apostolic_answers | Unsorted

Telegram-канал apostolic_answers - ሐዋርያዊ መልሶች

34175

በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

Subscribe to a channel

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ በጠዋቱ አንዳንዶች ሼር አድርገውልኝ.. በጣም ደስ የሚል ዜና በእውነት.. ምናልባት የ2016 የመጨረሻው ትልቁ ደስታዬ ይሆናል.. ሰዎች ወደ ጌታ ሲመጡ በጣም ነው በጌታ ደስ የሚለኝ..

ጌታ ካለው ትልቅ የሆነ ሰውን መውደድ የተነሳ ትንሽም ነገር ብትሆን ተጠቅሞ ያንን ሰው ያድነዋል.. ልብን ሚቀይር እርሱ ብቻ ነው.. በሞቱ ብቻ አይደለም የወደደን አሁንም ድረስ እንዳንጠፋበት ጠባቂያችን እርሱ ነው.. ከአሸናፊዎች የምንበልጥበት ማሸነፊያችን እርሱ ነው.. የኛ ድክመት ስንፍና የእርሱን የፍቅሩን መገለጥ አላገደውም.. ስለዚህም ደካማ እና በስንፍና ውስጥ ያለን እኛን ሳይሆን ኢየሱስን ብቻ እንድናመሰግን ያደርገናል.. እርሱ ብቻውን ይክበር..

“ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።”
[ሮሜ 16: 27]


@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

Instagram ላይ ካልመጣህ የሚሉም አሉ.. እቺ instagram የኔ ናት ዝም ብዬ ስሟን ለማስያዝ የከፈትኳት.. ይለቀቅባት እንዴ😁😁

https://www.instagram.com/apostolicanswers

——————

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ እኛ ሃገር ከሚሸጠው ይሄ የተወሰነ ይለያል ጸዴ ነው..

ምን ላድርግ አልቀበልም አይባል ነገር ሎል

ምን ማድረግ ይሻላል.. አለመቀበልም አይሻልም.. አለመቀበል ይሻላል እንዴ

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ብዙም አልጸልይም ለምትሉ.. አጭር ግን ደግሞ በጣም ታላቅ ጸሎት

https://vm.tiktok.com/ZMroVe8Ys/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ ፕሮቴስታንት ኮማቾች ግን አንዳንዴ የትም የሉም በቃ😁😁

ጋዲ እና ኢዮባን ምን ቢሏቸው..?? አቸኖ እና አዳነ 😆😆 (መንፈሳዊ አስጨፋሪዎች ሎል)

አቸኖ እና አዳነ የጊዮርጊስ እና የቡና እግር ኳስ ክለብ አስጨፋሪዎች መሆናቸው ነው😭😭

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እነርሱ :- “አክሊል እንትና ሚስትህ ናት አይደል..?? እያሉ የጠረጠሩትን እህቶች እየጠሩ ሲያዝጉኝ..

ምስኪኑ እኔ.. እንኳን ሚስት ምጀነጅነው እንኳ የሌለኝ😭😭

ቲም ጳውሎስ ነነ😁😁

በሌሊት ያሳስበኝ ጀመር ይሄ ሎል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አሁን እያነበብኩ ካገኘሁት ደስ የሚል ገለጻ..

"Emulation of the episcopal office is the mother of schisms."
[ጠርጡለስ - በእንተ ጥምቀት - 17]

"በጳጳሳት ብቻ የሚሠራውን ሥራ 'እኔ ካልሰራሁ' ማለት የመለያየቶች እናት ነው"

ትንሽ ለመተርጎም ይከብዳል ቃል በቃል ግን አሳቡ እንዲህ ነው.። እስቲ የተሻለ ሚተረጉም ካለ ኮመንት ላይ አያለሁ😁😁 ዛሬ እንቅልፍ የለም 10 ሰዓት ሆነብኝ እዚሁ ሎል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዓመተ ምህረት..

ከጌታችን መምጣት በኋላ ያሉ ዘመናትን ስንቆጥር ያው ጌታ በመስቀሉ ታላቅ ምህረት ያደረገበት ዘመን ላይ ስላለን “ዓመተ ምህረት”(የምህረት ዓመት) እያልን ነው ምንጠራው.. ቀደምት ክርስቲያን አባቶቻችንም ሃገራችንም በጣም ደስ ይላል..

