ከቅዱስ ቁርባን እኮ መካፈል እፈልግ ነበር.. ግን ቀሚስ ብቻ ልለብስ ነዋ.. ለሚሉ እህቶች እና ኃጢአት ብሰራስ ለሚሉ ሁሉ
https://vm.tiktok.com/ZMkrT7opD/
😁😁 እየጸፍኩ እያለ ይሄ ሰውዬ እንዲህ ያወረኝ ጀመር.. እና የምርም ገላገለኝ በቃ እንዲህ ዓይነት ነገር ከፈለጋችሁ ከእርሱ ጋር አውሩ.. እኔ ፈታ ብዬ ልኑርበት ትላልህ ሎል
የሱን አካውንት ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉት..
@christo_kentrikos
@christo_kentrikos
እኔ ያው መምህራንን መናገር አልወድም ሃይማኖትን የሚንድ ካልሆነ.. እና ቅድም በለቀኩት ቪዲዮ የደበራችሁ ካላችሁ ይቅርታ..
ግን መምህርም ልክ አይመስሉኝም.. እንዲሁ መተቸት ላይ ናቸው በቃ በስመአብ.. ባለፈው ታቦት ሌላ መሰዊያ ሌላ አሉ.. ደግሞ ዛሬ እንዲሁ ሌላ ነገር.. እና እየበዛ መሄዱ እንዲህ ዓይነት ነገር ምንም ደስ አላለኝም..
አዝናለሁ ግን ይሄንን ስል ማርያምን.. ያው ለብዙ ዘመን ከመድከማቸው የተነሳ መተቸት ራሱ ይከብዳል.. ግን ደግሞ ትንሽ..
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:
ወደ ሮሜ 3
24፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
25፤ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው..
1. ድኅነት የሆነልን እንዲሁ በጸጋው እንጂ አስቀድሞ በኛ መልካም ነገር ታይቶ አይደለም.. ስለዚህም ማንም አይመካም ከሥራ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥጦታ ነውና..
- ሥራ ያስፈልጋል ምንለው አንዴ ከዳንን በኋላ ድኅነቱን ለመፈጸም ጸጋውን በመጠቀም ፍሬ ቢስ ሳንሆን የቅድስና ሕይወትን መኖር ነው..
2. ይህንን ጸጋ ደግሞ ያገኘነው በክርስቶስ ቤዛነት ምክንያት ሲሆን እንዲሁ ዝም ብሎ ሰውን ሁሉ አዳነ አይባልም.. ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ የተገለጠ ቢሆንም ሰዎች ግን ይህንን ለማግኘት አስቀድመው ማመን አለባቸው.. “እርሱንም በእምነት የሚገኝ አድርጎ አቆመው” የሚለው ለዛ ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ፕሮቴስታንቲዝም ከጌታ ውጪ መሆናቸውን ከአባቶች አንጻር በጣም በቀላሉ ለማየት የጳጳሳትን ነገር ማየት ነው..
ማለትም ፕሮቴስታንቶች ከጳጳሳት ውጪ ናቸው.. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ደግሞ ያለ ጳጳስ ቤተ ክርስቲያን ትኖራለች ብሎ ያስተማረ ማግኘት ከባድ ነው.. በተቃራኒው እንደውም ጄሮም እንዲህ ይላል:-
“ያለ ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያን የሚባል ዓይነት ነገር የለም”
(Dialogue with the Luciferians, 21)
የዮሐንስ ወንጌላዊው ተማሪ ቅዱስ አግናጥዮስም እንዲህ ይላል፡-
“ከቤተ ክርስቲያን ጋር በተገናኘ ማንም ሰው ያለ ጳጳስ(ወይም እርሱ ከሾማቸው በቀር) ምንም አያድርግ... ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ያለ ጳጳስ በራሱ ማጥመቅ ሕጋዊ አይደለም።”
To the smyrneans: chap 8
ስለዛ በየመንደሩ የሚደረጉ የፕሮቴስታንትም ሆነ የማናቸውም ጥምቀቶች ያኔ የhighschool ተማሪ እያለን water day ብለን ከተራጨነው ውኃ የተለየ ነገር አይኖረውም ማለት ነው። ጥምቀት ያድናል የሚሉ ሉተራንንም ይመለከታል ይሄ።
ቆጵርያኖስም ለዛ ነው በነገራችን ላይ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድኅነት የለም.. ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለው ጥምቀት አያድንም ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት የሚያድነው ጥምቀት ያላት እያለ የሚናገረው(epistle 75: 2-3)
ያለጳጳሳት ምስጢራት አይፈጸሙም.. ሌሎች አገልጋዮችም አይሾሙም..
