ጋሽ ኢዮብ ዘሚካኤል ቴሌግራም ላይ በቻናል መጥተዋል.. እናም እነሆ ቻናሉ.. እንቀላቀለው😁😁
@eyobzmikael12
@eyobzmikael12
የጌታችን እናት ማርያም የተመረጠችው ንጽሕት ስለሆነች ነው ወይስ ንጽሕት የሆነችው ስለተመረጠች ነው..??
ሁለቱም አንድ ላይ ሳይነጣጠል ያስኬዳል ብዬ አስባለሁ.. የእመቤታችን መመረጥ ለተለየ ዓላማ ስለሆነ ንጽሕት እንድትሆን ወይም እንዳትበድል መንፈስ ቅዱስ ይጠብቃታል.. አባ ጊዮርጊስ “ድንግልን ከማሕጸን ጀምሮ እንዳትበድል የጠበቃት መንፈስ ቅዱስ ነው” እንዲሉ..
ግን ደግሞ ይህ መንፈስ ነጻ ፈቃዷን አያሳጣትምና እርሷም አሜን ብላ መተባበሯና ራሷን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መጠበቋና እሺታዋ ደግሞ በእርሷ በኩል የታሰበው ነገር እንዲፈጸም ያደርገዋል ማለት ነው..
@Apostolic_Answers
እስቲ በቅርቡ ይህን የዲያቆን ያረጋልን “ሳይንስ እና ሃይማኖት” መጽሐፍ አንብቤ ልጨርስና እንዳስሰዋለን..
በቃ አስተምህሮአዊ ጉዳዮችን ዲን ያረጋል ይጻፍ😁😁 ያው ግነታዊ ነው ሌሎቹም ይጻፉ😁😁
@Apostolic_Answers
ጸልዩልኝ እስቲ.. አትርሱኝ እንጂ😁😁
በጸሎታችሁ መሃል ስሜን ጠርታችሁ “በነገር ሁሉ የአንተ እርዳታና ጠብቆት አይለየው” ብላችሁ ለጌታ አሳስቡ.. በቃ እቺን ነው አታካብዱ🙄🙄ሎል
እስቲ ዌብሳይት developers አግኙኝ.. አንድ ሃሪፍ እና ተለቅ ያለ ዌብሳይት እፈልጋለሁ..
_____ላይ አውሩኝ.. website developers ብቻ ደግሞ😁😁
እስቲ ከእስልምና በጣም የሚያሳዝናችሁን(የሚያስጠላችሁን) ምንፍቅና ጥቀሱ..
ጠቅላላ በስህተት ትምህርት የተሞላ ነው ያው ግልጽ ነው ግን እስቲ አንድ ሰው አንድ ብቻ ይጥቀስ..
ቆይ ከኮመንቱ ሰው እንዲማር ከመልሱ ውጪ ያሉ ኮመንቶችን አጠፋለሁ😁😁
ቲክቶኩ ላይ ከላይቭ ፕሮግራም ውስጥ እየወሰዱ በጣም ቆንጆ አድርገው ከሚለቁት ውስጥ ሔና አንዱ ነው.. በጣም ጸዴ ናቸው ሁሌም ቪዲዮዎቹ..
እስቲ ይሄንንም እዩ በዛውም ፎሎው አድርጉት
https://vm.tiktok.com/ZMhSBxHtn/
እንደው መምህራኖቻችን ግን አንዳንድ ቀላል የሆኑ.. ምናልባት ግን አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ለምንድን ነው ዝም የሚሉት..?? ለምሳሌ የቅዱሳት መጽሐፍት ቀኖና ጉዳይ ላይ 81 ከማለት በዘለለ የትኞቹን የሚለው ላይ በግልጽ በሲኖዶስ ማሳየት ሲገባ ምንድን ነው ዝም ማለት..??
ከዚህ ቀደም በቪዲዮዎቼ ላይ ከተናገርኳቸው ውስጥ የተወሰኑትን በጽሑፍ ላስቀምጥ የግል እይታዬ ነው:
1. የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ዋናዎቹ 27ቱ እንደሆኑ ይታወቃል ከነዚህ ጋር የሚስተካከል መጽሐፍ መቼስ አይጨመርም ብዬ አስባለሁ.. ስለዚህም የቀሩት 8ቱ የሥርዓት መጽሐፍት ከምን አንጻር እንደሚታዩ በግልጽ ማሳወቅ
2. ብሉይ ኪዳን ላይ በፍትሃ ነገሥቱ አቆጣጠር ከሆነ “ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን” ብሎ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ይቆጥረዋል.. መቼስ ከክርስቶስ በኋላ ተነስቶ ግን ደግሞ ወደ ክርስትና እንኳ ባልመጣ አንድ “አይሁዳዊ” ያልዳነ ሰው የተጻፈ ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ አይሆንም ስለዛ ከምን አንጻር እንደሆነ ማሳወቅ
3. “መጽሐፈ መቃቢያን” ተብሎ ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ እውነተኛው መጽሐፈ መቃብያን እንዳልሆነ ይታወቃል.. ስለዚህም ትክክለኛውን ወደ አማርኛ መተርጎም
4. “ተረፈ ባሮክ” ከዚህ ቀደም ቀኖና ውስጥ የለም ብያለሁ.. ዋናው “ባሮክ” እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ በታሪክ ውስጥ ሁሉ የታመነ ነው.. ግን ደግሞ ይሄኛው “ተረፈ ባሮክ” እስካየሁት ድረስ በታሪክ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የማይታወቅ በእኛ ሃገርም በቀኖና ደረጃ ሲቆጠር አላየሁም.. ከኤርሚያስ ጋር የሚቆጠረው “ተረፈ ኤርሚያስ” እና “ባሮክ” እንጂ “ተረፈ ባሮክ” አይደለም.. እናም ምናልባት ሕትመት ውስጥ ሲታይ ቀኖና እንዳይመስል ቢወጣ እንደው ቀኖና እና ኅትመትን ለይቶ የማያውቅ ብዙ ስለሆነ..