እንጃ አሰብኩትና “ዓመተ ምህረት የሚባል ነገር የለም” ማለት እንዳይጀመር ፈራሁ አንድ ቀን😁😁

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል

“ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።”
[ዮሐንስ 6: 53]

ጌታችን ኢየሱስ የሰጠን ትልቁ ምስጢር ቅዱስ ቁርባን የራሱን ሥጋና ደም.. ጌታ ኢየሱስ ያለዚህ ሥጋ እና ደም በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም አለን.. በጣም የሚያሳዝነው ግን ጌታ እንዲህ እያለንም ልክ በራሳችን ሕይወት እንደሚኖረን ነገር ከቅዱስ ቁርባን አንሳተፍም..

የክርስትና ሕይወት ትልቁ ግብ ክርስቶስን መምሰል ነው.. ይህንን ግብ ደግሞ ማሳከት የሚቻለው ከቅዱስ ምስጢር ስንሳተፍ ብቻ ነው.. ሥጋችን ያለ ሥጋዊ ምግብ እንደማያድግ ሁሉ ያለ መንፈሳዊ ምግብም(ቅዱስ ቁርባንም) በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማደግ አንችልም.. የጌታ ሥጋና ደም አይሁድ እንደመሰላቸው ሥጋዊ የሆነ አባቶቻቸው በልተውት እንደሞቱት ያለ ሆድን የሚሞላ ሳይሆን ይህ ምግብ መንፈሳዊና ሕይወትን የሚሰጥ ነው.. ስለዚህም ጌታ የተናገረው መንፈስ ነው ሕይወትም ነው..

አንዘናጋ የኔ ተወዳጆች.. በቃ ዘሬ እናስብ ስለ ቅዱስ ቁርባን

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወንድማችን በጋሻው በቲክቶክ አገልግሎት ደስተኛ አይመስልም🤪🤪

https://vm.tiktok.com/ZMrTE1TyQ/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

የቃላት ብቻ እምነት


“ተሐድሶ” ሲነሳ 5ቱን “ብቻዎች” በማጮህ ነበር..
1. መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ
2. ክርስቶስ ብቻ
3. እምነት ብቻ
4. ጸጋ ብቻ
5. ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ

እነዚህ 5ቱ “ብቻዎች” ራሳቸውን ችለው ብቻቸውን የፕሮቴስታንቱ መሠረታዊ እምነት ሳይሆኑ ከሮም ቤተ ክርስቲያን የራሳቸውን የሚለዩባቸው ናቸው.. ለምሳሌ እዚህ ውስጥ በግልጽ ሥላሴ የለም.. ያው ዋናው ትኩረታቸው ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሚለያቸውን መያዛቸው ነው..

ሚያስቀው ፓርት ግን ሉተር ለምሳሌ “እምነት ብቻ” ብሎ ሲነሳ ጥምቀት ለድኅነት እንደሆነ ማመንንም ያካተተ እንጂ እሱን የለየ አይደለም.. መናፍቁ ዚዊንግሊ (እደግመዋለሁ መናፍቁ ዚዊንግሊ😆😆) ግን “እምነት ብቻ” ሲል ጥምቀትን ለድኅነት መሆኑን ክዶ ነው..

ሁላችንም “ብቻ ብቻ” እንበል ግን ሃሳቡን ባንመሳሰልም ችግር የለውም ነው ሚሉን የአሁኖቹም😁😁 የቃላት ብቻ እምነት

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኧረ የወንድማችን አቡ ጸጋው ብዛቱ..?? ደግሞ “ዘማሪ” ብሎ መጣ.. ታድሎ የምር😆😆

መምህር ወመዘምር ወቲክቶከር ወዩትዩበር ወንድምአገኝ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እመቤቴን እንዴት እንደደነገጥኩ🤣🤣 በተለይ ግጥሙ😭😭

አንድ ዓለማዊ ቪዲዮ ላይ የሆነ ሰው ሜንሽን አድርጎኝ ስገባ በኔ ፎቶ ተደርጎ ዘፈን ተለቋል እና በስህተት ዘፈኑ ገብቶባቸው ወይም የፕሮቴስታንት መዝሙር ይሆናል ብዬ ቼክ ሳደርግ ለካ ነገሩ እንዲህ ነው:

የመጀመሪያው ቪዲዮ ላይ “ደፋር ከሆንክ የምታፈቅረውን ሰው ስም ኮመንት ላይ ጻፍ” የሚል ተጽፎ ተለቅቆ ከ3700 በለይ ኮመንት አለው

