተት ነው እንደዛ ያለው..

ሪፖርት አድርጉ ፌኩን አካውንት

Report account የሚለውን መርጣችሁ ከዛም Frauds and scams በሚለው..

👇👇👇

yaregal.abegaz.ke?_t=8oYZgKIcDQL&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yaregal.abegaz.ke?_t=8oYZgKIcDQL&_r=1

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እኔኮ ሚዲያውን ልተወው አስባለሁ ግን እንደዚህ ዓይነት ቪዲዮ እያየሁ እንዴት ልፍታችሁ እሺ..??😁😁

ጌታ በጸጋ በቅድስና በጤንነት ያሳድግልሽ እህታችን..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንድ ፕሮቴስታንት ወንድም() ላይቭ ላይ “አኬ ፍጡር ወኢፍጡር በሚለው ተወግዟል በራሱ ሰዎች” ነገር አለ.. ያው የመምህር ቀሲስ ዘበነን ይዞ ነውና እነሆ ላለፈው አለመግባባት

https://vm.tiktok.com/ZMrCVStsD/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አሁን ደግሞ በአውሮፓና አሜሪካ ላሉ እህቶች ድምጽ እንሆናለን.. ሎል(ለሁሉም አይደለም)

ውጭ ሃገር ምን እየተካሄደ ነው ወገን..?? ወንድሞች ነቃ በሉ እየተባላችሁ ነው..

Europe ያለች አንዲት ወዳጄ አሁን እያወራችኝ ነበር እና ከሌላ ሰውም እንደሰማሁት ከሆነ ወንዶቹ ጌታችንን የሚወዱ አይመስሉም የቤተ ክርስቲያን ሰዎችም አይመስሉም ተብላችኋል..

ማለት የዘመኑ ወጣት ሆኖ ግን ደግሞ አምላኩን የሚወድና የሚፈራ የለም እየተባለ ነው.. ይቅርታና በአጭሩ ሰገጥ ይበዛል ነው ሚሉን ሎል.. ወይስ እርድና ዘንድሮም ከጌታ በመለየት መሆኑ አልቀረም..??😁😁 ነቃ እያልን ኧረ ከዚህ በፊት እንዳልነው አራዳ የሚያስቀድስ ነው አራዳ ኢየሱስን የሚወድ ነው..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የከተማዎቹም “ዲያቆኔ” እያሉ “ሲዘምሩ” እኮ የተወሰነ አስግተውን ነበር

ዲ.ያ.ማ በቃ ተረጋጉ ይኸው ነው

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ያስቀደስኩት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነበር እና በጣም ነው ደስ የሚለው.. ያው ቅዳሴው በብዛት ይመሳሰላል.. ያው ግን ቅዱስ ምስጢር ላይ የተገለጠ ነገር ስለሆነ ያለው ኅብስቱን አውጥተው ምናምን ሰው እያየው ይጻልያሉ.. ልክ ጌታችን እንዳደረገው ቆርሰውም ይሰጣሉ ለሚቆርቡ ሁሉ..

ዌል 80% የሚሆነው ሰው ቆርቧል.. በጣም ደስ ይላሉ.. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም እዚህ ላይ በደንብ መስራት አለባት..

እና ደግሞ ገድላት ተዓምራት መጽሐፍት ስለከበዱኝ ወደ ኦርቶዶክስ አልመጣም የምትሉ ፕሮቴስታንቶች ምንም እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጨመር የግድ እነዚህን መጽሐፍት ተቀበሉ ባትባሉም ግን ደግሞ እንዲሁ በቃ የያዛችሁ ነገር ካለ እዚው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን መጠመቅ ትችላላችሁ.. አውሩኝና እኔም ላግዛችሁ እችላለሁ.. እኔ ግን ምመክራችሁ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ብትረዱ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በአንድ ቪዲዮ 3 ቪዲዮ ሎል

- ክፉ ሥራቸው
- እስልምና ላይ
- አይ ጌታቸው😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrx2yyfR/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የእርስ በእርስ ጦርነትና በተፈጥሮ አደጋ የሚመጣ ሞት በጣም አደገኛ ነው.. በእምነት ያልጠነከረን ሰው የ እግዚአብሔርን መኖር እንኳ ያጠራጥሩታል.. የውስጥ ስብራቱ ከባድ ነው..

በጎፋ የምንሰማው ነገር እንዴት ያማል በጌታ.. ኧረ አምላካችን ሆይ የምታስፈልጋቸው አንተ ነህና በዚህ ሰዓት አብዝተህ ቅረባቸው.. በጸሎት እናስብ የሞቱትን ነፍስ እንዲምር ያሉትንም እንዲያጽናና

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቅዱስ ቁርባን ሲወሰድ ሊፈራ አይገባም..??😭😭

የመለኮት ሥጋና ደም አይባልም..??


https://vm.tiktok.com/ZMr9jTJJg/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ድክም ሲላችሁ.. ሲሰለቻችሁና መጸለይ እንኳ ሲከብዳችሁ.. የጌታችንን ትንሳዔ አስቡ.. የእርሱ ትንሳዔ የእኛን ትንሳዔ አረጋግጧልና ሞተን እንደማንቀር እንደምንነሳ ከእርሱም ጋር ለዘላለም እንደምንኖር አስቡ..

ያንን ሕይወት ስናስብ በዝች አላፊ ጠፉ በሆነችው ኑሮዋችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ቀላል ይሆኑብንና በዚህም ሰዓት ከጌታችን ጋር መኖር ከእርሱም ጋር መዋል ለእኛ መልካም እንደሆነ ያስተምረናል.. ለሁሉም ነገር ግን ጸጋው ያግዘን ያበርታን.. ምን ያህል አቅመ ቢሶች እንደሆንን ስለሚያውቅ በድካማችን የሚራራልን ሊቀ ካህናት ነው ያለን.. ስለዛ በምንም ሁኔታ ውስጥ ስንሆን እርሱን ተስፋ እናድርግ.. ተስፋችን እርሱ ነው..

መልካም ውሎ እናንተ በጌታ መንግስት(በቤተ ክርስቲያን) ውስጥ ያላችሁ የንጉሥ ልጆች.. እንደ ንጉሥ ልጅ የምንውልበት ቀን ይሁንልን.. ንጉሡ ትህትናውን አሳይቶናል እኛም እንደሱ በትህትና ሰዎችን በመውደድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም እንውል ዘንድ ይርዳን..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እመቤታችን ያው ለኮፕቲኮች(ግብጽ ኦርቶዶክሶች) በጣም ትገለጥላቸዋለች.. እንደምታውቁት በዚህ ዘመን እንኳን ቅርብ ጊዜ ላይ በዘይቱን ለብዙዎች ለሙስሊሞችም ጭምር በተደጋጋሚ በዛው በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን በብርሃን መልክ ተገልጣለች.. ጭራሽ አንዳንድ የተወሰነ ጥራት የጎደላቸው ቢሆኑም የተነሱ ፎቶዎች እና የዓይን እማኞች አሁንም ድረስ አሉ.. እና ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር እንዳደረገችላቸው በተደጋጋሚ እንሰማለን

እና ይሄንን ያስትዋለች አንዷ ጓድኛዬ ምን አለችኝ "ኮፕቲኮችን ትወዳቸዋለች"😁😁 አዎ እነርሱም በጣም ይወዷታል.. እኛንም ትወደናለች ምንም ጥያቄ የለውም ግን ልባችንን ከክፋት መልሰን ብቻ "በልጅሽ በኢየሱስ መንገድ እንድንሄድ እርጂን" እያሉ እርዳታዋን መጠየቅ ነው..

አንዳንዴ ሰይጣን ይህንን የነሱን ጸሎት እገዛ እንዳናገኝ "ቀጥታ ራሱን ጌታን መጠይቅ አልችልም እንዴ?" በሚል አሳብ ይህንን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደውን መተጋገዝ እንድንረሳና እንድንተው ያደርገናል። አዎ ጌታችንን ቀጥታ እናነጋግረዋለን.. ሐዋርያት "ጸልዩልን" እያሉ ሌሎችን ክርስቲያኖችን የጠየቁት ግን ይህ ጠፍቷቸው ሳይሆን ይህ መተጋገዝ ያለውን ቦታ ስለተረዱት ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጾም ገባ ደስ ይላል በጣም.. ይሄንን ወቅት በጣም ልንጠቀምበትና ምግብን ስንራብ ትህትናን እየተላበስን ክርስቶስን የምንራብበት የእመቤታችንን እገዛ የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባዋል..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ከ18 አመት በታች የሆናችሁ ባታነቡት ፒስ ነው ለክፉም ለደጉም

"friends with benefit" የሚባል የአሕዛብ ልምምድ ታውቁ ይሆን..?? ያው ሁላችሁም ባይሆንም ብዙዎቻችሁ ታውቁት ይሆናል.. ወንድ እና ሴት ኖርማል ጓደኛማቾች ይሆኑና ቀስ በቀስ እዛው ጓደኝነት ላይ sexual ነገሮችን(ግብረ ሥጋ ግንኙነትና የመሳሰሉትን) ምናምንም ይጨምሩበታል ያው ባልና ሚስት ለመሆን አያስቡም ፍላጎቱም አይኖራቸው ይሆናል ግን ደግሞ ዝሙትና መዳራትን ይፈጽማሉ..

የጌታ ኢየሱስ ወገኖች ሆይ.. እንደምታውቁት በእኛ ዘንድ እንዲህ ያለ ነውር ይቅር እና ሊጋቡ የወሰኑ እንኳ በምስጢረ ጋብቻ አንድ ሳይሆኑ እንዲህ ያለ ነገር አይደረግም.. ለዛም ነው ክቡር ጳውሎስ "መጋባት ክቡር ይሁን" ካለ በኋላ "መኝታውም ንጹሕ ይሁን" የሚለው። ከመጋባት ወጪ ያለ "መኝታ" ሁሉ ርኩሰት ነው.. ቀጠል አድርጎ ሐዋርያው፡ "ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።" ይላል..

ስለዚህም እናንተ የተመረጣችሁ በዋጋ የተገዛችሁ የእግዚአብሔር ውድ ልጆች ናችሁና እንዲህ ባለው የአሕዛብ ርኩሰት ውስጥ ወድቃችሁ አትገኙ.. ስለ ዝሙት ወይም መዳራት(ዝሙት ቀስቃሽ ድርጊቶች) ራሱን ችሎ በሌላ ርእስ እመጣበታለሁ ሌላ ቀን.. ከእናንተ ግን ምናልባት እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ ያለ ቢኖር እርሱ አሁን ይቅርታ ጠይቆ ወይም ጠይቃ ያቁም.. የሥጋ ምኞታችንን እንመርጣለን ወይስ ከሙታን የተነሣውን ለዘላለምም ከእርሱ ጋር የሚያኖረንን እስከ ሞት ድረስ የወደደንን ጌታ..?? አሁን ይምረጥ/ትምረጥ.. ይሄ ቀስ ተብሎ ይተው የሚባልም ኃጢአት አይደለም..

"አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና"
[ገላ 6፡7]

ጌታ በዚህ ኃጢአት ውስጥ ላሉ ወንድም እህቶቻችን ምህረትን ያድርግላቸው እርሱን መውደድን ይስጣቸው መውጫውን መንገድ ያመልክታቸው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዱ ወዳጄ አሁን ምን አለኝ..

መጸለይ በጣም እስኪከብድኝ ድረስ እሳነፍና.. አንዳንዴ ‘ኧረ ቢያንስ አባቶችን ሆይ ልበል’ ብዬ እቆምና ግን ደግሞ ሳላስበው በቦታው የጌታ መገኘት እየተሰማኝ በጣም ደስ የሚል ከስንት አንድ ጊዜ የሚያጋጥመኝን ዓይነት የጸሎት ጊዜ ኖሮኝ እጨርሳለሁ..

መላእክት በፊቱ የሚሰግዱለት ታላቁ አምላክ እርሱ ዝቅ ብሎ የኔን ድምጽ የኔን አሳብ እያየ እንደሆነ ሲሰማኝ ዝም ብዬ የኔን ድካምና የእርሱን ፍቅር፣ ትእግስት፣ ምህረት፣ ቸርነት እያሰብኩ ‘አመሰግንሃለው እወድሃለው አባ’ ብቻ እለዋለሁ..