ሃይማኖታችን ላይ ምንም ለውጥ ላያመጡ ይችላሉ እነዚህ ነገሮች ግን ደግሞ ክፍተቶችን መሸፈን መልካም ነው ብዬ አስባለሁ..
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
“በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።”
[ወደ ሮሜ 5: 20-21]
1. “በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ” ሲል ሰዎች እንዲበድሉ ያደረጋቸው ሕጉ በራሱ ነው ማለት ሳይሆን ያው በሕግ ግን በደሉ ይታወቃል ነው.. ማለትም ሕጉ ይህን አታድርግ ይህን አታድርግ ስለሚል ልክ ስታደርገው በደልክ እያለ ይናገራል ነው.. ስለዚህም በሕግ የበደል ብዛት ተገለጠ.. በዚሁ በሮሜ 3:20 ላይ “ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና” እንዳለው ማለት ነው..
2. “ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት ነገሠ” ተባለ የኃጢአት ደምወዙ ሞቱ ነው እንዲል እዚሁ ሮሜ 6:23 ላይ ኃጢአት ሰዎችን ወደ ሞት እየመራ በሁላችን ነገሠ
3. “ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ..” በማለት ንጽጽሩን ያቀርባል.. ኃጢአት ወደ ሞት በመምራት እንደ ነገሠ ጸጋ ግን ከጌታችን ኢየሱስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ሊነግሥ ተገለጠ.. ሁለት መንገዶች አሉ አንዱ ቀደ ሞት የሚወስድ አንዱም ወደ ዘላለም ሕይወት.. ኃጢአት ወደ ሞት፤ ጸጋ ወደ ዘላለም ሕይወት..
ስለዚህስ..??
4. “ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ” ሰዎች ከነገሠባቸው ኃጢአት ወይም የኃጢአት ባርነት ተላቀው ከሞት አምልጠው ከጌታ የተነሣ ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲሻገሩ ጸጋ ከኃጢአት ይልቅ በዛ በለጠ.. ስለዚህም ይህ ጸጋ ከኃጢአት ተለይተን ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ እንድንኖርና ሕያው ተስፋችንን ኢየሱስን እንድንጠባበቅ የሚያደርገን ኃይላችን ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:
“ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ፡ አለው።”
[ሉቃስ 5: 8]
ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ያለው አንድ ተአምርን ከጌታችን አይቶ ነው.. አሣ ለመያዝ መረብን ጥለው ነበር ነገር ግን ሌሊቱን ሁሉ ቢፈጉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ነበር
ነገር ግን ጌታችን ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብለው መረቦቻቸውን ለማጥመድ እንዲጥሉ ይነግራቸዋል.. እናም ጴጥሮስም “ሌሊቱን ሁሉ ደክመን ምንም አልያዝንም ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ” አለው.. እናም ጣለ መረቡም እስኪቀደድ ድረስ ብዙ አሣዎችን ያዘ..
አያችሁ የኔ ተወዳጆች ብዙ ያደከሙን ነገሮች ጌታ ሲገባበት ቀላል ይሆናል.. በሕይወታችን ፍሬን ማፍራት ቢከብደን በክርስቶስ ግን እናፈራለን.. ያለ እርሱ ምንም ልናደርግ አንችልም.. ጌታችንም “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናል..
የጌታን እርዳታ ለማግኘት ደግሞ እኛ በራሳችን ደካማና ኃጢአተኞች መሆናችንን ማወቅ አለብን.. ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታው ጉልበት ላይ ወድቆ እኔ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው.. ራሱን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ሲያስቀምጥ ጌታም ደግሞ መለስ አድርጎ “አትፍራ ከእንግዲህስ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው..
ከክርስቶስ የተነሣ ፍሬን የምናፈራ እንሁን
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ላይቫችንን እንዲህም የምታዩ አላችሁ ለካ😆😆 ኧረ የምር ሚዛናዊ አይደለም ይሄ.. እኔ ራሴ እንዲ ደቅ ብዬ ምወደውን የሆነ ነገር እየጠጣሁ ባይ😁😁
Читать полностью…ዮኒና ሚሞቹ😆😆 እስቲ አበረታቱት😁😁
ያው ያኛው ወንድም በስህተት ያለው ነው ሚሆነው ግን ለጭዌው ያህል😁😁
https://vm.tiktok.com/ZMhPkfyBD/
ጥምቀት ላይ ካህኑ የሴትን እርቃን ገላ ሊያይ አይገባም.. ስለዛ ስትጠመቁ የመጠመቂያ ልብስ ይኑራችሁና በዛ ተጠመቁ.. እርቃናችሁን አትሁኑ.. ወንድም በቦክሰርህ ተጠመቅ ከፈለግህ..
አጭር ማስታወሻ😁😁
@Apostolic_Answers
“ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ፡ አለው።”
[ማርቆስ 2: 5]
አንድ ሽባ ኃጢአተኛ ነበር.. እና ይህንን ሰው አራት ሰዎች ተሸክመው ወደ ክርስቶስ አመጡት.. የሚገርመው ደግሞ ቤቱ ሞልቶ ስለነበር በላይ በጣሪያ ነው ያስገቡት.. እናም ጌታችንም እምነታቸውን አይቶ “አንተ ልጅ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ” አለው..
1. ይህ ሰው ምናልባትም ኃጢአተኛ ሽባ ስለሆነ ፈሪሳውያኑ የማያቀርቡት ይሆናል.. ጌታችን ኢየሱስ ግን የማይጸየፈን ጌታ ነው.. “ልጅ” ብሎ እንኳ ጠራው..
2. ኃጢአተኞችን ማቅረብ ብቻ ደግሞ ሳይሆን አቅርቦ ከዛ ኃጢአትም የሚያነጻን ነው.. እርሱ ይቻለዋልና..
3. ጓደኞቹም የሚያስደንቁ ናቸው.. በታላቅ እምነት ወደ ኢየሱስ አቀረቡት.. እውነተኛ ጓደኛ ምክንያቶች ሳይዙት ወደ ኢየሱስ የሚያቀርብ ነው..
መልካም የጌታ ቀን
@Apostolic_Answers
ኧረ በቅዱስ ሚካኤል በ10 ደቂቃ ውስጥ የሃገር web developers መጡ በውስጥ.. ለካ እኛ አንሰራም እንጂ ኃይል አለን በጣም.. ሚገርም ነው..
Читать полностью…አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች አሁን ላይ የሚለቅቁት ቪዲዮ.. ከታች ኮመንት ላይም አስቀምጥላችኋለሁ😁😁
ዝናር ጨርሰዋል ሙሉ በሙሉ የምር ሊያነሱት ሚችሉት አሳብ ራሱ ጠፋ😁😁
አንድ ወዳጄ እንዲህ አለ.. “ጌታ የሚለው ቃል ለኢየሱስ ይመጥናል..?? እንደው ጌታ ከሚባል የጌቶች ጌታ ቢባል..??”
ሌላኛው ወዳጄ ደግሞ ቀበል አድርጎ እንዲህ አለው:
ያው ሰው ሰውኛ ቃላት በአጠቃለይ በራሳቸው ለእግዚአብሔር የሚመጥኑ ባይሆኑም እግዚአብሔር ግን እኛ እንድንረዳው ራሱን በሰው ቋንቋ ለእኛ ገልጧል.. ልክ አንተ ሕጻናት እንዲረዱህ በራሳቸው አወራር እየተንተባተብክ በሕጻናት አወራር እንደምታወራቸው.. እናም እገዚአብሔር ራሱን ለእኛ ሲገልጥም ስለራሱ ከተጠቀማቸው ቃላት ውስጥ አንዱ ለምሳሌ “ጌታ” ነው..
መጽሐፍ ቅዱሳችን ጠቅላላ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል.. ጭራሽ “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በልብህ ብታምን.. ትድናለህ” እየተባልክ አጉል የቃላት ጨዋታ ውስጥ መግባት አያስፈልግም.. ኢየሱስ ጌታ ሲባል “አንድ ጌታ” እየተባለ ነው.. ሐዋርያው ለእኛስ “አንድ ጌታ አለን” እንዳለው ማለት ነው..
እርግጥ ነው “የጌቶች ጌታ” የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ትልቅ implication ቢኖረውም “ጌታ” የሚለውም ግን ለኢየሱስ በተገባ የሚነገርለት ነው..
ስለዚህም “እግዚእ ኢየሱስ” [ ጌታ ኢየሱስ ] ትለዋለች ቤተ ክርስቲያናችን
@Apostolic_Answers
በእስልመና እና በክርስትና መካከል ያለው ልዩነት ከብዙ በጣም በጥቂቱ
ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2:30 ላይም ያሰብነው ነገር አለ
https://vm.tiktok.com/ZMhAXEFb4/
ቲክቶኩ ላይ አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ወደ ክርስትና እንመለሳለን ሲሉ ያየ ዮኒ: “ኧረ ሲኖዶሱን አስፈቅደን ውኃ ይዘን እንግባ ቲክቶክ ላይ” እያለኝ ነው😁😁
ያው ሊያጠምቃቸው መሆኑ ነው ሎል