እና እዛ ላይ አንዷ አክሊል(አኬ) ብላለች እና ጭራሽ ልጀቷን ሳያት ፕሮቴስታንት ናት ጭራሽ ደግሞ እኔ ላይም ሰርታብኛለች ቪዲዮ ሎል.. (ቆንጂት ፍቅርሽን እንዲ ነው ምትገልጪው..?? ታሳፍሪያለሽ ሎል)

ከዛ ሚያስቀውና እኔም ይሄንን ሁሉ እንዳይ ያደረገኝ ነገር.. አክሊል(አኬ) ሚለው ኮመንት ላይ እዛው ዓለማዊ ቪዲዮ ተሰርቶ ምን ቢሆን..?? የኔን ፎቶ አድርገው በዘፈን ለቅቀውታል😭😭 ግጥሙን እስቲ ገምቱ..

“ሥጦታዬ ገጸ በረከቴ
ምሰሶ በራፍ የቤቴ”😭😭

መጀመሪያ ቀፍፎኝ አየሁትና ግን ግጥሙ ላይ አልቻልኩም እመቤቴን🤣🤣 እና ቆንጂት ግን እስቲ ላስብበት😁😁 ያው እዚህ ላይ አታየውም ብዬ ነው ሎል.. ጌታ ይርዳን😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ላይቭ😬😬

https://vm.tiktok.com/ZMrcvgwcb/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አቦ እንደው ክርስቲያኑ ግን አልምጥ ሆኗል😁😁

ከላይ “ጨምላቃ ውረድ” ያልኩት ላይ ከታች አብዛኛው ሰው ኮመንት ላይ ምን ቢል..?? “ከፈለገ ይከስከስ አልወርድም”🤣🤣

ጭራሽ አላሰብኩትም ነበር እኔ😁😁 ያው የሚገባችሁ ይገባችኋል..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል..”
[ማቴ 25: 31]

ጌታችን ኢየሱስ ለፍርድ ይመጣል.. እና ከእኛም ፍሬን ይጠብቃል.. በዚህ ክፍል ላይ ጌታችን የጠየቀው ነገር በጣም ቀላል ነገሮችን ነው..

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡
ክርስቶስ ከአንተ የሚጠይቀው ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተመለከትክ..?? ታስሬ አስፈትተኸኛልን..?? ታምሜስ አድነኸኛልን..?? አይደለም ያለው ግን ደግሞ "መጥታችሁ ጠይቃችሁኛልን..??" ነው።

እውነትም በጣም ቀላል ነገር.. ግን ይህንንም ቀላል ነገር ከማድረግ ወደኋላ ብለን ደግሞ ፍሬ ቢሶችም አንሁን.. ሁሉን ስናደርግ ግን በፍቅር ይሁን.. ያለ ፍቅር የሚደረግ ነገር ተቀባይነት አይኖውምና..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ጸሐይ ስትጠልቅ የምትጠልቀው ጭቃ ያለው ምንጭ ውስጥ ነው..??😁😁

ቁርአኑን ቃል በቃል የፈጣሪ ከሆነና የሰው አገላለጽ ከሌለበት ይሄ ከባድ ይመስለኛል..

የዮሐዴን ይህንን አካውንት እባካችሁን ፎሎው አድርጉት.. ቪዲዮውንም ላይክ ምናምን አድርጉ

https://vm.tiktok.com/ZMh1R2nBj/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

“ተስፋችን ኢየሱስ”
[1
ጢሞ 1:1]

ተስፋ እንደሌለው ብን ብሎ ጠፍቶ እንደሚቀር ሰው አንዋል.. ተስፋችን ኢየሱስን ግን በልባችን ይዘን እንዋል.. አካሄዳችንም እንደ እርሱ ፈቃድ ይሆናል..

መልካም ውሎ እናንተ የጌታ ወዳጆች.. (በዛውም “የጌታ ወዳጅ” ተብሎ የሚጠራውን የአባ ቢሾይን የገድል ፊልም ጋበዝኳችሁ እዩት)

@Apostolic_Answers

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ለጌታችን ልደት(ለገና) ብቻ ሚዘመር ነው ይሄማ የምር.. በኖርማል ቀን ስንሰማው ራሱ የገናን ቫይብ ነው ሚያመጣብን😁😁 ግን በጣም ደስ የሚል ዝማሬ ነው

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

እሺ አንድ ነገር ግልጽ ላድርግ😁😁 ከላይ ባለው ፖስት አንድ አሳሳቢ ነገርም እያስተላለፍኩበት ነው እና በግልጽ ልንገራቸው መሰል..

