በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል.. YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥
ኢየሱስ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
@Apostolic_Answers
ኢየሱስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ አላለም.. ስለዚህ አምላክ አይደለም ለሚሉ ሙስሊሞች የተሰጠ መልስ..
በጌታ አካውንቱን ፎሎው ማድረግና ቪዲዮውንም ሼር ምናምን ማድረግ እንዳትረሱ.. በጣም ጠቃሚ ወንድም ነው.. አረብኛም ጎበዝ ነው..
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMh31UCp7/
👆👆
ስቃዥ አድሬ ምንድን ነው ብዬ ሳይ ለካ ጌቱ የተባለ የተመታ ወንድም እዛ ፌስቡክ ላይ ፎቶዬን ለጥፎ ሲጫወትብኝ ውሎ ነው😐😐
ሲንግል ነው እና ማመልከቻ አስገቡ የሚል ጽፎ አየሁ እና ደነገጥኩ(ቀልድ ቢሆንም ማርያምን ደነገጥኩ😆😆).. ከዛ እድሜው 22 ነው ሲል አልቻልኩም.. 22..?? ይሄማ የስም መመሳሰል ነው እኔ 28 ነኝ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ 29 መሄዴ አይቀርም.. ይሄ የማን ነው ጨቅላ የኔን ስም የያዘ ብዬ ፎቶውን ሳይ የኔ ይመስላል..
በሉ በተመሳሳይ ምርት እንዳትሸወዱ.. ጌቱ አንድ ቀን እመጣልሃለሁ እዛው ከመቃብር ሥፍራህ ጋር ነው ምለቅህ ሎል
ገብተናል ላይቭ
apostolicanswers/live?_r=1&source=h5_m&enter_from_merge=share&enter_method=share&share_from_user_id=7070016548064216069&ug_btm=b1736,b0&sec_user_id=MS4wLjABAAAA8rak5d5vXCJMW9WIpOEwQK8ypkPOq02hPaQymMuYfc3eEPeJLZnNqHvGkdhPewZZ&utm_source=copy&social_share_type=10&utm_campaign=client_share&utm_medium=ios&tt_from=copy&user_id=7070016548064216069&enable_checksum=1&share_link_id=4098E4BA-4225-4E72-B9B5-397922E28935&share_app_id=1233" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@apostolicanswers/live?_r=1&source=h5_m&enter_from_merge=share&enter_method=share&share_from_user_id=7070016548064216069&ug_btm=b1736,b0&sec_user_id=MS4wLjABAAAA8rak5d5vXCJMW9WIpOEwQK8ypkPOq02hPaQymMuYfc3eEPeJLZnNqHvGkdhPewZZ&utm_source=copy&social_share_type=10&utm_campaign=client_share&utm_medium=ios&tt_from=copy&user_id=7070016548064216069&enable_checksum=1&share_link_id=4098E4BA-4225-4E72-B9B5-397922E28935&share_app_id=1233
ያው እኔ የሚጠቅማችሁን ነው ማጋራችሁ.. የዛሬው ደግሞ በጣም የተወደደ እና ትንሽ ብታበረታቱት በጣም አብዝቶ ሚጠቅመን ወንድም ነው ማርያምን.. ሁላችሁም ተቀላቀሉት.. እስቲ እንደተለመደው ሺህ እናስገባው
👇👇
@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
👆👆
እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥
ጌታ ግን ያስብልኛል..
[መዝ 40: 17]
ችግረኛና ምስኪን እንደሆንን አንተ ታውቃለህ አባ.. አንተ ብቻ ነህ አጋዣችን.. ተስፋችንም አንተ ብቻ ነህ..
“..አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ፤
አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ። “
መልካም ቀን እናንተ አምላካችሁ የቅርባችሁ አባታችሁ የሆነላችሁ ሰዎች
@Apostolic_Answers
በቅርቡ ወደ ክርስትና የመጣው ተሙ ወንድማችን.. “ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ” በሚለው መዝሙር አንድ ቪዲዮ ሰርቶ.. ኮመንት ላይ ፕሮቴስታንቶቹ ምን ቢሉት..??
“ኧረ አንተ ካደግህ በኋላ ነው ሲጀመር የሄድከው”🤭🤭
በእርግጥ ባላወቅነው መንገድ የትም ሃይማኖት ላይ ሆነንም እግዚአብሔር በመልአኩ በኩል ሊጠብቀን ይችላል.. ያው ወደ ራሱ ሊያመጣን ስለሚፈልግ
መላእክት ምን ያህል ኃያል እንደሆኑ መቼስ ይታወቃል.. ቅዱስ ሚካኤል ደግሞ አለቃቸው ነው😎😎 የመላእክት አለቃ..
ቅዱስ ሚካኤል ተዋጊ ነው.. በተለይ የወደቁትን መላእክት ማለት ነው.. በራእይ 12 ላይም እንደተነገረን ዘንዶውን ሚካኤል ነበር ከመላእክቱ ጋር ሆኖ የተዋጋው.. እናማ ዘንዶው ሊቋቋመው አልቻለም ስለዚህም ከነ መላእክቱ ተጣሉ በሰማይም ሥፍራ አልተገኘላቸውም..
በጣም የሚገርመኝ ከሃገር ውጪ ያሉም exorcists(አጋንንት አባራሪ ካህናት) አጋንንቱን በሚገስጹበት ወቅት ቅዱስ ሚካኤልንም በጣም ይጣራሉ.. ስለዚህ አጋንንቱን ሲዋጉ የሚካኤልንም እርዳታ ያገኙበታል..
በጣም ነው ደስ የሚለኝ ያለንበት ወይም የቀረብንባት የ እግዚአብሔር ከተማ የ እግዚአብሔር መላእክትም ያሉባት ናት [ዕብ 12 ላይ እንደሚለው]
እግዚአብሔር አምላካችን መዳንን እንወርስ ዘንድ ወዳለን ወደ እኛ ያግዘን ዘንድ አሁንም ይህንን ታላቅ የመላእክት አለቃ በቸርነቱ ወደ እኛ ይላክ.. ከአጋንንትም ይጠብቀን..
@Apostolic_Answers
ቆይ ከላይ ላለው ጽሑፍ..
ሙስሊሞች ያልተጻፈውንም እያነበቡ እየተሳደቡ እንደ እብድ እየሆኑ እንደሚያናድዱ አውቃለሁ
ክርስቲያን ወንድምና እህቶቼ ደግሞ እስካየሁት ድረስ የተጻፈ ነው ሚያነቡት ለዚህም አመሰግናችኋለሁ.. ግን ያው ትንሽ ብታለሳልሱላቸው ማለቴ ነው.. ኢየሱስ እንዲታይልን ማለት ነው..
“ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን..”
[ኤፌሶን 4: 15]
በርቱ እናንተ ጀግኖች
ቲክቶክ ላይቭ ላይ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ነገር.. ቀለል አድርገህ ስታወራ ከሁሉም ጋር በጣም ስትቀራረብ ምናምን ቀስ በቀስ የሆነ ሰዓት ላይ በጣም የሕጻን ጭቅጭቅ እና ነቆራ ውስጥ ራስህን ልታገኘው ትችላለህ.. በጣም ማልወደው ነገር ማለት ነው ማርያምን..
እና የተረዳሁት ነገር ብዙም ከሰው ጋር መቀላቀልና መቀራረብ እንደማያስፈልግና የራስህን ሥራ ብቻ መስራት እንዳለብህ ነው..
ሙስሊም ኡስታዞች እባካችሁን እንዲህ ዓይነት ስድቦችን ተዉ አያንጽም.. ሕዝብን ወደ ክፉ ነገር አትምሩ.. ከቻላችሁ የተጻፈውንና የምናምነውን ብቻ አንሱና ጠይቁን
https://vm.tiktok.com/ZMhngK3Jj/
አቡነ በርናባስ የሚያገለግሉበት ቦታ የሚገለገሉ ምእመናን አብዛኛው ቆራቢ ነው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ..
ከሆነ አባታችን ጌታ አሁንም አብዝቶ ይርዳዎት እናመሰግናለን እንዲህ ያለ አባት ነው ምንፈልገው.. ማለትም የመንጋው መቁረብ አስጨንቆት ለቁርባን የሚያበቃ..
@Apostolic_Answers
አሰልቺ በሆነው ሚዲያ ላይ እንደዚህ ዓይነት ቪዲዮዎችን ሳይ የሚጠብቁ ሰዎች እንዳሉ ያስታውሰኛል.. እና ሃላፊነት እንዲሰማኝ ያደርገኛል..
ግን fan የሚለውን ቃል ቀይሩልኝ😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMh3mJfxk/
ሐዋዝዬ ወንድሜ በድጋሜ እንኳን ደህና መጣህ.. የምትወደው ኢየሱስ ያስፈጽምህ..
ጳውሎስ ፈቃዱ ደግሞ ምን አድርጉ ነው ሚሉን..??🙄😭
https://vm.tiktok.com/ZMh3eT2Jy/
ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመለሰ.. እንኳን ደስ አላችሁ.. ዮኒ ቀደም ብሎ በማታ የሰራው መሆኑ ነው😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMhcWaA7M/
ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእት ክፍል:
“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።”
[ወደ ቆላስይስ 1: 15-16]
ከጥቅሱ ላይ የተወሰኑ ነጥቦች:
1. በሰማይ ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
2. በምድር ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
3. የሚታዩት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
4. የማይታዩትም ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
5. ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር(መጀመሪያ የተወለደ) ነው
ቅዳሴው ላይ ከጴጥሮስ መልእክት የተነበበ የሕይወት ምክር:
1ኛ ጴጥሮስ 1
13፤ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
14፤ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
15-16፤ ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ፡ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
17፤ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ጋዲ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገለትን ተአምር ተናግሮ ቪዲዮ ሰርቶ ቫይራል ሲወጣለት..
የቲክቶክ ስሙን.. “ጋዲሳ-ዘሚካኤል” ሎል
ለዘማሪት ሶፊያ ፣ ለአርቲስቷ እና ለኤርሚያስ(aka ቀለሜ)
https://vm.tiktok.com/ZMh7vHky5/
ቅዱስ ሚካኤል ለኢዮባ.. በጣም ደስ ይላል😊😊 እቺን ትሬንድ ልቀላቀል እንዴ እኔም😁😁
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMh7xCr6d/
የእፎይ አዲሱ አካውንት አሁንም ዋርኒንግ እያሳየው ነው.. ጋይስ ታደጉለት እስቲ ከቻላችሁ..
አካውንቱ ላይ ገብታችሁ ኮፒ ሊንክ
https://vm.tiktok.com/ZMh7FanhY/
ዌል.. እግዚአብሔር እኮ ሲፈጥር የፈጠረውን ሁሉ አይቶ “እጅግ መልካም ነው” ተብሏል..
ግን እዛው ጋር ወረድ ስትሉ ደግሞ እግዚአብሔር አዳምን ብቻውን ያየውና “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ይላል.. ስለዛ አዳሞች ብቻችሁን ትሆኑ ዘንድ አዎ መልካም አይደለም..
ግን ደግሞ አንዱ ጀለስ አሁን ደውሎልኝ ከሴት ጓደኛዬ ጋር ተባጠስን ይለኛል.. 1 አመት ሆኖናል አለኝ.. ኧረ ቀልድ.. አመት..??😁😁 ከኔ ተማር ይለኛል ደግሞ😆😆 ቁጭ ብሎ የተጸለየበት ውኋ እየጠጣ እንዳይሆን በቮሚት እንዲወጣለት ሎል..
አላማ ይኑረን😉😁
አሁን አንድ ሰው በውስጥ መስመር እንዲህ አለኝ:
“እስልምና ላይ ሚሰሩ ልጆች ሲናገሩ ትንሽ የቃላት ምርጫ ቢያደርጉ”
መልካም አሳብ ነው.. ያው አንዳንድ ነገሮች እስልምና ላይ በራሳቸውም በጣም ከባድ ቢሆኑም ግን እኛ በተቻለን አቅም አለሳልሰን ዋናውን መልእክት ብናስተላልፍ መልካም ይመስለኛል.. ደግሞ ኢየሱስንም ሊያዩት ይገባል.. እርሱን ነው አይተው መምጣት ያለባቸው.. ስለዚህ የዋህነት ፍቅር እና መልከም ፍርሃት ሊኖረን ይገባል
በርቱልኝ
@Apostolic_Answers
ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሱን በጥንት አባቶች ማብራሪያ መሠረት ትርጓሜ አዘጋጅተዋል.. አስባችሁታል ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ.. በየጥቅሱ አባቶችን እየጠቀሱ ሲተረጉሙ..
ከሱ ውጪም አቦ እኔ ለማየት እስከሞከርኩት ወደ መቶ መጽሐፍትን አዘጋጅተዋል.. የምር ግን ሰው ናቸው..??🙄🙄 እስቲ አንዴ ተነስተን እናጨብጭብ😁😁
አባ ታድሮስ ማላቲ ይባላሉ.. የኮፕቲክ አባት ናቸው.. አሁን በሕይወት ካሉን ሊቃውንት መካከል ናቸው.. ግን ይለያሉ በጣም ጌታ የረዳቸው ሰው ናቸው..
ዘማሪዎቻችን "ኢየሱስ ቦኪሜ" ሲሉ ቦኪም ያው የቦታ ስም ነው እና መሳፍንት ላይ እንደተጻፈው እስራኤላውያን በአንድ ወቅት ከጥፋት መንገዳቸው ለመመለስ እጅጉን ያለቀሱበትና ለእግዚአብሔርም የሠዉበት ሥፍራ ነው.. በዚህም ምክንያት ያንን ሥፍራ ቦኪም ብለው ጠርተውታል.. ቦኪም ማለት የሚያለቅሱ ወይም የማልቀሻ ሥፍራ ማለት ነው።
ኢየሱስ ቦኪሜ ነህ ሲባል.. ይመስለኛል ሰው ወደ እርሱ ቀርቦ የሚያለቅስበት እውነትኛ ሥፍራ በኢየሱስ ፊት ስለሆነ ነው..
ምናልባት ሌላ ትርጉም ካላቸው ግን እንጃ😁😁
በቃ አይዞዎት😭😭
ኮመንት ምታደርጉ ሰዎች ፍቱ አባታችን ኮመንታችሁን አይተው ቅሬታቸውን በዜማ አሳውቀዋል እረፉ በቃ
ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንግል ክፍል..
“ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።”
[ማቴዎስ 13: 7]
ጌታ ቃሉን ወደ ልባችን ሲልክ ፍሬን እንድናፈራና ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገን ነው.. ታድያ ግን በልባችን ውስጥ የዓለም የሆነው ምድራዊ አሳብ ሲነግስብን እርሱ እንደ እሾህ ይሆንና ወደ ልባችን የሚመጣውን የጌታን ቃል እንዳያፈራ ያደርገዋል.. ስለዚህም እንዲህ ያለው እሾህ ሊቆረጥ ይገባዋል..
እግዚአብሔር አምላካችን ፍሬን እናፈራ ዘንድ በጸጋው መልካም መሬት ያድርገን
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers