በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።”
[ማቴ 21: 43]
ጌታችን ኢየሱስ በሚያስተምርበት ወቅት የወይን አትክልት ገበሬዎችን ምሳሌ አድርጎ ያስተማረበት ክፍል ነው.. በዚህም ምሳሌ ውስጥ እንደተገለጠው የወይን አትክልት የተከለ አንድ ጌታ ነበር እናም ለገበሬዎች አከራይቶት ይሄዳል.. የወይኑ አትክልትም ፍሬን የሚያፈራበት ጊዜ ሲቀርብ ፍሬን እንዲቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ..
ገበሬዎቹ ግን ፍሬን ከመስጠት ይልቅ የሚላኩትን የጌታውን ባሮች ሁሉ ደበደቡ ወገሩ ገድሉም.. በኋላ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ላከባቸው.. በልጁ በወራሹም ላይ ተመሳሳዩን አደረጉ ገደሉት..
ይሄንን ምሳሌ ይነግራቸውና እንግዲህ የአትክልቱ ጌታው በመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ላይ ምን ያደርግባቸዋል..?? ብሎ ራሳቸው ፈሪሳውያንን ጠየቃቸው.. እነርሱም ሲመልሱ ክፉዎቹን ገበሬዎች ያጠፋቸዋል.. የወይኑንም አትክልት ፍሬን ለሚሰጡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጡታል አሉት..
ጌታችን ግን ይህንን የተናገረው ስለራሳቸው ነበር.. በየዘመናቱ እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን ነቢያትን ባርያዎቹን ላከ.. አይሁዳውያን ግን የነቢያቱን ቃል አይሰሙም ነበር.. በኋላም ብቸኛ ልጁን ላከ.. ልጁንም አልተቀበሉም.. ልጁ ኢየሱስን ባለመቀበላቸው ምክንያት ወደ ውጭ ተጣሉ.. የወይን አትክልቱም ለሌሎች ገበሬዎች ማለትም ለሐዋርያትና ከዛም በኋላ ለሚነሱ መምህራን ተሰጠ..
አሁን ላይ ልጁን በካዱ በአይሁዳውያን ዘንድ የእግዚአብሔር መንግስት የለችም.. የእግዚአብሔር መንግስት ያለችው በእኛ ዘንድ ናት.. በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ናት..
ከዚች መንግሥት ውጪ የሆነ ሰው ኢየሱስ ንጉሡ ያልሆነለት ሰው ነው.. ከዚች መንግሥት ውጪ ያለ እርሱ የእግዚአብሔርም አይሆንም.. ጌታ ፍጻሜያችንን በዚች መንግሥት ያድርግ..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
“በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2: 8
መልካም ውሎ😊🤗
@Apostolic_Answers
በተደጋጋሚ ቅድስት ሥላሴ ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች ውስጥ..
1 + 1 + 1 = 1 ..??😭😭
https://vm.tiktok.com/ZMhQXtMXR/
እንደ ጀማሪ ፍቅረኛ ስንቴ እየጻፍኩ አጠፋሁ.. ሲረዝምብኝ ወይም ምን ይሰራል ይሄ ምናምን እያልኩ😁😁
አሁን ራሱ አጠፋሁ😭😭 በሉ ሰላም ዋሉ😭😭
ደግሞ ኖርማል ነገር እየጻፍኩ ነው ያጠፋሁት ምንም አይደለም.. ፍቅሬን ልገልጽላችሁ ምናምን አይደለም🙄🙄
ስለ እኔ አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ስሰማ.. እንደው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ነው ያለው እና ሰዎችንም ሊያጠፋ ነው እያሉ ሲጽፉ አየሁ.. ጥቂት ነጥቦችን ላስቀምጥ
1. ምናልባት አንዳንዱ ፕሮቴስታንቶች በፊት ከቤተ ክርስቲያን የወጡት እንዲህ ባለ በለብ ለብ እውቀት የተጠቁ ሰዎች ግፊት ይሆናል ብዬ አሰብሁ.. ያው የራሳቸውም ድክመት እንዳለ ሆኖ
2. “በአንዲት ቅድስት አለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የሚለውን ጸሎት ላይ ከማለት በዘለለ አብዛኞቹ ምኑንም የተረዱት አይመስልም..
3. ሰዎች እኔ ላይ እንዲደገፉ አላደረግም.. ጌታቸውን እና ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲወዱ እምነታቸውን እንዲያውቁ ብቻ ነው ጥረቴ.. ስለዚህም እኔ ብቀር እቀራለሁ.. ኤታባቴ😁😁
4. ግድ የሚላችሁ ጥቃቅን ጉዳዮች እንጂ የነፍሳት ጉዳይ አይመስለኝም.. ለዚህ ግን ያው ይቅርታ..
5. እዋዳችኋለሁ ግን አታብዙት🤪🤪
@Apostolic_Answers
‘አንዳንድ አገላለጾች ቢሻሻሉ’ ብዬ በጻፍኩት ላይ ከተሰጡ ኮመንቶች አንጻር ጥቂት አሳቦችን ልስጥ:
1. አንዳንድ ልጆች ምንም የሚሻሻል ነገር የለም ስትሉ ነበር😁😁 አሁን የጠቀስኩት መጽሐፍ ሊታረም ወይም ሊሻሻል የሚችል እኮ ነው.. ምናልባት አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ ብታሻሽለው እንደው በቃ ወደቀች እንዳትሉ ተጠንቀቁ
2. “ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይለኛል” ያለችውን ጠቅሳቸው ከዛ አንጻር የጠየቃችሁ አላችሁ.. እዛው ላይ እኮ ጽፌው ነበር.. ትውልድ ሁሉ ቢያመሰግናትም ግን ደግሞ የመፈጠራችንም
ምክንያት ይሄ ነው ማለት አይደለም ነው.. ለምሳሌ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ቢባርካቸው “አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ይሏችኋል” ተብለው ነበር(ሚል 3:12) ይህ ማለት አህዛብ እስራኤልን ብፁዓን ለማለት ነው የተፈጠሩትም ማለት አይደለም..
3. መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ሚከብድ ነገር ስለሚኖር እናሻሽለዋ የሚል ዓይነት ትችትም አይቻለሁ.. ማን ስለሆንክ ነው ታላቁን መጽሐፍ ምታሻሽለው..?? ሲጀመር ከእርሱ ጋር አስተካክለህ ታነጻጽራለህ እንዴ ሌሎችን መጽሐፍት..?? ስህተት ሊገኝባቸውም ስለሚችል ገና ከጅምሩ ምንም አይነጻጸሩም..
4. ይህ አገላለጽ እኮ ለምሳሌ “እንደው ለመከራ ተፈጠርኩ” እንደሚለው ያለ አይነት አገላለጽ ነው የሚልም አይቻለሁ.. እንደዛ አይመስለኝም.. እዛው ጋር ቀጣዩ ቃልም “አዳም እና ሔዋንም እመቤታችን ከእነርሱ ልትወለድ ተፈጠሩ” በማለት ለይቶ የአዳምና የሄዋንንም የመፈጠር ምክንያት ያስቀምጣል.. ሌሎች አሳቦችንም እዚህ ላይ ማስቀመጥ እችላለሁ ግን አስፈላጊ ስላልሆነ እንደው በቃ አገላለጿን መቀየር ሃሪፍ ይመስለኛል..
5. “እነ እገሌም እንዲህ ብለው ነበር ወደ ፕሮቴስታንት ከመሄዳቸው በፊት” እያለ ይህንን ከፕሮቴስታንት ጋር የሚያገናኝም አለ😁😁 እናንተ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን ተማሩ ከልቤ ነው..
ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር
ወደፊት በቀጣይ ክፍል እንገናኝ ይሆናል
@Apostolic_Answers
ዛሬ አጋጣሚ ሌላ ቦታ ሆኜ ቅዳሴ አርፍጄ ደረስኩ እና ወንጌል አለፈኝ..
በሉ እናንተ አካፍሉኝ ዛሬ ኮመንት ላይ.. ከጳውሎስ መልእክት እና ከወንጌል የተነበበውን.. አብራችሁ ደግሞ አንድ የምትወዱትን ጥቅስ ከመዝሙረ ዳዊት ለጥፉ
ክርስትናን በጽሑፍ ከሚያስተምሩ ወንድሞች መካከል እነ ኢዮብ መኮንን አሉ.. በጣም የተወደዱ ወብድሞች ናቸው..
እንደው በጌታ እስቲ join በሏቸው እና እናበረታታቸው.. በደንብ በሃላፊነት እንዲያገለግሉን
@EyobmekonenQ
@EyobmekonenQ
👆👆 2000 ሞልተነው እናስደምማቸው እስኪ
😁😁 ቀለል ያለ ነገር ስለሆነ አየር ላይ እዚው ለቴሌግራም በሚሆን መልኩ ትንሽ ነገር አልኩባት
ክላሲካል ፕሮቴስታንት vs ክላሲካል ፕሮቴስታንት ሎል
እስላምና ፕሮቴስታንት ከሚያመሳስላቸው ነገር ውስጥ ማኅበረሰብን የሚቀድም መጽሐፍ መፍጠራቸው ነው😁😁
ለወንድም ቃሌ የተሰጠ መልስ ቢሆንም ለእስላሞችም ይሆናል እዩት.. ወንድማችንንም አበረታቱት ፕሊስ
https://vm.tiktok.com/ZMhmGwCEU/
ከ5 ዓመት አካባቢ በፊት ራሴው ላይ ከገጠመኝ ነገር ላካፍላችሁ😁😁
ገድላት ምናምን መጽሐፍት ላይ የሚነሱ ነገሮችን ስመለከት በምን መልኩ ላስኬድ እንደሚገባኝ የተወሰነ ግራ ገብቶኝ ነበር ምክንያቱም በጣም ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ እና እኔ ደግሞ እነዚህ መጽሐፍት ላይ ያለኝ እይታ እንደ አብዛኛው አማኝ ነው እንጂ ትክክለኛውን ነገር አላውቅም ነበር..
እና የግሪክ ኦርቶዶክስን ስለመቀላቀል እንኳ አስቤ ነበር የሆነ ጊዜ ላይ.. ግን ደግሞ ገድላት እና ድርሳናት መጽሐፍት ላይ ያሉ ነገሮችን እንዴት መመልከት እንደምንችል ከንባብ ምናምን ተረዳሁ.. ያሉ አንዳንድ ችግሮችንም አየሁ.. ብቻ ግን ጌታ ይመስገንና በኦሬንታል ኦርቶዶክስ ቀጠልሁ ማለት ነው..
እና በእንደዚህ ዓይነት ቀላል ነገሮች ምክንያት ሰዎችን ወደ ድኅነት እንዳይመጡ የሚያደርጉ ሰዎችን ሳይ በጣም ነው ሚደብረኝ.. እና ቤተ ክርስቲያንን ከልምድ በዘለለ እንወቃት እላለሁ
@Apostolic_Answers
ለማርያም የአምልኮ መስዋእት..??🙄😁
https://vm.tiktok.com/ZMhmrHnQc/
….
ከዚህ ቀደም “መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ” በሚል ርእስ የተወያየኝ ወንድም ውይይቱን እንድገመው ብሎ እንደ አዲስ ጥሪ እያቀረበ ነው😁😁
አስፈላጊ አልነበረም ለኔ በቂ ነው የቀድሞው.. ግን ደግሞ እስከ ዛሬ ድረስ ተሰብስበው እዛው ርእስ ላይ ናቸው😁😁
እና ልቀበለው አሰብኩ.. ያኔ ያልጠራላቸው ነገር ካለም ምናልባት ቻሪተብል መሆናችን ስለሆነ ይህንን ሰዋዊ ትምህርት እነርሱም እንዳያነሱት አድርገን በድጋሜ እንምታው መሰል..