እና ደግሞ ነገረ ቤተ ክርስቲያን ላይ “የቅዱሳን ኅብረት” የሚለውን አሳብ ከማወቅ በዘለለ እየተረዳሁት ስመጣ የእመቤታችንንና የቅዱሳኑን አጋዠነት በበለጠ መጠቀም ጀመርሁ.. የቅድስት ድንግል ጸሎቷ ይደግፍህ አንተንም
———————————————

ደስ ይላል ስለዛ እኛም በትንሹ እንታመን እግዚአብሔር ደግሞ ቀስ በቀስ በብዙ ይሾመናል.. መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

👆👆👆👆
አንድ ወንድማችን ለቆንጂት ቀለበት አድርጎላት መሆኑ ነው.. እና ደስ የሚል ጊዜ ነበረን..

እና ይህ ወንድማችን ቀለበት ሊያደርግላት ሲል አቡ ምን መዝሙር ቢጋብዝ ጥሩ ነው..??

“የማደርገውን አላውቅም”😭😭

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ያው የምታውቁ ታውቃላችሁ

እና እንደምታውቁትም የሆነ አካል የኛን የቲክቶክ ላይቭ ብለር ነገር አድርጎ ያለምንም ማስረጃ “ሃራጥቃ ተሃድሶ” ምናምን እያለ ሲያወራ አይቼ ትንሽ አናደዱኝና መልስ ያስፈልገዋል ብዬ አስቤ ነበር..

ግን ደግሞ እዛ የለቀቁት ቪዲዮ ላይ በራሳቸው ቤት የተሰጠውን የሕዝብ ኮመንት ሳይ አብዛኛው ትክክል እንዳልሆኑ ሲነግሯቸው ነበር.. እንግዲህ ሰዉ ከተረዳን ምን አገባን እንደ አቅሚቲ ዝም ብለን መፍጨርጨር ነው ከእናንተው ጋር.. በእውቀት እንድናድግ እና ወደ ቅዱስ ምስጢር ቀርበን ጌታን እንድንመስል..

አንዱ ወዳጄ ብሏል ፌስቡኩ ላይ “ሥልጠና እንስጣችሁ ብለው ሰጥተው የፈጠነ ወር እንኳ ሳይሞላው ተሐድሶ አሉ” ለማንኛውም ማኅበሩን በሰው ፊት አታቃሉ እባካችሁን ትልቅና የተከበረ ማኅበር ነው.. ብትችሉ ሰው አሰልጥኑና ለሚዲያው በሚሆን መልኩ አድርጋችሁ አሰማሩ በየቦታው..

ሌላው ሲያገለግል የሚያገለግለው ከእናንተው ጋር አንድን መንግስት ነውና እስቲ ደስ ይበላችሁ በጌታ.. እንደምታውቁት መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን አሁንም ጥቂት ናቸው.. ጌታችን እኮ በአንድ ወቅት ላይ ብዙ ሕዝብ አይቶ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለው አይቶ አዘነ ይላል ወንጌል.. አሁንም እንደዛ ነው.. እናንተ ሕዝቡ ጋር መድረስን አስፍታችሁ ቀጥሉበት ሌላው ሲያግዝ “ሃራጥቃ ተሐድሶ” እያላችሁ ባለማወቅ ሰውን እንዳይማር ለማድረግ ከምትሞክሩ..

ማኅበሩ በዝች በሰሞኑ በእናንተ ሁኔታ እንደማይመዘን ልብ ይሏል..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዱ ምን አለ:

የጴንጤ መንፈስ ይመቸው አዳራሽ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ሁሉ ዘርሮ ካሜራ ማኑን ያልፈዋል.. ያው እንዲቀርጽ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እሺ ኢየሱስ ሞተላችሁ እና አመናችሁ.. ከውድቀትም አወጣን ትላላችሁ.. ግን ደግሞ ካላመኑት የተለየ ነገር ምን አለ እናንተ ጋር..??

ዌል እኛ ጋር ሰዎችን ሁሉ የሚያድነው ኡእግዚአብሔር ጸጋ አለ.. "ይህም ጸጋ" ይላል መምህራችን ጳውሎስ:-

"ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል"
ይለናል..

ስለዚህ ክርስቲያን ከሌላው ካልዳነው የሚለየው ጸጋ ጸጋ በማለት ሳይሆን በዛ ጸጋ ከኃጢአት ሁሉ እየተለየ እግዚአብሔርን በመምሰል ሕይወት ማደጉ ነው.. ይህ ያለ ቅዱስ ቁርባን አይሆንም.. ሥጋችን በሥጋዊ ምግብ እንድሚያድገው መንፈሳዊ ሕይወታችንም የሚያድገው በመንፍሳዊ ምግብ ነው.. ክርስቶስ በእኛ ሲኖር ከክርስቶስ የተነሣ ክርስቶስ ያሸነፋቸውን ሁሉ እናሸንፋለን.. ጌታችን ደግሞ ሲናገር "ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ እኔ በእርሱ እኖራለሁ እርሱም በእኔ" አለ..

ደግሞ አንዴ ብቻ ተቀበሉና በቃ አላልኩም.. መንፈሳዊ እድገት እግዚአብሔርን መምሰል ከሆነ ሁሌም ማይቋረጥ ነውና ሁሌም ቶሎ ቶሎ መቁረብ አለብን..

ስለዚህም አሕዛብ ከእኛ በምንም አትለዩም አይበሉን.. የክርስቶስ ወገኖች መሆናችን እርሱን በመምሰል በሕይወታችን ይታወቅ እንጂ በአንደበታችን አይሁን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እንዴት ልጸልይ..??

- አባታችን ሆይን ጸልይ መድኃኒታችን ኢየሱስ ያስተማረን ነው..

- ጸሎተ ሃይማኖትን መጸለይ.. በመንፈስ ሆነህ ጸልየው ምክንያቱም እግዚአብሔርን አንተ እንዲህ ነህ እናም በአንተ እናምናለን የሚል የሃይማኖት ምስክርነት አለው

- ከጸሎት መጽሐፍት ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ የቅዱሳንን ጸሎት ማየት ለምሳሌ የዳዊትን መዝሙር.. ብዙ ነገሮችን ስለሚነካ አባ ጊዮርጊስም እንደሚለው “የምስጋና ጎርፍ ከአፉ ፈሰሰ” ስለዚህ በእርሱ ምስጋና ማመስገን.. እንዲሁ የማንበብ ጉዳይ ሳይሆን ከልብ መጸለይ.. እንደ አቅም የቻላችሁትን ብቻ.. እንዲሁ ውዳሴ ማርያምንም..

- የልባችሁን ደግሞ ለአባታችሁ ለእግዚአብሔር ማውራት.. በእናንተው አነጋገር ለቃሉ ማማር ሳትጨነቁ ዝም ብላችሁ ከልባችሁ ማውራት..

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አንዲት ነገር ግልጽ ላድርግ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ስላለው የግድላት ድርሳናት ተዓምራት ጉዳይ..

ያው እኛ ሃገር አንዳንድ ሰው ባለማወቅ “ቤተ ክርስቲያን ስህተት ነው እስካላለች ድረስ ያለውን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለብህ” የሚል ትምህርትን የሚሰጡ አሉ.. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እኔ እስከማውቀው እንዲህ ያለ ነገር የለም.. ለመንፈሳዊ ሕይወትህ እንዲጠቅምህ አድርገህ ተጠቀምበት ከዛ ውጪ የተጻፈውን ሁሉ ተቀበል የሚባል ነገር የለም..

በግብጽ ያለው እንግዲህ እኔ እስከ ደረስኩበት ድረስ ቢያንስ ከታች ያሉትን ይመለከታል

1. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌም እንደተናገሩት በግብጽ ገድላት ተዓምራትን እንደ ታሪክ ለይተው አስቀመጧቸው እንጂ በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ ምናምን አያካትቷቸውም.. ስንክሳር ይነበባል

2. እንደዚህም ሆኖ በነዚህ መጽሐፍት ውስጥ እንደ እኛ ሃገር ብዙም ግራ ሚያጋቡ ነገሮች የሉም..

3. የዚህን ያህል ትውልድ ይማርልሃል የሚል ዓይነት እና የቦታ ቃል ኪዳኖች ከመዳን አንጻር የሉም(እስከ ጠየኩት ድረስ)

4. ድርሳነ መላእክት እንዲሁ ያሉ አልመሰለኝም እስከተመለሰልኝ ድረስ

አንድ ፕሮቴስታንት ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምጣት ቢፈልግ የነዚህን መጽሐፍት ነገር ሁሉ መቀበል አይጠበቅበትም.. ሲመጣ ብቻ ሳይሆን ሲኖርም.. ምናልባት ግን አይ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ አትልም ካላችሁ አንድ ቀን ኦፊሻሊ እስኪነገር ድረስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ ነው..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

“አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ፥ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረካቸው ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛርሙርቱ ሰጠ።”
[ሉቃስ 9: 16]

ጌታችን በተዓምሩ ምግብን አበርክቶ መገባቸው.. ጌታችን በሥጋዊ ነገሮችም ይባርካል.. ከ እኛ የሚጠበቀው ግን አስቀድመን ጽድቁን መንግስቱን መሻት ነው..

በሐዲስ ኪዳን ጌታችን የሰጠን ትልቁ ምግብ ራሱን ነው.. ይህም ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ ነው.. ከዚህ ማእድ ለመካፈል ደግሞ የሚያስፈልገን ንስሐ ብቻ ነው.. መድኃኒታችን ከእኛ የሚፈልገው መመለሳችንን ብቻ እንጂ ስንመለስ እርሱ ራሱ በደስታ አቅፎ ያኖረናል

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይቅርታ የኔ ተወዳጆች ምንም ርእሱ ላይ ለመናገር አይደለም ክርስቶስ በሚያውቀው.. ግን በቃ ቀሲስ ዶር ዘበነ በድጋሜ ተጠይቀው የመለሱትን ስሰማ እንደው ደስ አለኝም እና ደግሞ በቀደመው መልሳቸው ተጨንቀው የነበሩ ካሉም ለነሱም ይሆን ዘንድ ነው..

ይህንን ርእስ ግን እንደ ርእስ የትም ቤት አታንሱት በጌታ በቂ ነገር ስለተባለበት

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ”[ሉቃስ 1:13]

መልአኩ የዘካርያስ ጸሎት እንደተሰማለት ነግሮ መጀመሩ ቀድሞውኑ ጸሎቱ ምን እንደሆነ ያውቃል ማለት ነው.. እና ያ ጸሎትም በእግዚአብሔር ዘንድ እንደተሰማ ይነግረዋል.. ጸሎትንም የማሳረግ ሥራን ሊሰሩ ይችላሉና ነው.. ልክ ራዕይ ላይ እንዳለው..

የዮሐንስ ራእይ 8
3፤ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
4፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።

እዚህ ጋር መልአክ የሚለውን ለኢየሱስ የሚሰጡ አሉ ግን እኔ እስካየሁት ኢየሱስ መሆኑን የሚያመለክት ግልጽ የሆነ ነገር የለውም.. ሲቀጥል “ሌላም መልአክ” የሚለው አገላለጽ እንደሌሎቹ መልአክ መሆኑን አመልካች ነው..

እና ደግሞ “መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ” ተብለዋል[ዕብ 1:14]

እንዴት ነው የሚያግዙን..?? የሚያግዙን እንደሆነ ከተነገረን ከመላእክት ጋር ግንኙነት አታድርጉ የሚሉን ከየት አምጥተው ነው..??

መዳንን ትወርሱ ዘንድ ያላችሁ እናንተ.. መልአኩ ያግዛችሁ

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለሙስሊም ኡስታዞች✌️✌️

https://vm.tiktok.com/ZMrHgEQhe/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አይመስላችሁም..??

አንድ ያስተዋልኩት ከጉዋደኞቻችን ጋር ስንቃለድ ስናወራ ምናምን ቃላቶች እና ርእሶች የተወሰነ መገደብ አለባቸው..

ቀለል አድርገን ስናወራ ምናምን ለኛ ኖርማል የሆኑ ግን በጊዜ ሂደት እግዚአብሔርን መፍራትን የሚቀንሱና መዳፈርን የሚያለማምዱ ይመስለኛል.. በተለይ ደርቲ ሚመስል ነገርን መራቅ የተሻለ ይመስለኛል.. አይመስላችሁም..??

እዚው ሚዲያ ላይ ያለው ሳይሆን በአካል አልያም በውስጥ ስናወራ ማለቴ ነው

@Apostolic_Answers

Читать полностью…
Subscribe to a channel