ዲያቆን መኩን አወቃችሁት ቲክቶክ ላይ..?? እና እሱ እያወራኝ ነበር ባለፈው እና በኔ ስም የሆነ ሰው ቴሌግራም አካውንት ከፍቶ የኔን አወራር እየተጠቀመ እና አንዳንድ ድምጾቼንም ለሁኔታው የሚመቸው ሲሆን እየላከ እንደሚያወራ ምናምን ነገረኝ.. ያው victim ነኝ ምትለው ቆንጂት ነግራው መሰለኝ😁😁

ከዚህ በፊት ጽፌላችሁ ነበር እንደዚህ ዓይነት ነገር እና ራሱ ይመስለኛል እንደ አዲስ ለመኩ የተነገረው እና ግን በአጠቃላይ ምንድን ነው:-

1. ገንዘብ ላኪልኝ ካለሽ
2. አልያም ከጀነጀነሽ
እስክትደፊ ድረስ አምልጪው ነው..😁😁 ይሄ በጣም እቀርበዋለሁ ብላችሁ ለምታስቡም እህቶች ነው.. እንድትጠነቀቁ ነው እናንተ ምርጦች

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በትነን እናየዋለን ይላል እንዴ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrEJbW42/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ስለ መምህራን ብዙ ጊዜ አንጸልይም እና በጣም ልንጸልይ ይገባል.. ጳውሎስ ጸልዩልኝ ምነው አለ..??

በተለይ ያረጋሌን የኛ ተወዳጅ መምህር.. በጣም እንደምትወዱት አውቃለሁ.. ፍቅራችን የሚታወቀው አሁንም ጌታ አብዝቶ እንዲረዳውና በነገሮች ሁሉ ከጎኑ እንዲሆን ስንጸልይለት ነው.. እንደው በቅዱስ ሚካኤል በጸሎት አንርሳው.. እርሱንም ሌሎች መምህራንንም

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

በዚህ በሚገባው ዓመት ማውጣት ያለባችሁ ትልቁ እቅድ በክርስቶስ መደሰት ነው እያሉን ነው አባ.. በጣም ደስ ይላል የተወደዱ አባት..

እንደውም ዓመቱን ራሱ “በክርስቶስ መደሰት” ብለን እንሰይመውና እንጀምረው እንዴ😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

አይ በጋሻው..
ቅዱስ ቁርባን ሳይገባቸው ሲቀበሉ የሞቱት በጋን ጠጥተው ከመጠን በላይ ሆዳቸው እስኪተረተር በልተው ነው እያሉን ነው ኧረ😭😭

በደንብ ስሙ ስለ ቅዱስ ቁርባን

https://vm.tiktok.com/ZMrwmrN6R/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ወንድም በጋሻው የማንመልሰውን ከባድ ጥያቄ ጠየቀን ሎል😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrTrvGmr/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቆንጂት..??🙄🙄

ይሄንን ጩጬ ስታስቆሙት እኔም አቆማለሁ

ኧረ ይሄ ቤት ጭዌ በዛበት😬😬 ለቀጣይ 5 ቀናት ከትምህርት ውጪ ወፍ ሎል

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ኃጢአትን ኖርማል አናድርገው.. እንዲህ ከሚያደርጉም ጋር አንሩጥ.. በእርዚህ ከሰደቡን ይስደቡንም

“በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ”
[1ጴጥ 4: 4]

https://vm.tiktok.com/ZMr3UdEGc/

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ቆይ ርዕስ አታድርጉት😁😁 ትንሽ ቀን ስጠኝ ብላኛለች ጓደኛዋ ይሄንንም አጠፋዋለሁ.. ተጨነኩ እኮ ራሴው ብቻዬን እንደ አቅሜ ባደረግሁላት😁😁

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ይሄ መዝሙር..

ያወቀው ሽልማት አለው😁😁

መዝሙር እኮ ምስጋና ነው የምር ጸሎትም ነው.. በጸሎት መንፈስም ሆነን እናመስግን መዝሙር ስንሰማ..

Читать полностью…

ሐዋርያዊ መልሶች

ሰይጣን ክፉ የሃጢአት አሳብን
ሊያቀብልህ እየሞከረ እንደሆነ ስትረዳ😁😁

ሰይጣኑን ነው “ውረድ”😁😁

@Apostolic_Answers

Читать полностью…
Subscribe to a channel