ጋሽ ኢዮብ ዘሚካኤል ቴሌግራም ላይ በቻናል መጥተዋል.. እናም እነሆ ቻናሉ.. እንቀላቀለው😁😁
@eyobzmikael12
@eyobzmikael12
የሆነ ወቅት ላይ የመዝሙር እና የስበከት ማእበል አስነስተው ከዛም ግርር ብለው ከቤተ ክርስቲያን የወጡ ሰዎች.. የወጡበትን ምክንያቶች ስሰማ በጣም ነው ያሳዘነኝ..
1. ብዙዎቹ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን ተምረው አልኖሩም.. ስለዚህም የሆነ ሰው ሳያስነቃ የፕሮቴስታንት ትምህርትን ያስተምራቸዋል.. ለምሳሌ “ጥምቀት አያድንም” አይላቸውም ግን ደግሞ ያድናል እያለም አያስተምራቸውም.. ክርስቲያናዊውን በግልጽ ሳይቃወም ፕሮቴስታንታዊውን ብቻ ያስተምራቸዋል..
2. የተማሩት ሰዎች ደግሞ የሆነ ሰዓት ላይ በአንድም በሌላም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነቋቆር ሲኖርና ትንሽ መወቀጥ ሲጀምሩ እየተገፉ ይሄዳሉ..
3. ሲገፉ ደግሞ ሲጋቱ የኖሩት የፕሮቴስታንትን ትምህርት ስለነበረ ወደ ፕሮቴስታንቱ መሄድ ይቀናቸዋል.. እነዛም አለሳልሰው ይጠሯቸዋል..
የክርስትናን ትምህርት ጭራሽ እንዳልተማሩ የሚያሳየው ቢያንስ ከፕሮቴስታንት በፊት ማየት የሚችሉት ቤተ ክርስቲያን ነበር.. ለምሳሌ.. የግብጽን ለምን አላዩም ነበር..?? ኦሬንታልን ቢተዉ ራሱ ኢስተርንን እንዴት አላዩም እላለሁ.. ይህንን ሁሉ ባላየ አልፈው ወደ ፕሮቴስታንት ከሄዱ በቃ ገና ከጅምሩ ክርስትናን አልተረዱትም ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል..
አሁን መለስ ብለው ቢያስቡበት.. ጌታ ይርዳቸው ያሳዝኑኛል..
@Apostolic_Answers
ዌል.. እንዴት ታዩታላችሁ ይሄንን አጭር ታሪክ
እውን ነቢይ ነውን..??
https://vm.tiktok.com/ZMhCMxNtJ/
ላይቭ ነን ሁላችሁም ኑ…
ቅድስት ሥላሴ
https://vm.tiktok.com/ZMhQqh7nK/
ዛሬ እመቤታችን ናት.. እሰቲ አንድ ሽልማት ያለው ጥያቄ ልጠይቃችሁ
የጌታን ልደት ይዞ ሲናገር እንዲህ ያለው ማን ነው..??
"በወንጌል የተጻፈውን ከልብህ ብታምን ወደ ራስህ ሕይወት ታስገባዋለህ.. የኢየሱስን ልደት የራስህም ታደርጋለህ.. ጌታ በአንተ ውስጥ ዳግም ሲወለድ በድንግል ማርያም እቅፍ ታርፋለህ የእርሷ ውድ ልጇም ትሆናለህ"
ለምን ላስጨንቃችሁ እኔው ልንገራችሁ.. ጋሽ ሉተር ናቸው.. በረከታቸው አይደርባችሁና እርሳቸው ስለ እመቤታችን የተናገሯቸውን አንድ ቀን በሰፊው እናያለን.. በዛም ውስጥ ፕሮቴስታንቶች ለእመቤታችን ያላቸው ክብር ቀስ በቀስ በሚገርም ሁኔታ እንዴት እየቀነሰ እንደሄደ እናያለን
ኧረ አንዳንድ ሰው ግን በጌታ.. Monophysitism ምናምን ላይ እርግጠኛ ነኝ ዶር ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ልጅ የተሻለ ያውቃሉ..