የጵጵስና ሹመት እንዴት እንደሆነ ደግሞ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን
@christo_kentrikos
TS የሚል ስም ያለህ ሰው.. በውስጥ ጽፈህልኝ ልመልስልህ ስል አጠፋኸው ጽሑፍህን አይቼዋለሁ.. ካልከኝ ጋር በተያያዘ ብዙ ባልጠቅምህም ቢያንስ ለጻፍከው አላንስም እና ላገኝህም አልቻልኩም ካየኸው ላክልኝ በውስጥ ፕሊስ
Читать полностью…እህቶች ይቅርታ ግን😁😁
“የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥
ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት።”
[ምሳሌ 11: 22]
ቆንጆ መሆኗ እኮ ምርጥ ነው.. ግን ወፍ ጥበብ😭😭 ሎል..
የወርቅ ቀለበት በአሣማ አፍንጫ ላይ ቢገባ ወርቁ እርያውን ከፍ ሚያደርገው አይደለም.. እንደውም ወርቁ በእርያው ይሸፈናል ወይም ይረክሳል እንጂ.. ልክ እንዲሁ ቆንጂት የምርም ቆንጆ ሆና ግን ከጥበብ ከተለየችና በኃጢአት ምትመላለስ ከሆነ የሷ ቁንጅና በእርያ አፍንጫ ላይ እንዳለ ወርቅ ይሆናል..
እውነተኛው ጥበብ ኢየሱስ ነው.. ስለዚህ ቆነጃጅት ከኢየሱስ አትለዩ.. ትልቁ ውበት እርሱ ነው.. ለዘላለም የማይረግፍ ውበት ኢየሱስ..
@Apostolic_Answers
ስሙ ጋይስ አምና ያወራኋችሁን ነገር በቅርቡ ብናደርገው ብዬ አሰብኩ..
ምንድን ነው እሱ..?? የሆነ መንፈሳዊ ፕሮግራም አዘጋጅተህ ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ወንድም እህቶች ምሳ ጋብዘሃቸው ወንጌል ብትሰብክላቸው..
1. አምላካቸውን እንዲያውቁ ስለ አምላካቸው ምንነገርበት
2. ከዛ የመጽናኛ ስብከት ስለ ዘላለማዊ መኖሪያቸው ቢነገራቸው ስለ ተስፋቸው ኢየሱስ ምናምን
ያው የምናዘጋጅ ከሆነ ሳንቲም ትንሽ ትንሽ አጋጭተን ነው ምናዘጋጀው.. ለአዳራሽ ለስፒከር ለዲኮር ለምሳ ምናምን.. አንተው ተወጣው እሱንም አትሉኝም መቼስ ሎል..
ምን ይመስላችኋል..??
አንድ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጨመር ቢፈልግ.. የግድ ገድላት ተአምራትን ሙሉ በሙሉ መቀበል አለበት..??
አዳዲስ ሰው በመጣ ቁጥር እነርሱን ለማስረዳት ሲባል ደጋግሞ ይሄንን ነገር ማንሳት ትንሽ አድካሚ ነው ያው ጭቅጭቅም ስለሚኖርበት😁😁
ትንሽ ወቀጣ ያስፈልገኛል ሰሞኑን.. ሚዲያው ላይም ስለበዛሁ ሎል😁😁
1. ገድላትን ማንበብ ለሕይወታችን ለተጋድሎ ስለሚያግዙን ማንበብና መጠቀም አስፈላጊ ነው..
2. ነገር ግን በገድላትም ሆነ ተአምራት ውስጥ ያለውን ሁሉ የግድ መቀበል አለብህ የሚባል ነገር የለም.. ለምሳሌ እኔ በሚጠቅመኝ መልኩ እጠቀምባቸዋለሁ.. ግን ደግሞ ማልቀበላቸውም ነገሮች አሉ.. ይሄ ግን ከክርስትና አያስወጣኝም..
3. ገድላት ተአምራት ከተጻፉበት ዘመን አንጻርም አንዳንዴ በጣም ግነታዊ ነገሮች ሊገኙበት እንደሚችሉ አምናለሁ..
4. ቤተ ክርስቲያኔም ይህንን ሙሉ በሙሉ ካልተቀበልክ የኔ አትሆንም አትለኝም.. አንድም አባትም እንዲህ ያለ አጋጥሞኝ አያውቅም እኔ..
5. አይደለም ገድላት እና ተአምራት.. የቅዱሳን ሊቃውንት አባቶቻችንን መጽሐፍት እንኳ ሙሉ በሙሉ ተቀበል አይባልም (እዚህ ላይ ቀጣይ እመጣበታለሁ በቀጣይ ጽሑፍ)
@Apostolic_Answers
ወንድማችንን ቮት አድርጉት.. ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑና ከዛም ወደታች s ቤት ስትደርሱ “sudik” የሚል አለ.. እናም እሱን ተጭናችሁ submit በሉት ከዛ ስልክ ቁጥራችሁን አስገብታችሁ የተላከላችሁን ኮድ በማስገባት ጨርሱ
https://www.tiktokcreativeawards.com/categories/16
ኦው የኔ የአዳማው ፕሮግራም ተላልፏል ላልታወቀ ጊዜ.. ልጆቹ አዳራሽ ሊያገኙ አልቻሉም ነገር ነው.. የሚዲያ አዳራሽ ብቻ ነው ያለን😭😁
Читать полностью…አጠር ያለች ማስታወሻ
ሥጋዊ እድገት በሥጋዊ ምግብ እንደሆነ.. መንፈሳዊ እድገትም በመንፈሳዊ ምግብ በጌታችን ሥጋና ደም ነው..
መልካም አዳር
“ኢየሱስ ‘እኔን ጌታ ያለ ሁሉ ገሃነም ይገባል’ ብሎ ነው ያስተማረው” እያሉ ነው አንዱ ኡስታዝ😭😭
“ለእኛስ ሁሉ በእርሱ የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን” [1ቆሮ 8:6]
https://vm.tiktok.com/ZMkjTmRS8/
ጋዲ በድብቅ ይህንን ቀርጾኝ እያስፈራራኝ ስለሆነ ራሴው ቀድሜ ብለቀው ይሻላል😁😁
በፊት የማውቀው አንድ ሱሰኛ ጀለስ እንዴት እንደሚራመድ እያሳየሁ መሆኑ ነው😁😁
አማን ሻሎም እንዲህ አለ:
“ሚዲያ ላይ ያለችው ኦርቶዶክስ ሃሪፍ ትመስላላች የመሬቷን እናያታለን.. ላይፈህን ደብቀህ በፊልተር ትመጣለህ እንዴ..”
ከዛ አንዱ ኮመንት ላይ ምን ቢለው..
ራስህን ሮስት አደረግህ🤣🤣 እኛ መሬት ላይ ያለውን አማንን አናየውም እንዳታስብ ሎል.. የእኛን ቤተ ክርስቲያን ግን ኑና እዩዋት መሬት ላይ ያለውን አምልኮዋን ቅዳሴዋን.. ጭራሽ እሱን ስታይ ሚዲያው ላይ ያለው እንዳይደብርህ እንጂ😁😁
መምህር ብርሃኑ አድማስም ደገሙት😭😭 ደዋዩ አኬ ሲላቸው እርሳቸው “አክሊሉ”😭😭
ዮው ግን ታውቃላችሁ እየቀለድኩ ነው ለጭዌው ያህል እንጂ አክሊሉ ቢባልም ጣጣ የለውም😁😁 (ምንም እንኳ ስሜ አክሊል ቢሆንም ሎል)
ሌላ ቦታ አድሬ አርፍጄ ደረስኩ.. በጊዜ ነው መሰል ቅዳሴም የገቡት በጊዜ አለቀ.. እና እስቲ ምን እንደተነበበ አልያም ደግሞ ከመዝሙረ ዳዊት እናንተ በጣም የምትወዱትን ክፍል ኮመንት ሥር አስቀምጡልንና እናንብብ..
ሌላ ነገር መጻፍ አይቻልም..
መልካም የጌታ ቀን