ሁሉንም አውቃለሁ እንደማትሉ አስባለሁ አላለም😁😁 ሳያስበው በጣም የኢየሱስ ጠላት የሆነ ልጅ
https://vm.tiktok.com/ZMhxG75wN/
ክርስቲያን ካፕሎች(ፍቅረኛማቾች😁) እንዴት ናችሁ..?? በርግጥ እዚህ አብዛኛው ሲንግል ነው😁😁 ካፕሎች ግን እንደ ክርስቲያን ካፕል በመካከላችሁ ኢየሱስ ሊኖር የሚገባው ገና ከአሁኑ ጀምሮ ነው.. ኢየሱስ ሲኖር በቃ ከእርሱ አንጻር ስለምታደርጉ ነገሮችን ከጊዜያዊ ደስታ በዘለለ የምትዋደዱ ጸዴ ካፕል ትሆናላችሁ..
ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ሊኖረን ይገባል.. በተቻለ አቅም ራስን መጠበቅ መታገስ.. ትደርስበታለህ ማን የራስህ ነው የት ይሄድብሃል ጥድፍ ጥድፍ አትበል😁😁 ስቀልድ ነው ግን እንደው በቃ እስትጋቡ በጥንቃቄ አሳልፉ ከፈተናችሁም የፈጠነ መጋባት ነው.. ከዛ ውጪ አንዳችሁ ስትደክሙ አንዳችሁ እያበረታችሁ በመተጋገዝ ማለፍ ነው..
ሲንግሎች እናንተን ምንም ምለው ነገር የለኝም.. አይዟችሁ ሎል
በኢትዮጵያ ያለችው የጌታ ቤተ ክርስቲያን ብትሰራባቸው ብዬ በጣም ከማስበው:
ክፍል 2
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚነበቡ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አገላለጾች ከጊዜው አንጻር ታይተው ቢሻሻሉ.. ሃይማኖት ያልሆኑ ጉዳዮች ስለሆኑ ቀላል ይመስለኛል.. በተለይ እንደው ቢያንስ ዋና ዋናዎቹን
ለምሳሌ “ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ” የሚል ዓይነት አገላለጽ እኛ ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መልኩ ለመረዳት ብንሞክርም ቃሉ ግን የሰዎችን የመፈጠር ምክንያት የሳተ ይመስላል..
በእመቤታችን በኩል መድኃኒት እርሱ ኢየሱስ ቢመጣና ትውልድ ሁሉም ስለዚህ ቢያመሰግናትም.. ግን ደግሞ የመፈጠራችን ምክንያቱ ራሱ እንደው እመቤታችንን ለማመስገን ነው የሚለው አወዛጋቢ ስለሆነ ሃይማኖት ደግሞ ስላልሆነ(ይሰመርበት) አገላለጹ ቢቀየርና ለማለት በታሰበው መልኩ ቢገለጽ.. ያው ሰውን የሚያስትም እንዳይሆን ማለት ነው..
ሌሎችም እንዲህ ዓይነቶችን ይመለከታል
@Apostolic_Answers
ከገብረ ኢየሱስ ጋር ነኝ እና እንዲህ አለኝ..
ኤርሚያስ በባቢሎን ምርኮ ሥር ለነበሩ እስራኤላውያን ሲናገር.. ምንም እንኳን እነርሱ በአሕዛብ ተማርከው ከኢየሩሳሌም የራቁ ቢሆኑም እንዲህ አላቸው:
“እግዚአብሔርን ከሩቅ አስቡ፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አኑሩ” [ኤር 51:50]
አሁንም በተለያዩ ዓለማዊና ኃጢአታዊ ነገሮች ከቤተ ክርስቲያን(ከኢየሩሳሌም) የራቅን ብንኖር ኢየሱስን እና ቤተ ክርስቲያኑን ግን ከልባችን አናውጣ.. ካለንበት ቦታ ሆነን ኢየሱስን ከሩቅ እናስበው ቤተ ክርስቲያኑንም በልባችን እናኑር.. በዚህ ውስጥ አምላካችን ከተማረክንበት ነጻ ያወጣናል የእርሱ ብቻም ያደርገናል..
@Apostolic_Answers
ከአንድ ፕሮቴስታንት ወንድም ጋር አጋጣሚ ተገናኝተን እያወራን መሃል ላይ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው..??
ማኅበረ ቅዱሳን ደሞዝ ይከፍልሃላ..?? አለኝ😭😭 እሱንስ አልፈልግም ግን ጭራሽ ቪዲዮ እንደሰሩብን ባላየው አልኩ ሎል😆😆
ገብረ ኢየሱስ አንዴ እንዲህ አለኝ..
በጣም በደበረኝና ምንም ሚያስደስት ነገር በዙሪያዬ ምመለከተው ነገር ባጣሁባት በዛች አስቀያሚ ደቂቃ.. ዳግመኛ የሚመጣውን ኢየሱስን ሳስብ ልቤ በደስታ ይመላል..
@Apostolic_Answers
ስጦታ..?? አጠር ያለች ማሳሰቢያ😁😁
አሁን በዚች ሰዓት አንዲት እህቴ ደውላ የሆነ ሰው የቅዱስ ሚካኤል ስእል እንድንሰጠህ ነግሮን ነበር አለች.. እና የምትሰራዋ ልጅ ሰርታ ስለጨረሰች ውሰድ አሉኝ..
ደስ ይላል ግን በጣም ብዙ ስእላት ስለተላከልኝ ከአሁን በኋላ ስእል አትላኩልኝ ከይቅርታ ጋር😭😭 የሰው ስጦታ ሆኖ ራሱ ከራሴው ጋር ልይዛቸው አልችልም እሱ ደግሞ ይደብራል ትንሽ..
ግን እንዲህ የማይባል ከሆነ እንደው ይቅርታ😁🤗
አንድ በዚህ መልኩ የማልጠብቀው ሰው እንዲህ ብሎ ጽፎ አየሁት..
“ይሄ ሃይማኖት አይደለም ፤ ይሄ ዶግማ አይደለም ፤ ይሄን ባትቀበሉትም ችግር የለውም የሚለው ቀፋፊ አባባል ነው”
እንዳልኩትም ካልጠበኩት ሰው ነው ይህንን የሰማሁት😁😁 ይህ ንግግራቸው ደግሞ ስሜት እንዲሰጥ የሚጠቀሙበት መንገድ ልክ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቀኖና ደረጃ ምእመኖቿ እንዲፈጽሙት የሰጠቻቸውንም አንቀበልም ማለት እንደሚችሉ ያስተማረ ያለ በማስመሰል ነው.. ለምሳሌ የአብይ ጾም መጾም አለበት ብላ ተናግራ ልክ አንዳንዶች ደግሞ ኖ አለመጾም ትችላላችሁ ብለው እንደተነሱ በማስመሰል ማለት ነው..
(ሥጋዊ ወይም የአላዋቂ መንገድ ይመስላል ይሄ)
☝️ ሃይማኖት ካልሆነ አልሆነም ነው ያልሆነውን ለይተን ማሳወቅ መብታችን ሳይሆን ግዴታችን ነው.. ቅዱስ ይሁዳ በመልእክቱ “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ..” ይላል አንዳንዶች ደግሞ ተነስተው ሃይማኖት የሆነውን ካልሆነው ለይተህ አትናገር ሚመስል ነገር ይጽፋሉ..
✌️ ባትቀበሉት ችግር የለውም የሚባልባቸውም ጉዳዮች አዎ አሉ.. እነዚህ ነገሮች ቀኖናም አይደሉም እይታዎች እና በተለያዩ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ታሪኮችና ንግግሮች ናቸው.. እና እንዲሁ በግእዝ ወይም በግሪክ ወይም በቅብጥ የተጻፈውን ሁሉ ልታግበሰብስ ነው እንዴ..
ሳጠቃልለው እንደው ሰው ክርስትናውን አውቆት ወዶት እንዲኖር በማሰብ የሚሰራውን ሥራ የሚያበላሽ ነገር ባለማወቅ አትስሩ ከይቅርታ ጋር እንደው..
@Apostolic_Answers
ከላይ ላለው ጽሑፍ
"አይ ትንሽ ቆይተህ ነው የመለስክልኝ እና መች እንደምችል አላውቅም" ብሏል ወንድማችን😁😁
ያረጋል ምናምን እያሉ ሲንተባተቡ ሳይ ትንሽ ቦታቸውንም በዛው እናስታውሳቸው ብለን ነበር የተቀበልናቸው.. ይመስለኛል ግን እኛ ወደ ፊት ትምህርታችንን እንቀጥል..
ክላሲካል ፕሮቴስታንቲዝም ምናምን እያሉ ጴንጤዎችን ወደ ጎን አድርገው እነሱ የተሻለ ነገር ማምጣት የሚችሉ ለሚመስላቸው ጥቂት ልጆች ደግሞ አንድ ቀን እንገባላቸው ይሆናል😁😁
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቅዱስ ቁርባን ያለን ፍራቻና ክብር በጣም ነው ደስ የሚለኝ.. ይህንንው ክብር ይዘን ደግሞ በፍርሃት ወደ መቀበሉ ብንቀርብ አስበኸዋል.. ያበደ ነው የምር..
ግብጾች ጋር ሄደህ አስቀድሰህ አይ አልቀበልም ብትል የምር ለራስህ ራሱ ሃፍረት ያሸማቅቅሃል.. ምክንያቱም ሁሉም ነው ሚቀበለው.. ካህኑ ራሱ ይጠይቁሃል ለምን ሳትቆርብ ብለው.. እና ብቻ ሼም ይይዝሃል😁😁
እኛ ጋርም ሁላችንም ብንቆርብ ሃሪፍ ነው..
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ፡ አለው።”
[ሉቃስ 5: 8]
ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ያለው አንድ ተአምርን ከጌታችን አይቶ ነው.. አሣ ለመያዝ መረብን ጥለው ነበር ነገር ግን ሌሊቱን ሁሉ ቢፈጉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ነበር
ነገር ግን ጌታችን ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብለው መረቦቻቸውን ለማጥመድ እንዲጥሉ ይነግራቸዋል.. እናም ጴጥሮስም “ሌሊቱን ሁሉ ደክመን ምንም አልያዝንም ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ” አለው.. እናም ጣለ መረቡም እስኪቀደድ ድረስ ብዙ አሣዎችን ያዘ..
አያችሁ የኔ ተወዳጆች ብዙ ያደከሙን ነገሮች ጌታ ሲገባበት ቀላል ይሆናል.. በሕይወታችን ፍሬን ማፍራት ቢከብደን በክርስቶስ ግን እናፈራለን.. ያለ እርሱ ምንም ልናደርግ አንችልም.. ጌታችንም “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናል..
የጌታን እርዳታ ለማግኘት ደግሞ እኛ በራሳችን ደካማና ኃጢአተኞች መሆናችንን ማወቅ አለብን.. ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታው ጉልበት ላይ ወድቆ እኔ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው.. ራሱን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ሲያስቀምጥ ጌታም ደግሞ መለስ አድርጎ “አትፍራ ከእንግዲህስ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው..
ከክርስቶስ የተነሣ ፍሬን የምናፈራ እንሁን
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers